Кабинет

Посты канала 🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻

сначала новые

#12711Фото
Просмотры314−90%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12690Текст

#እንኳን_ለሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን♥♥♥           #ጎጆ_ቀለስኩልህ          (በሰመረ ፍስሃ) በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡ ...................ወዲህ ሲመልሰኝ ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ ...................ጉድፌን አፅድቶ ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡ ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡ ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡ የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡ ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ... የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡ ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡ እናም ሚካኤል ሆይ.... ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡ ❖==✿==❀==✞==❀==✿==❖ @MENFESAWItsufoche ✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧

Открыть в Telegram
Просмотры1 800−43%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#12665Фото
Просмотры3 380+7%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#12664Текст
Просмотры2 900−8%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#12663Текст
Просмотры3 260+4%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#12569Фото
Просмотры7 680+144%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#12566Фото

🙏 ለ ኦርቶዶክሳውያን የቀረበ የታላቅ በረከት ጥሪ 🙏 በጂንካ መ/ጵ/ደ/ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናገለግል እኛ የማህበረ እስትንፋሰ ክርስቶስ የዝክር ማህበር፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ህንጻ ስራ የሚሆን ገቢ የማሰባሰብ ስራ እንድንሰራ  ታዘናል። ስለዚህም ይህ ቤተመቅደስ ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን የእናንተ ትንሽ ድጋፍ ትልቅ አቅም አለው። ታዲያ እኛ ምን እናድርግ ካላችሁ፦ 👉 ባለን አቅም መባ ማበርከት ወይም 👉 ለሌሎች ወንድም እህቶቻችን ሼር ማድረግ ነው የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ፦ 🏦 ባንክ፦ CBE 🔢 የአካውንት ቁጥር፦ 1000794579974 👤 የአካውንት ስም፦ ጂንካ መ/ጵ/ደ/ብ/ቅ/ሥ/ቤተክርስቲያን። ጥቂቱም ቢሆን ለመቅደሱ ግንባታ ትልቅ ዋጋ መኖሩን ሳንዘነጋ ለፈጠሩን አጋእዝተ አለም ሥላሴ መቅደስ እጃችንን እንዘርጋ። ማሳሰቢያ 🫴 ገንዘብ ገቢ ካደረጉ screen shot ከክርስትና ስም ጋር በ👉 @abola_22 ይላኩ 🫴 ለበለጠ መረጃ ዲ/ን ታምራት አሰፋ በ 0974843199 ያናግሩ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ "ያላችሁን ስጡኝ" ብሎ አበርክቶላቸው አምስት ሺህ ህዝብን እንደመገበ፣ እናንተም እህት ወንድሞቻችን በምታደርጉት ድጋፍ ቅድስት ሥላሴ በረከትን ያድሏችሁ!!! 🙏

Открыть в Telegram
Просмотры5 490+74%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#12557Текст

፨ድንግል በስደትሽ፨ በወርሀ መስከረም በዓመቱ መግቢያ፣ እስኪ ትንሽ ልበል ስለ እመቤታችን ስደት በኢትዮጵያ። የወራት መነሻ የአበቦች ማፍሪያ፣ መአዛሽ ያውዳል የለሽም አምሳያ፣ ለ 7ቱ አጽዋማት መንገድ ጠራጊ ነሽ፣ ሰው ሁሉ በፍቃድ ሁሌ የሚጾምሽ፣ በአበባዎች ዘመን ሰው ሁሉ ሲደሰት፣ ወላዲተ አምላክ ወጣች ወደ ስደት። ህጻኑን ታቅፋ ከነዮሴፍ ጋራ፣ ስደትን ጀመረች አቋርጣ ተራራ፣ ይህ ሁሉ መከራ መች ለእሷ ይገባል፣ ለእኛ ለልጆችሽ ምሳሌ ሆኖናል። ስደት ጀማሪዋ ወላዲተ አምላክ፣ ሁሌ የምትሰጠን አዲስ ህይወት ታሪክ፣ በዛ በግብፅ ሀገር ሀሩር በበዛበት፣ እርሃብና ጽሙ የአሸዋውም ግለት፣ ሁሉንም ታግሰሽ ካሳ ከፈልሽልን፣ አንች ተቀብለሽ ስደት መከመነሻ። ያዳም ልጁ ተስፋ ከሞትም መነሻ፣ ድንግል እናታችን የገነት መውረሻ፣ የነገስታት ንጉሥ በእጅሽ ታቅፈሽ፣ ውሃ ጥሙን ሁሉ ኧረ እንደምን ቻልሽ፣ አንች መልካም እርግብ የትህትና እናት፣ በዛ በመከራ በስደትሽ ወራት፣ ዬሴፍ ሰሎሜ ከልጅሽ በስተቀር፣ ኧረ ማን ነበር የሚያጽናናሽ በፍቅር? ኮቲባ በንቀት ልጅሽን ስጥለው፣ የትዕማር ክፉ ሃሳብ ልብሽን ሲያደማት፣ አምላክነቱን ገልጦ ምድር ሲወጣቸው፣ አይተናል ሰምተናል ሁሉ ይቻለዋል፣ ለበዛው ምህረቱ ክብር ይገባዋል፣ የሽፍቶቹን ኮቴ ከእሩቅ ስትሰሚ፣ ልጄን ሊገድሉት ነው ብለሽ ስትሰጊ፣ ይህን ሁሉ ሰቆቃ መራሩ ሀዘንሽ፣ መዳኛ ሆኖናል ለአስራት ልጆችሽ። በስደትሽ ወራት ሀዘን በበዛበት፣ ሰሎሜና ዪሴፍ አገኙ በረከት፣ በጽጌ ማህሌት ካህናት ድያቆናቱ፣ ምዕመናን ምእመናት አዛውንት ወጣቱ፣ ንኢ ንኢ ብለው በፍቅር ሲጣሩ፣ የሁሉ እመቤት መጣች ከቤታቸው ለሁሉም ማህበሩ፣ ድንግል ባንቺ ስደት እንድንማር ጽናት፣ እኛንም አድኝን ከመከራ ጭንቀት። የልጆችሽን ልመና ድንግል ትሰሚያለሽ፣ እሩህሩህ ነሽና ታማልጂናሽ። ይህን ካልኩ ይብቃኝ ድንግል ለስደትሽ፣ መቼም አልጨረሰው ስዘረዝር ብውል። የአማኑኤል እናት ክብር ይገባሻል፣ የአስራት ልጆች ሁሌም ይጠሩሻል፣ ከጭንቅ ከመከራ ሁሌ እንድታወጭን፣ ሰላምና ጤና ፍቅርንም አድይን፣ በሄድንበት ሁሉ ጠበቃ ሁኚልን። ከዲ/ን ሃብተ ማርያም 2011ዓ.ም ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤ ✞@MENFESAWItsufoche✞ ✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤

Открыть в Telegram
Просмотры6 970+121%к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#12520Текст

♥♥ስደቷ ፍቅር ነው♥♥ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር _ ኤልሻዳይን አዝላ ሰሎሜም ሳትቀር_ወጡ ከገሊላ የአስራአምስት ዓመቷ_ድንግል ማርያም በግብፁ በረሀ_ ገጠማት ድካም። ዐፈሩ ረመጥ ነው_ እጅግ የሚያቃጥል አሸዋ ድንጋዩ_ እንደ ብረት የሚግል አየር እንፋሎቱ_ ልብን የሚሰውር የነበረው ስቃይ_እንደምን ይዘርዘር? ያስጨንቃል በጣም_የመከራሽ ነገር። በትንቢተ ሆሴዕ _የተጻፈውን ምስጢራዊ ትንቢት_ ሄደ ሊከውን የድንግል ማርያም ልጅ_ ኢየሱስ መድኽን እፁብ ድንቅ ያሰኛል_ የእግዚአብሔር ማዳን። በፈጣን ደመና _ ወደ ግብጽ በረረ በማለት ኢሳይያስ_ እውነት ተናገረ ፈጣኗ ደመና _ ወለተ ኢያቄም ማኅደረ መለኮት_ ነጻነቱ የአዳም። ከሦስቱ አካል አንዱ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል በበረት_ ሞትን ሊደመስስ በገባው ቃል ኪዳን_ በቀጠሮ መጣ ከሲዖል ቁራኛ_ ነፍሳትን ሊያወጣ። በከብቶቹ በረት_ ቢታይ በትሕትና የሕይወት እንጀራ _ የሰማዩ መና የዳዊት የሙሴ_የነቢያቱ ዜና ተፈፅሞ ስናይ_ ዘመርን በበገና። እረኞች በቦታው _ ከመላእክት ጋራ ሥብሐት ለሥላሴ_ብለዋል በጋራ ንጉሥ ተወለደ_ በዳዊት ከተማ አስይ የምሥራች_ በዓለም ይሰማ ነበር የዚያን ጊዜ_የደስታቸው ዓርማ። መወለዱን የሰማው_ ሄሮድስ በውሸት ተነስቶ ብዙ ሕጻናትን _ ቦታው አስጠርቶ እርዳታ ልሰጥ ነው_ በሚለው ትዕዛዙ የዋሓን እናቶች_ የሆዳቸውን ፍሬ ወደ እሱ አጋዙ። ገስግሰው ሲደርሱ_ የሆነው ሌላ ነው ለጨካኝ ሰራዊቱ_ ደም ለጠማቸው የሕጻናቱን አንገት_ ቆራርጡት አላቸው ለወንበር ለሥልጣን_ ስለ ተማረከ የሥላሴን ፍጥፈት_ በሰይፉ አወከ። የሰባ ሰገሎቹ_ ጥበብ ስላልገባው የተወለዱትን _ በሙሉ አስጠራቸው የተባለው ትንቢት_እንቅልፍ ስለ ነሳው የነገሥታት ንጉሥን_አስቦ ሊያገኘው ከዚህ ድንቁርና _ ሰውረን ማለት ነው። የነፍሳቱ ደም_ ወረደ እንደ ጎርፍ በዚያች ከተማ _ ቤተልሔም ደጃፍ በከንቱ ሰዋቸው_ በመሰለው ነገር ሕፃኑ ግን ሸሽቷል_ ወደ ሌላ ሀገር የሥላሴ ጥበብ _ ከቶ አይመረመር። ዛሬም በዚህ ዘመን_ አሉ ብዙ ሞኞች በአለማዊ ጥበብ_ በባዶ ተሟጋች ማመን አለማመን_የነሱ ድርሻቸው እውነትን መመስከር_የልጅ ግዴታ ነው ሂዱና አሰተምሩ_ መልሱ ነው የሚለው። ስለኛ ተሰዳ _ተስፋን ለሰጠችን በልጇ ቸርነት_ ስለተጎበኘን እንደ ቅዱሳኑ_ ነይ ነይ እንላለን። በአፀድ በቅጽሯ_ ጽዮንን ከበናል የአባ ጽጌ ድንግል_ በረከት ደርሶናል በሰማያዊው ስልት_ማኅሌት ቆመናል አቤት ያለው ደስታ_ዓለምን ያስረሳል። ዶግማ የማይሻር_ ከቶ የማይታደስ ሕጉ አምላካዊ_በፍፁም የማይፈርስ ቀኖና ፍትሐዊ_ጭንቀት የሚበጥስ ትውፊት ታሪካዊ_ ለልጅ ልጅ የሚደርስ የእውነት ቅብብሎሽ_አንዱም አይፋለስ ከዚህ ውጪ የሆነ_ ልቡ እንዲመለስ በዋሻ ገደሉ _ጤዛውን በመላስ ተግተው ይቆማሉ_ እንዳለው ጳውሎስ። በምድራችን ሰላም_እንዲሆን ደስታ ትውልዱ እንዲጠግብ_ በአጋፔው ገበታ በንሰሐ ታጥቦ_ ልቡ እንዲበረታ ድንግል ሆይ አሳስቢ_ ለታቀፍሽው ጌታ ። የቤሌሖር ልጁ_ ወድቆ እንዲሰበር ዳጎናዊው መንገድ_በእውነት እንዲታጠር የዲያቢሎስ ውጊያ_በቃልህ እንዲሞት አስነሳልን አምላክ_ የበረታ አባት ለመንጋው እራርቶ_የሚያፀና በእምነት። ነኽምያን ላከው_ ያንጽ ቤተመቅደስ የአምልኮ ሥፍራ_ለሁሉ እንዲዳረስ ሳሙኤልን ስጠን_ ወንጌልን ሰባኪ በፀጋው በጥበብ_ራዕይን አሳኪ። አባታችን ሙሴ_ የማርያም ወንድም ስማን አሳስብልን_ ለመድኃኒአለም በኑፋቄ ባሕር_ ገብተን እንዳንሰጥም ክፈልና አሻግረን_ ተጨንቀናል በጣም በተሰጠን ፍቅ_ ለመኖር አልቻልንም። ከውብ ዜማው ጋራ_ ቅዱስ ያሬድ ይምጣ ምስጢር በማፋለስ_ ከሕግ እንዳንወጣ እናንብብ እንጠይቅ_ እንማር ከአበው ከእውነተኛው መምህር_ለኛ ከሚገደው አምላክ ይሰውረን_ አሁን ከምንሰመው። እመቤታችን ሆይ አዘክሪልን! 💝🪔💝➴💝🪔💝➴💝🪔 @MENFESAWItsufoche 🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔🪔

Открыть в Telegram
Просмотры7 120+126%к среднему
Пересылки—
Реакции36
Комментарии—
#12513Текст
Просмотры5 360+70%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—
#12481Текст

ደረሰ ሰዓቱ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ደረሰ ሰዓቱ_እንገስግስ መቅደሱ ሊዘረጋልን ነው_ቅኔ መወድሱ የአባ ጽጌ ድንግል_የምስጋናው ሻማ ሊበራ ሊነድ ነው_ለነፍስ የሚስማማ። የተመረጠቱ _ እንደየ ፀጋቸው መቋሚያ ጽናጽል_ ከበሮውን ይዘው የድንግልን ስደት_ በዜማ እያዋዙ በአንደምታው ምስጢር_ በረከትን ገዙ። ተጠርተው በፍቅሩ_ የሄዱት ምዕመናን መስቀልያ አጣፍተው_ተውብው በብርሃን ሐሴት ተጎናፅፈው_በቅድስቷ ድንኳን ሲታይ በረከቱ_ መዓዛ ወ ዕጣን ይወስዳል በሀሳብ_ ወደ ሰማይ ዙፋን። የአምላክን ምሕረት_ፈቅዶ መሰደዱን ከከበረው ዙፋን_ ስለኛ መውረዱን የላከው ወደ ግብጽ_ ሙሴን ያናገረው እሱ ነው ጌታችን_ በማርያም ያደረው። የቅዱሳን አበው _ የነ ኢሳይያስ የአማልእክት አምላክ_ የሁሉም ንጉስ አዶናይ መሆኑን_የጽድቃችን ልብስ የማኅሌት ሲሳይ_ ለኛ ሲዳረስ ዕጹብ ድንቅ ያሰኛል_ ፍቅሩ የኢየሱስ። የቅዱሱን መጽሐፍ_ ተርጉመው ሊቃውንት አልቀው አርቅቀው_ ፈጽመው ሰማዕታት ግራ እንዳይገባን_ ቀምረው ስርዓት በደም አጥንታቸው_ለኛ አስቀመጡት ምስጋና ይግባቸው_ በቀን በሌሊት። የኪዳን የሳዓታት_ የቅዳሴን ትርጉም ያስተማረን ጌታ_ ቸሩ መድኃኒአለም ከመምህሩ ሰምተው_ ከተቡት በእምነት በክፉዎች ሴራ_ እንዳይፋቅ እውነት። ዛሬ የምናየው _ ኹከት ልብሱ የሆነው በሐሰት ኑፋቄ_ ትውልድ የሚያውከው የበግ ለምድ ለብሶ_ የዋሕ የሚያስተው ቀድሞ ይታወቃል_ አሁን ወቅቱ እኮ ነው። ይልቅ ይሄ ሲያይል_ ክኽደት ሲበረታ ፈርቶ ተደናግጦ_ በመጨነቅ ፈንታ የጸኑት ያሉትን_ የጻፉትን እንይ ቃሉን ከሸቀጡት_ በፍጥነት እንለይ ወርደን እንዳንጣል_ በትጋት እንጸልይ። የተዘጋች ደጃፍ_ሕዝቅኤል የሚላት የእሰይ ልጅ ዳዊት_ የሚያመሰግናት ሰሎሞንም ብሏል _ የታተመች ገነት ነቢዩ ኢሳይያስ_ የመሰከረላት ልዑል ለማደሪያው _ አንዴ የቀደሳት ከተሰጣት ክብር_ ማን ነው የሚያወርዳት? ይልቅ የታደለው_ስሟን እየጠራት በፍቅሯ ይኖራል_ ብጽዕይት እያላት። ጊዜ የማይሽረው_ በዐለት የተጻፈ ከሰማይ ከምድር_ እጅግ የገዘፈ ቃሉ የማይሻር_ በዘመን እርዝማኔ መርጧታል ኢየሱስ_ ምስክር ነኝ እኔ። የስደቷን ነገር_ መከራዋን አይቶ ከአለማመን መንፈስ_ ፈቅዶ ተለይቶ የክርስቶስ ፍቅር_ እውነቱ ሲገባው ጣቶቹን አንስቶ_ ማሕሌቷን ጻፈው አባ ጽጌ ድንግል_ የእውነት አበባ ነው። በብዙ ምሳሌ _ እያመሳጠረ ለትውልደ ትውልድ_ ቅኔን አስተማረ ኋላ የተጠራው_ ቀድሞ ተከበረ ወድቆ መነሳቱን_ ቆሞ መሰከረ እናት ተዋሕዶ_ምስጢርሽ ደመረ።             ድንግል ሆይ በስደትሽ ስደታችንን _ባርኪልን ከልጅሽ ቸርነት _ ለምኚልን ፍቅር አንድነትን_ ደራርቢልን ከክፉ መናፍስት_ በኪዳንሽ ጠብቂን መስሏቸው ከበረቱ_ ክደው የወጡትን በአማላጅነትሽ_ መልሽልን አሜን አሜን አሜን                    ከእህተ ማርያም ♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️ @MENFESAWItsufoche 👆👆👆👆👆👆👆👆👆

Открыть в Telegram
Просмотры8 040+155%к среднему
Пересылки—
Реакции44
Комментарии—
#12479Фото
Просмотры6 660+112%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—