" በተወሰደው ድንገተኛ እምርጃ ተቸግረናል " - የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ዜጎች ሰሞኑን ከተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም ለሊት ጀምሮ በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች በጅምላ ታግደዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ዜጎች ገንዘባቸውን አውጥተው መጠቀም፣ መገልገል አልቻሉም። በርካታ ዜጎችም እየተጉላሉ ይገኛሉ። መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ዜጎች፤ ምክንያቱ እንኳን ሳይነገር ለምን እንዲህ ያለው እርምጃ እንደተወሰደ እንዳልገባቸእ፣ በድንገተኛው እገዳ በጣም መቸገራቸውን ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበርም ችግር ገጥሟቸው እንደነበር ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በምን ምክንያት እገዳ እንደተጣለ ለህዝብ ወጥቶ ያስረዳ አንድም አካል የለም። አሁን ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ባንክ በአዲስ አበባ ያሉ ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሒሳብ ለማንቀሳቀስ ማመልከቻ እንዲያስገቡ እያደረገ ነው። ለደምበኞች መፍትሄ ለመስጠት በሚል 13 ቅርንጫፎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል። እነዚህም ፦ • አዲስ አበባ ቅርንጫፍ • አቃቂ • ተክለሃይማኖት • ንፋስ ስልክ • ሾቤ አያት • ስድስት ኪሎ • ሲኤምሲ (CMC) • ተፈራ ደግፌ • መሪ • ጠመንጃ ያዥ • ቴሌ መድኃኔዓለም • ጦር ኃይሎች ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጎ ነበር። በዚህም በርካታ በትግራይ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከፍተው የታገደባቸው ዜጎች ለማስለቀቅ ለበርካታ ሰዓታ ረጅም ሰልፍ ይዘው ታዝቧል። ከጥዋት ጀምረው የተሰለፉ በርካታ ዜጎችንም አግኝቷል። በተመለከትናቸው የባንኩ ቅርንጫፎች የሒሳብ ባለቤቶች (የሒሳቡ ሕጋዊ ወኪል) ወደ ተጠቀሱት ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ማንነታቸውን፣ ፊርማቸውንና አስፈላጊውን መረጃ ካረጋገጡ በኋላ የታገደውን ሒሳባቸውን ወደ አዲሶቹ ቅርንጫፎች የማዛወርና የማንቀሳቀስ ቅጽ እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል። ነገር ግን የሂሳብ ቁጥሮቹ መንቀሳቀስ የሚጀምሩት አስፈላጊውን የማረጋገጥ ስራ ከተሰራ በኋላ መሆኑ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደንበኞችን በማስተናገድ ላይ ከሚገኙት የንግድ ባንክ ሰራተኞች አንዱን አናግሯል። ይኸው ሰራተኛ " ተገልጋዮቹ የፋይዳ መታወቂያቸውን ኮፒ በመያዝ በአካል ባመለከቱበት በ24 ሰዓታት ወስጥ የታገደው የባንክ ሂሳባቸው ይለቀቃል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን የባንክ ሒሳቦች እንደታገዱ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይሰራል። በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አፋር እንዲሁም አማራ ክልሎች ዳግም ባገረሸው ጦርነት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸው ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስረከም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegram
" በተወሰደው ድንገተኛ እምርጃ ተቸግረናል " - የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ዜጎች
Views57,400−74%vs avg
Forwards69
Reactions—
Comments—
Links and mentions
Mentions@tikvahethiopia
More from TIKVAH-ETHIOPIA
- 01Views324KForwards1.07KReactions—Comments—
- 02Views318KForwards1.15KReactions—Comments—
- 03Views315KForwards1.92KReactions157Comments—
- 04Views315KForwards633Reactions—Comments—
- 05Views314KForwards1.11KReactions388Comments—