Переслано из ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት
#ክብረ_መነኮሳት ጣማፍ ኄራኒ በአባ ጳኩሚየስ የአንድነቱን ሥርዓት እንዴት እንደ ተቀበለች እንዲህ በማለት ነግራናለች:- "በክብር ጌታ ፊት ተንበረከኩ፡፡ ድንግል እናቱ በቀኝ ቆማለች፡፡ ጌታችንም ሊቀ መልአኩን 'ስለ ገዳማዊ ቀኖና ትረዳ ዘንድ ወደ አባ ጳኩሚየስ ይዘኻት ሂድ ስላለው፣ በረጅም እና ብርሃናማ መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ሄደ፡፡ እንደ አልማዝ የሚያበራና በመስቀል የተዋበ ዙፋን አየሁ፡፡ በዙፋኑ ላይ ግርማው የሚያበራ ሰው ተቀምጧል፡፡ የለበሰው ልብስ በወርቅ መስቀሎች ያሸበረቀ እና ልዩ፣ግሩም፣ ዐይንን የሚማርክ ነው፡፡ በእጁም መስቀል ይዟል፡፡ ሊቀ መልአኩም 'ሂጂና ለአባ ጳኩሚየስ ሰላምታ አቅርቢ' አለኝ፡፡ ስሄድ በመተላለፊያው ግራና ቀኝ በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና መነኮሳይያት ነጭ ለብሰው ቆመዋል..." *ቀሪውን ከመጽሐፉ እንድታነቡ እናበረታታለን፡፡ መጽሐፉን ከዚህ ቻናል በ'pdf' መልክ አውርደው ይጠቀሙ፡፡ https://t.me/hiwotemenekosatgroup/199 @hiwotemenekosat
Открыть в Telegram






