ቅዱስ ዮሐንስ በስብከቱ ጥልቀት፣ በትምህርቱ ጥበብና በንግግሩ ጣፋጭነት «አፈ ወርቅ» ተብሎ ታወቀ። በርካታ ድርሳናትንና ትርጓሜዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ ትምህርቶቹም እስከ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ሀብት ሆነው ይገኛሉ። ከዕረፍቱ ከሠላሳ አምስት ዓመታት በኋላ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ትእዛዝ ኅዳር 17 አፅሙ በታላቅ ክብር ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሶ ተቀበረ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ ፊትን ዓይቶ የማያዳላ እውነተኛ ሰባኪ፣ የድሆች ጠበቃ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት አስተማሪ እና የሃይማኖት ዓምድ ነው። እግዚአብሔር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከሁላችን ጋር ትሁን። አሜን! 📝ምንጭ፦ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🕯🍂🍃🕯🍂🍃🕯🍂🍃
Open in TelegramPosts of ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
🕯🍂🍃🕯🍂🍃🕯🍂🍃 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ኅዳር 17 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች አንዱ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በመልካም አስተዳደግና በትምህርት ያደገ ሲሆን፣ በወጣትነቱ ዓለማዊ ሀብትና ክብርን ንቆ ወደ ምንኩስና ገባ። ከወላጆቹ የወረሰውንም ሀብት ለድሆችና ለምስኪኖች አከፋፈለ። በጸሎት፣ በትሩፋትና በመንፈሳዊ ትጋት የጠነከረው ቅዱስ ዮሐንስ በብዙ መንፈሳዊ መጻሕፍትና ተግሣጻት የታወቀ ሆነ። በኋላም የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ በታላቅ ትጋት ምእመናንን አስተማረ። አገለገለ። ቅዱሱ በሹመትና በሀብት የተመኩ ሰዎችንም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ከኃጢአትና ከዓመፅ ሥራቸው እንዲታቀቡ ይገሥጽ ነበር። በተለይም ንግሥት አውዶክስያ የአንዲትን ድሃ መበለት መሬት በግፍ በወሰደች ጊዜ እንድትመልስ በመጠየቁና ክፉ ሥራዋን እንድታቆም በመገሠጹ በእርሷ ምክንያት ለሁለት ጊዜ ወደ ስደት ተላከ። በመጀመሪያው ስደት ወደ ቀናች ሃይማኖት ያልገቡ ሰዎችን በማስተማር ወደ እምነት መለሰ። በሁለተኛው ስደት ግን ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ። የመጨረሻ ቃሉም፦ «ለሁሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን» የሚል ነበር።
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ሰማዕት_ወጻድቅ ለሆነችው በጣና ባሕር ላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ለነበረችው ለታላቋ እናት #ለቅድስት_ወለተ_ጴጥሮስ_ለዕረፍት_በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዐፅማቸውን የተሸከች በቅሎም ለወለደችና ለመካኖች ልዩ ቃል ኪዳን ለተሰጣቸው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሲኖዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሕዳር ፲፫ ፳፻፲፱ ዓ.ም. ጋብቻችኹን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸማችኹት የውሉደ ያሬድ ፍሬዎች መኮንን ዳኘ(ገብረ ጻድቅ)እና እህታችን አልማዝ ከተማ(ወለተ ጻድቅ ) የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ 🙏 ስታገለግሉት የኖራችኹት ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #በሮሜ_አገር በከሀዲ መኰንን በእስክድሮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች #ለቅድስት_ጣጡስ_ለዕረፍት በዓል፣ ለመነኰስ #አባ_ዳንኤልና #ለንጉሥ_አኖርዮስ_ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለእስክድርያ አገር አርባ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበረና ለተመሰገነ #ለገዳማዊ_አባ_አቡናፍር ከምስር ከተማ ውጭ ለተሰራች ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት፣ #ለቅዱስ ኪስጦስ በመኰንኑ በመክሲሞስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ በሐይቅ ዳር እንዳለ ጽጌ ረዳ መዐዛው ከሚጥም #ከቅዱስ_ፊቅጦር_ከመታሰቢያው፣ #ከንጉሥ_አኖሬዎስ_መምህር_ከአባ_አውሎጊስና #ከንጉሥ_አኖሬዎስ_ረድኡ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿 ''እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ'' መዝ ፬:፫ 🔔ዝክረ ቅዱስ ያሬድ🔔 ወርኃዊው የዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጉባኤያችን 🗓 ዛሬ 🕰ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ ✨ ዝማሬ እና ኪናዊ ሥራዎችም ተዘጋጅተዋል በረከት የሚያተርፉበት ጉባኤ ነውና እንዳትቀሩ ይኹን! ✨"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም" ቅዱስ ያሬድ✨ ⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿
Open in Telegram"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሕዳር ፲፫ ፳፻፲፱ ዓ.ም. ጋብቻችኹን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸማችኹት የውሉደ ያሬድ ፍሬዎች ወንድማች ተስፋዬ በሬሳ(ኃይለ ዮሴፍ)እና እህታችን ኢየሩስዓሌም ስዩም(ወለተ ተክለሐይማኖት )የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ 🙏 ስታገለግሉት የኖራችኹት ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!
Open in Telegram🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 ጾምን እንጹም፥ ወንድሞቻችንን እንውደድ፥ የጾምን ታላቅነት ተመልከቱ፤ ጾም ለሰነፎች ሐዘን ስትሆን ለአዋቂዎች ደስታ ናት፤ ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች የሥጋ ፍላጎቶችንም ጸጥ ታደርጋለች፤ ለወጣቶች ጸጥታንና መረጋጋትን ታስተምራቸዋለች።" ቅዱስ ያሬድ 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ ለሆነ #ለቅዱስ_ሚናስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ_ለልደት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከሚታሰበው፦ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ አባት ከሁለተኛው #አባ_ሚናስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram✨✨✨🍁✨🍁✨🍁✨🍁✨✨✨ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ✨✨🍁 ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም ( የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡ ✨✨🍁 በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ✨ምንጭ፡ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡ ✨ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ✨✨✨🍁✨🍁✨🍁✨🍁✨✨✨
Open in Telegram☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘ “አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡" ✨ቅዱስ_ኤፍሬም✨ 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #ለአገረ_ጠራክያ_ኤጲስ_ቆጶስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_መርትያኖስ_ለዕረፍት_በዓል፣ ለፋርስ ንጉሥ ተአምራት ላደረገና ክቡር ይግባንና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላሳመነ #ለአባ_ዳንኤል_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን #ሱራስጦስ_ከእንድራዎስ_ከመብራኖስ_ከራጢስና #ከይስጥ_ከጋርሴስ_ከበጥላንና ከመታሰቢያቸው #በደብረ_ቀልሞን ከተሠራች ቤተ ክስትያን ከከበረችበት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #ለቅዱስ_እግዚአብሔር አብና #ለአእላፍ_መላእክት_ለዓመታዊ_መታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ዐሥራ_ሦስት_ወንበዴዎች ስርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ #ከከበረ_ባለጸጋ_ከቅዱስ_አስከናፍር ዕረፍትና ከአገረ እንጽና ኤጲስቆጶስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ስልሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዘካርያስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram✨መልአከ ምክሩ ለልዑል ተብሎም ይጠራል። እንዲህ ተብሎ መጠራቱ ለአምላካችን እጅግ ቅርብ ባለሟል ከሚባሉት ሊቃነ መላእክት ቀዳሚው በመኾኑ ነው። ከዚህም ባለፈ ቅድመ ዓለም አዳምን ከመፍጠሩ በፊት እመቤታችን በአምላክ ሕሊና ታስባ ስትኖር አዳምን ሊፈጥረው እንዳሰበ ለመላእክት ነገራቸው። ቅዱሳን መላእክትም አዳም የሚፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል መኾኑን ሲሰሙ አምላካቸውን ለማየት እጅግ ጓጒተው እርሱን ከመፍጠር እንዳይዘገይ ጠየቁት። እንደሚበድለው በነገራቸው ጊዜ ደግሞ ይህስ ከኾነ አትፍጠረው አሉት። ኋላ ግን እመቤታችንን ከእርሱ አብራክ እንደሚፈጥራት ሲነግራቸው እጅግ ተደስተዋል። በዚህም ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ እመቤታችንን ሥሎለታል። ✨ዲያብሎስ ከክብሩ ሲዋረድ ሠራዊተ መላእክትን እየመራ ተዋግቶ የጣለው እርሱ ነው። በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሚካኤል ልዩ ቃልኪዳን ስላለው ሰዳዴ ሳጥናኤል እየተባለ ይጠራል። ✨በብሉይ ኪዳን ከነበረው ተራዳኢነት የተነሣ መጋቤ ብሉይ ይባላል። እሥራኤል ዘሥጋን በደመና እየጋረደ እና በብርሃን ፋና እየመራ ከምድረ ርስት እንዳገባቸው፣ በብሉይ ብዙ ደጋግ አበውንም ሲራዳቸው እንደነበር ተጠቅሶ ስሙ ስለሚጎላ መጋቤ ብሉይ ይባላል። ይቆየን እንኳን የመላእክት አለቃ ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። 🙏
Open in Telegramኅዳር ፲፪ በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እሥራኤልን ከግብፅ (ከፈርዖን) አገዛዝ ነጻ ያወጣበት የመታሰቢያ በዓል ነው። ✨ሚካኤል፥ ማለት መኑ ከመ አምላክ (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው። መልአኩ በዕለተ እሑድ ከተፈጠሩት መቶ ነገደ መላእክት ውስጥ በልዩነት ኃይላት ለሚባሉት ዐሥሩ ነገደ መላእክት አለቃ ነው። ከዚያም ባለፈ ሳጥናኤል በወደቀ ጊዜ ሳጥናኤልን አንከተልም ብለው በእምነት የጸኑት የሳጥናኤል ተወራጅ የኾኑት ዘጠኙ ቀሪ ነገደ መላእክት ከእርሱ ሥር ኹነዋል።
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #ለሰው_ወገን_ለሚያዝንና_ለሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረት ሁሉ ለሚማልድ #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል_እስራኤልን_ከግብፅ_ባርነት ሲወጡ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር በሆነ ሕዝብ በመንዳቸው ሁሉ እየመራ የኤርትራ ባሕር ለከፈለበት፣ #ለነዌ_ልጅ_ለነቢዩ_ለቅዱስ_ኢያሱ ለተገለጠለት፣ #ዱራታዎስና_ሚስቱን_ቴዎብስታ_ለረዳበት_ዓመታዊ_በዓልና #ለኢትዮያዊው_ንጉሥ #ለጻድቁ_ለዐፄ_በእደ_ማርያም_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ራሱ በደብረ ማህው ከታየችበት፣ ከእስክድርያ ስልሳ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ፊላታዎስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram🙏🙏🙏ሰላም ለዘባንኪ🙏🙏🙏 ሰላም ለዘባንኪ ዘተሐዝለት ቦቱ፥ ማርያም ድንግል ዘድንግልናሃ ክልኤቱ፥ ለዋሕደ አካል ሐና እምነ አካላት ሠለስቱ፥ ኮነቶ እመ ወለትኪ እንዘ አበ ምድር አልቦቱ፥ ወእም በሰማይ ኢሀለወት ሎቱ። ትርጉም ብጽዕት ሐና ሆይ ድንግል በክልኤ የምትባለውን ማርያም ድንግልን ላዘለ ጀርባሽ ሰላምታ ይገባል። ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ለሆነው ለወልድ በምድር አባት ለሌለው ለእርሱ ልጅሽ እናቱ የሆነችለት ሐና ሆይ፤ እርሱ በምድር አባት እንደሌለው ሁሉ በሰማይም እንዲሁ እናት የለችውም። መልክአ ቅድስት ሐና 💐💐💐💐🙏🙏🙏🙏💐💐💐💐
Open in Telegram✨🌿🌿✨🌿🌿✨🌿🌿✨ መልክዓ ቅዱስ ያሬድ ሰላም ለገጽከ እምነ ፀሓይ ዘያዋኪ፤ ወእምነ ጽዱል ወርኅ ዘኑኃ ሌሊት መላኪ፡፡ መምህረ ሃይማኖት ያሬድ ትንሣኤ ክርስቶስ ሰባኪ፤አድኅነኒ ወሰውረኒ እምልሣነ ሰብእ ሀዋኪ፤እስመ እንዘ ንስቲት ይእቲ እምኵሉ ተአኪ ከሚያቃጥል ፀሐይ ይልቅ ለፊትህ ሰላም ይሁን፤ ረጅም ሌሊትን ከሚመራ ጠራርቶ ከሚያበራ ጨረቃም ይልቅ (ሰላም ይሁን)፤የሃይማኖት መምህር የክርስቶስን ትንሣኤ ሰባኪ ያሬድ፤ ከሚያወናብድ (ከሚያታልል) የሰው ምላስ አድነኝና ሰውረኝ፤እርሷ ጥቂት ስትሆን ከሁሉ ትበልጣለችና (በክፋት ትበረታለችና)። ✨🌿🌿✨🌿🌿✨🌿🌿✨
Open in Telegram🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴 እንኳን #አምላክ_ለወለደች_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_እናት ለሆነች ለተመሰገነነች #ለቅድስት_ሐና_ለዕረፍት_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሁለተኛው #ከቅዱስ_አርኬላዖስ_ሰማዕት፣ #ከአበምኔት_ኤልሳዕ፣ #ከመነኰስ_ጳኵሚስና #ከሰማዕቱ_ቅዱስ_ሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Open in Telegram