Account

Posts of የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

newest first

#55036Text

ካሪንግተን በድሮን ሲሰለል የተመለከትነው የማንቸስተር ዩናይትድ አስተላልፍ 🔥 ምቤሞ በቀኝ በኩል ወደ መስመር ቦታ አስፍቶ ሲይዝ፣ ሾው በግራ በኩል ወደ መስመር አስፋቶ ቦታውን ይዞ ይታያል እና ዚርክዚ እንደ ተንቀሳቃሽ የፊት መስመር አጥቂ ማለትም በእግር ኳሱ ቀንቋ roaming number nine ሆኖ ሲጫወት ማየት አስደሳች ነው። ​የእኔ ግምታዊ አሰላለፍ ይህንን በድሮን ከተቀረፀውና የፖቸቲኒሆ አጨዋወት ከግምት በማስገባት ክለባችን ኳስ በሚያዝበት ጊዜ 3-2-5 ቅርጽ ይኖረዋል። ​ዮሮ የቀኝ ተከላካይ (RB)፣ማጓየር እና ማርቲኔዝ የመሃል ተከላካይ (CB)፣ሾው የግራ ተከላካይ (LB)፤ማይኖ እና ሳንቶስ የመሃል ሜዳው ሃላፊዎች፤ምቤሞ የቀኝ ክንፍ አጥቂ (RW)፣ብሩኖ የቀኝ የአጥቂ አማካይ (RAM)፣ኩኛ የግራ አጥቂ አማካይ (LAM) እና ዚርክዚ የፊት አጥቂ (ST) ሆነው ይተውናሉ ማለት ነወ። ​ከዚህ አስተላለፍ ከሁሉም ይበልጥ አስደሳች የሚሆነው የዚርክዚ ሚና ይመስለኛል።​ከመሃል ተከላካዮች መሃል ከመቆየት ይልቅ ኳስ ለመቀበል ወደ ኋላ በጥልቀት በመውረድ ከሊቨርፑል የመሃል ተከላካዮች አንዱን ከቦታው በማስወጣት የተከላካይ መስመራቸውን ግራ የማጋባት እድል ይሰጣል። ​ያ የዝርክዚ እንቅስቃሴ በዙሪያው ላሉ ወደ ፊት ለሚሮጡ ተጫዋቾች ክፍተትና እድልን ይፈጥራል። ​ምቤሞ ከቀኝ በኩል ማጥቃት ይችላል፣ብሩኖ ከቀኝ ከግማሽ ክፍተት በእግር ኳሱ ቀንቋ right half-space ቦታ ወደ ፊት መሮጥ ይችላል፣ ኩኛ ደግሞ ከግራ በኩል ያለውን ክፍተት ማጥቃት ይችላል። ​ይህንን ቪዲዮ ካየሁ በኋላ እንደ ኬን አይነት የፊት መስመር አጥቂ ቢፈልግ አልገረምም ማለትም በመስመሮች መሃል ዝቅ ብሎ በመውረድ ጨዋታን የሚያገናኝ የተጋጣሚ የመሃል ተከላካዮችን ወደ ራሱ የሚስብ እና በዙሪያው ላሉ ፈጣን አጥቂዎች የመሮጫ ቦታ መፍጠር የሚችል ተጫዋች ለፖቸቲኖ ያስፈልጉታልና ሼሽኮ ይህንን እንደሚሰጠው ተስፋ አረጋለው። የፖቼ በማቅቃት ወቅት ​ክፍተት የሚፈጥር ፈጠራ ያለው የፊት መስመር አጥቂ ይፈልጋል በዙሪያው ደግሞ ያንን ክፍተት የሚጠቀሙ ሯጮችም እንዲሁ ያስፈልጉታል።ይህን መስጠትም መጠቀምም የሚችሉ ተጫዋቾች ደሞ አሁን ላይ በአለው የማንቸስተር ዩናይትድ ስብስብ ውስጥ ይገኛሉ 100% መስጠት ባይችሉም። በማንቸስተር ዩናይትድ ምርጥ ምርጡን ንፋስ መንፈሱ በርግጥም በደንብ ይጀምራል🔥❤🔥

Open in Telegram
Views2,720−18%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—
#55028Photo

በጊዜ የማንቸስተር ዩናይትድ አመራሮች አይናቸው መግለፅ አለባቸው ይህ የማይክል ካሪክ ቡድን ስሜት የለው፣የመፋለም ስሜት የለውም..ምንም ዓይነት የማጠቃት ፍላጎት የለውም። እጅግ በጣም አሰልቺና መጥፎ ኳስ የሚጫወት ቡድን ነው ማይክል ካሪክ ለውድድር አመቱ ይዞ የቀረበልን፤ጭራሽ የእሱ የአሰልጣኞች ቦታ ላይ ቆሞ የስሜት አልባነት ፊትና ሪያክሽን ደግሞ ነገሩን ይበልጥ እያባባሰው ይገኛል። ይቅርታ አርጉልኝ ከዚህ በፊት ካሪክ ወደፊት የተሻለ አሰልጣኝ ይሆናል ብዬ ለፃፍኳቸው ፁፎችና ፖስቶች🙏​በዚህ ሳት ስለ ካሪክ ምንም ነገር ወደፊት ጥሩ አሰልጣኝ ይሆናል ይሻሻላል የሚል ተስፋ ምንም የለኝም አይሆንምም በዚህ አመት ብቻ ካልተሳሳትኩኝ በሶስት ጫወታዎች ከተጋጣሚው ቡድን እንኳን በቀይ ወጥቶለት ምንም መፈየድ አልቻለም ጭራሽ የሱ ቡድን ኳስ ይጠፋበታል😂 በዛሬው ጫወታ ለይቼ የምተቸው ተጫዋች የለም ከአሰልጣኙ ውጪ ጠዋት ካሪክ ተሰናበተ የሚል ዜና ብሰማ ከኔ በላይ የሚደሰት ደጋፊ አይኖርም ልቤ ለጣሊያናዊው ኮንቴ መምታት ጀምሯል❤ 🔥ባሌባ ለአማካይ ክፍላችን ግርማ ሞገስ ይዞ ነው የመጣው ካሪክ እሱንም ሳያቀረዝዘው በጊዜ ቢሰናበት 🙏      🙏Michael Carrick out🙏 ሸውዶናል😂 ፌስቡክ ላይ ቤተሰብ እንሁን❤ https://www.facebook.com/Abduselam.hashim1314

Open in Telegram
Views9,530+188%vs avg
Forwards—
Reactions30
Comments—
#55025Photo
Views9,150+177%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#55024Text

የ4-2ቱ ሽንፈት ለዩናይትድ ጣፋጭ ሲኦል ነው! ⚽️🔴 ​ማንችስተር ዩናይትድ በዛሬው ዕለት 4 ለ 2 ተሸንፏል፤ እንደ እኔ ግን ይህ ውጤት እጅግ አስተማሪ እና የቡድናችንን እውነተኛ ገጽታ ያሳየ አጋጣሚ ነው! 💡 ​ባለፉት ጨዋታዎች በነበረው ውጤት ተሸፍነው የነበሩ በርካታ ክፍተቶች ዛሬ በግልጽ ወጥተዋል። ጨዋታውን አሸንፈን ቢሆን ኖሮ በውሸት ተስፋ ተሸውደን የፕሪሚየር ሊጉን ጅማሮ በመጥፎ ጠባሳ በጀመርን ነበር። ስለዚህ የዛሬው ሽንፈት ከወዲሁ ድክመታችንን እንድናርም የሚያነቃቃ "ጣፋጭ ሲኦል" ነው ማለት ይቻላል! 🔥 ​ከጨዋታው የታዘብናቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​➡️ የግራ መስመር ተከላካይ ስጋት፦ ሉክ ሾው አቅሙ ከነጠፈበት ቆይቷል፤ በማጥቃቱም ሆነ በመከላከሉ ላይ እጅግ ደካማ ነበር። በተለይ የመጀመሪያው ጎል ሲቆጠርበት የነበረው ክፍተት አስቂኝ የሚባል አይነት ነው። ጎሎቹ በሙሉ ማለት ይቻላል በእሱ በኩል የመጡ ናቸው። ኒውካስልን ለመልቀቅ ፍላጎት ያለው ሉዊስ ሃልን ለማስፈረም ዩናይትድ አሁንም ጆሮ ደባስ ማለቱና በዜና ብቻ መወሰኑ ዋጋ እያስከፈለው ነው። ​➡️ የመሃል ክፍል ክፍተት፦ በአሞሪም ስር አሁንም የመሃል ክፍላችን ላይ እጅግ ሰፊ ክፍተት ይታያል። አስቸኳይ የደረጃ ኤል አማካይ ተጫዋች ያስፈልገናል። ​➡️ የፊት መስመርና አጨራረስ፦ የማጥቃት እንቅስቃሴያችን እና እድሎችን የመፍጠር ሂደታችን ጥሩ የነበረ ቢሆንም፣ የፊት መስመራችን ግን አሁንም የደከመና አጨራረስ ላይ ችግር ያለበት ነው። ​➡️ የተጫዋቾች ቅያሬ፦ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ከገባ በኋላ የተከላካይ መስመሩ የተሻለ መረጋጋት አሳይቷል (ሄቨን ዛሬ ጥሩ አልነበረም)። Mbeumo (ምበምቦ)፣ ራሽፎርድ እና ማይኑ ከገቡ በኋላም የተሻሉ እንቅስቃሴዎችን ተመልክተናል። ​በአጠቃላይ፦ አሁንም ቢሆን ዩናይትድ በአስቸኳይ አንድ ጥራት ያለው የመሃል አማካይ እና በሉክ ሾው ቦታ የሚጫወት አስተማማኝ የግራ መስመር ተከላካይ ያፈልገዋል። ይህ ሽንፈት ወቅቱ ሳይረፍድ ክፍተታችንን እንድንደፍን ትልቅ ፍንጭ የሰጠ ነው።

Open in Telegram
Views8,530+158%vs avg
Forwards—
Reactions35
Comments—
#55021Photo
Views14,000+324%vs avg
Forwards—
Reactions67
Comments—