
መንፈሳዊ ግጥሞች
በዚህ ቻናል እግዚአብሔር እንደ ፈቀደ መንፈሳዊ ወኔያችንን የሚቀሰቅሱና ዕውቀት የሚያስጨብጡ መንፈሳዊ ግጥሞችን እናስተላልፋለን፡፡ ለአስተያየት @atnatioss ቻናሉ@spritualpoem
Подписчики, 30 дней
28 нояб. – 29 нояб.−3 (−0,1%)
Показать таблицей
| Дата | Подписчики |
|---|---|
| 28 нояб. 2026 г. | 2 528 |
| 29 нояб. 2026 г. | 2 525 |
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 23 нояб. 2026 г. | 334 |
| 25 нояб. 2026 г. | 229 |
| 28 нояб. 2026 г. | 78 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры334Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 02Просмотры229Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 03Просмотры78Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
አሁን ስንት ሰዓት ነው?! ለተልዕኮ የሚፋጠኑ ፤ ለአገልግሎት የሚቀኑ ትጉሃን ቅዱሳን (መላእክት እና ሰዎች) ፤ ልጆች መሆንን በተግባር መግለጥ ልባምነት ነው። በሥራ እንጅ በወሬ እና በፉከራ በቀረርቶ የተጠበቀች እና የተሻገረች ደግሞም የምትሻገር ሃገር እና ቤ/ክን የለችንም። እንኳን ሌሎችን ራሳችን ለማሻገር እንኳ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል። ተቆጥሮ የማያልቅ የምናራግፈው አቧራ ፣ የምናነሣው የእንቅፋት ደንጋይ ፤ የምንነቅለው እሾህ እና አሜካላ ፤ የምንሰብረው የጠላት ወጥመድ ፣ ልንከፍለው የሚገባን የትውልድ ዕዳ የብዙ ብዙ ነው። ልንወጣበት ከሚገባን ክፉ ልማድ እና አኗኗር ለመውጣት ፤ ልንገነባው ወደሚያሻን በጎ እሴት እና ባህል ለመምጣት እጅግ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል። እያንዳንዳችን ልንሠራ የማንችልበት የሕይዎት ሌሊት አለን። ከዚያ በፊት ሠርተን ፤ አከናውነን ልንገኝ የሚገባ የቤት ሥራችን ምን ይሆን? በእኛ መኖር ሊፈታ የሚገባው ሕልም/ውል/ቋጠሮ ፣ የዕድሜያችን ጀምበር ሲዘቀዝቅ ፥ ፀሐያችን ስትጠልቅ ፤ ለትውልድ ልንተወው/ልናስተላልፈው የሚገባን ዐብይ ቁም ነገር ምን ይሆን?! ነገ ወይም የዛሬ ዓመት ትሞታላችሁ ብንባል ፥ ይህን ሳናደርግ ብለን ልንቆጭበት የምንችለው ጉዳይ ምን ይሆን?! ታዲያ ለዚህ ዛሬ ምን እየሠራን ይሆን?! የምናወራለትን እውነት ፤ መሆን የምንሻውን የልባችንን ናፍቆት/ምኞት መኖር የምንጀምረው መቼ ይሆን?! የዕለት ከዕለት የሥራ ክንውናችንስ ይህንን ለማሳካት የሚያስችል ተግባር ባለበት እንቅስቃሴ የታጀበ ይሆን ወይስ እንዲሁ በከንቱ ስንናውዝ ጊዜው ያልፋል?! 🙊ለመሆኑ !🙊 አሁን ስንት ሰዓት ነው?! <<አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሀል።>> ኤፌ 5:14 ©ዮሴፍ ጌትነት ህዳር 15/2019 ዓ•ም
Открыть в Telegram♦ዳዊትነት ይለምልም♦ ጎልያዶች የበዙባት ሃገር ፥ ከሰቆቃ እንድታርፍ ዳዊትነት ይለምልም ፥ ወንጭፍ ቦታ ያግኝ ፥ ጎልያድ ይቀሰፍ። ©ዮሴፍ ጌትነት 13/05/2014 ዓ.ም
Открыть в Telegram♦የሕይዎት ተቃርኖ♦ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ የንጉሥ ልጅ ነው። ስለዚህም የወደፊት እጩ ንጉሥ ነበር ለማለት እንችላለን። መልከ መልካም የሆነች ፥ የንጉሥ ልጅ ሚስት ትሆነው ዘንድ ታጨችለት። ሰርግ ተሰረገ። ገብረ ክርስቶስ በሰርጉ ዕለት ፥ በሙሽርነት ዋለ። ከሙሽሪት ጋር ለጫጉላ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ገቡ። እነሆ ጸሎትን አደረገ ፣ ቃልኪዳን አስገባት ፣ በሌሊት ከጫጉላ ቤት ወጣ ፤ የክርስቶስን ሙሽርነት ወዷልና። በመርከብ ተሳፍሮ ረጅም መንገድ ተጓዘ። በአንድ ቤተክርስቲያን አጥር ተቀምጦ ብዙ ዓመት ኖረ። እመቤታችን ለአንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋይ ክብሩን ገለጠችለት። ገብረ ክርስቶስም እመቤቴ ሆይ ስለምን ክብሬን ለሰው ገለጥሽብኝ ብሎ ሸሸ። በመርከብ ተሳፍሮ ሲሄድ መርከቡ ወደ አባቱ ቤት አደረሰው። እርሱም በአባቱ ቤት አጥር ተጥሎ ኖረ። ያወቀው ማንም አልነበረም። የአባቱ ሰራተኞችም ሸተተን እያሉ ይጠየፉት ነበር። ቦታውን እንዲለቅ ውሃ ይደፉበት ፣ ቆሻሻ ይጥሉበት ነበር። ውሻ እንበላው ብለውም ስጋ ወደ ሱ ይጥሉ ነበር። ውሻወቹ ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር። በእንዲህ አይነት አኗኗር በአባቱ (በንጉሥ) ቤት አጥር 15 ዓመት ተጥሎ ኖረ። የሚሞትበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ የሕይዎቱን ታሪክ ፥ በወረቀት ፅፎ በእጆ ይዞ በሰላም አረፈ። በንጉሡ ደጅ የሞተውን ቅዱስ ሂዳችሁ አምጡት የሚል ድምፅ በቤተክርስቲያን ተሰማ። ሂደው አገኙት ። ወረቀቱን ሊቀበሉት ቢሞክሩ ከእጁ ማላቀቅ ተሳናቸው። ጸሎት አደረጉ ለቀቀላቸው። እርሱንም ወደ ቤ/ክን ወሰዱት ፥ ብዙ ድውያን በርሱ ተፈወሱ። በረከትን አገኙ። በረከቱ ይድረሰን። === የርሱን ሕይዎት አስቤ የእኔ ሕይዎት ስመለከት፦ ✔ርሱ በንጉሥ ቤት ያደገ ፣ የንጉሥ ልጅ ሆኖ ከትዳር ሕይዎት ይልቅ ምናኔን ወደደ። ✔በተፈቀደለት በሙሽርነት የጫጉላ ቤት ሆኖ ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተነደፈ ነው። እኔ በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሁኜ ፥ ልቤ በስጋ ፍትወት የተነደፈ ነው። የተፈቀደልኝን ያይደል ያልተፈቀደልኝን በማሰብ የምባክን ነኝ። ✔በክብር በንግሥና ወንበር ከመቀመጥ ይልቅ በቤ/ክን ደጅ መጣልን መረጠ። እኔ ሥልጣንና ክብርን ለማግኜት እንቅልፍ የማይወስደኝ ጉስቁል ነኝ። ✔ርሱ ክብሩ ሲገለጥ ይሸሻል። በሰው ዘንድ መናቅን ተግቶ ይፈልጋታል። በአባቱ ደጅ ሆኖ ፣ አባቱ እንዳያውቀው ራሱን ይሰውራል። እኔ ግን የሌለኝን ክብር ፥ እንዳለኝ ለማስመሰል እተጋለሁ። በሰው ዘንድ መከበርን አሳድዳለሁ። ✔ከምቾትና ድሎት ይሸሻል ፤ ለስጋው መከራና ችግር በፈቃዱ ይከተላል። እኔ መከራና ችግርን እሸሻለሁ። ምቾትን ደጅ እጠናለሁ። ✔ እርሱ በሰዎች ዘንድ ይረሳ ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቅ ዘንድ ወደደ። እግዚአብሔርም ሞቶም እንኳን በስራው የሚናገር ና የበረከት ምንጭ አድርጎ ክብሩን ለሰዎች ሁሉ እንዲህ ገለጠው። ፍፃሜው ያማረና የተወደደ ሆነ። እኔ በሰዎች ዘንድ መታወቅ እንጅ በእግዚአብሔር ዘንድ መታወቅ እንቅልፍ አሳጥቶኝ አያውቅም። የእኔስ ፍፃሜ ... ምን ይሆን? በርግጥም በእኔና በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መካከል የሕይዎት ተቃርኖ አለ። ለጸሎት ቆሜ በስሙ ስማፀን ፥ በጥቂቱ እንኳን ልመስለው ያልተጋሁ ፤ ለችግሬ ስሙን የጠራሁ መሆኔ አሳፈረኝ። እግዚአብሔር የሁላችንም ፍፃሜ ያሳምርልን። ©ዮሴፍ ጌትነት 14/02/2015 ዓ.ም
Открыть в Telegram♦የሕይዎት ተቃርኖ ♦ ይቀጥላል ... ! ሰላም ለገብረ ክርስቶስ እንተ አንደየ አባሎ በዴዴ አቡሁ አክልብት እስከነ ለሐሱ ቁስሎ አፅረፍ ዮም ለእግዚአብሔር ከመ ሰአሎ እም እደ አግብርት ተኮንኖ ወእም እደ አእማት ተጽዕሎ እምድኅረ ፈጸመ ወሠለጠ ገድሎ =====
Открыть в Telegramእንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሠን ፥ አደረሣችሁ። በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይቁሙልን። የተሰጣቸው የምሕረት ቃል ኪዳን በእግዚአብሔር ፊት የሚቆምልን የሚያማልድልን ይሁንልን። ስለ ጻድቁ ብሎ እግዚአብሔር ይማረን ፥ ይቅር ይበለን።
Открыть в Telegram♦አዚም ሕይዎት ♦ የነፍስን ጥማት የልብን መሻት ዘንግቶና ረስቶ ከጸጋ ልብስ ተራቁቶ ከድኅነት መንገድ ሸሽቶ ከጽድቅ ጉዞ ዘግይቶ ... ስለ ኃላፊና ከንቱው ነቅቶ/ተግቶ በዓለም ምኞት ተወስዶ/ተገርኝቶ ስለ ዓለም ፥ ሁሉን ትቶ ከሕይዎት ራስ ፥ ተለይቶ የስጋን እንቅብ ፥ በራስ ላይ ደፍቶ... ከክብር ማማ ወርዶ የህሊናን ክስ አፍኖ/ክዶ ከጉስቁልና ተዋድዶ/ተላምዶ... ላመኑበት ሳይታመኑ የጽድቅን ልብስ ሳይሸምኑ ከመታዘዝ ፍሬ ሳይዘግኑ ... መውጣት መግባት መምሸት መንጋት የዘመን መሸኘት የዘመን መተካት አዚም ኑሮ ፥ ከንቱ ሕይዎት በሰም ኖሮ ፥ በወርቅ መሞት 07/08/2013 ዓ.ም ©ዮሴፍ ጌትነት
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Best kerim@bestkerimРелигия2,53 тыс.
PEACE MESSAGE 📡🛰️🔊📜@peacetv0Религия2,52 тыс.
Winners Way TV@winnerswaytvРелигия2,52 тыс.
ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox@moa_tewahidoРелигия2,54 тыс.
Ustaz Ali Husen (Abu Abduslam)@alihuesnРелигия2,51 тыс.
አተ-ውሒድ.ኮም@atwhiddcomРелигия2,5 тыс.
Dagi ለፍቅር 🫶@mymotto1Религия2,48 тыс.
አህሉል ቁርአን@ahlulqurannРелигия2,58 тыс.