Переслано из 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
⁉️የፍጥረታት መጀመሪያ እና የስድስት ቀናት እውነተኛ ታሪክ እንዴት ተጻፈ❔ 📖«መጽሐፈ አክሲማሮስ» ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሙሉ ፒዲኤፍ (PDF) በአማርኛ ለማንበብ ይቀላቀሉ 👇 👇👇 ✅https://t.me/BookMereja ✅https://t.me/BookMereja
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ። . . . ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።
По дню публикации
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 28 окт. 2026 г. | 6 585 |
| 14 нояб. 2026 г. | 3 260 |
| 15 нояб. 2026 г. | 3 140 |
| 21 нояб. 2026 г. | 1 800 |
| 25 нояб. 2026 г. | 336 |
Переслано из 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
⁉️የፍጥረታት መጀመሪያ እና የስድስት ቀናት እውነተኛ ታሪክ እንዴት ተጻፈ❔ 📖«መጽሐፈ አክሲማሮስ» ዘቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሙሉ ፒዲኤፍ (PDF) በአማርኛ ለማንበብ ይቀላቀሉ 👇 👇👇 ✅https://t.me/BookMereja ✅https://t.me/BookMereja
Открыть в TelegramПереслано из Orthodox Tewahedo
❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ መልካም ዕድል!!!
Открыть в Telegram#እንኳን_ለሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን♥♥♥ #ጎጆ_ቀለስኩልህ (በሰመረ ፍስሃ) በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡ ...................ወዲህ ሲመልሰኝ ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ ...................ጉድፌን አፅድቶ ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡ ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡ ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡ የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡ ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ... የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ ሁሌ 'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡ ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡ እናም ሚካኤል ሆይ.... ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡ ❖==✿==❀==✞==❀==✿==❖ @MENFESAWItsufoche ✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
Открыть в Telegramእንኳን ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቁስቋም በዓል እና ለወረሃ ጽጌ ፆም ፋፃሜ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን! ገሊላ እትዊ ሀገርኪ ገሊላ እትዊ 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 @MENFESAWItsufoche 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
Открыть в Telegram፨ጨረስኩ ሳልጀምረው፨ 📝✏️ ከፊደላት ተራ ከሆህያት ገብቼ ክብርሽን ለመግለጽ አሙልቼ አስፍቼ አበው ሲናገሩ ስላንቺ ሰምቼ ቃላትን ከቃላት መርጬ አሳክቼ። <ሀ>ብዬ ጀመርኩኝ ልናገር ጸጋሽን መጽሐፍ ከሚለው በልቢም ያለውን አባቶች ቅዱሳት ያስተላለፉትን በሕይወት ከነሱ የተቀበልኩትን። ከነ<ሀ> ነጎርቤት ከነ <ለ> አዝማዳት በሰባት በሰባት ከተከፋፈሉት ከላይ እስከታች የተደረደሩት እስከነ <ፐ >ድረስ ከተሰበሰቡት። ያንንም ሳወጣው ይንንም ስመዘው ጥንት የመረጥኩትን መልሼ ስተወው ፊት ያስገባሁትን ኃላ ስመልሰው አንዱን አስገብቼ ሌላውን ሳወጣው ፈጽሜአለሁ ብዬ የፃፍኩትን ሳየው ድንግል ውዳሴሽን ጨረስኩ ሳልጀምረው። 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ @MENFESAWItsufoche 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
Открыть в Telegram*እቴ ውቤ* እቴ ውቤ ሙሽራዬ/2/ የባሕርየ መመኪያዬ የክብር አክሊል መጽናኛዬ፡፡ ምሥራቅ ሆነሽ ፀሐይን ወልደሽ ደኅንነት ሰላም በእጅሽ ይዘሽ ለዲያብሎስ መርዶ ሆነሽ፡፡ ሻማ ሆነሽ ልታበሪ ድርሺልኝ ስትበሪ፡፡ ሱላማጢስ አንቺ እናቴ/2/ ፈጥነሽ ነይ እመቤቴ በአንቺ ሊጠግ የአዳም ቁስሉ ሊጠፋልን ሊከስምልን ያ የሲኦል ነበልባሉ፡፡ እቴ ውቤ እመቤቴ/2/ ፍጠኚልኝ ነይ በሞቴ ለእርቃኔ ልትሆኚኝ ልብስ ለሕመሜ ልትሰጪኝ ፈውስ ረሀቤም እንዲታገስ ሕብስት ይዘሽ ሆነሽ መቅደስ ውዴ ነይ ከሊባኖስ፡፡ ክብር ሰጥቶሽ ህያው ልጅሽ ወረቅ ለብሰሽ ተጎናፅፈሽ የምትቆሚ በልጅሽ ቀኝ እኔ ኃጡኧን አማልጅኝ አክብሪኝ ውዴ እርሺው ያን ቤትሽን የቀድሞውን ያባትሽን፡፡ ውቤ ውዴ እመቤቴ/2/ የክብር ማማ ሰገነቴ መርሕ ፋና ለህይወቴ ፈጠኚልኝ ነይ በሞቴ/2/ ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤ ✞@MENFESAWItsufoche✞ ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
Открыть в Telegram🙏 የአርሲ ወገኖቻችን ይጠብቁናል! እኛስ ምን እናድርግ? 🕊️ 💔 ወገኖቻችን በመከራ ውስጥ ሲያልፉ፣ ዝምታችንን በርህራሄ፣ ርህራሄያችንንም በተግባር እንቀይር! 🤝 ዛሬ የምንሰጠው እጅ የነገውን ሕይወት ሊያድን ይችላል። በገንዘብ፣ በሐሳብ፣ በማስተባበርና ሌሎችን በማሳተፍ ወገኖቻችንን እንደግፍ። ትንሽ የሚመስለው እገዛችን ለሌላው ትልቅ ተስፋ ነው! #አለሁ_እኔ_ለአርሲው_ወገኔ! CBE - 1000309803648 Ahadu - 0025393810901 Wegagen - 0837331610101 Abysinia - 37235458 Awash - 01329817420400 Dashen- 5171156335011 Telebir 0975005994 🔷ያደረጉትን ድጋፍ🔷 https://t.me/ArsiSupport ላይ ይላኩልን። ©ማኅበረ ቅዱሳን
Открыть в Telegram🙏 ለ ኦርቶዶክሳውያን የቀረበ የታላቅ በረከት ጥሪ 🙏 በጂንካ መ/ጵ/ደ/ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናገለግል እኛ የማህበረ እስትንፋሰ ክርስቶስ የዝክር ማህበር፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ህንጻ ስራ የሚሆን ገቢ የማሰባሰብ ስራ እንድንሰራ ታዘናል። ስለዚህም ይህ ቤተመቅደስ ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን የእናንተ ትንሽ ድጋፍ ትልቅ አቅም አለው። ታዲያ እኛ ምን እናድርግ ካላችሁ፦ 👉 ባለን አቅም መባ ማበርከት ወይም 👉 ለሌሎች ወንድም እህቶቻችን ሼር ማድረግ ነው የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ፦ 🏦 ባንክ፦ CBE 🔢 የአካውንት ቁጥር፦ 1000794579974 👤 የአካውንት ስም፦ ጂንካ መ/ጵ/ደ/ብ/ቅ/ሥ/ቤተክርስቲያን። ጥቂቱም ቢሆን ለመቅደሱ ግንባታ ትልቅ ዋጋ መኖሩን ሳንዘነጋ ለፈጠሩን አጋእዝተ አለም ሥላሴ መቅደስ እጃችንን እንዘርጋ። ማሳሰቢያ 🫴 ገንዘብ ገቢ ካደረጉ screen shot ከክርስትና ስም ጋር በ👉 @abola_22 ይላኩ 🫴 ለበለጠ መረጃ ዲ/ን ታምራት አሰፋ በ 0974843199 ያናግሩ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ "ያላችሁን ስጡኝ" ብሎ አበርክቶላቸው አምስት ሺህ ህዝብን እንደመገበ፣ እናንተም እህት ወንድሞቻችን በምታደርጉት ድጋፍ ቅድስት ሥላሴ በረከትን ያድሏችሁ!!! 🙏
Открыть в Telegram፨ድንግል በስደትሽ፨ በወርሀ መስከረም በዓመቱ መግቢያ፣ እስኪ ትንሽ ልበል ስለ እመቤታችን ስደት በኢትዮጵያ። የወራት መነሻ የአበቦች ማፍሪያ፣ መአዛሽ ያውዳል የለሽም አምሳያ፣ ለ 7ቱ አጽዋማት መንገድ ጠራጊ ነሽ፣ ሰው ሁሉ በፍቃድ ሁሌ የሚጾምሽ፣ በአበባዎች ዘመን ሰው ሁሉ ሲደሰት፣ ወላዲተ አምላክ ወጣች ወደ ስደት። ህጻኑን ታቅፋ ከነዮሴፍ ጋራ፣ ስደትን ጀመረች አቋርጣ ተራራ፣ ይህ ሁሉ መከራ መች ለእሷ ይገባል፣ ለእኛ ለልጆችሽ ምሳሌ ሆኖናል። ስደት ጀማሪዋ ወላዲተ አምላክ፣ ሁሌ የምትሰጠን አዲስ ህይወት ታሪክ፣ በዛ በግብፅ ሀገር ሀሩር በበዛበት፣ እርሃብና ጽሙ የአሸዋውም ግለት፣ ሁሉንም ታግሰሽ ካሳ ከፈልሽልን፣ አንች ተቀብለሽ ስደት መከመነሻ። ያዳም ልጁ ተስፋ ከሞትም መነሻ፣ ድንግል እናታችን የገነት መውረሻ፣ የነገስታት ንጉሥ በእጅሽ ታቅፈሽ፣ ውሃ ጥሙን ሁሉ ኧረ እንደምን ቻልሽ፣ አንች መልካም እርግብ የትህትና እናት፣ በዛ በመከራ በስደትሽ ወራት፣ ዬሴፍ ሰሎሜ ከልጅሽ በስተቀር፣ ኧረ ማን ነበር የሚያጽናናሽ በፍቅር? ኮቲባ በንቀት ልጅሽን ስጥለው፣ የትዕማር ክፉ ሃሳብ ልብሽን ሲያደማት፣ አምላክነቱን ገልጦ ምድር ሲወጣቸው፣ አይተናል ሰምተናል ሁሉ ይቻለዋል፣ ለበዛው ምህረቱ ክብር ይገባዋል፣ የሽፍቶቹን ኮቴ ከእሩቅ ስትሰሚ፣ ልጄን ሊገድሉት ነው ብለሽ ስትሰጊ፣ ይህን ሁሉ ሰቆቃ መራሩ ሀዘንሽ፣ መዳኛ ሆኖናል ለአስራት ልጆችሽ። በስደትሽ ወራት ሀዘን በበዛበት፣ ሰሎሜና ዪሴፍ አገኙ በረከት፣ በጽጌ ማህሌት ካህናት ድያቆናቱ፣ ምዕመናን ምእመናት አዛውንት ወጣቱ፣ ንኢ ንኢ ብለው በፍቅር ሲጣሩ፣ የሁሉ እመቤት መጣች ከቤታቸው ለሁሉም ማህበሩ፣ ድንግል ባንቺ ስደት እንድንማር ጽናት፣ እኛንም አድኝን ከመከራ ጭንቀት። የልጆችሽን ልመና ድንግል ትሰሚያለሽ፣ እሩህሩህ ነሽና ታማልጂናሽ። ይህን ካልኩ ይብቃኝ ድንግል ለስደትሽ፣ መቼም አልጨረሰው ስዘረዝር ብውል። የአማኑኤል እናት ክብር ይገባሻል፣ የአስራት ልጆች ሁሌም ይጠሩሻል፣ ከጭንቅ ከመከራ ሁሌ እንድታወጭን፣ ሰላምና ጤና ፍቅርንም አድይን፣ በሄድንበት ሁሉ ጠበቃ ሁኚልን። ከዲ/ን ሃብተ ማርያም 2011ዓ.ም ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤ ✞@MENFESAWItsufoche✞ ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
Открыть в Telegram♥♥ስደቷ ፍቅር ነው♥♥ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር _ ኤልሻዳይን አዝላ ሰሎሜም ሳትቀር_ወጡ ከገሊላ የአስራአምስት ዓመቷ_ድንግል ማርያም በግብፁ በረሀ_ ገጠማት ድካም። ዐፈሩ ረመጥ ነው_ እጅግ የሚያቃጥል አሸዋ ድንጋዩ_ እንደ ብረት የሚግል አየር እንፋሎቱ_ ልብን የሚሰውር የነበረው ስቃይ_እንደምን ይዘርዘር? ያስጨንቃል በጣም_የመከራሽ ነገር። በትንቢተ ሆሴዕ _የተጻፈውን ምስጢራዊ ትንቢት_ ሄደ ሊከውን የድንግል ማርያም ልጅ_ ኢየሱስ መድኽን እፁብ ድንቅ ያሰኛል_ የእግዚአብሔር ማዳን። በፈጣን ደመና _ ወደ ግብጽ በረረ በማለት ኢሳይያስ_ እውነት ተናገረ ፈጣኗ ደመና _ ወለተ ኢያቄም ማኅደረ መለኮት_ ነጻነቱ የአዳም። ከሦስቱ አካል አንዱ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል በበረት_ ሞትን ሊደመስስ በገባው ቃል ኪዳን_ በቀጠሮ መጣ ከሲዖል ቁራኛ_ ነፍሳትን ሊያወጣ። በከብቶቹ በረት_ ቢታይ በትሕትና የሕይወት እንጀራ _ የሰማዩ መና የዳዊት የሙሴ_የነቢያቱ ዜና ተፈፅሞ ስናይ_ ዘመርን በበገና። እረኞች በቦታው _ ከመላእክት ጋራ ሥብሐት ለሥላሴ_ብለዋል በጋራ ንጉሥ ተወለደ_ በዳዊት ከተማ አስይ የምሥራች_ በዓለም ይሰማ ነበር የዚያን ጊዜ_የደስታቸው ዓርማ። መወለዱን የሰማው_ ሄሮድስ በውሸት ተነስቶ ብዙ ሕጻናትን _ ቦታው አስጠርቶ እርዳታ ልሰጥ ነው_ በሚለው ትዕዛዙ የዋሓን እናቶች_ የሆዳቸውን ፍሬ ወደ እሱ አጋዙ። ገስግሰው ሲደርሱ_ የሆነው ሌላ ነው ለጨካኝ ሰራዊቱ_ ደም ለጠማቸው የሕጻናቱን አንገት_ ቆራርጡት አላቸው ለወንበር ለሥልጣን_ ስለ ተማረከ የሥላሴን ፍጥፈት_ በሰይፉ አወከ። የሰባ ሰገሎቹ_ ጥበብ ስላልገባው የተወለዱትን _ በሙሉ አስጠራቸው የተባለው ትንቢት_እንቅልፍ ስለ ነሳው የነገሥታት ንጉሥን_አስቦ ሊያገኘው ከዚህ ድንቁርና _ ሰውረን ማለት ነው። የነፍሳቱ ደም_ ወረደ እንደ ጎርፍ በዚያች ከተማ _ ቤተልሔም ደጃፍ በከንቱ ሰዋቸው_ በመሰለው ነገር ሕፃኑ ግን ሸሽቷል_ ወደ ሌላ ሀገር የሥላሴ ጥበብ _ ከቶ አይመረመር። ዛሬም በዚህ ዘመን_ አሉ ብዙ ሞኞች በአለማዊ ጥበብ_ በባዶ ተሟጋች ማመን አለማመን_የነሱ ድርሻቸው እውነትን መመስከር_የልጅ ግዴታ ነው ሂዱና አሰተምሩ_ መልሱ ነው የሚለው። ስለኛ ተሰዳ _ተስፋን ለሰጠችን በልጇ ቸርነት_ ስለተጎበኘን እንደ ቅዱሳኑ_ ነይ ነይ እንላለን። በአፀድ በቅጽሯ_ ጽዮንን ከበናል የአባ ጽጌ ድንግል_ በረከት ደርሶናል በሰማያዊው ስልት_ማኅሌት ቆመናል አቤት ያለው ደስታ_ዓለምን ያስረሳል። ዶግማ የማይሻር_ ከቶ የማይታደስ ሕጉ አምላካዊ_በፍፁም የማይፈርስ ቀኖና ፍትሐዊ_ጭንቀት የሚበጥስ ትውፊት ታሪካዊ_ ለልጅ ልጅ የሚደርስ የእውነት ቅብብሎሽ_አንዱም አይፋለስ ከዚህ ውጪ የሆነ_ ልቡ እንዲመለስ በዋሻ ገደሉ _ጤዛውን በመላስ ተግተው ይቆማሉ_ እንዳለው ጳውሎስ። በምድራችን ሰላም_እንዲሆን ደስታ ትውልዱ እንዲጠግብ_ በአጋፔው ገበታ በንሰሐ ታጥቦ_ ልቡ እንዲበረታ ድንግል ሆይ አሳስቢ_ ለታቀፍሽው ጌታ ። የቤሌሖር ልጁ_ ወድቆ እንዲሰበር ዳጎናዊው መንገድ_በእውነት እንዲታጠር የዲያቢሎስ ውጊያ_በቃልህ እንዲሞት አስነሳልን አምላክ_ የበረታ አባት ለመንጋው እራርቶ_የሚያፀና በእምነት። ነኽምያን ላከው_ ያንጽ ቤተመቅደስ የአምልኮ ሥፍራ_ለሁሉ እንዲዳረስ ሳሙኤልን ስጠን_ ወንጌልን ሰባኪ በፀጋው በጥበብ_ራዕይን አሳኪ። አባታችን ሙሴ_ የማርያም ወንድም ስማን አሳስብልን_ ለመድኃኒአለም በኑፋቄ ባሕር_ ገብተን እንዳንሰጥም ክፈልና አሻግረን_ ተጨንቀናል በጣም በተሰጠን ፍቅ_ ለመኖር አልቻልንም። ከውብ ዜማው ጋራ_ ቅዱስ ያሬድ ይምጣ ምስጢር በማፋለስ_ ከሕግ እንዳንወጣ እናንብብ እንጠይቅ_ እንማር ከአበው ከእውነተኛው መምህር_ለኛ ከሚገደው አምላክ ይሰውረን_ አሁን ከምንሰመው። እመቤታችን ሆይ አዘክሪልን! 💝🪔💝➴💝🪔💝➴💝🪔 @MENFESAWItsufoche 🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔
Открыть в Telegram
📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔@amharicspritualbooksРелигия30,3 тыс.
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች@ethiopian_orthodoxРелигия33,6 тыс.
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن@nuredinal_arebiРелигия28 тыс.
ተስፋ በኢየሱስ Channel@hopeofjesuschannelРелигия27,4 тыс.
CHRIST TUBE - ETH🇪🇹@christ_tubeРелигия25,5 тыс.
⚓️ሐመረ ኖኅ⚓️@orthotekРелигия24,5 тыс.
Minber TV@minbertvРелигия43,7 тыс.
አፍሪካ ቲቪ | Africa TV1@africatv1Религия22 тыс.