ኃላፊው አያይዘውም የጥያቄና መልስ ውድድሩ "በብዝሀነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪቃል መካሄዱ ልዩነትን የሚያከብሩ ፣ በንግግርና ምክክር የሚያምኑ እንዲሁም ዕውቀታቸውንና ችሎታቸውን ለጋራ አላማ የሚያውሉ ዜጎችን ለመፍጠር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን በየደረጃው አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ትምህርት ቤቶች የሀገራችን ኢትዮጵያ ሕብረብሔራዊ ውበት በተግባር የሚታዩባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መአዛ መንግስቱ ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገትና ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባው አስረድተዋል። በመርሀግብሩ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በተካሄደ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ዘመናዊ ታብሌት ሞባይል ከመበርከቱ ባሻገር ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት የዕውቅና ተሰጥቷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc ነጻ የስልክ መስመር ፡- 6258
Open in Telegram
Addis Ababa Education Bureau
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 24, 2026 | 11,800 |
| Nov 25, 2026 | 8,430 |
| Nov 26, 2026 | 1,350 |
Most viewed this month
- 01Views11.8KForwards—Reactions28Comments—
- 02Views9.26KForwards—Reactions16Comments—
- 03Views8.02KForwards—Reactions14Comments—
- 04Views8.01KForwards—Reactions11Comments—
Latest posts
21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል ከተማ አቀፍ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ። (ህዳር 17/2019 ዓ.ም) የጥያቄና መልስ ውድድሩ 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ሲካሄድ በነበረ ውድድር አሸናፊ ሆነው በቀረቡ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተካሄደ ሲሆን በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድርን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክርቤት ዋና አፈጉባኤና የመርሀግብሩ የክብር እንግዳ ክብርት ወይዘሮ ቡዜና አልከድር ትምህርት ቤቶች የዕውቀት ማስተላለፊያ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ስብዕናው የተገነባና በክህሎት የበለጸገ ዜጋ የሚፈጠርባቸው ተቋማት መሆናቸውን ጠቁመው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ ብዝሀነትን የተረዳና የሌላውን ማንነት የሚያከበር ዜጋ ለመፍጠር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ውጤታማ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው በተካሄደ የማጣሪያ ውድድር አሸናፊ ሆነው በቀረቡ ተማሪዎች መካከል መካሄዱን ገልጸው በውድድሩ ከፌደራል ስርአቱ እና ከህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ጥያቄዎች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
Open in Telegramአያይዘውም ስልጠናው የበጀት መሰረትና ሚና፤ ውጤታማ የበጀት ቅድመ ሁኔታ ፤ የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አወቃቀር እንዲሁም የበጀት አይነቶችና ቀጣይ የፕሮግራም በጀት ለማዘጋጀትና ለማስተዳደር የሚጠቅሙ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠናው እንደተሰጠ አብራርተዋል፡፡ ስልጠናው ለቢሮ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች እንደተሰጠም ገልጸዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc ነጻ የስልክ መስመር ፡- 6258
Open in Telegramፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር የመንግስት በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚያደርግ መሆኑ ተገለጸ፡፡ (ህዳር 16/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ዝግጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ስልጠናው በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የመንግስት በጀት በተገቢ እቅድ ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አበበች ስልጠናውን የሚወስዱ አካላት በቂና እኩል የሆነ የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር ግንዛቤ ይዘው ወደተግባር እንዲገቡ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው ሰልጣኞች ቴክኒካል እውቀታችሁ እንዲያድግና የምታውቁት እውቀት እንዲዳብር ለስልጠናው ልዩ ትኩረት በመስጠት ስልጠናውን እንድትከታተሉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የእቅድ በጀት ዝግጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት የበጀት አደላደል ስርዓቱ ቀድሞ እንደነበረው ግምታዊ ሳይሆን ውጤትን መሰረት ባደረገ መልኩ በጀትን መድቦ ለመስራት የሚያስችል ክህሎት ለማዳበርና ወደተግባር ለመግባት ስልጠናው ሰፊ ግንዛቤ እንደሚያስጨብጥ ተናግረዋል፡፡
Open in Telegramመስማት ለተሳናቸው የቢሮው ተገልጋዮች አገልግሎት ለመስጠት የምልክት ቋንቋ ትምህርት መሰረታዊ ፋይዳ እንዳለው ተመላከተ፡፡ (ህዳር 17/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት መስማት ለተሳናቸው የቢሮው ባለጉዳዮች አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የምልክት ቋንቋ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፃል። የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት ስራው በቢሮው አገልግሎት ለማግኘት ለሚመጡ ተገልጋዮች በቀላሉ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል። አያይዘውም የቢሮው ባለሙያዎችም መስማት ለተሳናቸው ባለጉዳዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ተነሳሽነትን አድንቀው በቀጣይም ቋንቋውን በቀላሉ እንዳይረሱት በቢሮው ባለሙያዎች ተከታታይ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Open in Telegramየስነምግባርና ጸረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው የውይይት ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ሙስና የሚቀረፈው ማህበረሰቡን በማንቃት መሆኑን ገልጸው ሙስና ትስስሮችና በማጋለጥ ፤ሙስናን የመጸየፍ ባህልን በትምህርት ተቋማት በማሳደግና በመንግስት ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራርን በማስፈን የሀገርን ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ እድገት የሚያቀጭ የዜጎቸችን የመልማት ተስፋ የሚያጨልም አለማቀፋዊ ችግር የሆነውን ሙስና በጋራ ልንዋጋ ይገባል በማለት አብራርተዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc ነጻ የስልክ መስመር ፡- 6258
Open in TelegramConnections
Similar channels
🇪🇹ኢትዮ University@ethiouniversity1Education152K
Temari News@temarinewsEducation129K
Entrance Tricks@entrance_tricksEducation121K
ABDII SABAA UNIVERSITY@abdii_sabaa_universityEducation117K
ትምህርታዊ መረጃ™@tmhrt_ministers1Education234K
Sanyii Guddataa@segnigudetaEducation245K
ቀለሜ Exams@keleme_2013Education107K
Ministry Of Education News@tmhrt_minister0Education250K