. ❓የመዝሙር ጥያቄ❓ 💿ይህ መዝሙር የማነው?💿 👇 🎶የደህንነቴ መደምደሚያ🎶 🎶የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ🎶 🎶ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ🎶 🎶እኔም ተባልኩኝ ልጅህ🎶 ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ጠቃሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።
Open in TelegramPosts of የገጣሚያን ማኅበር
ባለመብቱን...! በሰነፍ ቃል ፡ እንደሁ ለምን ? ፡ እንዳልለው እግዚአብሔር ፡ ሌላም ቢሆን ፡ መንገድ አለው ያለኝን አንድ የተስፋ ቀን ፥ እንዲያነጋው ተማምዬ አምላኬን ሌት ብማፀነው ፥ ያን መሻቴን ስጠኝ ብዬ በአባይ ሚዛን አልመዝነው ፥ ባያሳየኝ ቀን አንግቶ አልወቅሰዉም እንዴት ብዬ ፥ እልፍ ይከፍታል አንዱን ዘግቶ፤ @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramየዛሬ አራት አመት ገደማ ነበር እንደማንኛውም ሞካሪ ገጣሚ ተንቀልቅዬ ይህን ቻናል የከፈትኩት 😁 ይኸው ዛሬ ከ24k በላይ አንባቢያን የሉበት channel ሆነ ፤ለእኔም ብዙ ወዳጆችን አፍርችያለሁ። ደስ ትላላችሁ በእውነት በጣም ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ተቀብያለሁ ሁላችሁም ትመሰገናላችሁ!ሁላችሁም
Open in Telegram"በዚህ ዓለም ውስጥ የምናደርጋቸው ተስፋዎች ሁሉ ሊቋረጡ ወይም ሊያሳዝኑ ይችላሉ፤ ክርስቶስ ግን ፈጽሞ የማይከዳ፣ የማይለወጥና ለዘላለም ሕያው የሆነ የተስፋችን መሠረት ነው። ልባችንን በክርስቶስ ላይ ስናደርግ፣ በሕይወታችን የሚነሳው ማንኛውም ማዕበል ቢበዛ እንኳ አንሰምጥም፤ ምክንያቱም እርሱ የነፍሳችን ጽኑ መልህቅና የደኅንነታችን አለት ነው።" @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegram[ አንተ ይድላህ እንጂ ! ] 👈 ብታስደግመኝ ፥ ኅልቁ ዳዊቴን ዜማ አልባዉን ፥ ደረቅ ሕይቴን ባገኝ ጓጉቼ ፥ ቢመረኝ አንዱ ቢጠበኝ እንኳ ፥ ሰማይ መንገዱ አልከራከር እምቢታን አልመዝ እጠበኝ በጨው ፥ እስክመዘመዝ ፤ : መዝሙር ካማረህ ፥ ከበገናዬ ያንተ ከሆነ ፥ ሁለመናዬ የውጊያ ሰልፉን ፥ ልታስተምረኝ እንደ በጎቹ ፥ ሜዳ ብታስረኝ ቀንደቅባቱን ፥ እስክትቀባኝ ለንጉሥ መንበር ፥ እስክታገባኝ አንዴ ደርሰኸኝ ፥ እስክገላገል ከዱር ውላለው ፥ ከድብ ስታገል ፤ : ደላኝ በል እንጂ ህልሜን ብትፈልግ ከመከዳዬ ደጄን አማትረህ ቀርበህ ጓዳዬ እንዲቀር ልቤ አንተን ተላምዶ የኔን ብትልከው ከወንዙ ማዶ እሺ እልሃለሁ አልልም እምቢ መሆኑ መች ጠፋኝ! የአንተ ፈቃድ አፍርሶ ገምቢ ። 👇👇 @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramአጋድመህ ምሰሶ በአይንህ ያለውን ጉድፍህን ላውጣ ትላለህ ወንድምህን አይን ራሱን አይቶ አያውቅ ከፍጥረቱ ዙሪያውን ሊቃኝ ነው ግራ ቀኝ ማለቱ በአይኖችህ መካከል የተገነደሰው ምሰሶው ካልታየህ አንተ ግብዙ ሰው ሂድ መስታወት ፈልግ ተመልከት ቁምና ማንም ማይነግርህን ያሳይሀልና ሂድ ወደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ማይዋሸው ምሰሶውን ማያው ማውጫውም እርሱ ነው! 07/03/2018E.C ከምሽቱ 05:30 LT Ab.J @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramኢየሩሳሌም የዳዊት ከተማ ናት የተባለላት የሰለሞን አይነት ጥበብ የታየባት ከሰለሞን የሚበልጥ ከርሷ የወጣባት የነገሥታት ንጉስ ለሷ የመጣላት ያቺ ውብ ከተማ እየሩሳሌም ናት የሰላም ከተማ የሰላም መሰረት የቅዱሳን አባት ብርሃን የሆነላት የእረፍት ከተማ እየሩሳሌም ናት ሊቀ ካህናችን በሰው አምሳል ሆኖ በበረት ተወልዶ 33 አመት ሰውነትን ለብሶ በሷ የኖረባት የዘለአለም አባት በርሷ የሚነግስባት የፍቅር ሁሉ ምንጭ የፍጥረታት ማማ ስምሽ ሁሉ መልካም የቅዱሳን ዜማ አለማት በሙሉ የተጠሩበት ቃል አንቺ እየሩሳሌም በአንቺ ይታያል ዘለአለም ይነግሳል በአንቺ ያበራል እየሩሳሌም ሆይ የሰላም መሰረት ድንቅ መካር ሀያል ጎልቶብሽ ይታያል ዘለአለም ይደምቃል እየሩሳሌም አንቺ ውብ ከተማ ብርሃንሽ እርሱ ለአለማት ተሰማ እየሩሳሌም ነሽ የህይወቴ ሚስጥር ከጌታዬ ጋራ የምገናኝብሽ በግርማ በክብር እየሩሳሌም ነሽ የበጉ ከተማ ፍቅር የሚነግስብሽ የአለማት ማማ ተፃፈ በዲናኦል ተሾመ ✍️ @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramእና ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ያበቃ፤ያለቀ ይመስላል አይደል😔? Let me tell you one truth🤗 ታያለህ ከልኩ አያልፍም እናም አንድ ቀን መጨረሻ ላይ የምትስቀው አንተ ትሆናለህ። እኔ'ኮ አንዳንዴ ሳስበው ያመኛል መሰለ አላቅም ...እግዚአብሔር የምባል የለም ብዬ እደመድማለው። ታውቁ እንደሆነ አላቅም እርሱ"ኮ የችግራችን ያክል ታላቅ አይደለም። ደግሞ ጥሎን አሸሽም።እናም ዝም ብሎ ማየት መልካም ነው። ሰልፉን ለእርሱ ማስረከብ። አንዳንድ ጊዜ ብቻችንን የምንችል መስሎን ስንታገል እንወድቃለን። አለመቻላችንን ለእርሱ አሳውቅን ዳር ብንይዝ አሸናፊዎች እኛ ነን። እናም ምን ልላችሁ ነው... ትንሽ ስደክማችሁ፤ ስከፋችሁ በእርሱ ታመኑና ተደገፉ ጠንካራ ትሆናላችሁ።🤗 እናም ከሙለቱ የምያልፍ ነገር የለም።እስክሞላ ነው ሁሉም ነገር። ህዳር 9/2019 @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramበጣም የምንወዳት ዘማሪት ሃና ተክሌ ምን አለች..... "የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ የምፈልገው ደስታ ጋር አልደርስም ስደርስበት ይቀልብኛል ሳልጠግበው ይሰለቸኛል የእኔ ክፍተት ሌላ ነው ብርም ወርቅም አይደለም ኢየሱስ ነው እረሀቤ መንፈስ ነው ጥጋቤ..... ምንም አዲስ ነገር የለም የምንጓጓለት ሁሉ ስንደርስበት ይቀላል። መንፈሱን እንያዝ.... @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramምኞቴን ግታልኝ : አርገኝ እንዳ መናኝ፣ ትናንት የጠየኩህ ሊጥለኝ ከሆነ : እንኳንም አልቀናኝ። By Abebaw Hailu @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramሰማዩን አየሁት መንበርህ ሰፊ ነው፣ ምድሩን ታዘብኹት ዙፋንህ ዳር የለው፣ ታዲያ ታስበው ዘንድ፥ የሰውልጅ ምንህነው?! እስመ ለአለም ምህረቱ🪽 [𝓪𝓵𝓮𝓶] @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramየእምነት መሪው "የዛሬ አመት ወንድ ልጅ ትገላገያለሽ" ብሏት ልጅ ስትጠብቅ ጭራሽ ባሏ ጥሏት ሄደ እሷም ተናዳ እንዴት እንዲህ ሆነ ስትለው የእምነት መሪው : "ወንድ ልጅ ትገላገያለሽ ነበር ያልኩሽ ይሄው ከባልሽ ተገላገልሽ" ሁሁይ😂 For funny @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramአሁን አምንሀለሁ እያደኩ ስመጣ ነፍሴ ስትወጠር አደርጋለሁ ብላ በአቅሟ ስትፍጨረጨር መረቤን ወደ ራሷ ቀራሷ መንገድ ላይ ማንንም ላታምን ግራ ቀኝም ላታይ ነበረ ደምድማ አምላኳንም ረስታ የከፈለላትን ያንን ሁሉ ትታ ነገር ግን ደከማት ለሞት ተቃረበች በራሷ ተጉዛ ሀጢአት ስላበዛች መረቧን ብታይ ወና ዙሪያዋን ስትቃኝ የቀረችው መና አሁን ግን ተረዳች መረቧን አነሳች ፊት ወደነሳችው ቀልቧን ሰበሰበች ምን ላርግልህ አባ ምኔን ትወዳለህ ምንስ ብሆንልህ ፈገግ ትላለህ የኔ ነገር ይቅር ላንተ ልኑርልህ ልቤንም ቀልቤንም ላንተ ልተውልህ አሁን አምንሀለሁ መረቤን እጥላለሁ አንተን ባልኩ ቁጥር እጥፍ እጠግባለሁ ገጣሚ ዲናኦል @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramአቤት ፍቅር 🥰🥰🥰 ታርቀናል በደሙ ነፃነት አገኘን በደላችን ሽሮ ልጆችም አስባለን ስማኝማ አንተ እየሡስ ወዶሀል አንተን ሊያድንህ እሱ ክብሩን ጥሏል ሀጢያት የሌለበት በደል የማያዉቀዉ እሡማ ነበረ ፍፁም የፍቅር ሰዉ እኛን ሊያድነን ሊታደገን ወዶ ክብሩን ጥሎ መጣ ከሰማያት ወርዶ። አይምሠልህ አንተ መዳንህ በቀላል ጌታ እኛን ወዶ በንጨት ተንጠልጥሏል እሡ እኛን ወዶ ያልሆነዉ ምን አለ ነብሱን እስከመስጠት መስቀል ላይ ዋለ። የተናቀ ሆነ እጅግ የተጠላ ደሞም የህመም ሰዉ ስናየዉ ጎስቋላ ደም ግባት የሌለዉ በደዌ የደቀቀ የሱስ ለኛ ሞቶ ሀጢያት ከኛ ረቀ። ያስገርማል ፍቅሩ እኛኑ ያየበት የኛን ህመም ታሞ እሱ ያቃሠተበት አላየሁም እኔ እንዲህ ያለ ፍቅር ለጠላቱ ሞቶ ህይወትን የሚችር። ግርፋት ሲገርፉት በሱ ሲሳለቁ የአይድ ንጉስ ሆይ ብለዉ ሲሳሳቁ ዝም አለ ስለኛ ያ ትልቁ ጌታ ህመማችን ታሞ በችንካር ተመታ። የአይሁድ ንጉስ ሆይ እራስህን አድን ከመስቀሉ ዉረድ እስኪ ከሆንክ መድን እያሉ ሲጮሁ ፍቅሩ ያልገባቸዉ እሱ ግን እንዲያለ አባት ሆይ ማራቸዉ። ✍✍ተጻፈ በዮናስ ግጥሜን ለኢየሱስ 💙እወዳችኋለሁ 💙 ማንበባችሁን በ ❤️👍😍😭🔥 SHARE Contact me @abu_ND8 @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegramተማጽኖ (በእውቀቱ ስዩም) አቤቱ የጠፈር ባለቤቱ በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ? በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ አቤቱ የፍጥረት አባት ከሰማኸኝ ምናልባት ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው አልልህም! ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች ! ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ ወሰን የሌለህ ዝምታ እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ ባይመችህም ስማኝ ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ ከአውሎ ነፋስም በላይ ከመሬት መራድም ይልቅ ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ ሰው ነው የሰው አደጋ ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ ! @Ye_Getamian_Mahiber @Ye_Getamian_Mahiber
Open in Telegram