Кабинет
Dn. Mekuria Murashe || ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ

Dn. Mekuria Murashe || ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ

እንኳን ወደዚህ መንፈሳዊ ማደርያ በሰላም መጡ! 🕊️ ሕይወት ሰጪ አዳዲስ ሐሳቦች፣ ልብን የሚነኩ ጥልቅ መንፈሳዊ ጽሑፎች፣ እንዲሁም ነፍስን የሚያረኩ እውነታዎች በዚህ ቻናል ይጋራሉ። ከዕለት ተዕለት ኑሯችን ጋር የሚጣጣሙ አነቃቂ መልዕክቶችን፣ እምነትን የሚያጸኑ አጫጭር ሐሳቦች እና ቆንጆ ስንኞች እዚህ ያገኛሉ። መልካም ቆይታ!✨

Юзернейм
@mekuriyam
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики19 661
Просмотров на пост, 7 дн.1 049−62,4% к пред. 7 дн.
ERR5,33 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
9 нояб. 2026 г.4 020
10 нояб. 2026 г.5 260
11 нояб. 2026 г.567
12 нояб. 2026 г.852
16 нояб. 2026 г.2 790
24 нояб. 2026 г.716
26 нояб. 2026 г.1 480
27 нояб. 2026 г.950

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    መንፈሳዊነትን በይቅርታ...! መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው። መንፈሳዊነት ማለት በአንድ ዓይን መተያየት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት ከሰው ጋር ለመጋጨት ተብሎ ነገርን ከሥር መሠረቱ መመርመር ማለት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት መተው ማለት ነው። ሲዘልፋህ፣ ሲነቅፉህ፣ ሲያንቋሽሹህ ይቅር ካልካቸው፣ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። “ተናገር እንጂ ምን ይዘጋሃል?” ሲሉህ ዝም ካልክ አንተ መይፈሳዊ ሰው ነህ ማለት ነው። ክፋታቸውን አውቀህ ክፉ ላለመነጋገር ብለህ "block" ካደረካቸው ራሱ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። ልብህ ለይቅርታ የማይሰበር ከሆነና ከይቅርታ በኋላ እንደ ቀድሞ መሆን የማትችል ከሆነ ግን ገና መንፈሳዊነትን አልጀመርከውም። ወንበዴው ፈያታዊ ዘየማንን አስታውስ...! በሰንከንዳት ውስጥ በተናገራት የጸጸት ቃል ነበር ጌታው ይቅር ብሎት ወደ ገነት ለመግባት ቀዳሚ የሆነው፤ ስለዚህ ወንጀለኛ በይቅርታ ታላቅነት ገነት ከገባ አንተም ይቅርታ ስትባል የቀድሞውን ክፋት ሙሉ ለሙሉ መተው ይኖርብሃል ማለት ነው፤ ይህ ነው መንፈሳዊነት። በመንፈሳዊነት ያለ ይቅርታ እኮ ሲኦልን ዘግቶ ገነትን ከፍቷል። ከይቅርታ በኋላ የራስህ የሆነ ሌላ መንገድ የምታበጅና ቀድሞ የነበረህን ጓደኛ የምትተው ከሆነ መንፈሳዊነት አይደለም። ሐዋርያው ጴጥሮስን አትመለከትምን...? ጌታውን ክዶ ነበር፣ ከዚያም በይቅርታ ሲመለስ ክብሩ እንደ መጀመርያው ክብር ነበር እንጂ ያ ክህደት ከክብር አላጎደለውም፤ ክርስቶስ መንፈሳዊ ስለሆና የመንፈሳዊነት መገለጫም እንደ ክርስቶስ መሆን ስለሆነ ነው። ታዲያ አባታችን ጴጥሮስ፥ ጌታውን ክዶ ከዚያም ተመልሶ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ ክርስቶስ ካልተቀየረበት፣ እኛ ከማን ስለተማርን ነው ከይቅርታ በኋላ ሌላ ድንበር የምናበጀው? መንፈሳዊነት ማለት አለመበደል ማለት ነው ለማለት አይደለም፤ በደልን በይቅርታ ማለፍ ማለት እንጂ። ለዚህም ነው መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው የምለው። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 1/2019 ዓ.ም ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ #ንነጽር_213 #መንፈሳዊነትን #በይቅርታ t.me/MekuriyaM ይቀላቀሉን

    Текст
    Просмотры5,26 тыс.
    Пересылки—
    Реакции19
    Комментарии—
  2. 02

    ስም ወይስ ሕሊና? አንዳዳዶቻችን በውሸት የጠለሸው ስማችንን ለማጥራት ብዙ ርቀት እንሄዳለን። አንዳንዶች ደግሞ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጡትና፤ ስማቸውን በሌላ መንገድ ላነሣው ሰው፣ ይቅር በለው ብለው ይጸልዩለታል። እነዚህ ሁለተኛዎቹ ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያምኑና በፈጣሪ ሥራ የሚታመኑ ናቸው። ምድራዊውን ነገር የቀበሩና ቃለ እግዚአብሔርን ብቻ ትውስ የሚላቸው ናቸው። የመጀመርያዎቹ ሰዎች ደግሞ የራሳቸውን ስም ለማጥራት ብለው ሲሮጡ፣ የሌላ የንጹሑን ግለሰብ ስም ያጠፋሉ። ከዚያም ጸጸት ውስጥ ይገቡና፤ ገና መልሰው የሌላ ሰው ስም ላለማጥፋትና ላለማስቀየም ብለው ያስቀየሙትን ሰው ይቅርታ ይጠይቁና፤ የራሳቸውን ስም እንደጠለሸ፣ ልክ እንደሁለተኛዎቹ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነውና ተማምነው ዝም ይላሉ። ነገርን ሁሉ ለእግዚአብሔር መተው ጥበብ እንጂ ስንፍና አይደለም! ስምህን ለማጥራት ስትል ሕሊናህን አታርክስ፤ ሰዎች እንዲያምኑህ ስትል እግዚአብሔርን አትርሳ። በቃ እግዚአብሔርን አምኖ መቀበል ብቻ ነው አማራጭ ማድረግ ያለብን። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም #ንነጽር_212 #ስም #ወይስ #ሕሊና

    Текст
    Просмотры4,02 тыс.
    Пересылки—
    Реакции21
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры2,79 тыс.
    Пересылки—
    Реакции34
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры1,48 тыс.
    Пересылки—
    Реакции20
    Комментарии—

Новые посты

#13469Текст

እንኳን የሰው ሰው ይቅርና የራሳችን ጥላ እንኳ ወዳጅነቱ ከብርሃን ጋር ነው። በዚህ ምድር፣ መደነቅም ሆነ መገረም የማያስፈልገው አንድ ነገር ቢኖር፣ የሰው ልጅ የፀባይ መቀያየር ነው። ምክንያቱም የሚቀያየር ፀባይ አንዱ የሰው ልጅ ፀባይ ስለሆነ ነው። ትላንት ወዳጆቻችን የነበራችኹ፣ ዛሬ ግን በስውር የጠላችሁን ሰዎች እንዴት ናችሁ? እኛ ዛሬም እንወዳችኋለን፣ እናንተ የጠላችሁን እኮ ፈልጋችሁት አይደለም፤ ፀባያችሁ አስገድዷችሁ እንደሆነ ተረድተናል። ስታዩን አትሸማቀቁ፣ ስማችንን ስታነቡ በተንኮል አትዋጡ፣ ሥራችን ከሥራችሁ ሲበልጥ አትመቅዩ፤ ምክንያቱም እኛ እንወዳችኋለን። ልብ በሉ! ልንጠላችሁ ያልቻልነውና ከመጀመርያው ይልቅ አብልጠን የወደድናችሁ እኮ፣ ምናልባት እሳት ላይ ፍም ለመጨመርም ፈልገን ሊሆን ስለሚችል፣ ይሄ ፍም ከመጀመርያው እሳት ጋር ተያይዞ ሳይቀጣጠል በፊት ውደዱን! ወዳጅነቱን ከአየር ጋር እንዲመሠርት የፈቀድንለት ለጥላችን ብቻ እንጂ ለእናንተ አይደለም፤ ያ የመቀያየር ፀባያችሁን እንዳለ ቢሆንም፣ ለፍቅር አምላክ ብላችሁ በፍቅር ተዉት! ሰዎችን መውደድ ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም! ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 18/2019 ዓ.ም ጉራጌ ዞን፣ እዣ ወረዳ #ንነጽር_215 #ሰዎችን #መውደድ #ግዴታችን #ነው @MekuriyaM ይቀላቀሉን!

Открыть в Telegram
Просмотры950−54%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#13468Текст
Просмотры1 480−29%к среднему
Пересылки—
Реакции20
Комментарии—
#13464Текст
Просмотры2 790+34%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#13462Текст

ሁላችንም የምናውቀው፣ ግን ደግሞ ለሁላችንም ቀላል የሚመስለን ትልቅ ኃይለ ቃል። «ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።» ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ብሎ ሲናገር፣ የዚህን ዓለም ጊዜያዊነትና ተለዋዋጭነት እያሳየን ነው። ዛሬ የምናየው ዓለም፣ የምንመካበት ሀብት፣ ሥልጣን፣ ውበትና ክብር ሁሉ ዘለዓለማዊ አይደሉም። የሚለወጡና የሚያልፉ ናቸው። ስለዚህ በሚያልፍ ነገር ላይ ዘላለማዊ ተስፋችንን መጣል አይገባንም። «ቃሌ ግን አያልፍም» ይህ ማለት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል እውነትነቱን፣ ታማኝነቱንና ፍጻሜውን ፈጽሞ አያጣም ማለት ነው። ✨ሰው ቢክደውም ቃሉ እውነት ነው። ✨ ዘመናት ቢለወጡም ቃሉ አይለወጥም። ✨ ሰዎች ተስፋ ቢቆርጡም የጌታ ተስፋ አይፈርስም። ✨ የተናገረው ትንቢትና ቃል በጊዜው ይፈጸማል። ማቴዎስ 24 ስለ ዓለም መጨረሻ፣ ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መከራዎችና ስለ ምልክቶች ይናገራል። በዚህ ሁኔታ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን አንድ ታላቅ እውነት ያስተምራቸዋል፤ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቢለወጥም እርሱ የተናገረው ቃል ግን አይለወጥም። አንድ ሰው ዛሬ ቃል ገብቶልን ነገ ሊክድ ይችላል። ዛሬ የምንመካበት ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላል። ዛሬ የምንታመንበት ዓለም ነገ ሊለወጥ ይችላል። ነገር ግን የጌታ ቃል አይከዳም፤ አይረሳም፤ አይሻርም። ስለዚህ ክርስቲያን ሰው ተስፋውን በሚያልፍ ዓለም ላይ ሳይሆን በማያልፈው ቃለ እግዚአብሔር ላይ ሊጥል ይገባል። ዓለም ቢለወጥ እውነት አይለወጥም፤ ዘመን ቢያልፍ የክርስቶስ ቃል አያልፍም! 🙏 t.me/MekuriyaM ይቀላቀሉን ✨

Открыть в Telegram
Просмотры852−59%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#13460Текст

መንፈሳዊነትን በይቅርታ...! መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው። መንፈሳዊነት ማለት በአንድ ዓይን መተያየት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት ከሰው ጋር ለመጋጨት ተብሎ ነገርን ከሥር መሠረቱ መመርመር ማለት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት መተው ማለት ነው። ሲዘልፋህ፣ ሲነቅፉህ፣ ሲያንቋሽሹህ ይቅር ካልካቸው፣ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። “ተናገር እንጂ ምን ይዘጋሃል?” ሲሉህ ዝም ካልክ አንተ መይፈሳዊ ሰው ነህ ማለት ነው። ክፋታቸውን አውቀህ ክፉ ላለመነጋገር ብለህ "block" ካደረካቸው ራሱ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። ልብህ ለይቅርታ የማይሰበር ከሆነና ከይቅርታ በኋላ እንደ ቀድሞ መሆን የማትችል ከሆነ ግን ገና መንፈሳዊነትን አልጀመርከውም። ወንበዴው ፈያታዊ ዘየማንን አስታውስ...! በሰንከንዳት ውስጥ በተናገራት የጸጸት ቃል ነበር ጌታው ይቅር ብሎት ወደ ገነት ለመግባት ቀዳሚ የሆነው፤ ስለዚህ ወንጀለኛ በይቅርታ ታላቅነት ገነት ከገባ አንተም ይቅርታ ስትባል የቀድሞውን ክፋት ሙሉ ለሙሉ መተው ይኖርብሃል ማለት ነው፤ ይህ ነው መንፈሳዊነት። በመንፈሳዊነት ያለ ይቅርታ እኮ ሲኦልን ዘግቶ ገነትን ከፍቷል። ከይቅርታ በኋላ የራስህ የሆነ ሌላ መንገድ የምታበጅና ቀድሞ የነበረህን ጓደኛ የምትተው ከሆነ መንፈሳዊነት አይደለም። ሐዋርያው ጴጥሮስን አትመለከትምን...? ጌታውን ክዶ ነበር፣ ከዚያም በይቅርታ ሲመለስ ክብሩ እንደ መጀመርያው ክብር ነበር እንጂ ያ ክህደት ከክብር አላጎደለውም፤ ክርስቶስ መንፈሳዊ ስለሆና የመንፈሳዊነት መገለጫም እንደ ክርስቶስ መሆን ስለሆነ ነው። ታዲያ አባታችን ጴጥሮስ፥ ጌታውን ክዶ ከዚያም ተመልሶ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ ክርስቶስ ካልተቀየረበት፣ እኛ ከማን ስለተማርን ነው ከይቅርታ በኋላ ሌላ ድንበር የምናበጀው? መንፈሳዊነት ማለት አለመበደል ማለት ነው ለማለት አይደለም፤ በደልን በይቅርታ ማለፍ ማለት እንጂ። ለዚህም ነው መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው የምለው። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 1/2019 ዓ.ም ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ #ንነጽር_213 #መንፈሳዊነትን #በይቅርታ t.me/MekuriyaM ይቀላቀሉን

Открыть в Telegram
Просмотры5 260+153%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#13459Текст

ስም ወይስ ሕሊና? አንዳዳዶቻችን በውሸት የጠለሸው ስማችንን ለማጥራት ብዙ ርቀት እንሄዳለን። አንዳንዶች ደግሞ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጡትና፤ ስማቸውን በሌላ መንገድ ላነሣው ሰው፣ ይቅር በለው ብለው ይጸልዩለታል። እነዚህ ሁለተኛዎቹ ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያምኑና በፈጣሪ ሥራ የሚታመኑ ናቸው። ምድራዊውን ነገር የቀበሩና ቃለ እግዚአብሔርን ብቻ ትውስ የሚላቸው ናቸው። የመጀመርያዎቹ ሰዎች ደግሞ የራሳቸውን ስም ለማጥራት ብለው ሲሮጡ፣ የሌላ የንጹሑን ግለሰብ ስም ያጠፋሉ። ከዚያም ጸጸት ውስጥ ይገቡና፤ ገና መልሰው የሌላ ሰው ስም ላለማጥፋትና ላለማስቀየም ብለው ያስቀየሙትን ሰው ይቅርታ ይጠይቁና፤ የራሳቸውን ስም እንደጠለሸ፣ ልክ እንደሁለተኛዎቹ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነውና ተማምነው ዝም ይላሉ። ነገርን ሁሉ ለእግዚአብሔር መተው ጥበብ እንጂ ስንፍና አይደለም! ስምህን ለማጥራት ስትል ሕሊናህን አታርክስ፤ ሰዎች እንዲያምኑህ ስትል እግዚአብሔርን አትርሳ። በቃ እግዚአብሔርን አምኖ መቀበል ብቻ ነው አማራጭ ማድረግ ያለብን። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም #ንነጽር_212 #ስም #ወይስ #ሕሊና

Открыть в Telegram
Просмотры4 020+93%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—
#13455Текст

ለምን አርሲ ላይ ብቻ? ይሄ ነገር ለብዙ ዓመታት ታቅዶበት እየተሠራ ያለ ነገር ነው፤ ዕቅድ መሆኑን ደግሞ ለማረጋገጥ ትንሽ አቀዝቅዞ ድጋሚ መነሣቱ በቂ ማረጋገጫ ነው። ግን አርሲ ላይ ብቻ ለምን? እውነት ለመናገር ይሄም ጥያቄ፣ ይሄ ነገር ዕቅድ ስለመሆኑ ሁለተኛ ማረጋገጫ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት አርሲ ላይ ብቻ ይህ ጥቃት የሚፈጸምበት ምክንያት ምንድነው? 😑ምክንያቱም... በመጀመርያ አርሲ ላይ ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ነው። ከዚያስ? ከዚያ ደግሞ ሊኖር የተፈለገው እምነት ሙሉ ለሙሉ ማስፈን። ከዚያ በኋላ አርሲን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር። ከዚያም አርሲ ላይ ስጋት ማጫር፤ ይሄም ስጋት አርሲ የዚያች እምነት ቦታ ስለሆነች ሌላ እምነት እንዳይገባ ማድረግ። ከዚያም ለአርሲ አቅራቢያ ያለው ሰፈርም በተመሳሳይ መልኩ ግድ*ያን መፈጸምና ይህቺም ሰፈር ያንን እምነት መዝራት። ወይም ደግሞ የአካባቢውን ነዋሪ በግዴታ ሌላ እምነት እንዲቀበሉ ማድረግ። ከዚያም ቀስ በቀስ ነገሩን አረሳስቶ ወደ ቀጣዩ ሰፈር መሄድ.... መጨረሻ ላይ የኦርቶዶክስ እምነትን እስከነሙሉው ማጥፋት! እየታየ ያለዎ ዕቅድ ይሄ ነው! አመንክም አላመንክም ይሄ እምነትን የማጥፋት ሴራ ተጀምሯል! ኅቡዕ ነኝ!

Открыть в Telegram
Просмотры2 320+12%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#13454Фото

የገዳይን የመግደል ወኔን ግደልልን! በምድረ አርሲ ወንድሞቼን አጣኋቸው፣ አባቶቼንም እንዲሁ ተቀማኹ። “አንተን በማመን ውስጥ ያለ ሰው እንዴት ይሞታል?” ተብለህ የምትከሰስ አምላክ እንዳልሆንክና ነገርን ሁሉ ውብ አድርገህ እንደምትሠራም ጭምር እናውቃለን። ነገር ግን የእኛን ድካም ታውቀው የለ? የምናየው ስቃይ ከእኛ በላይ ሲሆን ጩኸታችን ወደ አንተ ያዘነብላል። ከአንተ በቀር የሚሰማ ማንም የለማ! የገዳዩን ልብ ሌላ ልብ ሰጥተህ ማኖር የምትችለው አንተ ስለሆንክ፤ እባክህን ፍረድ እያልን ብንጮህ፣ ፍርዱ ደግሞ እኛ ላይ እንዳይደርስ እየሰጋን "የገዳይን የመግደል ወኔ ግደልልን!" እያልን በልዩነት መጮህ ምርጫችንን አድርገናል። ጌታ ሆይ በአንተ እጅ የተሠራው ዕቃ(ሰው) በሰው እጅ ሲበላሽ ዝም ያልከው ስለምን ይሆን? ባበጃጀሃት ምድር ላይ ደም ሲዘንብባት ዓይተህ ያረመምከውስ ስለ ምን ይሆን? ገዳይ በአንተ መኖር ጥርጣሬ አጭሮ ልጅህን እያቆሰለ የሚያርድብህስ ስለምን ይሆን? እንግዲያስ እኛ እንደሆንን፣ ከማንም መልስን መጠበቅም ሆነ መጠባበቅ አቁመን ወደ አንተ ቀና ብለን “ሕዝብህን አድን፣ ርስትህን ጠብቅ፣ ምድርህንም አጽዳ!” እያልንህ ነው። በዚህ ሀሉ ውስጥ... ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር መታረቅ እንሻለን! እሺ በለን🙏 ✍️ ኅቡዕ

Открыть в Telegram
Просмотры3 070+48%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—

Все посты

Связи