የልጅሽ ጥያቄ እስኪ ልጠይቅሺ ከሄድኩኝ ቡኋላ፤ ከእልፍኝሺ አዳራሺ ሳለሁ በሞት ጥላ። ባልሺስ ይወድሻል የልጅሽ ቀባሪ፤ ያ'ላዋቂው ሙሁር የቀለም ዘማሪ። እማ አይመስኝም፤ እውነተ አይወድሽም። ያ እንጀራ አባቴ የቤታችን አውራ፤ ብዬ ለመናገር እጠራጠራለሁ ስሙንም ስጠራ። ብቻ አይወድሽም የልጅሽ አስለቃሽ፤ መቃብር ቆፋሪው ላንቺ 'ሚስቅልሽ። እኔን ክበር ብለሽ ጠርተሺ ከምኩራቡ አዳራሺ፤ መሆኔን ስታውቂ ያአባቴ አልጋ ወራሽ? በእሳት ፈተንሺኝ ከወርቅም አብልጠሽ፤ በፍቅር ነበልባል እኔም ወደኩልሽ። ይሄው ደስ ይበልሽ እንግድህ እረፊው በሬሳዬ ኩሪ፤ ጥሩ ባል ሰቶሻል ለሆዱ አዳሪ፤ ደግሺ ሰርጊ ከጫጉላሽ እደሪ። ለታሪክ ድርሳናት እኔን ተይኝና፤ ከልብሽ ቅበርሪኝ ላንቺ እንዳልቃና። ሀዘንሽን እርሽ ተመለሽ ለባልሽ፤ ሌላ ልጅ ውለጅ መካን የሚያስብልሽ። የኮኮብ ልጅ✍️ Please join this chanel https://t.me/AB_Bier
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 15 h | 97 |
| 27 h | 112 |
- After 24 hours112
- Total to date112