የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።

TIKVAH-ETHIOPIA, @tikvahethiopia

Open in Telegram
#108213File

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል። ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦ - ጀማሪ መምህር፣ - መለስተኛ መምህር፣ - መምህር፣ - ከፍተኛ መምህር፣ - ተባባሪ መሪ መምህር፣ - መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው። በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው። ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል። መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Open in Telegram
Views229,4150%vs avg
Forwards954
Reactions258
Comments—

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h35,257
17 h229,415
  1. After 1 hour35,257
  2. After 24 hours229,415
  3. Total to date229,415

Reactions

  • ❤183
  • 😁37
  • 😡20
  • 👏9
  • 🕊4
  • 😭3
  • 🙏2

More from TIKVAH-ETHIOPIA

  1. 01

    የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና ዝውውር በአንድ ወጥ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲፈጸም አቅጣጫ ሰጠ። ሚኒስቴሩ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በተመሳሳይ የአሠራር መርህ እንዲስተናገዱ በማስቀመጠው ሰርኩላር፣ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ሂደቶችን በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት ብቻ እንዲያከናውኑ አሳስቧል። 1. የተማሪዎች ቅበላ በሰርኩላሩ መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር በይፋ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች የምደባ መረጃና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ካጣሩ በኋላ በወቅቱ መቀበልና መመዝገብ አለባቸው። ዩኒቨርሲቲዎች ከሚኒስቴሩ ከተላለፈው የምደባ ውጤት ውጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ተማሪ መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደሌለባቸውም ተገልጿል። የመግቢያ ፈተና እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ተቋማትም ቅበላውን በተቀመጠው መስፈርትና ግልጽ በሆነ የውጤት አያያዝ ሥርዓት ማከናወን ይኖርባቸዋል። 2. የትምህርት መስክ ምደባ የትምህርት መስክ ምደባ ሲከናወን የሀገሪቱን የሰው ኃይል ፍላጎት፣ በኢኮኖሚ ሽግግሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መስኮች፣ የተማሪውን ውጤትና ምርጫ እንዲሁም የተቋሙን የቅበላ አቅም ታሳቢ እንዲደረግ ተደንግጓል። ምደባውም በግልጽ፣ ቀድሞ በሚታወቅና ለሁሉም ተማሪዎች በወጥነት በሚተገበር መስፈርት መፈጸም እንዳለበት ሰርኩላሩ ያስቀምጣል። በምደባው ወቅት ፦ - የተማሪው የመጀመሪያ ዓመት ወይም የዓመቱ አማካይ ውጤት፣ - የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት፣ - የተማሪው ምርጫ፣ - የትምህርት መስኩ የቅበላ አቅም፣ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ በተቋሙ የሚሰጥ የመግቢያ ፈተና ታሳቢ እንዲደረጉ ተገልጿል። ተቋሙ የትምህርት መስክ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ፣ የመጀመሪያ ዓመት አማካይ ውጤት 50 በመቶ፣ የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እና የመስክ መግቢያ ፈተና 30 በመቶ እንዲያዝ ተቀምጧል። መግቢያ ፈተና በማይሰጥበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ዓመት ለሚከናወን ምደባ የዓመቱ አማካይ ውጤት 70 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 30 በመቶ እንዲያዝ ተገልጿል። በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ለሚከናወን ምደባ ደግሞ የዓመቱ አማካይ ውጤት 80 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እንዲያዝ ተደንግጓል። በተጨማሪም ለሴት ተማሪዎች፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ለሌሎች ተገቢ የሆነ እዎንታዊ ድጋፍ በወጥነት እንዲተገበር ተመላክቷል። ለሴትና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በምደባ ወቅት በውጤታቸው ላይ 5 ነጥብ ተጨምሮ እንዲወዳደሩ የሚያደርግ አሠራርም ተቀምጧል። ዩኒቨርሲቲዎች ከተቀመጠው መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ ወይም በልዩ ትዕዛዝ የትምህርት መስክ ምደባን መቀየር እንደሌለባቸውም ሚኒስቴሩ አስቀምጧል። 3. የተማሪዎች ዝውውር ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ የሚደረግ የተማሪ ዝውውር የሚፈጸመው የላኪውና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። ዝውውሩ ከተፈጸመም በኋላ ትምህርት ሚኒስቴሩ በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት። የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስተር ከተማረ እና ከፕሮግራሙ ከ50 በመቶ በላይ ካልጨረሰ እንደሆነ ሰርኩላሩ ይገልጻል። ተማሪው የአካዳሚክ ጉድለት (F፣ NG ወይም I) የሌለበት፣ አማካይ ውጤቱ 2.00 እና ከዚያ በላይ የሆነ እና የዲሲፕሊን ጥፋት ያልፈጸመ መሆን አለበት። በደኅንነት ስጋት፣ በጤና ችግር ወይም በሌላ ተመሳሳይ ልዩ ሁኔታ የሚቀርብ የዝውውር ጥያቄም በሕጋዊና በተረጋገጠ ማስረጃ መደገፍ እንዳለበት ተገልጿል። በተጨማሪም ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር የሚፈቀድ ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር እንደማይፈቀድ ተቀምጧል። ዝውውር በአንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች መካከል፣ ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ወይም ከአንድ ፕሮግራም ወደ ሌላ ፕሮግራም ሊፈጸም እንደሚችልም ሰነዱ ያስቀምጣል። በተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሠራሽ አደጋ፣ በደኅንነት ችግር ወይም በሌላ ልዩ ሁኔታ ከመደበኛው የዝውውር አቅም በላይ የሆነ የቡድን ዝውውር የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ውሳኔ ከመፈጸም ይልቅ ጉዳዩን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲፈጽሙ ታዘዋል። 4. ቅሬታዎችና ግልጽነት ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች የሚቀርቡ የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ቅሬታዎችን የሚቀበል፣ የሚመረምርና በወቅቱ ምላሽ የሚሰጥ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት እንዲኖራቸው ተብሏል። የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ውሳኔዎችም በግልጽ መስፈርት፣ በተሟላ ማስረጃና በሰነድ የተደገፉ መሆን እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በመጨረሻም ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሰርኩላሩ ጋር የሚቃረን የተለየ አሠራር እንዳይከተሉ፣ በተማሪዎች ቅበላ፣ በትምህርት መስክ ምደባና በዝውውር ወቅት የተቀመጡትን መስፈርቶች በወጥነት እንዲፈጽሙ ተመላክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Photoalbum
    Views324K
    Forwards1.07K
    Reactions—
    Comments—
  2. 02
    Views318K
    Forwards1.15K
    Reactions—
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photoalbum
    Views315K
    Forwards1.92K
    Reactions157
    Comments—
  4. 04

    ‎" ግለሰቡ ' ተሰድቤያለሁ ሰው እገድላለሁ ፤ እኔም እራሴን አጠፋለሁ ' በሚል ' ቤተሰቦቼ የሚያለቅሱበትን የሀዘን መግለጫ ባነር ነው ያሰራሁት ' ነው ያለን " - የሰሜን ቤንች ፖሊስ አዛዥ ‎ ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሼኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዳ በተባለ አካባቢ የራሱን " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " የሚል የሐዘን መግለጫ ባነር በማሰራት፣ የተቀየመውን ሰው ገድሎ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሺካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ኢንስፔክተር ዘለቀ እንደገለፁት ድርጊቱን የፈጸመው አቶ ማሌች ሚቲኩ ገተራሻ የተባለ የ31 ዓመት አባወራ እና የሁለት ልጆች አባት ነው። አቶ ማልች ከተጣላው አካል ጋር በነበረው አለመግባባት ግለሰቡ " ሟርተኛ " ሲል ሰድቦኛል በሚል በትናንትናው ዕለት መስከረም 12/2019 ዓ/ም በቂም በቀል ተነሳስቶ ግለሰቡን ለመግደልና እራሱንም ለማጥፋት አቅዶ ለዚሁ እቅዱ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ የራሱን የሐዘን መግለጫ ባነር በቅድሚያ አሳትሞ በማምጣት በዕለቱ መጠጥ እየጠጣና በማስፈራሪያዎች ሲፎክር ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዙን ገልፀዋል። ‎ ‎ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ " ባነሩን ያዘጋጀሁት ቤተሰቦቼ እኔን እያሰቡ እንዲያለቅሱበት ነው " በሚል ለፖሊስ ቃሉን መስጠቱን ያነሱት ​የፖሊስ አዛዡ ድርጊቱ በአካባቢው አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን በሚዲያ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ‎ ‎​በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ በሕግ አሰራር መሠረት የሚኖረውን ቀጣይ አካሄድ ከሚመለከታቸው የሕግ አካላት ጋር እየተመረመረ ይገኛል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Photoalbum
    Views315K
    Forwards633
    Reactions—
    Comments—
  5. 05

    No text

    Photoalbum
    Views314K
    Forwards1.11K
    Reactions388
    Comments—

All posts of TIKVAH-ETHIOPIA