Кабинет

Посты канала ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

сначала новые

#12526Текст
Просмотры415−47%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#12525Фото

🕯🍂🍃🕯🍂🍃🕯🍂🍃 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ኅዳር 17 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች አንዱ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በመልካም አስተዳደግና በትምህርት ያደገ ሲሆን፣ በወጣትነቱ ዓለማዊ ሀብትና ክብርን ንቆ ወደ ምንኩስና ገባ። ከወላጆቹ የወረሰውንም ሀብት ለድሆችና ለምስኪኖች አከፋፈለ። በጸሎት፣ በትሩፋትና በመንፈሳዊ ትጋት የጠነከረው ቅዱስ ዮሐንስ በብዙ መንፈሳዊ መጻሕፍትና ተግሣጻት የታወቀ ሆነ። በኋላም የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ በታላቅ ትጋት ምእመናንን አስተማረ። አገለገለ። ቅዱሱ በሹመትና በሀብት የተመኩ ሰዎችንም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ከኃጢአትና ከዓመፅ ሥራቸው እንዲታቀቡ ይገሥጽ ነበር። በተለይም ንግሥት አውዶክስያ የአንዲትን ድሃ መበለት መሬት በግፍ በወሰደች ጊዜ እንድትመልስ በመጠየቁና ክፉ ሥራዋን እንድታቆም በመገሠጹ በእርሷ ምክንያት ለሁለት ጊዜ ወደ ስደት ተላከ። በመጀመሪያው ስደት ወደ ቀናች ሃይማኖት ያልገቡ ሰዎችን በማስተማር ወደ እምነት መለሰ። በሁለተኛው ስደት ግን ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ። የመጨረሻ ቃሉም፦ «ለሁሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን» የሚል ነበር።

Открыть в Telegram
Просмотры419−47%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12524Фото
Просмотры397−49%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#12523Фото
Просмотры623−21%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#12522Фото
Просмотры711−9%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#12520Фото
Просмотры795+1%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#12519Фото
Просмотры685−13%к среднему
Пересылки—
Реакции30
Комментарии—
#12518Фото
Просмотры642−18%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#12517Фото
Просмотры626−20%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#12516Текст

✨✨✨🍁✨🍁✨🍁✨🍁✨✨✨ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ✨✨🍁 ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም ( የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡ ✨✨🍁 በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ✨ምንጭ፡ ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡ ✨ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ✨✨✨🍁✨🍁✨🍁✨🍁✨✨✨

Открыть в Telegram
Просмотры861+10%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#12515Текст
Просмотры745−5%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#12514Фото
Просмотры729−7%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#12513Фото
Просмотры799+2%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#12512Текст

✨መልአከ ምክሩ ለልዑል ተብሎም ይጠራል። እንዲህ ተብሎ መጠራቱ ለአምላካችን እጅግ ቅርብ ባለሟል ከሚባሉት ሊቃነ መላእክት ቀዳሚው በመኾኑ ነው። ከዚህም ባለፈ ቅድመ ዓለም አዳምን ከመፍጠሩ በፊት እመቤታችን በአምላክ ሕሊና ታስባ ስትኖር አዳምን ሊፈጥረው እንዳሰበ ለመላእክት ነገራቸው። ቅዱሳን መላእክትም አዳም የሚፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል መኾኑን ሲሰሙ አምላካቸውን ለማየት እጅግ ጓጒተው እርሱን ከመፍጠር እንዳይዘገይ ጠየቁት። እንደሚበድለው በነገራቸው ጊዜ ደግሞ ይህስ ከኾነ አትፍጠረው አሉት። ኋላ ግን እመቤታችንን ከእርሱ አብራክ እንደሚፈጥራት ሲነግራቸው እጅግ ተደስተዋል። በዚህም ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ እመቤታችንን ሥሎለታል። ✨ዲያብሎስ ከክብሩ ሲዋረድ ሠራዊተ መላእክትን እየመራ ተዋግቶ የጣለው እርሱ ነው። በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሚካኤል ልዩ ቃልኪዳን ስላለው ሰዳዴ ሳጥናኤል እየተባለ ይጠራል። ✨በብሉይ ኪዳን ከነበረው ተራዳኢነት የተነሣ መጋቤ ብሉይ ይባላል። እሥራኤል ዘሥጋን በደመና እየጋረደ እና በብርሃን ፋና እየመራ ከምድረ ርስት እንዳገባቸው፣ በብሉይ ብዙ ደጋግ አበውንም ሲራዳቸው እንደነበር ተጠቅሶ ስሙ ስለሚጎላ መጋቤ ብሉይ ይባላል። ይቆየን እንኳን  የመላእክት አለቃ ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።  🙏

Открыть в Telegram
Просмотры1 440+84%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#12511Фото
Просмотры1 300+66%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#12510Фото
Просмотры893+14%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#12509Фото
Просмотры1 080+38%к среднему
Пересылки—
Реакции21
Комментарии—
#12508Фото
Просмотры891+14%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#12507Фото
Просмотры870+11%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—