Кабинет

Посты канала መንፈሳዊ ግጥሞች

сначала новые

#235Текст

አሁን ስንት ሰዓት ነው?! ለተልዕኮ የሚፋጠኑ ፤ ለአገልግሎት የሚቀኑ ትጉሃን ቅዱሳን (መላእክት እና ሰዎች) ፤ ልጆች መሆንን በተግባር መግለጥ ልባምነት ነው። በሥራ እንጅ በወሬ እና በፉከራ በቀረርቶ የተጠበቀች እና የተሻገረች ደግሞም የምትሻገር ሃገር እና ቤ/ክን የለችንም። እንኳን ሌሎችን ራሳችን ለማሻገር እንኳ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል። ተቆጥሮ የማያልቅ የምናራግፈው አቧራ ፣ የምናነሣው የእንቅፋት ደንጋይ ፤ የምንነቅለው እሾህ እና አሜካላ ፤ የምንሰብረው የጠላት ወጥመድ ፣ ልንከፍለው የሚገባን የትውልድ ዕዳ የብዙ ብዙ ነው። ልንወጣበት ከሚገባን ክፉ ልማድ እና አኗኗር ለመውጣት ፤ ልንገነባው ወደሚያሻን በጎ እሴት እና ባህል ለመምጣት እጅግ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል። እያንዳንዳችን ልንሠራ የማንችልበት የሕይዎት ሌሊት አለን። ከዚያ በፊት ሠርተን ፤ አከናውነን ልንገኝ የሚገባ የቤት ሥራችን ምን ይሆን? በእኛ መኖር ሊፈታ የሚገባው ሕልም/ውል/ቋጠሮ ፣ የዕድሜያችን ጀምበር ሲዘቀዝቅ ፥ ፀሐያችን ስትጠልቅ ፤ ለትውልድ ልንተወው/ልናስተላልፈው የሚገባን ዐብይ ቁም ነገር ምን ይሆን?! ነገ ወይም የዛሬ ዓመት ትሞታላችሁ ብንባል ፥ ይህን ሳናደርግ ብለን ልንቆጭበት የምንችለው ጉዳይ ምን ይሆን?! ታዲያ ለዚህ ዛሬ ምን እየሠራን ይሆን?! የምናወራለትን እውነት ፤ መሆን የምንሻውን የልባችንን ናፍቆት/ምኞት መኖር የምንጀምረው መቼ ይሆን?! የዕለት ከዕለት የሥራ ክንውናችንስ ይህንን ለማሳካት የሚያስችል ተግባር ባለበት እንቅስቃሴ የታጀበ ይሆን ወይስ እንዲሁ በከንቱ ስንናውዝ ጊዜው ያልፋል?! 🙊ለመሆኑ !🙊 አሁን ስንት ሰዓት ነው?! <<አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሀል።>> ኤፌ 5:14 ©ዮሴፍ ጌትነት ህዳር 15/2019 ዓ•ም

Открыть в Telegram
Просмотры334+56%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#231Текст

♦የሕይዎት ተቃርኖ♦ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ የንጉሥ ልጅ ነው። ስለዚህም የወደፊት እጩ ንጉሥ ነበር ለማለት እንችላለን። መልከ መልካም የሆነች ፥ የንጉሥ ልጅ ሚስት ትሆነው ዘንድ ታጨችለት። ሰርግ ተሰረገ። ገብረ ክርስቶስ በሰርጉ ዕለት ፥ በሙሽርነት ዋለ። ከሙሽሪት ጋር ለጫጉላ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ገቡ። እነሆ ጸሎትን አደረገ ፣ ቃልኪዳን አስገባት ፣ በሌሊት ከጫጉላ ቤት ወጣ ፤ የክርስቶስን ሙሽርነት ወዷልና። በመርከብ ተሳፍሮ ረጅም መንገድ ተጓዘ። በአንድ ቤተክርስቲያን አጥር ተቀምጦ ብዙ ዓመት ኖረ። እመቤታችን ለአንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋይ ክብሩን ገለጠችለት። ገብረ ክርስቶስም እመቤቴ ሆይ ስለምን ክብሬን ለሰው ገለጥሽብኝ ብሎ ሸሸ። በመርከብ ተሳፍሮ ሲሄድ መርከቡ ወደ አባቱ ቤት አደረሰው። እርሱም በአባቱ ቤት አጥር ተጥሎ ኖረ። ያወቀው ማንም አልነበረም። የአባቱ ሰራተኞችም ሸተተን እያሉ ይጠየፉት ነበር። ቦታውን እንዲለቅ ውሃ ይደፉበት ፣ ቆሻሻ ይጥሉበት ነበር። ውሻ እንበላው ብለውም ስጋ ወደ ሱ ይጥሉ ነበር። ውሻወቹ ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር። በእንዲህ አይነት አኗኗር በአባቱ (በንጉሥ) ቤት አጥር 15 ዓመት ተጥሎ ኖረ። የሚሞትበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ የሕይዎቱን ታሪክ ፥ በወረቀት ፅፎ በእጆ ይዞ በሰላም አረፈ። በንጉሡ ደጅ የሞተውን ቅዱስ ሂዳችሁ አምጡት የሚል ድምፅ በቤተክርስቲያን ተሰማ። ሂደው አገኙት ። ወረቀቱን ሊቀበሉት ቢሞክሩ ከእጁ ማላቀቅ ተሳናቸው። ጸሎት አደረጉ ለቀቀላቸው። እርሱንም ወደ ቤ/ክን ወሰዱት ፥ ብዙ ድውያን በርሱ ተፈወሱ። በረከትን አገኙ። በረከቱ ይድረሰን። === የርሱን ሕይዎት አስቤ የእኔ ሕይዎት ስመለከት፦ ✔ርሱ በንጉሥ ቤት ያደገ ፣ የንጉሥ ልጅ ሆኖ ከትዳር ሕይዎት ይልቅ ምናኔን ወደደ። ✔በተፈቀደለት በሙሽርነት የጫጉላ ቤት ሆኖ ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተነደፈ ነው። እኔ በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሁኜ ፥ ልቤ በስጋ ፍትወት የተነደፈ ነው። የተፈቀደልኝን ያይደል ያልተፈቀደልኝን በማሰብ የምባክን ነኝ። ✔በክብር በንግሥና ወንበር ከመቀመጥ ይልቅ በቤ/ክን ደጅ መጣልን መረጠ። እኔ ሥልጣንና ክብርን ለማግኜት እንቅልፍ የማይወስደኝ ጉስቁል ነኝ። ✔ርሱ ክብሩ ሲገለጥ ይሸሻል። በሰው ዘንድ መናቅን ተግቶ ይፈልጋታል። በአባቱ ደጅ ሆኖ ፣ አባቱ እንዳያውቀው ራሱን ይሰውራል። እኔ ግን የሌለኝን ክብር ፥ እንዳለኝ ለማስመሰል እተጋለሁ። በሰው ዘንድ መከበርን አሳድዳለሁ። ✔ከምቾትና ድሎት ይሸሻል ፤ ለስጋው መከራና ችግር በፈቃዱ ይከተላል። እኔ መከራና ችግርን እሸሻለሁ። ምቾትን ደጅ እጠናለሁ። ✔ እርሱ በሰዎች ዘንድ ይረሳ ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቅ ዘንድ ወደደ። እግዚአብሔርም ሞቶም እንኳን በስራው የሚናገር ና የበረከት ምንጭ አድርጎ ክብሩን ለሰዎች ሁሉ እንዲህ ገለጠው። ፍፃሜው ያማረና የተወደደ ሆነ። እኔ በሰዎች ዘንድ መታወቅ እንጅ በእግዚአብሔር ዘንድ መታወቅ እንቅልፍ አሳጥቶኝ አያውቅም። የእኔስ ፍፃሜ ... ምን ይሆን? በርግጥም በእኔና በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መካከል የሕይዎት ተቃርኖ አለ። ለጸሎት ቆሜ በስሙ ስማፀን ፥ በጥቂቱ እንኳን ልመስለው ያልተጋሁ ፤ ለችግሬ ስሙን የጠራሁ መሆኔ አሳፈረኝ። እግዚአብሔር የሁላችንም ፍፃሜ ያሳምርልን። ©ዮሴፍ ጌትነት 14/02/2015 ዓ.ም

Открыть в Telegram
Просмотры828+288%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#230Фото
Просмотры600+181%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#229Фото
Просмотры905+324%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#228Фото
Просмотры789+269%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#226Превью ссылки

ጌታችን ሆይ ! የስደተኞች መጠጊያ የመሰደዱ ነገር ድንቅ ነው። የዓለም ሲሳይ የመራቡ ነገር ዕፁብ ነው። የውሃ ፈጣሪ ውሃን የመከልከሉ ፥ ውሃን የመጠማቱ ነገር ግሩም ድንቅ ነው። የሰራዊት ጌታ ከሄሮድስ ፊት የመሸሹን ነገር ማሰብ እጅግ ልብን ይነካል። ♦እርሱ ነቢያትን በእሳት ሰረገላ የሚነጥቅ ፤ በነፋሳት ትከሻ የሚያመላልስ ያለ ድካም የሚያመላልስ ነው። እርሱ ግን ከእናቱ ፣ ከዮሴፍ ና ከሰሎሜ ጋር የግብፅን በርሃ የአሽዋ ግለት ፣ የፀሐይ ትኩሳት ፣ የእሾህ መወጋት ይታገስ ዘንድ ወደደ። አቤቱ ምን አይነት ትፅግስት ነው? ♦እርሱ ለእስራኤላውያን ፥ መናን ከሰማይ እያወረደ የሚመግብ ፣ ውሃን ከዓለት ድንጋይ ላይ ያፈለቀላቸው ነው። መጋቤ ዓለማት የፍጥረታት ሁሉ ሲሳይ ነው። አንድም ! ቅዱሳን ምግብ ና ውሃ ሳይሹ ፥ ጠግበው እንዲኖሩ የሚያስችላቸውን ጸጋ የሚያድል ባለ-ጸጋ ነው። ርሱ ግን ስለ እኛ ይራብ ፣ ይጠማ ዘንድ ወደደ። የሚበላ ቁራሽ ምግብን ና የሚጠጣ ውሃን ይለምን ዘንድ ፈቃዱ ሆነ። "ራሱን ድሃ አደረገ" እንዲል መጽሐፍ። አቤቱ ! ምን አይነት ትህትና ነው? ♦መላእክት እንደ ሻሽ ተነጥፈው ፣ እንደ ቅጠል ረግፈው ፣ በፊቱ ወድቀው የሚሰግዱለት ፤ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት ፤ የሰራዊት ጌታ ልዑል ሆኖ ሳለ ፤ ከፈርዖን ሽሽት ወደ ግብፅ ተሰደደ። አቤቱ ምን አይነት ቸርነት ነው? ♦የስደተኞች መጠጊያ ፤ ተሰደደ ። ፍጥረታትን ከድካማቸው የሚያሳርፍ እርሱ በስጋ ደከመ። ጌታ ሆይ "ይህን ሁሉ ስለምን አደረግህ?" ብዬ እጠይቃለሁ። በእውነት ፥ የሰውን ልጅ ስለማፍቀርህ ፣ እኔን ስለመውደድህ ያደረግከው ነው። አወ ! ♣ አቤቱ መሰደድህ ፥ መፍለስህ ፣ ወደ ግብፅ መውረድህ ፤ ከፍቅርህ የተሰደድኩ ፤ ካዘጋጀህልኝ መንግስት የፈለስኩ ፤ ከክብር የወረድኩ እኔን ወደ አንተ ትመልሰኝ ፣ ወደ መንግስትህ ታፈልሰኝ /ርስትህን ታወርሰኝ/ ፣ ወደ ላይ/ክብር ቦታ/ ታወጣኝ ዘንድ ነው። ♣ አቤቱ ወደ ተዳደፈች ዓለም መምጣትህ ፣ ጣዖት ወደ ሚመለክባት ግብፅ መውረድህ ፤ በኪደተ እግርህ የረከሰውን ትቀድስ ፣ ትባርክ ፥ ጣዖታትን ትሰባብር ዘንድ ነው። ♣አቤቱ መራብ መጠማትህ ፤ የተራብኩ የተጠማሁ እኔ እጠግብ እረካ ዘንድ ነው። ♣አቤቱ የበረሃውን ዋዕይ ግለት ፣ በእሾህ መወጋት መታገስህ ፤ ከሲዖል እሳት ታድነኝ በነፍሴ ላይ የተተከሉ እሾህና አሜካላዎችን ትነቅልልኝ ዘንድ ነው። ጌታዬ ሆይ ! ጣዖት አምልኮ ወደ ነገሰባት ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ወደማታውቅ ወደ ረከሰች ስፍራ አንተ ከእናትህና ከወዳጆችህ ጋር ሄድክ። ጣዖቱን ሰባበርክ ፣ ምድሪቷን በኪደተ እግርህ ቀደስክ ስለዚህም የገዳማውያንና የቅዱሳን መፍለቂያ ለመሆነ የሚያስቻላትን በረከት አገኘች። በቅዱሳኑ ላይ አድረህ በቅድስና ሰማይ ከብረህ የምትመሰገን አንተ ና ወደ "ግብፅ እኔ" ተሰደድ ፤ ወደ እኔ የሕይወት ዝቅታ ውረድ። ይህም ስደተኛውን ልጅህን ከስደት ትመልሰኝ ፣ ከፍ ታደርገኝና ለክብር ታበቃኝ ዘንድ ነው። አቤቱ ግብፅን የሚመስል ሕይዎት ወዳለኝ ወደ እኔ ሕይዎት ከወዳጆችህ ጋር ቶሎ ና ስል እለምንሃለሁ። ይህም የረከሰ ሃሳቤን ፣ የተዳደፈ ልቤን ትቀድስና ትባርክልኝ ፥ በረሃ ልቡናዬን የበረከትና የፍሬ መገኛ የበጎ ሃሳብ መፍለቂያ ታደርግልኝ ዘንድ ነው። ደግሞም በልቤ የነገሠ በአእምሮዬ የሚመላለስ ና አሳቤን የተቆጣጠረውን አምልኮ ጣዖት ትሰባብርልኝ ፣ ታጠፋልኝ ፣ ታቀልጥልኝ ዘንድ። ይህም በእኔ የሰለጠኑትን የእውቀትና የውበት ፣ የገንዘብንና የስልጣን ፣ የክብርና የዝናን ፣... ጣዖታት ከእኔ ታጠፋልኝ ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ እንደ ሾህ የሚወጉኝ ክፉ ፍትወታትን ነቃቅለህ ትጥልልኝ ዘንድ የማቀርብልህ ልመናዬ ነው። ኢሳ 19፥1 ድንግል ሆይ ! ከልጅሽ ከፍቅርሽ ፥ለተሰደድኩ ልጅሽ መድኃኒትና ፈውስ ፥ ይሁነኝ ስደትሽ። ©ዮሴፍ ጌትነት 27/01/2014 ዓ.ም https://t.me/bieteyoseph

Открыть в Telegram
Просмотры892+317%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#225Фото

ወንድሞች ሆይ ! እናንተም የሥጋውን መዳን እንደተመኘ ወንበዴ ሳይሆን ከዘላለማዊ ሕይዎት ውጭ ለሌላ ለምንም ነገር ደንታ እንዳልነበረው ሰው መንፈሳዊያን ሁኑ። ጌታችን በመንግሥቱ እንዲያስብህ የምትሻ ከሆነ አንተም በምድር አስበው። ጌታችን በማፍቀርና በማክበር ላይ የተመሠረተ ምድራዊ ሕይዎት ሳይኖርህ ፤ በሰማይ ከእርሱ ጋር የመኔር ዕቅድ ልትነድፍ አትችልም። በጸናት ታገል እንጅ ፥ መከራን ተሰቅቀህ <<ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ>> የሚለውን የርህራሄ ድምፅ ከምታደምጥበት መስቀልህ አትውረድ። እውነተኛ ፀፀት ፣ ለንስሓ ያዘነበለ ልብና በእምነት የተሞላ ልመና ፤ የአንድን የተበላሸ የሕይዎት ታሪክ ያለውን ሰው ዕድል እንዴት እንደወሰኑት ልብ በል። ጌታችን ለወንበዴው ጥያቄ የሰጠው ፈጣን ምላሽ እግዚአብሔር ለልመናችን ቅርብ ስለመሆኑ በቂ ማሳያ ነው። የጥጦስ የመስቀል ላይ ቆይታ የጌታ ወዳጅ የመሆን የማይተመን ዋጋ አስገኝቶለታል። በእርግጥ ! በገነት መኖር አስደሳ ነው ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከጌታችን ጋር ለመኖር የሚያስችል ዕድል ስለሚሰጠን ነው። ገነት ያለ ጌታ ፥ ምንም ነች ፤ የደስታ ምንጭ ልትሆን አትችልም። እነዚህ ጥቂት ሰዓታት የሚያስገነዝቡን እውነት ፥ እውነተኛና ጥልቀት ያለው እምነት የጌታችንን ልብ መንካት እንደሚችሉ ነው። ዋናው ጉዳይ ልምናህን ያቀረብከው ምን ያህል ከልብህ ነው የሚለው ነው። የጸሎት ርዝመትና ውትወታ ብቻውን ልዩነት መፍጠር አይችልም። ከዚህ ይልቅ ጥልቅ ስሜትህን የተሸከሙ ቃላት እጅግ ሲበዛ ውጤታማ ናቸው። በጥልቀት ተናገር ከጌታችንም ጋር ጥልቅ ግንኙነት መሥርት ፤ ያኔ ጥልቀት ያለውን የጌታችንን እምነት ታገኛለህ።

Открыть в Telegram
Просмотры500+134%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#224Фото
Просмотры488+128%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#223Текст

🌹አመ አሚሩ ለጥቅምት ዘቀዳማይ ጽጌ በዓለ ልደታ ወራጉኤል ሥርዓተ ማሕሌት🌹 ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ🥇 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። ትርጕም🌹 አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ፤ ጩኸቴም በፊትኽ ይድረስ ምስጋና አቀርባለኹ፤ ፊትኽን ከእኔ አትመልስ በችግሬ ጊዜ ጆሮኽን ወደ እኔ አድምጥ ምስጋና አቀርባለኹ በምጠራኽ ጊዜም ፈጥነኽ ስማኝ ምስጋና አቀርባለኹ ለዘለዓለሙ ምስጋና አቀርባለኹ።ይህ ማለት ያለ ልዑል እግዚአብሔርን እናመስግነው ማለት ነው። በአንዲት ቃል ዓለምን ኹሉ የፈጠረ አምላክ ፈጽሞ የተመሰገነ ነው። መልክዐ ሥላሴ 🥇 ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም። ትርጕም🌹 መዝጊያው ሰላም ለሆነ ለአፋችሁ ሰላምታ ይገባል፤ የተዋህዶ ዱር አበባ ሥላሴ! አምልኮቴን በፍጹም ጸጋችሁ ጣዖትን ከማምለክ አንድ ዲናር ወደመጪው ዓለም ገንዘብ አንድ አምላክ ለውጡ። ዚቅ🥇 ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎሙ፤ናርዶስ ጸገየ ውስተ አፉሆሙ፤ ትርጕም 🌹 የሥሉስ ቅዱስ ቃላቸው ጣፋጭ ነው፤ ሽቱ በአፋው አበበ። መልክዐ ሥላሴ(ዘላይ ቤት) 🥇 ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዐለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡ ትርጕም 🌹 በአካል ለተካከሉ ኵልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል፤ ሥላሴ! ከእናንተ አንዱ እግዚአብሔር ቃል ዓለማችሁን ለይቅርታ በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ በቀራንዮመሰ መድኀኒት መስቀል ተተከለ። ዚቅ 🥇 እምሥርወ ዕሴይ ሠሪፃ፤ ወእምዘርዐ ዳዊት ተወሊዳ፤ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ ወከመ ሮማን መላትሒሃ፤ ኅብስተ ሕይወት በየማና ወጽዋዐ ወይን በጸጋማ፤ ጸሎታ ወበረከታ ይኩነነ ወልታ። ትርጕም 🌹 ውቧ ድንግል ከዕሤይ ሥር በቅላ ከዳዊትም ዘር ተወልዳ ነፍሴ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች አለች፤ ከንፈሮቿ እንደ ቀይ አበባ ናቸው ጉንጮቿም እንደ ሮማን ናቸው፤ የሕይወት እንጀራ በቀኟ የወይን ጽዋም በግራዋ አለ፤ ልመናዋና በረከቷ ጋሻ ይሁነን። ማሕሌተ ጽጌ 🌹 ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ  እምዐጽሙ፤ለዘአምኀኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ወበእንተዝ ማርያም ሶበ  ሐወዘኒ መዐዛ ጣዕሙ፤ለተኣምርኪ አሐሊ እሙ፤ማሕሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡ ትርጕም 🌹 አበባ የተባልሽ ድንግል! ከገብርኤል ሰላምታ ጋር እጅ ከነሣሽ ሰው አጽም አበባ በቅሎ ታየ፤ ስለዚህም እናቱ ማርያም! የተአምርሽ የጣዕሙ መዓዛ ደስ ባሰኘኝ ጊዜ ስሙ ማሕሌተ ጽጌ የተባለ ምስጋናን አመሰግናለሁ። ዚቅ🥇 ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዐቢይ ልዕልናከ ወመንክር ስብሓቲከ፤ለዕረፍት ሰንበተ ሠራዕከ ። ትርጕም 🌹 እነሆ አበባ ታየ፤ ሙሽራይቱም ወልድ ወንድሜ እንደ ከርቤ ይሸታል አለች፤ ነቢዩ ዕንባቆምም የወልድን ሥራ አደቅሁ አለ፤ ልዕልናህ ታላቅ ጌትነትህም የሚያስደንቅ የሆነ የሰላም ንጉሥ ክርስቶስ! ሰንበትን ለእረፍት አዘጋጀህ። ማሕሌተ ጽጌ(ዘላይ ቤት) 🥇 ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ፤ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ፤ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ፤እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ፤መድኀኒተ ኵሉ ዐለም እስመ ኮንኪ አንቲ። ትርጕም 🌹 ሐና አንቺን ያበበችባትና ሟች ኢያቄም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት የደስታ ሰዓት ምንኛ የተባረከች የተቀደሰች ናት?! አንዲቷ ርግቤ! ተአምርሽን አከብራለሁ የዓለም ሁሉ መድኀኒት አንቺ ሆነሻልና። ዚቅ🥇 ሰአሉ ለነ ሐና ወኢያቄም ዘወለድክምዋ ለማርያም ቤዛዊተ ኲሉ ዐለም። ትርጕም 🌹 ዐለምን ሁሉ የምታድን ማርያምን የወለዳችሁ ሐና እና ኢያቄም! ለኛ ለምኑልን። ማሕሌተ ጽጌ 🌹 ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተኣምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ። ትርጕም 🌹 መሽራይቱ! ከትንቢት አንበሳ ጉድጓድ በወጣሽ ዕለት የንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ ተአምርሽን በሚናገሩ በደስተኞች ማኅበር መካከል የሐና አበባ! እዘምርልሻለሁ፤ የደስታ መንገድንም ወተትን እንደሚጠባ እንቦሳ አስተውላለሁ። ዚቅ 🥇 ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን። ትርጕም🌹 ሰሎሞን የሐና እና የኢያቄም ልጅ ማርያምን የብርሃን ደመና አበባ ነሽ። ማሕሌተ ጽጌ🌹 እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተኣምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ትርጕም 🌹 ርግቤ! ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን አቅፈሽው በንጽሕናና በተአምር ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ከለቅሶ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ፤ መላካሜ! ደስ ከተሰኘ (ከሚያሰኝ) ገብርኤልና እንዳንቺ ቸር ከሆነ ሚካኤል ጋርም ነይ። ዚቅ 🥇 ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር፤ ወኢ ምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ። ትርጕም 🌹 ከአንበሶች ጉድጓድ ትወጣለች፤ መልካሟ ርግብ! ከነገሥታት አዳራሽ ከሃይማኖት በፊት ነይ፤ ሁለመናሽ መልካም ነው በላይሽ ላይ ነውር ምንም ምን የለብሽም፤ መልካሟ ርግብ ነይ፤ ርግቤ ነይ። ማሕሌተ ጽጌ 🌹 ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ ትርጕም🌹 የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቍር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) እርሱም ላንቺ ይሰግዳል ። ዚቅ🥇 ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ፤ ወትምክህተ ቤቱ ለ፳ኤል። ትርጕም🌹 አንቺ በነቢያት አፍ የተመሰገንሽ ነሽ፤ በሐዋርያትም የከበርሽ ነሽ፤ የጊዮርጊስ የመባረኩ አክሊል የያዕቆብም የወገኑ መመኪያ ነሽ። ዓዲ ዚቅ🥇 ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቍ ድዳ፤ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ፤ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ፡፡ ትርጕም🌹 መሠረቷ ዕንቍ የሆነላት አዳራሿም ጳዝዮን የሆነላት ነጯ ርግብ ዛሬ በይሁዳ ምድር ተወለደች። ሰቆቃወ ድንግል 🌹 በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕፀተ ግጻዌ ዘአልቦ፤ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤ከማሃ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ በኵለሄ ረከቦ፤ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ። ትርጕም🌹 የገጽ ጉድለት በሌለው ሦስትነት ባለው እግዚአብሔር ስም የድንግልን ለቅሶ በእንባ ቀለም እጽፋለሁ፤ ያነበበውም ወዮ  ይበል፤ ዓይነ ልቡና ያለውም እንደሷ ኀዘንና ስደት በየቦታው ባገኘው ጊዜ አይቶ ያልቅስ። ዚቅ🥇 እወ አማን እምውሉደ ሰብእ አልቦ፤ምንዳቤ ወግፍዕ ዘከማኪ በውስተ ኵሉ ዘረከቦ፤ ትርጕም🌹 አዎ በእውነት ከሰው ልጆች እንዳንቺ ችግርና መገፋት በየቦታው የደረሰበት የለም። መዝሙር🌹🌹🌹 ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ትዌድሶ መርዓት፤እንዘ ትብል ነዓ ወልድ እኁየ፤ንፃዕ ሐቅለ፤ትዌድሶ መርዓት ንርዓይ ለእመ ጸገየ ወይን፤ወለእመ ፈረየ ሮማን፤ትዌድሶ መርዓት አሠርገወ ሰማየ በከዋክብት፤ወምድረኒ በስነ ጽጌያት፤ትዌድሶ መርዓት እስመ ውእቱ ወልድ ዋሕድ፤እግዚኣ ለሰንበት፤ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ፤ ወልድ እኁየ ቃለከ አዳም። ትርጕም🌹 ሙሽራዋ ወንድሜ ወልድ! ወይን ካበበ ሮማንም ካፈራ እናይ ዘንድ  ወደ በረሐ እንወጣ ዘንድ ና እያለች ታመሰግነዋለች፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርንም በአበባዎች ውበት ሸለመ ዋሕድ ወልድ የሰንበት ጌታዋ ነውና፤ ወንድሜ ወልድ ቃልህ ያማረ ነው እያለች ሙሽራዋ ታመሰግነዋለች። @geeZzlekulu 1️⃣ @geeZzlekulu2 👉

Открыть в Telegram
Просмотры835+291%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#222Фото

እመቤቴ የተመረጥሽ ድንግል ማርያም ሆይ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ አምላክ ካንች ጋር በመሰደዱ በግብፅ መከራሽ እማልድሻለሁ፡፡ መንገድ በመሄድ የድካምሽ አሳብ በልጅሽ ፊት ይቆም፡፡ ስለ ኃጢአቴ መማለጃ ይሆን ዘንድ፡፡ ካይንሽ የፈሰሰው የዕንባ ጎርፍ በፊትሽ የተንጠባጠበው በልጅሽ በወዳጅሽ ፊትም የወረደው አሁንም ደግሞ በልጅሽ በወዳጅሽ ፊት ይቁም፡፡ ስለ ኃጢአቴ ማዘከርያ ይሆን ዘንድ፡፡ የሠራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ ፡፡ አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናየ እጅግ ደነገጠ፡፡ የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናየ እጅግ ደነገጠ፡፡ አንድ ሰዓት ስንኩዋን ኃጢአት ለመሥራት አላቁዋረጥኩም፡፡ በሰውና በመላእክት ጉባኤ መሐል ራቁቴን መቆሜን አሰብኩ፡፡ በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስኩ፡፡ ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ ፤ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሣምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ፡፡ ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትችይውን አንችን አማላጅ አገኘሁ፡፡ ዘወትር ከእኔ እንዳትርቂ አወቅሁ፡፡ እንድህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቸ አይደለም፡፡ በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም፡፡ በዕደ ሕሊና ያዝሁሽ በዕደ ሥጋ አይደለም፡፡ እደ ሕሊናየን ግን የሰው ኃይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም፡፡ ልትደግፊኝ ያዝሁሽ ልትጥይኝ አይደለም፡፡ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጅኝ ግን አይደለም፡፡ ለዘላለሙ ያዝሁሽ ለዕድሜ ልክ ብቻ አይደለም፡፡ እናቴ ሆይ ነፍሴ ባንች ዘንድ ትክበር ስለ ቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ፡፡ ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደ ወደቅሁም እቀር ዘንድ አትርሽኝ፡፡ [አርጋኖን ዘሠሉስ]

Открыть в Telegram
Просмотры660+209%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#220Фото
Просмотры723+238%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#219Текст

ስለ ትህትና <<ትሕትና ያለ ሥራ እንኳን ቢሆን ለብዙ በደሎች ይቅርታን ታስገኛለች ፤ ያለ እርሷ ግን ምግባሮቻችን ሁሉ ምንም በቁዔት የላቸውም።>> [ማር ይስሐቅ] <<ትሕትና ዘወትር ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትን ትቀበላለች ፤ የልብ ጥንካሬና የእምነት ማነስ ግን ከአስፈሪ መከራዎች ጋር ያታግላሉ።>> [ማር ይስሐቅ] <<በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ስትወድቅ ፥ በአሳብህ እንደ ጉንዳን ፥ በምድር ላይ እንደሚሳቡ ፍጥረታት ፣ እንደ ዐልቅትና ንግግር እንደማይችል ትንሽ ሕፃን ኹን። በእውቀት ተሞልተህ በፊቱ ምንም አትናገር ፤ ነገር ግን አባቶች ለታናናሽ ልጆቻቸው የሚያሳዩትን ያን አባታዊ ጥበቃ ትቀበል ዘንድ ፥ በሕፃንነት አሳብ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ ፥ በፊቱም ተመላለስ። <እግዚአብሔር ሕፃናትን ይጠብቃል> ተብሎ የጽፏልና። ••• ይህም በአካል ትናንሽ ለሆኑት ብቻ ሳይኾን በዚህ ዓለም ጥበበኞች ሁነው ሳለ ዕውቀታቸውን ለሚተውና ሙሉ በሙሉ በዚያች በሌላዋና ኹሉን ቻይ በኾነችው ጥበብ ለሚተማመኑትም ጭምር ነው። እነዚህ በገዛ ፈቃዳቸው እንደ ሕፃን በመኾን በትምሕርት ድካም የማይገኘውን ያን ሌላ ጥበብ ይማራሉ።>> [ማር ይስሐቅ>> <<በጸሎት ድካምና በልብህ ጭንቀት አማካኝነት ልባቸው ከታወከ ሰዎች ጋር ተባበር ፤ ያን ጊዜ የምሕረት ምንጭ ለልመናህ ይከፈታል።>> [ማር ይስሐቅ] መንፈሰ ጠንካራ የሆኑ ሰዎች ስድብንና መቃለልን በክብርና በውዴታ ይታገሣሉ። ያለ ምንም ጉዳት በምስጋናና በውዳሴ መካከል ማለፍ የሚችሉት ግን ቅዱሳንን ንጹሐን ብቻ ናቸው። [ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው] <<ትሕትናውን የሚገልጠው ራሱን የሚነቅፍ ሰው አይደለም (ደግሞስ እያንዳንዱ ሰው በሆነ መንገድ ራሱን መያገሥ የለበትምን?) ፤ ይልቅስ ትክክለኛው ትሑት ፥ የነቀፈውን ሰው መውደዱን የሚቀጥል ነው እንጅ።>> [ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋሰው] <<ራስህ በዓይንህ የተናቀ ቢሆን የአጋንንት ሠራዊት ይገዙልሃል ፤ የእውቀትም ምንጭ ይከፈታል።>> [ማር ይስሐቅ]

Открыть в Telegram
Просмотры776+263%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#218Текст

<<የInsulin እጥረት>> [የሃገራችን ጽኑ ደዌ] ስለ ስኳር በሽታ ሳስብ/ሳስተምር ፥ ቀድማ የምትመጣልኝ ታማሚ ፥ ሃገራችን ናት። አሁን ከተደረሰበት ሳይንስ አንፃር በጎላ እና በተረዳ የተወቁትን የስኳር በሽታ አይነቶች በሦስት ምድብ ልንከፍላቸው እንችላለን። (ሌሎች ቢኖሩም ከጠባያቸው እና ከመሠረታዊ የሕክምና እንዲሁም የክትትል ጠባያቸው አንፃር በዚሁ እናካታቸው።) እነዚህም፦ 1- Type 1 DM 2- Type 2 DM 3- Gestational DM በሚል ምድብ ሊካተቱ ይችላሉ። የመጀመርያው አይነት የስኳር በሽታ በInsulin እጦት ይከሰታል። (Absolute/relative Insulin defficiency) ሁለተኛው የስኳር በሽታ አይነት ላይ ደግሞ Insulin ተጠቅመው ሥራቸውን ሚሠሩ Cells ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠት እንዲሁም በInsulin መጠን ማነስ ሊከሰት ይችላል። (Insulin resistance and relative insulin deficiency) ሦስተኛውን አይነት የስኳር በሽያ ከእነዚህ ምድብ አለማካተቴ ዋነኛ ችግሩ ከ Insulin የዘለለ በመሆኑ ሳይሆን ፤ የችግሩ ታሪክ ፣ የበሽታው ጠባይ እና የክትትሉም አይነት ከእርግዝና ጋር የተገናኘ ሰሞንኛ አጃንዳ ስለሆነ ነው። እስኪ ለዛሬ ስለ መጀመርያው የስኳር በሽታ አይነት እናውራ! በሽታው ከሽማግሌዎች ይልቅ ሕፃናት እና አዳጊዎች ወጣቶች ላይ ይዘወተራል። ከሁለተኛ ደረጃ አይነት የስኳር በሽታ በተለዬ መልኩ ከወፍራሞች ይልቅ ቀጭኖች ላይ የተለመደ ነው። (ቀጭን በመሆን ይመጣል ማለቴ ሳይሆን ፤  ወፍራም የሆኑ ሰዎች የበሽታው ምልክት ኑሮባቸው ቢመጡ ዕድሜያቸውንም ጭምር አገናዝበን ፤ ሁለተኛውን አይነት የስኳር በሽታ የበለጠ እናስባለን።) ምልክቶቹ ብዙ ውሃ መጠጣት - ብዙ መሽናት ፤ ብዙ መራብ ፣ ብዙ መብላት እናም መክሳት። የምርመራ ውጤት የስኳር መጠን መብዛት (ከልክ ማለፍ) Blood Sugar የችግሩ ምክንያት የInsulin እጥረት ! ለሰውነታችን የInsulin ጥቅሙ ምን ነበር? 1- የሰውነታችን Cells - glucose እንዲጠቀሙ ማድረግ 2- የሰውነት ግንባታ - ይህም Glucoseን ከመጠቀም ባለፈ እንዲጠራቀም (Storage) ፣ Protein & Fat በተደራጀ እና በሚፈለግ ሁኔታ እንዲቀመጡ እና ሰውነታችን እንዲገነባ ያደርጋል። በመጀመርያው አይነት የስኳር በሽታ ምን ያጋጥመናል! የInsulin እጥረት ! ስለዚህም ሰውነታችን ውስጥ ብዙ ስኳር አለ ሕዋሳቶቻችን ግን ስኳርን ይራባሉ። ምክንያቱም ለመጠቀም የሚያስችላቸው ድልድይ (Insulin) የላቸውምና። ስለዚህም አእምሮ የሕዋሳትን መራብ ተረድቶ የስኳር መጠንን ለመጨመር የምግብ ፍላጎትን ይጨምራል። በአንድም በሌላም በሰውነታቸውን ያለውን የስኳር መጠን ይጨምራል። የሚመረተው ስኳር ግን ፥ ለሚያስፈልጋቸው እና ተጠቀመው ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ለሚፈለጉ ሕዋሳት አይደርስም። ይህም ከኩላሊት የማጣራት አቅም በላይ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ሰውነት እየተራበ ስኳር  ከሰውነት ተርፎ በሽንት መልኩ ይወገዳል። ይህንንም ስኳር ተከትሎ ውሃ ይወጣል። ብዙ ስኳር ብዙ ውሃ እያስከተለ መውጣቱን ይቀጥላል። ይህም ስኳት መሽናት ውሃ መጠማትን ይወልዳል። መሽናት መጠጣት ይቀጥላል •••። ለሰውነት ግንባታ ሊውል የሚገባው ቅባት (Lipid) እና ገንቢ ንጥረ ነገር (Protein) ፤ ስኳርን ተክቶ ኃይል እንዲሰጥ መመዝበር ይጀምራል። <<ለምን?>> ከተባለ ! Insulin ስለጎደለ። ጉዳይ እና ባለ ጉዳይን የሚያገናኝ ስለጠፋ። ይገርማል ! ስኳር ተርፎ የሚደፋበት ሰውነት (በሽንት) ፤ ሙሉ የሰውነት ሕዋሶቹ ስኳር አጥተው እና ተርበው የሚሰቃዩ ፥ ከሌላ ተውሰው (ስብ አቅልጠው) ለመኖር የሚገደዱ ይሆናሉ። እየበሉ መራብ ፣ እየበሉ መክሳት እየጠጡ መጠማት። የሰውነት ታሪክ ሁኖ ይቀጥላል። በሃገራችን ላይ የተከሰተው ትልቅ እና መሠረታዊ በሽታ ይሄው እንደሆነ አስባለሁ። በብዙ የሙያ ዘርፎች የካበተ ልምድ ፣ እውቀት እና ክህሎት ያላቸው ብዛት ያላቸው ምሁራን ( የሰው ሀብት) እያላት ፤ ሰው ትራባለች። በሀገራችን በሁሉም ዘርፍ ብዙ  ጽኑ ሕመሞች ብቻም ሳይሆን ብዙ ብልህ እና አዋቂ ባለመድኃኒቶችም አሉ። ነገር ግን ሁለቱን የሚያገናኝ ስርዓት ይጎድላል። ሀገራችን መጠቀም ያቃታት የሰው ሀብት ከእርሷ በአፍኣ ወዳሉት ወደ ጎረቤት ሃገራት እንደዘበት ይፈስሳል/ይደፋል። እርሷ ልትጠቀመው ያልቻለችው ፥ የተፈጥሮ ሀብት (ጥሬ ዕቃ) ወደ ሌሎች ሀገሮች ይደፋል። እርሷ ግን አሁንም ሰው እና የተፈጥሮ ሀብትን በጉያዋ ታቅፋ ደግሞም እየደፋች የምትራብ ምስኪን ሃገር በመሆን ጸንታለች። በዚህም ያለንን ስኳር መጠቀም አቅቶን ለብዙ ትላልቅ ጉዳዮቻችን የሚያስፈልገንን እምቅ ጉልበት እና አቅም (Lipid & Protein) ወደ ስኳርነት ደረጃ እያወረድን ለመጠቀም ተገድደናል። ስለዚህም ምንም ያክል የተትረፈረፈ ሀብት (Glucose) ቢኖረን ፤ መጠቀም የቻልነው አይደለም። ሊገነባን የሚችለው የሰውነት ቅባት እና ገንቡ ንጥረ ነገር በከንቱ ይቀልጣል ፥ ይቃጠላል። ዕድሜን ስለማስቀጠል ከቅባትነት እና ከገንቢነት ማዕረጉ ወርዶ በስኳርነት ግብር ዘመኑን ይሸኛል። ስለዚህም ከመወፈር ፣ ከመታደስ ከመገንባት ይልቅ ፤ በልተን መክሳት ፣ እያደርን መጠውለግ እና መፍረስ የሰውነት (የሀገር) ግብር ሁኖ ይገኛል። ለምን ከተባለ በሃገር ሰውነትነት ውስጥ የሰው ሀብትን ከተፈጥሮ አገናኝቶ ለሀገር ጤና የሚያመጣ ድልድይ Insulin ይጎድላታል። እግዚአብሔር ከበሽታችን ይፈውሰን ! ©ዮሴፍ ጌትነት 25/03/2018 ዓ•ም https://t.me/bieteyoseph

Открыть в Telegram
Просмотры649+204%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—