የሙሥሊሙ ቁጥር በ 10 ዓመት ውስጥ ከ 1.6 ቢልዮን ወደ 2.2 ቢልዮን አሻቅቧል። በእዚህ ፍጥነቱ ኢን ሻ አሏህ! መጪው ዘመን የዲኑ ኢሥላም ነው።
Open in Telegram
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 3, 2026 | 19,000 |
| Nov 7, 2026 | 15,950 |
| Nov 11, 2026 | 19,100 |
| Nov 12, 2026 | 18,000 |
| Nov 20, 2026 | 9,490 |
Most viewed this month
- 01Views19.1KForwards—Reactions—Comments—
- 02Views19KForwards—Reactions—Comments—
- 03Views18.6KForwards—Reactions—Comments—
- 04Views18KForwards—Reactions—Comments—
Latest posts
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጉያዋ የታቀፈቻቸው የጥንቆላ፣ የመተት እና የድግምት መጻሕፍት እነዚህ ናቸው፦ 1. ጥቁር አስማት 2. ጸሎተ ንድራ 3. መብረቀ ሰማይ 4. መጽሐፈ ልፋፈ ጽድቅ 5. ጸሎተ ሐመር 6. መጽሐፈ አልፋ ሰገድ 7. ጸሎተ አይሁድ 8. ጸሎተ ሙሴ 9. ጸሎተ ንድራ ወዓይነ ጥላ 10. የመስቀል አጥር ጸሎት ይህንን ስንላቸው "ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ እርሱ ፋል የሚባል ጥንቆላ ነው" ይሉናል፦ የሐዋርያት ሥራ 7፥22 ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉ እና በሥራውም የበረታ ሆነ። የሐዋርያት ሥራ 7፥33 አንድምታ ሙሴ በፈረዖን ቤት ባደገ ጊዜ ፋል የሚባል ጥንቆላ ተምሮ ስለነበረ አንድም ጫማህን ከእግርህ አውልቅ ያለው እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን የተማርከውን ጥንቆላህን አውልቀህ ወደ እኔ ና ሲለው ነው። ሙሴ የግብፆችን ጥበብ ጥንቆላ ሁሉ ተምሮ ነበር፦ "ፋል የሚባል ጥንቆላ አንድ ነቢይ ተምሮ ነበር" ማለት ስድብ ነው፦ ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ አንድምታ "ሙሴ ፋል የሚባል ጥንቆላ ተምሮ ነበር" ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Open in Telegramነጥብ ሁለት "ጎደሎ" ሁለት እና ሦስት ሴት ልጆች ወራሽ ሲሆኑ፦ 1. ⅛ ለሚስት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 8 = 12,500 ይሆናል። 2. ⅔ ለሁለት እና ለሦስት ሴቶች ሲሆን 100,000 × 2 ÷ 3 = 66,600 ይሆናል። 3. ⅙ ለአባት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። 4. ⅙ ለእናት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። ሁሉም ሲደመር፦ 1. 12,500 2. 66,600 3. 16,666 4. 16,666 ----------------------------- = 112,432 ሲመጣ ከ100,000 ውርሱ ላይ ተከፋፍሎ 12,432 ይጎድላል፥ ስሌቱ 112,432 - 100,000 = 12,432 ይሆናል። ምሳሌ፦ ½ ስንል 1 "በሥጥ" بَسْط ስትሆን 2 ደግሞ "መቃም" مَقَام ነው፥ "በሥጥ" بَسْط ማለት "አንሺ"Numerator" ማለት ሲሆን "መቃም" مَقَام ማለት ደግሞ "አካፋይ"Denominator" ማለት ነው። ½ አንድ ሁለተኛ ማለት ከመቶ እጅ ግማሽ 50% ማለት ነው፥ ⅔ ሁለት ሦስተኛ ማለት ከሁለት መቶ እጅ ሲሶ 66.67 % ማለት ነው። 50+66.67 = 116.67 ነው፥ 116.67 ከመቶ ያለፈ ከሁለት መቶ ያነሰ መሆኑ ስህተት ካልሆነ በተመሳሳይ 112,432 ከመቶ ያለፈ ከሁለት መቶ ያነሰ መሆኑ ስህተት አይደለም። ታዲያ 100000 ብሩን ⅛ ለሚስት፣ ⅔ ለሁለት ከሁለት በላይ ለሆኑ ሴት ልጆች፣ ⅙ ለአባት እና ⅙ ለእናት እንዴት አድርገን እናካፍል? "ዐውል" عَوْل የሚለው ቃል "ዐወለ" عَوَّلَ ማለትም "ፈለገ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አስፈላጊ" ማለት ነው፥ በሒሣብ የክፍፍል"Fraction" ሕግ ከፍተኛው የጋራ አካፋይ"Highest Common Factor(HCF) ሲሆን በዐረቢኛ "ዐውል" عَوْل ይባላል። ስለዚህ ⅛ + ⅔ + ⅙ + ⅙ = 24 ነው፥ በዚህ ስሌት ትንሹ የጋራ ብዜት 24 ሲሆን ከፍተኛው የጋራ አካፋይ 27 ነው። በሒሣብ ሕግ ክፍልፋዩ ሲጎድል የምንጠቀመው ከፍተኛው የጋራ አካፋይ ነው፥ ከፍተኛው የጋራ አካፋይ ለማግኘት በአስፈላጊ ጉዳይ የመጣ ነገር "ዐውሊይ" عَوْلِيّ ሲባል የአስፈላጊ ሂደቱ ደግሞ "ኢሥቲእዋል" اِسْتِئْوَال ይባላል። በኢሥቲእዋል ሕግ ⅛ ለሚስት፣ ⅔ ለሴቶች ልጆች፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ሲሆን፦ 1. ሚስት 24 × 1 ÷ 8 = 3 2. ሴት ልጆች 24 × 2 ÷ 3 = 16 3. አባት 24 × 1 ÷ 6 = 4 4. እናት 24 × 1 ÷ 6 = 4 3 + 16 + 4 + 4 = 27 ይሆናል። ይህንን ክፍፍል ስናካፍል በሒሣብ ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት የሆነውን 24 መሠረት አርገን ከፍተኛው የጋራ አካፋይ 27 ስናገኝ ለጎዶሎ መሙያ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ" ብለዋል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 85 ሐዲስ 53 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " أَلْحِقُوا الْفَرَائِضَ بِأَهْلِهَا በሒሣቡ 100000 ÷ 27 = 3703 ይሆናል፥ ይህንን ለእያንዳዳቸው ባለድርሻ አካላት ስንሰጥ፦ 1. ለሚስት 3 × 3703 = 11,109 2. ለሴት ልጆች 16 × 3703 = 59,248 3. ለአባት 4 × 3703 = 14,812 4. ለእናት 4 × 3703 = 14,812 ድምሩ 11,109 + 59,248 + 14,812 + 14,812 = 100,000 ይሆናል። ስለዚህ በቁርኣን እና በሐዲስ "አካፍሉ" ስንባል የሒሣብ "ክፍፍል"Fraction" ሕግ ተጠቅመን ትርፍ እና ጎደሎን እናካፍላለን እንጂ በራሳችን ሚጥጢዬ አስተሳሰብ መዝነን የዓለማቱን ጌታ የአሏህን ንግግር ሕፀፅ እና ስሑት ለማስባል መዳዳት አያዋጣም። አምላካችን አሏህ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት" ብሎናልና፦ 59፥7 መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡ አሏህንም ፍሩ፡፡ አሏህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ⅛ + ⅔ + ⅙ + ⅙ በቁርኣን ተንዚል የተደረገ ሲሆን ተንፊድ የተደረገው ደግሞ በሥስተኛው ኸሊፋው በዑመር አል ኽጧብ"ረ.ዐ." ጊዜ ነው፥ ይህ ተንፊድ ሙሉ ለሙሉ የሶሓባዎች ኢጅማዕ"Consensus" አለበት። ይህ ደግሞ ከአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ የተገኘ ሡናህ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ"፦ "የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ" ብለውናል፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 12 አል-ዒርባድ እደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእኔ በኃላ ከእናንተ ማንም ቢኖር እና ብዙ ልዩነት ቢያይ የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል-ኺላፈቱ አር-ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ! መጤ ነገርን አስወግዱ! መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው"። فَقَالَ الْعِرْبَاضُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ... فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلاَفًا كَثِيرًا فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الْمَهْدِيِّينَ الرَّاشِدِينَ تَمَسَّكُوا بِهَا وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلاَلَةٌ " የአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ ሡናህ ደግሞ በረሡል የተደገፈ ሡናህ እንጂ መጤ ቢድዓህ ስላልሆነ የጎደሎ ውርስ በኢሥቲእዋል ሕግ እንዲህ ይፈታል። በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን"ረሂመሁሏህ" የተዘጋጀ ኪታብ "ተስሒሉል ፈራኢድ" تسهيل الفرائض ተመልከቱ! “አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم አምላካችን አሏህ ለአህሉል ኩፍር ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Open in Telegramየውርስ ሒሣብ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 59፥7 መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አሏህንም ፍሩ፡፡ አሏህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ “ሚራስ” ነው፥ “ሚራስ” مِيرَاثٌ የሚለው ቃል “ወሪሰ” وَرِثَ ማለትም “ወረሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ውርስ” ማለት ነው፥ ይህም ውርስ የሟች መብት፣ ግዴታ እና ሀብት በሕይወት ላሉት ወራሾቹ የሚተላለፍበት መንገድ ነው። ለምሳሌ የውርስ ሒሳብ ሚስት ባል ቢሞትባት ልጅ ካላቸው አንድ ስምንተኛ ⅛ ልጅ ከሌላቸው አንድ አራተኛ ¼ ትወርሳለች፦ 4፥12 ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ለሚስቶች "ከአራት አንድ" አላቸው፡፡ ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ "ከስምንት አንድ" አላቸው። ይህም በእርሷ ከምትናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡ وَلَهُنَّ الرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ ۚ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ الثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم ۚ مِّن بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَا أَوْ دَيْنٍ አንዲት ሴት ግማሽ አንድ ሁለተኛ ½ ሁለት እና ሦስት ሴት ልጆች ሁለት ሦስተኛ ⅔ ይወርሳሉ፦ 4፥11 ከሁለት በላይም የኾኑ ሴቶች ብቻ ቢኾኑ ለእነርሱ ሟቹ ከተወው ውርስ ድርሻ ሁለት ወይም ከሦስት ሁለት እጁ አላቸው፥ አንዲትም ብትኾን ለእርሷ ግማሹ አላት፡፡ ፡፡ يُوصِيكُمُ اللَّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ ۖ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۚ فَإِن كُنَّ نِسَاءً فَوْقَ اثْنَتَيْنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَ ۖ وَإِن كَانَتْ وَاحِدَةً فَلَهَا النِّصْفُ እናት እና አባት ከስድስት እጅ አንድ እጅ ⅙ ያገኛሉ፦ 4፥11 ለአባት እና ለእናቱም ለእርሱ ልጅ እንዳለው ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው፡፡ وَلِأَبَوَيْهِ لِكُلِّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا السُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِن كَانَ لَهُ وَلَدٌ ۚ በእነዚህ አናቅጽ መሠረት ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንድ ሴት ልጅ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ነው፥ ለምሳሌ፦ አንድ አውራሽ 100,000 ብር ቢኖረው ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንድ ሴት ልጅ፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለማካፈል ሒሣቡን እናስላው! ነጥብ አንድ "ትርፍ" አንዲት ሴት ልጅ ወራሽ ስትሆን፦ 1. ⅛ ለሚስት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 8 = 12,500 ይሆናል። 2. ½ ለአንድ ሴት ልጅ ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 2 = 50,000 ይሆናል። 3. ⅙ ለአባት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። 4. ⅙ ለእናት ሲሆን 100,000 × 1 ÷ 6 = 16,666 ይሆናል። ሁሉም ሲደመር፦ 1. 12,500 2. 50,000 3. 16,666 4. 16,666 ----------------------------- =95,832 ሲመጣ ከ100,000 ውርሱ ላይ ተከፋፍሎ 4,168 ትርፍ ይመጣል፥ ስሌቱ 100,000 - 95,832= 4,168 ይሆናል። "አስል" أَصْل የሚለው ቃል "አሶለ" أَصَّلَ ማለትም "መሠረተ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሠረት" ማለት ነው፥ በሒሣብ የክፍፍል"Fraction" ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት"Lowest Common Multiple(LCM) ሲሆን በዐረቢኛ "አስል" أَصْل ይባላል። ስለዚህ ⅛ + ½ + ⅙ + ⅙ = 24 ነው፥ በዚህ ስሌት ትንሹ የጋራ ብዜት 24 ነው። በመሠረታዊ ጉዳይ የመጣ ነገር "አስሊይ" أَصْلِيّ ሲባል መሠረታዊ ሂደቱ ደግሞ "ኢሥቲእሷል" اِسْتِئْصَال ይባላል። በኢሥቲእሷል ሕግ ⅛ ለሚስት፣ ½ ለአንዲት ሴት ልጅ፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ሲሆን፦ 1. ሚስት 24 × 1 ÷ 8 = 3 2. ሴት ልጅ 24 × 1 ÷ 2 = 12 3. አባት 24 × 1 ÷ 6 = 4 4. እናት 24 × 1 ÷ 6 = 4 ነው። 3 + 12 +4 + 4 = 23 ሲሆን 1 ትርፍ ይኖራል። 24 - 23 = 1 ይሆናል። ነቢያችንም"ﷺ"፦ "ከፈራኢድ የወጣውን ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሄዳል" ብለውናል፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በአሏህ መጽሐፍ በተቀመጠው በአህለል ፈራኢድ መካከል በትክክል አካፍሉ! ከፈራኢድ የወጣውን ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሄዳል"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " اقْسِمُوا الْمَالَ بَيْنَ أَهْلِ الْفَرَائِضِ عَلَى كِتَابِ اللَّهِ فَمَا تَرَكَتِ الْفَرَائِضُ فَلأَوْلَى رَجُلٍ ذَكَرٍ " "ፈሪዳህ" فَرِيضَة ማለት በዚህ ዐውድ "ክፍፍል"Fraction" ማለት ሲሆን "ፈሪዳህ" فَرِيضَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ደግሞ "ፈራኢድ" فَرَائِضِ ነው፥ "ዒልመል ፈራኢድ" عِلْم الْفَرَائِض ማለት "የውርስ ክፍፍል ሕግ" ማለት ነው፥ ስለዚህ ከ 100,000 ላይ የተረፈው 4,168 ወይም ከ 24% ላይ 1% ትርፍ ለቅርብ ወንድ ልጅ ይሆናል።
Open in Telegram"እኔ መኪና አለኝ፥ ወደ መኪናዬ እሄዳለው" እያልኩኝ ከዚያ ሰዎች "መኪና ነህ" አሉኝ። ኢየሱስ፦ "እኔ አምላክ አለኝ፥ ወደ አምላኬ እሄዳለው" እያለ ከዚያ ሰዎች "እርሱ አምላክ ነው" አሉት። እኔን "መኪና ነህ" ያሉኝ እና ኢየሱስን "አምላክ ነህ" ያሉት ጤነኞች ናቸው? የክርስትና ውዝግብ
Open in Telegramበጀነት መዋለድ አለን? በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ አምላካችን አሏህ ለወንድ እና ለሴት ባሮቹ በእርሱ ያመኑትን ጀነት ያስገባቸዋል፥ በጀናህ ውስጥ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፦ 4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا 39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ 16፥31 “ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል”፡፡ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ “ተቅዋእ” تَقْوَى ማለት “አሏህ መፍራት” ማለት ሲሆን አሏህን የሚፈሩ ወንድ እና ሴት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላሉ፥ ለሙተቂን በጀነት ውስጥ ከአሏህ የኾነ ውዴታ ጥንዶች ማግኘታቸው አካላዊ ጸጋ ናቸው፦ 44፥54 ነገሩ እንደዚሁ ነው፥ ሁር ዒን እናጠናዳቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ አማንያን በጀነት ውስጥ የሚፈልጉት ሁሉ አለ ማለት ግን ጀነት ውስጥ መዘወጅ እንጂ ልጅ መውለድ የለም፦ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38 ሐዲስ 41 "አቢ ረዚን አል ዑቀይሊይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የጀናህ ባለቤቶች በጀናህ ውስጥ ልጅ አይወልዱም።"።عَنْ أَبِي رَزِينٍ الْعُقَيْلِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ أَهْلَ الْجَنَّةِ لاَ يَكُونُ لَهُمْ فِيهَا وَلَدٌ " . አሏህ የመውለድ ፍላጎት ስለማይሰጣቸው አይወልዱም፥ ፍላጎት ግን ሰቷቸው ልጅን በጀነት ቢፈልጉ እንደ ፍላጎታቸው የሕፃኑ እርግዝናው፣ መወለዱ እና እድገቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይሆናል፦ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38 ሐዲስ 41 "ኢብኑ ሠዒድ አል ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሙእሚን ልጅን በጀነት ቢፈልግ እንደ ፍላጎቱ እርግዝናው፣ መወለዱ እና እድገቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይሆናል።"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " الْمُؤْمِنُ إِذَا اشْتَهَى الْوَلَدَ فِي الْجَنَّةِ كَانَ حَمْلُهُ وَوَضْعُهُ وَسِنُّهُ فِي سَاعَةٍ كَمَا يَشْتَهِي " "ሐምል ሁ" حَمْلُهُ "ወድዑ ሁ" وَضْعُهُ "ሢንን ሁ" سِنُّهُ የሚለው የሚጠጋው ወደ ሕፃኑ ነው፥ "ሢንን ሁ" سِنُّهُ ማለት "ዕድገቱ" ማለት ሲሆን የሚያድገው ሕፃኑ ነው። "ወለድ" وَلَد ማለት "ልጅ" ማለት ሲሆን "ሁ" የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ወለድ" وَلَد የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ይህ ሐዲስ ገሪብ ቢሆንም አሏህ ለሙእሚን በሰጠው ፍላጎት የሚፈልጉት ሁሉ እንዳለ ለማመላከት የገባ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Open in Telegramፍጡር አታምልኩ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥47 ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ የነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" ላይ "ታሕታይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት"Lower Christology" ማለት በአንፆኪያ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ከሰውነት ወደ አምላክነት የሚደረግ አሪስጣጣሊሳዊ ፍልስፍና"Aristotelian Philosophy" መሠረት ያረገ ጥናት ሲሆን ሙግት አዋቅሮ እና አደራጅቶ ድባቅ ለማስገባት ከታሕታይ ነገረ ክርስቶስ መጀመሩ ጥሩ ነው። አንድ አምላክ አለ፥ ይህ አንድ አምላክ ሰውን በማኅፀን የሚፈጥር ነው፦ ኢዮብ 31፥15 እኔን በማኅፀን የፈጠረ እርሱንስ የፈጠረው አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለንምን? πότερον οὐχ ὡς καὶ ἐγὼ ἐγενόμην ἐν γαστρί, καὶ ἐκεῖνοι γεγόνασι; γεγόναμεν δὲ ἐν τῇ αὐτῇ κοιλίᾳ. አንዱ አምላክ ከአዳም የጎን አጥንት ያለ ወንድ ሕዋስ እና ያለ ሴት ሕዋስ ሰው መፍጠር ከቻለ ከሴት የአብራክ ሕዋስ ያለ ወንድ ሕዋስ ኢየሱስን መፍጠር ችሏል። ኢየሱስ በትንቢት መነጽር "ከማኅፀን የሠራኝ" በማለት ይናገራል፦ ኢሳይያስ 49፥5 አሁንም በሐሼም ዓይን ከብሬአለሁና፣ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና፣ ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን የሠራኝ ሐሼም እንዲህ ይላል። וְעַתָּ֣ה׀ אָמַ֣ר יְהוָ֗ה יֹצְרִ֤י מִבֶּ֙טֶן֙ לְעֶ֣בֶד ל֔וֹ לְשׁוֹבֵ֤ב יַֽעֲקֹב֙ אֵלָ֔יו וְיִשְׂרָאֵ֖ל לֹא יֵאָסֵ֑ף וְאֶכָּבֵד֙ בְּעֵינֵ֣י יְהוָ֔ה וֵאלֹהַ֖י הָיָ֥ה עֻזִּֽי׃ የግዕዙ ላይ "ዘፈጠረኒ በውስጠ ከርሰ እምየ" ሲለው ትርጉሙ "ከእናቴ ማሕፀን የፈጠረኝ" ማለት ነው፥ የእነርሱ የሚሊኒየሙ ላይም በግልጽ "የፈጠረኝ" ብለው አስቀምጠውታል። ኢሳይያስ 49፥5 ላይ "የፈጠረኝ" የሚለው ተናጋሪ ኢየሱስ እንደሆነ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 21 "ዳግመኛም የያዕቆብን ወገን አንድ ለማድረግ እስራኤልን ለማዳን አገልጋይ እሆነው ዘንድ "በማኅፀን የፈጠረኝ" እግዚአብሔር እርሱ ይወደኛልና"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 22 "ይህ በቅድስት ድንግል ማርያም የተፈጠረበት ምክንያት እስራኤልን ብቻ ለማዳን አይደለም፥ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉን አሕዛብን ለማዳን ነው እንጂ"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 76 ቁጥር 19 "ዳግመኛም መድኅን ክርስቶስ ከድንግል ስለመወለዱ በኢሳይያስ አፍ “ብዙ ሥራ እሠራ ዘንድ የያዕቆብንም ወገን አጸና ዘንድ አስራኤልንም አንድ አደርግ ዘንድ ከድንግል ማኅፀን "ተፈጠርኩ" አለ"። ዐማርኛው ላይ "ተጸነስኩ" ቢሉትም ግዕዙ ላይ "ተፈጥረ" ብሎ አስቀምጠውታል፥ "ፍጡረ" ማለት "ፍጡር" ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም የተፈጠረ ፍጡር ነው፦ ፨ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 56 ቁጥር 21 "ሰው ስለሆነ "ፍጡር" ቢባል ወዲህ በር ተባለ"። ፨ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 19 “ወዲህም ከሴት በሥጋ ስለተወለደ "ፍጡር" እንላለን”። ዐማርኛ ላይ "ሰው" ብለው ቢያስቀምጥም ግዕዙ "ፍጡረ" ብሎ አስቀምጦታል፦ "ወዓዲመ ንብሎ "ፍጡረ" እስመ ውእቱ ተወልዶ በሥጋ እም ብእሲት"። ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ በእርግጥ በሥጋ ፍጡር ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 29 "ቃል እርሱ በሥጋ ፍጡር እና ሟች ነው"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 35 ቁጥር 6 "ዳግመኛም ሥጋ ስለሆነ ፍጡር ይባላል"። ግዕዙ፦ "ወዓዲመ ይትበሃል "ፍጡረ" በእንተ ዘኮነ ሥጋ" ይለዋል፥ ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረው እና የተወለደው መለኮት ሳይሆን ፍጡር ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 38 ቁጥር 25 "መለኮት ፍጡር አይደለም፥ ሥጋ ግን ፍጡር ነው"። ግዕዙ፦ "መለኮትሰ ኢ ፍጡር ውእቱ ወሥጋሰ ፍጡር ውእቱ" ይለዋል፥ "ሥጋ" ሲባል "ሰው" ማለት እንጂ መንፈስ እና ነፍስ የሌለው ቁርበት እና ቅርፊት ማለት አይደለም። ፍጥረትን የፈጠረ አምላክ ነገርን ይሠራል እንጂ እርሱ አይሠራም፥ "ፍጡር" ለተፈጠረ ነገር እንጂ አምላክ አይፈጠርም። ሐሼም ለኢሳይያስ ከመናገሩ በፊት አምላክ አልተሠራም፥ ለኢሳይያስ ከመናገሩ በኃላ አምላክ አይሠራም፦ ኢሳይያስ 43፥10 ከእኔ በፊት "አምላክ አልተሠራም" ከእኔም በኋላ አይሆንም። לְפָנַי֙ לֹא־נ֣וֹצַר אֵ֔ל וְאַחֲרַ֖י לֹ֥א יִהְיֶֽה׃ס "አምላክ አይሠራም" እያለ "አምላክ በሥጋ ተሠራ፣ ተፈጠረ፣ ፍጡር ነው" ማለት ጤናማ ትምህርት አይደለም፥ ሃይማኖተ አበው ላይ "ኢየሱስ ፍጡር ነው" የሚል በቁና ሰፍሮ እያለ "ፍጡር አይደለም፥ ፍጡር አይባልም" ማለት "አሞኛችሁ ዘንድ ዓይናችሁን ጨፍኑ" ማለት ነው። ኢየሱስ ሰው ከሆነ በሙግት አወቃቀር ስሙር ሙግት"Valid Argument" እንደዚህ ነው፦ 1. የሙግት ነጥብ"Premise" አንድ፦ "ሰው ሁሉ ፍጡር ነው"። 2. የሙግት ነጥብ"Premise" ሁለት፦ "ኢየሱስ ሰው ነው"። 3.ድምዳሜ"Conclusion"፦ ስለዚህ ኢየሱስ ፍጡር ነው። መርየም አሏህን፦ "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፦ 3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ አሏህም በመልአኩ፦ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦ 3፥47 ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ አሏህ ያለ ወንድ እና ያለ ሴት ዘር አደምን ከአፈር ከፈጠረ እና ሐዋን ያለ ሴት ዘር ከአደም አጥንት ከፈጠረ ዒሣን ካለ ወንድ ዘር ከመርየም ብቻ መፍጠር ይችላል፥ ዒሣ በድንግልና መፀነሱ እና እናቱ መርየም በድንግልና መፅነሷ በእርግጥ ተአምር ናቸው፦ 23፥50 የመርየምን ልጅ እና እናቱን ተአምር አደረግናቸው፡፡ وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً 21፥91 እርሷን እና ልጅዋን ለዓለማት ተአምር ያደረግናትን አስታውስ፡፡ وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ ክርስቲያኖች ሆይ! ከማርያም ማኅፀን የተፈጠረውን ፍጡር አታምልኩ! ወደ አሏህ ኑ እና እርሱን በብቸኝነት እናምልክ፥ በዲኑል ኢሥላም የሚመለከው በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ኻሊቁ ብቻ ነው። ኻሊቁና አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Open in Telegramሰው አያነብም ብለው ይጫወቱበታል። "ፈጣሪ እና ፍጡር" አይባልም ይሉና ግን በግዕዝ "ፈጣሪ ወፍጡር" ይባላል ይሉናል። ለመሆኑ ሰው ግዕዝ አያውቅም እያላችሁ ለምን በሕዝቡ ትጫወታላችሁ? "ወ" ማለት በግዕዝ እኮ "እና" ማለት ነው፦ ማቴዎስ 2፥21 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑን እና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። ግዕዙ፦ ወተንሢኦ ነሥአ ሕፃነ "ወ"እሞ ወቦአ ውስተ ምድረ እስራኤል። ይህንን ከተረዳን "ፈጣሪ ወፍጡር" ማለት "ፈጣሪ እና ፍጡር" ማለት ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 124 ቁጥር 18 "እኛስ ይህን አንድ ወልድን አምላክ እና ሰው፣ ገዥ እና ተገዥ፣ ሠዋዒ እና ተሠዋዒ፣ ፍጡር እና ፈጣሪ ሆኖ እናገኘዋለን"። "ወ" ማለት በግዕዝ "እና" ማለት ከሆነ "ፍጡር ወፈጣሪ" ማለት "ፍጡር እና ፈጣሪ" ማለት ነው። ፈጣሪ አምላክ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ቻይ፣ የማይሞት፣ የማይተኛ ነው፥ ፍጡር ሰው ደግሞ "ሁሉን ዐላዋቂ፣ ሁሉን የማይችል፣ የሚሞት፣ የሚተኛ ነው። ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን ዐላዋቂ፣ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፣ የማይሞት እና የሚሞት፣ የማይተኛ እና የሚተኛ ማለት እርስ በእርስ ግጭት አይደለምን? ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Open in Telegramፍትወት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ! እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፥ መንገድነቱም ከፋ። وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا "ዚና" زِّنَىٰ የሚለው ቃል "ዘነ" زَنَى ማለትም "ዞሞተ" "ተመኘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ዝሙት"Fornication" "አምሮት" "ፍትወት"Lust" ማለት ነው፥ ዚና "ሸህዋህ" شَهْوَة በሚል ይመጣል። አሏህ በአደም ልጅ ላይ የግድ ማድረግ ያለበትን ከፍትወት ክፍሉን ጽፏል፥ ይህም የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት መናገር ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46 ሐዲስ 32 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በአደም ልጅ ላይ የግድ ማድረግ ያለበትን ከፍትወት ክፍሉን ጽፏል፥ ይህም የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት መናገር ነው። የነፍስ ፍላጎት እና ምኞት ያ ሊተገበር ወይም ላይተገበር ይችላል"። قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ عَلَى ابْنِ آدَمَ حَظَّهُ مِنَ الزِّنَى أَدْرَكَ ذَلِكَ لاَ مَحَالَةَ فَزِنَى الْعَيْنَيْنِ النَّظَرُ وَزِنَى اللِّسَانِ النُّطْقُ وَالنَّفْسُ تَمَنَّى وَتَشْتَهِي وَالْفَرْجُ يُصَدِّقُ ذَلِكَ أَوْ يُكَذِّبُهُ " "ፍትወት" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "ጎምጅታ" "አምሮት" "ምኞት" ማለት ነው፥ "አላ አሐዱ አሐዱ ይትሜከር በፍትወተ እንቲኣሁ ወይወፅእ ኀቤሃ ወይደነግፅ" ሲል ይህንን ታሳቢ አርጎ ነው፦ ያዕቆብ 1፥14 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ "ምኞት" ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል። እዚህ ጥቅስ ላይ "ምኞት" ለሚለው በግዕዙ የገባው ቃል "ፍትወት" ነው፥ ፍትወት በተፈጥሮ የተቀመጠ ነገር ሲሆን ሊተገበር ወይም ላይተገበር ይችላል። የተራክቦ ፍትወት አሏህ በሁሉም ላይ እንድናደርግ የጻፈው ነው፥ ይህንን የተራክቦ ፍትወት በትዳር ካደረግን ሐላል ሲሆን ከትዳር ውጪ ካደረግነው ግን ሐራም ነው። የተራክቦ ፍትወት ሊተገበር ላይተገበር የሚችል ነገር ሲሆን ያለ ትዳር በሐራም ተፈልጎ እስካልተሠራ ድረስ መላእክት አይጽፉትም። በሐራም ቢሠራት ግን ቢጤዋን ይጽፋሉ፥ ነገር ግን አንድ ሰው ለአሏህ ሲል በሐራም ከመሥራት ቢመለስ ለእርሱ አንድ ሐሠናህ ይጻፍለታል። በሐላል የፍትወት ተራክቦ መልካም ሥራ ነውና አንድ ሰው በሐላል ለመሥራት በፈለገ ጊዜ ግን ካልሠራት አንድ ሐሠናህ ይጻፍለታል፥ በሐላል ቢሠራ ግን ለእርሱ ከአስር እስከ ሰባ ሐሠናት ይጻፍለታል፦ ኢማም በኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 126 አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "አሏህ ለመላእክት፦ "ባሪያዬ መጥፎ ሥራ ለመሥራት በፈለገ ጊዜ እስካልሠራት ድረስ አትጻፏት፣ ቢሠራት ግን ቢጤዋን ጻፏት፣ ነገር ግን ለእኔ ሲል እርሷን ከመሥራት ቢመለስ ለእርሱ አንድ ሐሠናህ ጻፉለት፣ መልካም ሥራ ለመሥራት በፈለገ ጊዜ ግን ካልሠራት አንድ ሐሠናህ ጻፉለት፣ ቢሠራት ግን ለእርሱ ከአስር እስከ ሰባ ሐሠናት ጻፉለት" ይላቸዋል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " يَقُولُ اللَّهُ إِذَا أَرَادَ عَبْدِي أَنْ يَعْمَلَ سَيِّئَةً فَلاَ تَكْتُبُوهَا عَلَيْهِ حَتَّى يَعْمَلَهَا، فَإِنْ عَمِلَهَا فَاكْتُبُوهَا بِمِثْلِهَا وَإِنْ تَرَكَهَا مِنْ أَجْلِي فَاكْتُبُوهَا لَهُ حَسَنَةً وَإِذَا أَرَادَ أَنْ يَعْمَلَ حَسَنَةً فَلَمْ يَعْمَلْهَا فَاكْتُبُوهَا لَهُ حَسَنَةً، فَإِنْ عَمِلَهَا فَاكْتُبُوهَا لَهُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِمِائَةٍ ስለዚህ "ሰው የግድ ዝሙት እንዲያደርግ ተጽፎበታል" የሚል የሚሽነሪዎች የሐሠት ክስ"False Allegation" እንዲህ ድባቅ ይገባል፥ ሐዲሱ ላይ "ዚና" زِّنَىٰ ሲል ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት ሳይሆን በግልጽ እንደተቀመጠው የዓይን ፍትወት ማየት እና የምላስ ፍትወት እንዲሁ ያ ሊተገበር ወይም ላይተገበር የሚችል የነፍስ ፍላጎት እና ምኞት ነው። በእርግጥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት መጥፎ ሥራ ነውና መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን ይቀጣል፥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙትንማ መጥፎ ሥራ ስለሆነ እና ስለሚያስቀጣ አሏህ "አትቅረቡ" ብሎ ከልክሎናል፦ 40፥40 መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን እንጂ አይቀጣም፡፡ مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا 17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ! እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፥ መንገድነቱም ከፋ። وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት እንድናደርገው ተጽፎ ቢሆን ኖሮ "አትቅረቡ" ብሎ አይከለክልም ነበር፥ ትእዛዙን ስንተላለፍም አንቀጣም ነበር። "አትቅረቡ" የሚል ክልክለላ የሚሰጠው መቅረብ እና አለመቅረብ ነጻ ፈቃድ እና ምርጫ ያለው አካል ነው፥ ወንድ እና ሴት በተራክቦ ከትዳር ውጪ የሚያረጉት ዝሙት እንድናደርገው የተጻፈ ሳይሆን መንገድነቱም የከፋ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Open in TelegramConnections
Similar channels
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል@mkpublicrelationReligion54.8K
✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴@tewahedo12Religion54.7K
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)@zikirekdusnReligion53.2K
Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር@christian_mezmurReligion80.2K
Minber TV@minbertvReligion43.7K
Munib Network@munib_netReligion90.1K
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች@ethiopian_orthodoxReligion33.6K
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹@muradtadesseReligion118K