እግዚአብሔር ኀያል፣ ስሙም ቅዱስ ነው። የቀረቡት ይህንን ይረዳሉ፤ ይቀኙለታልም። ማርያም በውዳሴዋ ይህንኑ አቀረበች፤ "ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤ ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል" (ሉቃ 1፥49-50)። አምላኳን ይዛ (በማሕፀኗ)፣ አምላኳን ባረከች። እግዚአብሔርን ከሚፈራ ትውልድ ወጥታ የጽድቅ ትውልድ አስቀጠለች። የምሕረቱን ስፋት አስቀጠለች። Luke 1:49-50 for the Mighty One has done great things for me— holy is his name. His mercy extends to those who fear him,from generation to generation. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegram
Daily Injera
A Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible everyday in partnership with @ethbiblica. www.dailyinjera.org Follow us on FB • IG • Twitter • Viber • YT - @dailyinjera
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 7 нояб. 2026 г. | 1 240 |
| 8 нояб. 2026 г. | 1 260 |
| 9 нояб. 2026 г. | 1 400 |
| 10 нояб. 2026 г. | 1 270 |
| 11 нояб. 2026 г. | 1 200 |
| 12 нояб. 2026 г. | 1 160 |
| 13 нояб. 2026 г. | 1 140 |
| 14 нояб. 2026 г. | 1 100 |
| 15 нояб. 2026 г. | 1 100 |
| 16 нояб. 2026 г. | 1 060 |
| 17 нояб. 2026 г. | 1 090 |
| 18 нояб. 2026 г. | 1 050 |
| 19 нояб. 2026 г. | 950 |
| 20 нояб. 2026 г. | 838 |
| 21 нояб. 2026 г. | 775 |
| 22 нояб. 2026 г. | 729 |
| 23 нояб. 2026 г. | 740 |
| 24 нояб. 2026 г. | 656 |
| 25 нояб. 2026 г. | 509 |
| 26 нояб. 2026 г. | 327 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры1,4 тыс.Пересылки—Реакции32Комментарии—
- 02Просмотры1,27 тыс.Пересылки—Реакции20Комментарии—
- 03Просмотры1,26 тыс.Пересылки—Реакции22Комментарии—
- 04Просмотры1,24 тыс.Пересылки—Реакции25Комментарии—
Новые посты
በእግዚአብሔር የታሰቡ፣ እግዚአብሔርን ያስባሉ። መክበር ለማክበር፣ መጎብኘትም ለውዳሴ ያበቃል። ኤልዛቤል ማርያምን ለመገናኘት በቀረበች ጊዜና ድምፅዋን ስትሰማ በሆዷ የነበረው ጽንስ ዘለለ፤ በመንፈስም ተሞላች። ማርያምም ቀጥላ እንዲህ አለች፤ "ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤ መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች" (ሉቃ 1፥46-47)። ከነፍስ የሆነ ምስጋና፣ ከመንፈስም የሆነ አምልኮ አቀረበች። በመድኀኒቷ ደስ ስለ ተሰች ምስጋና አቀረበች። በውዳሴዋ ደስታዋን አበዛች። Luke 1:46-47 And Mary said: 'My soul glorifies the Lord and my spirit rejoices in God my Savior' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramየሐና ልብ በእግዚአብሔር ጸና። ለርሱ መሸነፉን ግን ቀጠለ፤ የምስጋናን መዝሙር አመነጨ፤ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም" (1ሳሙ 2፥2)። እግዚአብሔር ሰጪ ነው፤ የሰጠውንም ይቆጣጠራል። ሰጥቶ የሚወስድ፣ የሚሰስት አምላክ አይደለም። በማንነቱ ሰጪ ነው፤ ካሻውም ይነሣል፤ ሁሉ ለርሱ ነውና። ሁሉን ግን እንደ ቅድስናው ያደርጋል። ከርሱ ለሚቀበሉና ለሚጸኑም ዐለት ነው። በዘመናቸውም መታመኛና ዝማሬ ይሆናቸዋል። 1 Samuel 2:2 there is no one holy like the Lord; there is no one besides you; there is no Rock like our God. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramያመለጠ ሕዝብ ላስመለጠው አምላክ ይቀኛል። የድል መዝሙር ይዘምራል። ሙሴ፣ ማርያምና ሕዝቡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" ብለው ዘመሩ (ዘፀ 15፥3)። "ማርያምም ቀጥላ 'ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏል፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏልና' እያለች ዘመረችላቸው" (ቁ. 21)። እግዚአብሔር ለጦር አይዘጋጅም፤ ግን ድንገት ያጠቃል። ሕዝቡን ከወጥመድ ያድናል፤ ከቅርቃር ያወጣል። እየረታ ከፍ ከፍ ይላል። የምስጋና ምርኮንም ይወስዳል። Exodus 15:3 The Lord is a warrior; the Lord is his name. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramየእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚያከብሩ እርሱን ያወቁ ናቸው። ይህ ዕውቀት ደግሞ መቅረብን ያቀርባል፣ በፊቱም ንጹሕ ድፍረትም ይሆናል። እነርሱም ከዮሐንስ ጋራ እንዲህ ማለት ይችላሉ፤ "ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን" (1ዮሐ 3፥22)። መታዘዛቸው ልመናቸውን ያስውባል፤ ጥያቄያቸውም አቅርቦቱን ይገናኛል። 1 John 3:22 and receive from him anything we ask, because we keep his commands and do what pleases him. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegram#ArtSaturdays ባርነት መገዛትን ብቻ ይጠይቃል። ነጻነት ደግሞ መታዘዝን። በክርስቶስ ለሆኑ ደግሞ የተሰጠው ሕግ (ትእዛዝ) አርነትን የሚያጎናጽፍ ነው፤ "ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ ተመልክቶ የሚጸና፣ የሰማውን የሚያደርግና የማይረሳ ሰው በሥራው ብሩክ ይሆናል" (ያዕ 1፥25)። ቃሉ ከሸክም ወደ ዕረፍት ያመጣል። ይህ ዕረፍት ደግሞ ጠቃሚና ውጤታማ የሚያደርግ እንጂ ለሌላ ባርነት የሚዳርግ አይደለም፤ አንዳንዶች ዕፎይታቸውን ወደ ባሰ እስራት እንደሚለውጡበት። በሰሙት የሚጸኑ ግን ብሩካን ይሆናሉ። ነጻነታቸውም የብዙ ፍሬ ምክንያት ይሆናቸዋል። James 1:25 But whoever looks intently into the perfect law that gives freedom, and continues in it—not forgetting what they have heard, but doing it—they will be blessed in what they do. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramያዕቆብ በማሕፀን ሳለ ታላቁ (ዔሳው) እንደሚገዛለት ተነገረ። ከትንቢቱ በላይ ግን ጥረቱ አየለ፤ በረከትንም አታልሎ ወሰደ። ይህም ከወላጆቹ እንዲሰደድ አደረገው። በመንገድ ሳለ ግን እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም” (ዘፍ 28፥15)። ከሥጋት ወደ አጎቱ ቤት ባርነት ተሻገር፤ ብዙ መከራ አሳለፈ። ጌታ አምላክ ግን ቃሉን ጠብቆ አብሮት ዘለቀ። የሕይወት ምዕራፉ ከባድ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር እስከ ስህተቱ ታገሠው፤ ተስፋውንም ፈጸመለት። Genesis 28:15 I am with you and will watch over you wherever you go, and I will bring you back to this land. I will not leave you until I have done what I have promised you. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramበምድር ላይ የሚወድቅ ዘር ያበቃቀል ሥርዓት እንዳለው ሁሉ፣ የሰዎችም ዕድገት እንዲሁ ነው። ጌታችን በወይን ተክል በተመሰለበት የዮሐንስ 15ቱ ምሳሌ እንዲህ አለ፤ "በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም" (ቁ. 7)። ቅርንጫፍ የራሱ ሕይወት የለውም። አቅርቦቱን ሁሉ ከተክሉ ያገኛል። ከላይ የሚወርደው ዝናብ ቢያረጥበውም እንኳን ሕይወት አይሆነውም። ለልምላሜ የሚሆነውን የሚያገኘው በግንዱ በኩል ነው። እኛም የሚያስፈልገንንና የምንፈልገውን የምናገኘው በርሱ በመኖር ነው። ቃሎቹንም ስንኖር በፈቃዱ ክልል ያቆዩናል። የሚሰጠንን ሁሉ እንድንለምንም ያበቁናል። John 15:7 If you remain in me and my words remain in you, ask whatever you wish, and it will be done for you. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramየሚያምኑትንና የሚወድዱትን መታዘዝ ቀላል ነው። ከእግዚአብሔር በላይ ለዚህ ብቁ የሚሆንስ የት ይገኛል?የሚጠበቀውም መስማማት ብቻ ነው፤ አቅም ከርሱ ዘንድ ይመጣልና። ቃሉ እንዲህ ይላል፤ "ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ" (ኢሳ 1፥19)። የዚህ ግልባጩ ደግሞ ለአጥፊው አልፎ መሰጠት ነው። እግዚአብሔርን ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ 'ዕሺ' አይሉትም፤ ሁልጊዜ እንጂ! እርሱ ለተወሰኑ ጉዳዮችና ለተለዩ ሁኔታዎች ብቻ የሚፈለግ አይደለም፤ ለሁለመናና ለሁልጊዜ እንጂ። Isaiah 1:19 If you are willing and obedient, you will eat the good things of the land; @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в Telegramጽድቅና ዓመፅ በሚነጻጸሩበት ብቻ ሳይሆን አንዱ ሌላውን በሚቃረንበት ጊዜ፣ ሕያው አምላክንና የርሱን ብቻ ይዞ መጽናት የባሕርይ ልቀት ነው። እርሱ ዘመኑን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ሰዎችንም እንዲሁ ይለያል፤ "እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል" (መዝ 37፥18)። ዕውቀቱ በአቅርቦቱ ይታጀባል፤ በሚሰጠው ተስፋም ያብባል።እርሱን በመስማትና በመታዘዝ ልዩነትን ለሚያሳዩም መዝገቡ ሙሉ ነው። Psalms 37:18 The blameless spend their days under the Lord’s care, and their inheritance will endure forever. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ኢስላማዊ ግጥም@abdul_fettahРелигия7,57 тыс.
በረከተ እስጢፋኖስ | Saint Stephen's blessings@ststephenblessingsРелигия8,18 тыс.
የቅዱሳን ታሪክ@sihela_adhnoРелигия8,51 тыс.
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ@abutoibaРелигия8,61 тыс.
🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮@ibnyahya7Религия8,66 тыс.
Meleket Tube@meleket_tubeРелигия8,82 тыс.
"ቃለ እግዚአብሔር "@kaleegziabeherРелигия6,83 тыс.
قناة دروس أبي قتادة حفظه الله የአቡ ቀታዳህ አጠቃላይ ትምህርቶች@qanathabuqetadaРелигия9 тыс.