እንኳን የሰው ሰው ይቅርና የራሳችን ጥላ እንኳ ወዳጅነቱ ከብርሃን ጋር ነው። በዚህ ምድር፣ መደነቅም ሆነ መገረም የማያስፈልገው አንድ ነገር ቢኖር፣ የሰው ልጅ የፀባይ መቀያየር ነው። ምክንያቱም የሚቀያየር ፀባይ አንዱ የሰው ልጅ ፀባይ ስለሆነ ነው። ትላንት ወዳጆቻችን የነበራችኹ፣ ዛሬ ግን በስውር የጠላችሁን ሰዎች እንዴት ናችሁ? እኛ ዛሬም እንወዳችኋለን፣ እናንተ የጠላችሁን እኮ ፈልጋችሁት አይደለም፤ ፀባያችሁ አስገድዷችሁ እንደሆነ ተረድተናል። ስታዩን አትሸማቀቁ፣ ስማችንን ስታነቡ በተንኮል አትዋጡ፣ ሥራችን ከሥራችሁ ሲበልጥ አትመቅዩ፤ ምክንያቱም እኛ እንወዳችኋለን። ልብ በሉ! ልንጠላችሁ ያልቻልነውና ከመጀመርያው ይልቅ አብልጠን የወደድናችሁ እኮ፣ ምናልባት እሳት ላይ ፍም ለመጨመርም ፈልገን ሊሆን ስለሚችል፣ ይሄ ፍም ከመጀመርያው እሳት ጋር ተያይዞ ሳይቀጣጠል በፊት ውደዱን! ወዳጅነቱን ከአየር ጋር እንዲመሠርት የፈቀድንለት ለጥላችን ብቻ እንጂ ለእናንተ አይደለም፤ ያ የመቀያየር ፀባያችሁን እንዳለ ቢሆንም፣ ለፍቅር አምላክ ብላችሁ በፍቅር ተዉት! ሰዎችን መውደድ ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም! ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 18/2019 ዓ.ም ጉራጌ ዞን፣ እዣ ወረዳ #ንነጽር_215 #ሰዎችን #መውደድ #ግዴታችን #ነው @MekuriyaM ይቀላቀሉን!
Открыть в TelegramПосты канала Dn. Mekuria Murashe || ዲ/ን መኩሪያ ሙራሼ
ሊኖረን የሚገባ አስፈላጊ ክህሎት ወዳጅነት በሌሎች ሰዎች የተለየ ውጤት የምታገኝበት መሣሪያ ነው። ሰዎች የአንተ አስፈላጊ ሀብቶች ናቸው። ወዳጅነት ደግሞ ሀብቱን የምታወጣበት ዘዴ ነው። በሕይወትህ ምንም ነገር ብትፈልግ፣ ከትክክለኛው ሰው ጋር ወዳጅነት ከመሠረትክ፣ የእነሱን ፍላጎት መሙላት ከቻልክ፣ እነሱም የአንተን ፍላጎት ይሞሉልሃል። ወዳጅነት የመመሥረት ችሎታ፣ ለሰው ልጅ ሊኖረው የሚገባ አስፈላጊ ክህሎት ነው። በሁሉም መስክ ጥሩ ሰው ለመሆን፣ ጥሩ ወዳጅ መሆን አለብህ። ጠንካራ የሆነ የሰው ልጅ ትስስር የመመሥረት ችሎታና ተገቢውን ምላሽ የሚሰጥ ትስስር የሚፈጠረው በወዳጅነት ነው። ANTHONY ROBBINS
Открыть в Telegramሾፌር በመኪናው አስክሬን ይዞ እየሄደ፣ ሾፌሩ ራሱ መኪናው ተገልብጦበት ሞተና እሱም በቅጽበት አስክሬን ሆኖ፣ ቀድሞ ጭኖት ከነበረው አስክሬን ጋር ተጫነ። አያችኋት ዓለምን?
Открыть в Telegramመልካም ልደት ለእኔ😍 ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው፤ አንድ ሥጦታ ልስጣችኹ። ይሁዳ የሠራቸው 7 ስህተቶችን ተመልከቱ! 1. ገንዘብን ከመጠን በላይ መውደድ። 2. ከገንዘብ ፍቅር የተነሣ የጌታውን እምነት መክዳት። 3. ጌታውን በ፴ ብር አሳልፎ መስጠት። 4. አባቱን መግደል። 5. እናቱን ማግባት። 6. ወደ ንስሐ አለመመለስ። 7. ታንቆ መሞት። ከሁሉም በላይ ትልቅ ስህተት የሠራው ግን “ብልጥ ለመሆን ማሰቡ” ወይም ወደ ንስሐ አለመመለሱ ነው። ብልጥ ለመሆን ባያስብና የዋሕ ሆኖ ጌታውን ይቅርታ ቢጠይቅ እነዚያ ኃጢአቶቹ በሙሉ ሊፋቁለት ይችሉ ነበር። አንድ ነገር አስተውሉ! የይሁዳ ሞት የጀመረው ገንዘብን አብዝቶ ከመውደድ ነው። ይሄ የገንዘብ መውደድ፣ ምሕረት ወደሌለው ሞት አድርሶታል። ስለዚህ ጥቂት የሚመስል ስህተት፣ ሞት ያመጣልና ከእንደዚህ ዓይነቱ ስህተትና በደል ፈጣሪ ይጠብቀን። 👆 ይህ ነው ሥጦታዬ😍 ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 7/2019 ዓ.ም #ንነጽር_214 #ሰባቱ #የይሁዳ #ስህተቶች
Открыть в Telegramሁላችንም የምናውቀው፣ ግን ደግሞ ለሁላችንም ቀላል የሚመስለን ትልቅ ኃይለ ቃል። «ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።» ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ብሎ ሲናገር፣ የዚህን ዓለም ጊዜያዊነትና ተለዋዋጭነት እያሳየን ነው። ዛሬ የምናየው ዓለም፣ የምንመካበት ሀብት፣ ሥልጣን፣ ውበትና ክብር ሁሉ ዘለዓለማዊ አይደሉም። የሚለወጡና የሚያልፉ ናቸው። ስለዚህ በሚያልፍ ነገር ላይ ዘላለማዊ ተስፋችንን መጣል አይገባንም። «ቃሌ ግን አያልፍም» ይህ ማለት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል እውነትነቱን፣ ታማኝነቱንና ፍጻሜውን ፈጽሞ አያጣም ማለት ነው። ✨ሰው ቢክደውም ቃሉ እውነት ነው። ✨ ዘመናት ቢለወጡም ቃሉ አይለወጥም። ✨ ሰዎች ተስፋ ቢቆርጡም የጌታ ተስፋ አይፈርስም። ✨ የተናገረው ትንቢትና ቃል በጊዜው ይፈጸማል። ማቴዎስ 24 ስለ ዓለም መጨረሻ፣ ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መከራዎችና ስለ ምልክቶች ይናገራል። በዚህ ሁኔታ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን አንድ ታላቅ እውነት ያስተምራቸዋል፤ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቢለወጥም እርሱ የተናገረው ቃል ግን አይለወጥም። አንድ ሰው ዛሬ ቃል ገብቶልን ነገ ሊክድ ይችላል። ዛሬ የምንመካበት ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላል። ዛሬ የምንታመንበት ዓለም ነገ ሊለወጥ ይችላል። ነገር ግን የጌታ ቃል አይከዳም፤ አይረሳም፤ አይሻርም። ስለዚህ ክርስቲያን ሰው ተስፋውን በሚያልፍ ዓለም ላይ ሳይሆን በማያልፈው ቃለ እግዚአብሔር ላይ ሊጥል ይገባል። ዓለም ቢለወጥ እውነት አይለወጥም፤ ዘመን ቢያልፍ የክርስቶስ ቃል አያልፍም! 🙏 t.me/MekuriyaM ይቀላቀሉን ✨
Открыть в Telegramመንፈሳዊነትን በይቅርታ...! መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው። መንፈሳዊነት ማለት በአንድ ዓይን መተያየት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት ከሰው ጋር ለመጋጨት ተብሎ ነገርን ከሥር መሠረቱ መመርመር ማለት አይደለም። መንፈሳዊነት ማለት መተው ማለት ነው። ሲዘልፋህ፣ ሲነቅፉህ፣ ሲያንቋሽሹህ ይቅር ካልካቸው፣ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። “ተናገር እንጂ ምን ይዘጋሃል?” ሲሉህ ዝም ካልክ አንተ መይፈሳዊ ሰው ነህ ማለት ነው። ክፋታቸውን አውቀህ ክፉ ላለመነጋገር ብለህ "block" ካደረካቸው ራሱ መንፈሳዊነት ገብቶሃል ማለት ነው። ልብህ ለይቅርታ የማይሰበር ከሆነና ከይቅርታ በኋላ እንደ ቀድሞ መሆን የማትችል ከሆነ ግን ገና መንፈሳዊነትን አልጀመርከውም። ወንበዴው ፈያታዊ ዘየማንን አስታውስ...! በሰንከንዳት ውስጥ በተናገራት የጸጸት ቃል ነበር ጌታው ይቅር ብሎት ወደ ገነት ለመግባት ቀዳሚ የሆነው፤ ስለዚህ ወንጀለኛ በይቅርታ ታላቅነት ገነት ከገባ አንተም ይቅርታ ስትባል የቀድሞውን ክፋት ሙሉ ለሙሉ መተው ይኖርብሃል ማለት ነው፤ ይህ ነው መንፈሳዊነት። በመንፈሳዊነት ያለ ይቅርታ እኮ ሲኦልን ዘግቶ ገነትን ከፍቷል። ከይቅርታ በኋላ የራስህ የሆነ ሌላ መንገድ የምታበጅና ቀድሞ የነበረህን ጓደኛ የምትተው ከሆነ መንፈሳዊነት አይደለም። ሐዋርያው ጴጥሮስን አትመለከትምን...? ጌታውን ክዶ ነበር፣ ከዚያም በይቅርታ ሲመለስ ክብሩ እንደ መጀመርያው ክብር ነበር እንጂ ያ ክህደት ከክብር አላጎደለውም፤ ክርስቶስ መንፈሳዊ ስለሆና የመንፈሳዊነት መገለጫም እንደ ክርስቶስ መሆን ስለሆነ ነው። ታዲያ አባታችን ጴጥሮስ፥ ጌታውን ክዶ ከዚያም ተመልሶ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ ክርስቶስ ካልተቀየረበት፣ እኛ ከማን ስለተማርን ነው ከይቅርታ በኋላ ሌላ ድንበር የምናበጀው? መንፈሳዊነት ማለት አለመበደል ማለት ነው ለማለት አይደለም፤ በደልን በይቅርታ ማለፍ ማለት እንጂ። ለዚህም ነው መንፈሳዊነት መተቃቀፍ ነው የምለው። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ኅዳር 1/2019 ዓ.ም ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ #ንነጽር_213 #መንፈሳዊነትን #በይቅርታ t.me/MekuriyaM ይቀላቀሉን
Открыть в Telegramስም ወይስ ሕሊና? አንዳዳዶቻችን በውሸት የጠለሸው ስማችንን ለማጥራት ብዙ ርቀት እንሄዳለን። አንዳንዶች ደግሞ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጡትና፤ ስማቸውን በሌላ መንገድ ላነሣው ሰው፣ ይቅር በለው ብለው ይጸልዩለታል። እነዚህ ሁለተኛዎቹ ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያምኑና በፈጣሪ ሥራ የሚታመኑ ናቸው። ምድራዊውን ነገር የቀበሩና ቃለ እግዚአብሔርን ብቻ ትውስ የሚላቸው ናቸው። የመጀመርያዎቹ ሰዎች ደግሞ የራሳቸውን ስም ለማጥራት ብለው ሲሮጡ፣ የሌላ የንጹሑን ግለሰብ ስም ያጠፋሉ። ከዚያም ጸጸት ውስጥ ይገቡና፤ ገና መልሰው የሌላ ሰው ስም ላለማጥፋትና ላለማስቀየም ብለው ያስቀየሙትን ሰው ይቅርታ ይጠይቁና፤ የራሳቸውን ስም እንደጠለሸ፣ ልክ እንደሁለተኛዎቹ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነውና ተማምነው ዝም ይላሉ። ነገርን ሁሉ ለእግዚአብሔር መተው ጥበብ እንጂ ስንፍና አይደለም! ስምህን ለማጥራት ስትል ሕሊናህን አታርክስ፤ ሰዎች እንዲያምኑህ ስትል እግዚአብሔርን አትርሳ። በቃ እግዚአብሔርን አምኖ መቀበል ብቻ ነው አማራጭ ማድረግ ያለብን። ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም #ንነጽር_212 #ስም #ወይስ #ሕሊና
Открыть в Telegramለምን አርሲ ላይ ብቻ? ይሄ ነገር ለብዙ ዓመታት ታቅዶበት እየተሠራ ያለ ነገር ነው፤ ዕቅድ መሆኑን ደግሞ ለማረጋገጥ ትንሽ አቀዝቅዞ ድጋሚ መነሣቱ በቂ ማረጋገጫ ነው። ግን አርሲ ላይ ብቻ ለምን? እውነት ለመናገር ይሄም ጥያቄ፣ ይሄ ነገር ዕቅድ ስለመሆኑ ሁለተኛ ማረጋገጫ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት አርሲ ላይ ብቻ ይህ ጥቃት የሚፈጸምበት ምክንያት ምንድነው? 😑ምክንያቱም... በመጀመርያ አርሲ ላይ ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ነው። ከዚያስ? ከዚያ ደግሞ ሊኖር የተፈለገው እምነት ሙሉ ለሙሉ ማስፈን። ከዚያ በኋላ አርሲን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር። ከዚያም አርሲ ላይ ስጋት ማጫር፤ ይሄም ስጋት አርሲ የዚያች እምነት ቦታ ስለሆነች ሌላ እምነት እንዳይገባ ማድረግ። ከዚያም ለአርሲ አቅራቢያ ያለው ሰፈርም በተመሳሳይ መልኩ ግድ*ያን መፈጸምና ይህቺም ሰፈር ያንን እምነት መዝራት። ወይም ደግሞ የአካባቢውን ነዋሪ በግዴታ ሌላ እምነት እንዲቀበሉ ማድረግ። ከዚያም ቀስ በቀስ ነገሩን አረሳስቶ ወደ ቀጣዩ ሰፈር መሄድ.... መጨረሻ ላይ የኦርቶዶክስ እምነትን እስከነሙሉው ማጥፋት! እየታየ ያለዎ ዕቅድ ይሄ ነው! አመንክም አላመንክም ይሄ እምነትን የማጥፋት ሴራ ተጀምሯል! ኅቡዕ ነኝ!
Открыть в Telegramየገዳይን የመግደል ወኔን ግደልልን! በምድረ አርሲ ወንድሞቼን አጣኋቸው፣ አባቶቼንም እንዲሁ ተቀማኹ። “አንተን በማመን ውስጥ ያለ ሰው እንዴት ይሞታል?” ተብለህ የምትከሰስ አምላክ እንዳልሆንክና ነገርን ሁሉ ውብ አድርገህ እንደምትሠራም ጭምር እናውቃለን። ነገር ግን የእኛን ድካም ታውቀው የለ? የምናየው ስቃይ ከእኛ በላይ ሲሆን ጩኸታችን ወደ አንተ ያዘነብላል። ከአንተ በቀር የሚሰማ ማንም የለማ! የገዳዩን ልብ ሌላ ልብ ሰጥተህ ማኖር የምትችለው አንተ ስለሆንክ፤ እባክህን ፍረድ እያልን ብንጮህ፣ ፍርዱ ደግሞ እኛ ላይ እንዳይደርስ እየሰጋን "የገዳይን የመግደል ወኔ ግደልልን!" እያልን በልዩነት መጮህ ምርጫችንን አድርገናል። ጌታ ሆይ በአንተ እጅ የተሠራው ዕቃ(ሰው) በሰው እጅ ሲበላሽ ዝም ያልከው ስለምን ይሆን? ባበጃጀሃት ምድር ላይ ደም ሲዘንብባት ዓይተህ ያረመምከውስ ስለ ምን ይሆን? ገዳይ በአንተ መኖር ጥርጣሬ አጭሮ ልጅህን እያቆሰለ የሚያርድብህስ ስለምን ይሆን? እንግዲያስ እኛ እንደሆንን፣ ከማንም መልስን መጠበቅም ሆነ መጠባበቅ አቁመን ወደ አንተ ቀና ብለን “ሕዝብህን አድን፣ ርስትህን ጠብቅ፣ ምድርህንም አጽዳ!” እያልንህ ነው። በዚህ ሀሉ ውስጥ... ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር መታረቅ እንሻለን! እሺ በለን🙏 ✍️ ኅቡዕ
Открыть в Telegramሥር አለመስደድ...! አንድ ተክል ከተተከለ በኋላ፣ ይሄ ተክል እንዲበቅል መጀመርያ የግድ ሥር መስደድ ይኖርበታል። በእርግጥ ሥር እስኪሰድና ሥር ከሰደደም በኋላ እንክብካቤ ያስፈልገዋል፤ እንጂ ልክ እንደተተከለ ሥር አይሰድም፣ ትንሽ ይቆያል። ብዙዎቻችን ችግኝን ተክለን፣ ተንከባክበን፣ እስከ ዛፍ አድርሰን፣ ቆርጠን ሽጠነዋል(ተጠቅመንበታል)፦ ለእኛ ግን ቃሉ ከተዘራብን በጣም ቆይቷል፤ ግን ዛሬም ሥር አልሰደድንም። ያ ተክል ሥር ካልሰደደ አይበቅልም እዚያው ይሞታል፤ እኛም ሥር ሳንሰድ ከተቆረጥን አናድግም፣ አንጠቅምም እንሞታለን። በቃሉ አጥር ውስጥ የቆምነውና ቃል የተዘራብን ሆይ! አንድ ቀን ይሄ ቃል ወደ ልባችን ይገባ ይሆናል በሚል ተስፋ ዓመታትን አስቆጥረናል ግን ዛሬም የለመለመ ልብ ሊኖረን አልቻለም። ቀን በቀን ቃል ይዘራብናል፣ ነገር ግን ፍሬ የለንም! ቀን በቀን ቃል ይዘራብናል፣ ነገር ግን ሥር መስደድ አቅቶናል። ነገር ግን አሁንም ተስፋ አለን፣ ሥር ሳንሰድ አይቆርጠንም እናምነዋለን! ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን ጥቅምት 14/2019 #ንነጽር_211 #ሥር #መስደድ #ይኖርብናል
Открыть в Telegramየመጨረሻው ክፍል እነሆ! 20 የአገልጋይ ዓይነቶች 16ኛ. #የሰውን_ልብ_ሳይሆን_የሰውን_ኪስ_የሚያውቀው ይህ አገልጋይ ሰውን ሲያይ በመጀመሪያ የሚጠይቀው «እንዴት ነህ?» ብቻ አይደለም፤ «ምን ሊያደርግልኝ ይችላል?» የሚለውም ነው። ገንዘብ ያለው ሰው ሲመጣ በክብር ይቀበላል። የገንዘብ አቅም የሌለው ሰው ሲመጣ ግን የሚሰጠው ትኩረት ይቀንሳል። ለገንዘብ የሚያሳየው ፍቅር ለሰው የሚያሳየውን ፍቅር ሲበልጥ አገልግሎቱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ድሃው ምዕመን «እግዚአብሔር ይስጥህ!» ሲል በፈገግታ ይሰናበታል፤ ሀብታሙ ምዕመን ግን «እግዚአብሔር ይስጥህ!» ብሎ ሲሄድ እስከ በሩ ድረስ ይሸኘዋል! 17ኛ. #በሌላው_ስህተት_ላይ_የሚያድገው ይህ አገልጋይ ራሱ ታላቅ ሥራ ለመሥራት አይቸኩልም፤ ሌላው ሰው እንዳይሠራም ይፈልጋል። አንድ ሰው ሥራ ሲጀምር ይተቻል። ሲያሳካ ይጠራጠራል። ሲወደድ ይቀናል። ሲሳሳት ግን ከሁሉም በፊት ተገኝቶ ስህተቱን ይናገራል። ሌላው ሰው በሥራው እንዲያድግ ከመርዳት ይልቅ እንዲወድቅ መጠበቅ ይመርጣል። እሱ የራሱን ስኬት በሥራ ማምጣት ካልቻለ፣ የሌላውን ስኬት በማውረድ ራሱን ከፍ ለማድረግ ይሞክራል። ግን የሌላውን መብራት በማጥፋት የራስ ብርሃን አይጨምርም! 18ኛ. #ሁሉንም_ለማስደሰት_የሚሞክረው ይህ አገልጋይ ከማንም ጋር ላለመጋጨት ይፈልጋል። ለአንዱ አዎ ይላል፤ ለሌላውም አዎ ይላል። አንዱ ሐሳብ ከሌላው ጋር ቢጋጭም ሁለቱንም ይደግፋል። በስብሰባ ላይ አንዱ ሰው «ይህ መንገድ ትክክል ነው!» ቢል፣ «እውነት ነው!» ይላል። ሌላው ደግሞ ተቃራኒውን ሲናገር፣ «አንተም ትክክል ነህ!» ይላል። ስብሰባው ሲያበቃ ግን ሁለቱ ተቃርነው ይወጣሉ፤ እሱ ብቻ ከሁለቱም ጋር ተስማምቶ ይወጣል። ሁሉንም ለማስደሰት ሲሞክር እውነትን ሊያሳዝን ይችላል። ምክንያቱም አንዳንዴ ሰላምን ለመጠበቅ ከመናገር መቆጠብ ይሻላል፤ ሌላ ጊዜ ግን እውነትን ላለመናገር የሚደረግ ዝምታ ችግሩን ያሳድጋል። 19ኛ. #የቀድሞ_ስኬቱን_ብቻ_እያወራ_የሚኖረው ይህ አገልጋይ በፊት የሠራው ሥራ አለው። ምናልባት በእውነት ብዙ ደክሞ ይሆናል። ሆኖም ያንን የቀድሞ ስኬት የዛሬው የአገልግሎት ማስረጃ እንደሆነ ይቆጥራል። «በዘመኔ እንዲህ አድርጌ ነበር፤ ያንን ሠርቼ ነበር፤ ይህን አስጀምሬ ነበር!» ማለት የዘወትር ንግግሩ ነው። የዛሬው ሥራ ሲጠየቅ ግን የትናንቱን ስኬት ያስታውሳል። አሮጌ የሥራ ሪፖርት እያነበበ ዛሬን ማለፍ ይፈልጋል። ትናንት የሠራኸው ሥራ የሚያስከብርህ ነው፤ ግን ትናንት የሠራኸውን ብቻ እያወራህ ዛሬን ካሳለፍክ፣ የዛሬው ትውልድ በትናንትህ ብቻ ሊኖር አይችልም! 20ኛ. #ሁሉንም_ተስፋ_የሚያስቆርጠው ይህ አገልጋይ በራሱ ብቻ ተስፋ አይቆርጥም፤ ሌሎችንም ተስፋ ያስቆርጣል። አንድ ወጣት አገልግሎት ለመጀመር ሲነሳ፣ «እዚህ አታድግም!» ይለዋል። አንድ ሰው ሐሳብ ሲያቀርብ፣ «ይህ አይሳካም!» ይላል። ሌላው ለመማር ሲፈልግ፣ «በእኛ ዘመን እንኳ አልተሳካም!» ይለዋል። ለራሱ የማይቻል የሚመስለውን ነገር ለሌላውም እንዳይቻል ይመኛል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከባዱ እንቅፋት ሁልጊዜ የገንዘብ እጥረት ወይም የቦታ እጥረት አይደለም፤ አንዳንዴ የሚበቅል ተስፋን ገና ከመብቀሉ በፊት የሚቆርጥ አስተሳሰብ ነው! ከእነዚህ 20 ዓይነት አገልጋዮች ውስጥ እኔ የትኛው ነኝ? ስትከታተሉ ከነበራችሁ እስኪ የመፍትሔ ሐሳብ ነው የምትሉትን ጻፉ! ምናልባት በእናንተ ሐሳብ ወደ ትክክለኛው አገልግሎት የሚመጣም አይጠፋምና ቸል ሳትሉ ሐሳባችሁን አካፍሉ! ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን
Открыть в Telegramራሳችሁን ስንተኛው ላይ አገኛችሁት? 20 የአገልጋይ ዓይነቶች | ክፍል 3 10ኛ. #ሰው_ሲያየው_ብቻ_የሚያገለግለው ይህ አገልጋይ ሰው ባለበት ቦታ ከእሱ የበለጠ ትጉህ ሰው አይገኝም። ሥራ ሲኖር ቀድሞ ይደርሳል፤ ኃላፊ ሲመጣ ከሁሉም በላይ ይሯሯጣል። ካሜራ ሲነሳ ደግሞ ድካሙ ይረሳዋል። ሰው ከሌለ ግን አገልግሎቱም አብሮ ይጠፋል። ማንም የማያየውን ሥራ እንዲሠራ ከተጠየቀ ወዲያውኑ ሌላ ሥራ ያስታውሰዋል። ለእሱ አገልግሎት ማለት ሥራ መሥራት ብቻ ሳይሆን ሰው ሲያይ ሥራ መሥራት ነው! ካሜራው ከጠፋ አገልጋዩም ይጠፋል። 😁 11ኛ. #የምስጋና_ሱሰኛው ይህ አገልጋይ ሥራ ሲሠራ አንድ ጥያቄ በውስጡ ያዘወትራል፦ «ሰዎች ምን ይሉኛል?» አንድ ቀን ሙሉ ቢደክም፣ ማንም «እናመሰግናለን!» ካላለው ልቡ ይሰበራል። ሌላ ሰው ምስጋና ካገኘ ደግሞ የራሱ ድካም ይታወሰዋል። «እኔ ይህን ያህል ሠርቼ ማንም አልተናገረም!» ይላል። ሰዎች ሲያመሰግኑት ሥራውን እንደ እግዚአብሔር ክብር ያቀርባል፤ ሲያልፉት ግን አገልግሎቱን ሊተው ይደርሳል። ምናልባት የሚፈልገው የአገልግሎት ዋጋ ሳይሆን የምስጋና ድምፅ ይሆናል፤ የሚያሳዝነው ግን ምስጋናው ሲቆም አገልግሎቱም አብሮ መቆሙ ነው! 12ኛ. #የስብሰባ_ጀግናው ይህ ሰው በስብሰባ ላይ እንደ እሳት ይነዳል። ሐሳብ ያቀርባል፣ ይከራከራል፣ ይወቅሳል፣ መፍትሔም ያስቀምጣል። «ይህ መሠራት አለበት! ያ መታረም አለበት! እንዲህ መቀጠል አይቻልም!» ይላል። ስብሰባው ሲያበቃ ግን የተወሰነውን ሥራ ማን ይሠራል? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ፣ በድንገት የስብሰባው ጀግና የሥራው ተመልካች ይሆናል። በስብሰባ ላይ የተናገረውን ያህል ቢሠራ ኖሮ ቤተክርስቲያኒቱ ብዙ ችግሮችን በፈታች ነበር። ስብሰባው ላይ መፍትሔ ፈጣሪ፤ ሥራው ላይ ግን ተሳታፊ እንኳ ለመሆን የሚያመነታ! 😄 13ኛ. #የሰውን_ስህተት_ብቻ_የሚያይ ይህ አገልጋይ በቤተክርስቲያን ውስጥ ማንም ስህተት ሳይሠራ እንደማይውል ያረጋግጣል። አንዱ ተሳስቶ ከተናገረ፣ ያስታውሰዋል። ሌላው ከተሳሳተ፣ ያስታውሰዋል። አንድ ሰው ጥሩ ሥራ ከሠራ ግን ዝምታው ይበዛል። ለራሱ ስህተት ሲሆን «ሰው ነኝ፤ እሳሳታለሁ!» ይላል። ለሌላው ሰው ሲሆን ግን «ይህ እንዴት ይሆናል? አገልጋይ ነኝ አይልም?» ይላል። ለራሱ ስህተት የምሕረት መነጽር፣ ለሌላው ስህተት የፍርድ መነጽር አለው። የሌሎችን ትንኝ ያያል፤ የራሱን ግን ግመል እንኳ አያየውም! 😅 ቱቱቱ 14ኛ. #የሐሜት_መረጃ_ማዕከሉ ይህ አገልጋይ ለአገልግሎት ከመጣው ጊዜ በላይ የሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል ጊዜ ያገኛል። ማን ከማን ጋር ተጣላ? ማን ከሥልጣን ሊወርድ ነው? ማን ማንን አልተቀበለም? ማን ምን ተናገረ? እነዚህ ጉዳዮች ከእሱ አይሰወሩም። ዜና ከሌለ ደግሞ ዜና ማቅረብ ይችላል፤ ግምትን እንደ እውነት ሊያስተላልፍም ይችላል። የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ አገልግሎትን ከማጠናከር ይልቅ አንድነትን ሊያዳክም መቻሉ ነው። አንዳንድ ቦታ የቤተክርስቲያን ማስታወቂያ ከመውጣቱ በፊት የሐሜት ማስታወቂያ ይወጣል፤ የሚያሳዝነው የሐሜቱ ዜና ከእውነቱ ቀድሞ መድረሱ ነው! 15ኛ. #ለሥራ_ሳይሆን_ለማዕረግ_የሚጥረው ይህ ሰው ለአገልግሎት ቦታ ሲኖር ከሁሉም በፊት ይገኛል። የሥራው ኃላፊነት ግን ሲነገር ወደ ኋላ ይላል። ሊታወቅ ይፈልጋል፤ ሊሾም ይፈልጋል፤ ስሙ ከሌሎች በላይ እንዲጠራ ይፈልጋል። ነገር ግን ሥራው ሲመጣ ሌላ ሰው እንዲሠራው ይጠብቃል። በእሱ አስተሳሰብ የአገልግሎት ደረጃ የሚለካው በተሸከመው ኃላፊነት ሳይሆን በተሰጠው ማዕረግ ነው። ማዕረግ ሲሰጥ ፊቱ ይበራል፤ ኃላፊነት ሲሰጥ ግን ስልኩ ይዘጋል! 😁 16ኛ. ይቀጥላል..... ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን
Открыть в Telegramወገንታት ራሳችሁን መርምሩበት😁 20 የአገልጋይ ዓይነቶች ክፍል 2 6ኛ. #ችግሩን_እያየ_ግን_አገልግሎቱን_የማይተወው1ምዕመን ይህ ምዕመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች፣ ግጭቶችና አላስፈላጊ ድርጊቶች በሚገባ ያውቃል። ሁሉንም እያየ ቢሆንም ከአገልግሎቱ አይርቅም። ልክ ጴጥሮስ ጌታውን ከሩቅ ሆኖ ይከተል እንደነበር፣ ይህም ምዕመን ከሚያየው ችግር የተነሳ ሊርቅ ቢፈተንም በቻለው መጠን አገልግሎቱን ይቀጥላል። እንደ አቅሙ በቅዳሴ ይሳተፋል፣ በጸሎት ይተጋል፣ በአገልግሎቱም ይቆያል። ሌላው ምዕመን ግን ይህን ሁሉ እያየ፦ «እኔ እዚህ መጥቼ ከምበሳጭ፣ እቤቴ ብቀመጥ ምናለ?» ብሎ ይወስናል። ከዚያም እቤቱ ይቀመጣል። በኋላ ግን ለቤተክርስቲያን ያለው ፍቅር አይቀንስም፤ ከሩቅ ሆኖ ችግሮቹን ይተቻል። አንዱ ችግሩን ለማቃናት በውስጡ ይታገላል፤ ሌላው ግን ከውጭ ሆኖ የመፍትሔ ሐሳብ ይሰጣል። ሁለቱም የቤተክርስቲያን ፍቅር አለን ይላሉ፤ የሚለያያቸው ግን የሚወስዱት እርምጃ ነው! 7ኛ. #ለመዝሙር_ብቻ_የሚመጣው_አገልጋይ ይህ አገልጋይ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣው በዋናነት ለሰንበት ትምህርት ቤትና ለመዝሙር ጥናት ነው። ኪዳን ማድረስ አያውቅም፤ ቅዳሴንም በሙሉ አገልግሎት መከታተል ለእሱ የሚያውቀው ልማድ አይደለም። ለመዝሙር ጥናት ግን ማንም አይቀድመውም። ይመጣል፣ ይለማመዳል፣ በሙሉ ድምፁ ይዘምራል፤ ጥናቱ እንዳበቃም ወደ ቤቱ ይሄዳል። ንግሥ ሲኖር ልብሰ ስብሐቱን ለብሶ፣ ከበሮውን እያዟዟረ መዝሙሩን በሙሉ ጉልበቱ ይጮኻል። ከዚያ ሲደክመው ወደ ዘኬ ለቀማ፤ ከዚያም ወደ ቤት፤ በሌላ ቀን ደግሞ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት! ለእሱ ኪዳን ማድረስ ድካም ነው፤ ቅዳሴ ማስቀደስ ጭራሽ በአስተሳሰቡ ውስጥ አይገባም። እዚህ ላይ ግን ማንንም ለማውገዝ ፈልጌ ሳይሆን የአገልግሎትን ስፋት ለማሳየት ነው። መዝሙር ጥሩ ነው፤ ሰንበት ትምህርትም ጥሩ ነው። ግን ከእነዚህ በተጨማሪ የጸሎት፣ የኪዳንና የቅዳሴ አገልግሎትንም በሚቻለው መጠን ማወቅና መሳተፍ የበለጠ ያበለጽጋል።ዐአንዳንዴ መዝሙሩን በድምፅ ከማስታወስ በፊት የአገልግሎቱን ትርጉም በልብ ማስታወስ ያስፈልጋል! ከበሮው ቢያምርም አገልግሎቱ ከዚያ የበለጠ ሰፊ ነው። 8ኛ. #የሰንበት_ትምህርት_ቤቱን_ከቤተክርስቲያን_የሚለየው_አገልጋይ ይህ ሰው የሰንበት ትምህርት ቤቱ ከዓመት ዓመት በተለያዩ በዓላትና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ገቢ ሲሰበስብ ያስተዳድራል። ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ልማት ገንዘብ ማዋሉ ተገቢ ነው። ችግሩ ግን ያ ገቢ ለራሱ ክፍል ብቻ እንዲሆን ሲፈለግ ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ሕንጻ ስትሠራ፣ ልማት ስታካሂድ ወይም ሌላ አስፈላጊ ጉዳይ ሲኖር ትንሽ ድጋፍ ለማድረግ እንኳ ፈቃደኛ አይሆንም። ከዚያም ከበላይ አካል የተለየ መንገድ እየያዘ፣ «እኔ በግሌ ካልተንቀሳቀስኩ አይሆንም!» ይላል። አባቶችንም ይወቅሳል። ከማኅበረ ቅዱሳንና ከሌሎች የቤተክርስቲያን አካላት ጋር በትብብር ከመሥራት ይልቅ በግል ፍላጎቱ መሠረት እየተለያየ ይሄዳል። አንድነት ሊኖር በሚገባበት ቦታ መከፋፈልን ያበዛል። የሚያስቀው ግን፦ ገቢ ሲሰበስብ «የእኛ ገንዘብ!» ይላል፤ ወጪ ሲመጣ «የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው!» ይላል። የሚያስደንቀው ገንዘቡ ሲገባ ድንበር አለው፤ ሲያስፈልግ ግን ድንበሩ ይሰፋል!🤭 9ኛ. #ለማቃናት_ተነሥቶ_በመጨረሻ_በአርምሞ_የሚያገለግለው ይህ ሰው የቤተክርስቲያኒቱንና የሀገረ ስብከቱን ችግሮች ተረድቷል። በችግሮቹ ላይ ለመወያየት፣ መፍትሔ ለማቅረብና ነገሮችን ለማቃናት ደፋ ቀና ይላል። ለምን ተቀመጥክ? ለምን አልተንቀሳቀስክም? ብሎ ይጠይቃል። የሚታየውን ስህተት በሥርዓት ለማስተካከል ይሞክራል። ግን ምላሹ ሁልጊዜ እንደሚጠብቀው አይሆንም። «እዚያው ደፍቶ ባስቀረህ!» ተብሎ 152ኛው መዝሙረ ዳዊት ይዘመርለታል! 😁 ይለፋል፤ ይደክማል፤ ይሞግታል፤ መፍትሔ ያቀርባል። በመጨረሻ ግን አንዳንዶች እንደ ተቃዋሚ ይቆጥሩታል፣ ሌሎች ደግሞ እንደ ችግር ፈጣሪ ያዩታል። የሚያቀርበው ሐሳብ ከመመዘኑ በፊት እሱ ራሱ ይመዘናል። እንዲህ እያለ ሲደክም፣ በመጨረሻ በአርምሞ ማገልገል ይጀምራል። አገልግሎቱን አይተውም፤ ግን ሁሉንም ለማስተካከል የነበረውን ትጋት ይቀንሳል። መጀመሪያ ችግሩን ለማቃናት ይመጣል፤ በመጨረሻ ግን ችግሩን እያየ እንዳይደክም ራሱን ማቃናት ይጀምራል! 10ኛ. ይቀጥላል ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን
Открыть в Telegram20 የአገልጋይ ዓይነቶች 1ኛ. ሥልጣንን እንደ የግል ንብረት የሚቆጥረው አገልጋይ ይህ አገልጋይ እንደምንም ብሎ ሥልጣን ላይ ይወጣል። ከዚያም ሥልጣኑን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ከመጠቀም ይልቅ ለግል ጥቅሙ ማስፈጸሚያ ያደርገዋል። የሚለውንረ የሚሰሙትን፣ የሚያጨበጭቡለትንና በማንኛውም ጉዳይ «አዎ አባታችን!» የሚሉትን ብቻ ሥልጣን ይሰጣል። እንደ እሱ አመራር፣ ብቃት ያለው ሰው ሳይሆን ታዛዥ ሰው ነው የሚፈለገው። እውነትን የሚናገር ሰው ከመሾም ይልቅ ስህተቱን የሚያጨበጭብለትን ይመርጣል። ቀስ በቀስም ሥርዓቱን እያፈረሰ፣ ለራሱ የሚመቸውን መንገድ እያበጀ ይቀጥላል። በመጨረሻም ቤተክርስቲያኒቱ «የእሱ ነች!» እስኪባል ድረስ ይደርሳል። ምዕመናን ግን የሚያዩትን እያዩ በቀስታ ይርቃሉ። ሰውዬው ቤተክርስቲያንን ለራሱ ለማስገዛት ሲሮጥ፣ ምዕመናኑ ግን ከቤተክርስቲያን ለመራቅ ይሮጣሉ! 2ኛ. ብቃት ኖሮት በሴራ የሚወድቀው አገልጋይ የማስተዳደር አቅም፣ ልምድ፣ ዕውቀትና የአገልግሎት ፍላጎት ያለው ሰው ይመጣል። ቤተክርስቲያኒቱን ለማሳደግ፣ ሥርዓትን ለማስጠበቅና ምዕመናንን ለማገልገል ይጥራል። ይሁን እንጂ በአስመሳይነት፣ በቅናትና በግል ጥቅም ፍለጋ በተጠመዱ ሰዎች መካከል ይገኛል። እነዚህም ተሰብስበው በሐሜት፣ በሴራና በውሸት ክስ ሥራውን ያደናቅፉታል። ለማቃናት የገባው ሰው ራሱ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ ይቆጠራል። በመጨረሻም ደክሞት፣ «አይ፣ ቤተክርስቲያኔ!» እያለ ኀዘኑን ለፈጣሪ እየነገረ በራሱ ፈቃድ ከሥልጣኑ ይወርዳል። ሥራ የማይሠራው በሥልጣን ይቆያል፤ ሥራ ሊሠራ የመጣው ግን ሥራውን ሳይጨርስ ይሄዳል! 3ኛ. እውነትን አይቶ ሥልጣኑን የሚፈራው አገልጋይ ይህ አገልጋይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸሙ አላስፈላጊ ድርጊቶችን በግልጽ ያያል። ስህተቱንም ያውቃል። የሚያስተካክለው ነገር እንዳለ ይገነዘባል። ሆኖም ዝም ይላል። ለምን? «ከተናገርኩ ሥልጣን አጣለሁ፤ ሰዎችም ይጠሉኛል።» ብሎ ይፈራል። ለእሱ የሚታየው ሥልጣኑ ነው፤ የሚያሳስበውም ወንበሩ ነው። «እግዚአብሔር ምን ይለኛል?» ከሚለው ይልቅ «ሰዎች ምን ይሉኛል?» የሚለው ያሳስበዋል። በዚህ ምክንያት ችግሩ እየተባባሰ ቢሄድም በአርምሞ ይቀመጣል። እንዲያውም አንዳንዴ ሰውዬው ዝም ብሎ የሚቀመጠው ከጥበብ ብዛት አይደለም፤ ከሥልጣን ፍቅር ብዛት ነው! ወንበሩ ከእውነት ጋር ሲጋጭ፣ ወንበሩ ያሸንፋል። 4ኛ. ሥልጣን አለው፤ የመሪነት ብቃት የለውም! ይህ ሰው በሀገረ ስብከት ደረጃ ከፍ ባለ የሥልጣን ቦታ ላይ ተሹሟል። ሆኖም የመሪነት ዕውቀት፣ የአስተዳደር ብቃትና ሰዎችን በጥበብ የመምራት ክህሎት ይጎድለዋል። በእጁ ያለው ሥልጣን ከብቃቱ ይበልጣል። ሊያስተዳድር የሚገባውን ጉዳይ በሥርዓት ከማስኬድ ይልቅ ጊዜውን በሥራ የማይዛመዱ ቦታዎች ማሳለፍ ይመርጣል። በስሙና በማዕረጉ እየተንጓለለ ይኖራል፤ ቤተክርስቲያኒቱ ግን በእሱ አመራር ሥር ሕዝቦቿን ለማብቃት፣ ለማስተማርና ለማሳደግ ትጠብቃለች። ሕዝቡ ከመሪው መሪነትን ይጠብቃል፤ መሪው ግን ሕዝቡ ለማዕረጉ ክብር እንዲሰጠው ብቻ ይጠብቃል! 5ኛ. ማገልገል የሚፈልግ ግን መንገድ የሚዘጋበት አገልጋይ ይህ ሰው በእውነት ማገልገል ይፈልጋል። ዕውቀት አለው፣ ችሎታ አለው፣ ፍላጎትም አለው። ግን የሚያገለግልበትን በር ማግኘት ይቸገራል። አስተዳዳሪው በዘረኝነት፣ አንዳንድ ካህናት በአስመሳይነት፣ አንዳንድ ዲያቆናትም በቅንዓት የተያዙበት ሁኔታ ሲያጋጥመው ለማገልገል የመጣው ሰው እንደ ወንጀለኛ ይታያል። በተለይ ተቀጣሪ ዲያቆን ሆኖ በችሎታው ከተለየ፣ ድምፁ ካማረና ሥራው ከተደነቀ፣ ከእሱ ያነሰ ችሎታ ያላቸው አንዳንድ ሰዎች በቅንዓት ሊነሱበት ይችላሉ። ከዚያም ተደጋጋሚ የውሸት ክስ ይቀርብበታል። እሱም፦ «እንደምንም ብዬ አዲስ አበባ ከገባሁ ነገሮች ይለወጣሉ!» ብሎ ተስፋ ያደርጋል። ነገር ግን እዚያ ለመግባት የሚጠየቀው ወጪ ሲገጥመው፣ ከችሎታው በላይ የገንዘብ ግድግዳ ቆሞ ያገኘዋል። በመጨረሻ ተስፋ ቆርጦ ይቀመጣል። የትሩፋት አገልጋይ ከሆነ ደግሞ «ይህ ሰው ምን አገልግሎት አለው?» በሚል ዕይታ የሚንቁት ሰዎች ይኖራሉ። ሆኖም ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንዳለው የሚያስታውሰው፣ የሚያበረታታውና እንዳይተው የሚያስተምረው ጠንካራ አስተማሪ ሊያገኝ ይችላል። አንዳንዴ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሥራ ለማግኘት የሚፈለገው ችሎታ ብቻ ቢሆን ኖሮ ችግር አይኖርም ነበር፤ ችሎታውን ከማሳየቱ በፊት ተስፋው እንዳይሞት መጠበቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ! 6ኛ... ይቀጥላል ✍️ኅቡዕ ነኝ ዘደብረ ጽዮን
Открыть в Telegramየማንነት ትምህርት ለአንድ ወዳጄ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩት። ታዲያ አንድ ቀን ወደ አንደኛው ጓደኛው ጋር ይደውልና ሊያገባ እንደሆነና ሚዜ ሊሆነው እንደሚፈልግ ይነግረዋል። ጓደኛውም እሺ ብሎ በደስታ ይቀበለዋል። ለሁለተኛው ጓደኛው ግን አልነገረውም፤ ከሌላ ሰው እንዳይሰማም አስጠነቀቀ። የሰርጉም ቀን ደርሰና አገባ... ካገባ በኋላ ሁለተኛው ጓደኛው ማግባቱን ይሰማና ስልክ ይደውላል። "እንዴት ስታገባ አልነገርከኝም?" ብሎ ጠየቀው። አዝማቹም መለሰና "እንደማገባ ብነግርህ ኖሮ አንተ የእኔን ሰርግ አምኖ ከመቀበል ይልቅ፤ እንዴት በዚህ ዕድሜው ያገባል? ገና ልጅ አይደለም እንዴ? ኧረ እኔስ አልሄድም ምክንያት ፈጥሬ እቀራለኹ" ብለህ ስታማኝ ትከርም ነበር። ስለዚህ ከሀሜት ነው የጠበቅኩህ አለው። ተመልከት! አንዳንድ አዋቂ ሰዎች እናንተን ሲያወሩኣችሁ በማንነታችሁ ልክ ነው። ለምን አልነገርከኝም? ለምን በዚህ ልክ ነገርከኝ? ብሎ ጓ ከማለት ይልቅ ማንነት ላይ መሥራት አስፈላጊ ነው። መመዘኛ ሚዛን እንኳ ለሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቁጥርን አያሳይም፤ እንደየክብደታችን መጠን መጠናችንን ነው የሚያሳየን። ሰውም እንዲሁ ነው ለሁሉም ሰው ተመሳሳይ ነገር አይናገርም። እንደየምልከታችን አቅም የምንችለውን ይነግረናል። ዲ/ን መኩሪያ (ዘከተፋ) ጽዮን 27/01/2019 ዓ.ም አገና፣ ኢትዮጵያ #ንነጽር_210 #ማንነት #ላይ #መሥራት
Открыть в Telegram✨ስለ #ኢየሱስ አንድ ብቻ አይደለም ብዙ እንድል ይፈቅድልኝ❤️✝️ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ። የታረደው የፋሲካው በግ፣ ሥጋውን የበሉት ሁሉ ደሙ ምልክት ሆኗቸው ከሞት የተረፉበት የዘፀአቱ በግ። ትንቢት ነቢያትም መዝሙራትም የተናገሩለት። የእባቡን አናት /ሥልጣንና አለቅነት የሻረው የሴቲቱ ዘር። ከጽድቅ መካከል ይነሣል የተባለው ታላቁ ሙሴ። አብርሃም ቀኑን ያይ ዘንድ የናፈቀው እግዚአብሔር ያዘጋጀው የመሥዋዕቱ በግ፣ ነቢያቱ ከሩቅ አይተው የተነበዩለት፣ በተስፋ አይተው የዳኑበት፤ እነሆ ከሰለሞን ጥበብ የሚበልጥ ራሱ ጥበብ የሆነ፣ የዘጋውን ማንም የማይከፍትበት፣ የከፈተውን ማንም የማይዘጋበት ታላቁ ኤልያቄም፤ አልፋና ኦሜጋ፣ ፊተኛና ኋለኛ፣ ያለና የሚኖር፣ ትላንትም ዛሬም እስከ ለዘለዓለም ያው የሆነ፣ ክብሩ የማይቀንስ፣ ግርማው የማይወርድ ዘለዓለማዊ መለኮት። ስሙ ከስሞች ሁሉ የሚበልጥ፣ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክለት፣ አጋንንት የሚንቀጠቀጡለት፣ በመጀመሪያው የነበረ፣ ሁሉን የሚገዛ፣ ግንበኞች የናቁት ግን የማዕዘን ራስ የሆነ፣ የሁላችን ራስ የሆነ፣ የድነታችን መሐንዲስ፣ ደንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የሰላም አለቃ የተባለ፣ የጽድቅ ንጉሥ፣ የንጋት ኮከብ፣ የይሁዳ አንበሳ፣ የሳሮን ጽጌረዳ፣ የዳዊት ሥር፣ የአብርሃም ዘር፣ የያዕቆብ መሠላል፣ አዲሴ መገናኛ፣ የቅዱሳን ተስፋ፣ መጽሐፉን ይወስድ ዘንድ የተገባው፣ ማኅተሙን የፈታ፣ የታረደ፣ በደሙም ለእግዚአብሔር ሰዎችን ከነገድ ከቋንቋ የዋጀ፣ ወገንና ካህናት ያደረገንና ያነገሠን፣ ሰው ሆኖ የወረደ፣ ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በመካከላችን ያደረ፣ የአባቱ ልጆች እንሆን ዘንድ ሥልጣንን የሰጠን፣ በመገረፉ ቁስል ያዳነን፣ መሥዋዕት ሆኖ ያስታረቀን፣ በደላችንንም በሥጋው ጠርቆ ያስወገደልን፣ ደዌያችንን የተሸከመ፣ ሊታረድ እንደሚሄድ በግ በሸላችሁ ፊት ስለ እኛ ሲል ዝም ያለ፣ የደቀቀልን፣ ከሰማይ የወረደው እውነተኛ እንጀራ፣ የእግዚአብሔር እንጀራ፣ እውነተኛ የወይን ግንድ፣ እውነተኛው ብርሃን፣ ሎጎስ የተባለ የእግዚአብሔር ቃል፣ ያለና የሚኖር… ✨ኢየሱስ መድኃኒት ነው፤ የተሰበረውን ልብ የሚያድን። ✨ኢየሱስ ፍቅር ነው፤ የፍቅርን ጥግ በመስቀሉ ያሳየን። ✨ኢየሱስ እውነተኛ ወዳጅ ነው፤ ሁሉም ሲርቅ ከእኛ የማይርቅ። ✨ኢየሱስ ርኅራኄ ነው፤ በድካማችን የማይንቀን። ✨ኢየሱስ ማጽናኛ ነው፤ በእንባችን መካከል የሚያበረታን። ✨ኢየሱስ ብርሃን ነው፤ በጨለማችን የሚመራን። ✨ኢየሱስ ሰላም ነው፤ በተረበሸ ልባችን ውስጥ ዕረፍትን የሚሰጠን። ✨ኢየሱስ ተስፋ ነው፤ ተስፋ በቆረጥንበት ጊዜ እጃችንን የሚይዝ። ✨ኢየሱስ መጠጊያ ነው፤ ከሰው ሁሉ ብንርቅ እንኳ ወደ እርሱ የምንሮጥ። ✨ኢየሱስ አለኝታ ነው፤ ብቻችንን እንዳንሆን የሚያደርገን። ✨ኢየሱስ ይቅርታ ነው፤ በንስሐ የሚቀበለን። ✨ኢየሱስ ደስታ ነው፤ በውስጣችን የማይጠፋ ተስፋን የሚያበራ። ✨ኢየሱስ ሕይወት ነው፤ የደከመችውን ነፍሳችንን እንደገና የሚያነቃ። ✨ኢየሱስ መንገድ ነው፤ ወደ አብ የሚመራን። ✨ኢየሱስ እውነት ነው፤ ልባችንን ነፃ የሚያወጣ። ኢየሱስ የነፍሴ ዕረፍት ነው፤ ❤️ ኃይልና ባለጠግነት፣ ጥበብም ብርታትም፣ ክብርም ምስጋናም፣ በረከትና ውዳሴ ለእርሱ ይሁን።
Открыть в Telegramእነዚህ ሁለት እውነታዎች ብልቡናህ አኑር። በኃጥአን ላይ ስለሚመጣው ፍርድ ስትል አልቅስ። ምን አልባት አንተም እነዛን ስቃዮች እምደምትቀበል አድርገህ ለራስህ እዘን። በጻድቃን ዕጣ ፈንታ ደግሞ ደስ ይበልህ። እነዛን ጸጋዎች ለማግኘት ተጋደል። አባ ኢቫግሪስ
Открыть в Telegram"እሷን መሆን የተመኘሁትን እኔን ልጅህን ይቅር በለኝ አባት ሆይ🥹❤️🩹 ማቴዎስ 26:6-7 ኢየሱስም በቢታንያ በለጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥ አንዲት ሴት እጅግ ዋጋው የከበረ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፥ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ማርቆስ 14:3 እርሱም በቢታንያ በለጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ እውነተኛ የናርዶስ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ዮሐንስ 12:3 ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ እውነተኛ የናርዶስ ሽቱ ንጥር አራት ሊትር ያህል ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባችው፥ በጠጉርዋም እግሩን አበሰችው፤ ቤቱም ከሽቱው መዓዛ ተሞላ። ሉቃስ 7:37-38 እነሆም፥ በከተማይቱ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፥ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ አመጣች፤ በስተኋላውም እግር ስር ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመር፥ በጠጉርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱውም ትቀባው ነበረ።🥹🙏
Открыть в Telegram