ህዳር 16 ቀን 1956 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 63 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ (JFK) ስርዓተ ቀብራቸው የተፈጸመበት ዕለት ነበር። በወቅቱ በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት 26 የሀገራት መሪዎች እና 85 የአለም ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ፤ ከእነዚህም መሪዎች መካከል ብቸኛው "ጥቁር" መሪ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ነበሩ። የቀብር ስርዓቱ ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኋላ በኋይት ሐውስ (White House) የፕሬዝዳንቱ ቤተሰቦች ለማጽናናት በተዘጋጀው መርዓ ግብር ላይ እንዲገኙ የተመረጡት ከአራቱ የሀገር መሪዎች መካከል አንዱ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ናቸው። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in TelegramPosts of ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala
ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ 👇 youtu.be/IrjaTQfFGd4 #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramየቡፌ ምግብ ለአንድ ሰው በ 3 ብር የነበረበት ዘመን !!! የቅዱስ ጊዮርጊስ ቲም የተቋቋመበትን 32ኛውን ዓመት በሚያከብርበት ሐምሌ 6 ቀን 1960 ዓ.ም በገነት ሆቴል ለሚደረገው የቡፌ ግብዣ አስፈላጊ የሆነው ምግብ ለ 900 ሰው በሆቴላችን አዘጋጅተን እንድናቀርብ ስለተጠየቅን ፣ ከዚህ በታች በዝርዝር ተጽፈው የሚገኙትን ልዩ ልዩ ዓይነት ምግቦች በሚገባ አዘጋጅተን ለማቅረብ በሰው ሦስት (3) ብር ሂሳብ የምንጠይቅ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን። ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፤ ሠኔ 28 ቀን 1960 ዓ.ም #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 295 |
| 6 h | 654 |
- After 1 hour295
- After 6 hours654
- Total to date654
ከ 107 ዓመት በፊት በሀገራችን የተከሰተውን የህዳር በሽታ (ስፓኒሽ ፍሉ) ወረርሺኝ ለመከላከል የአ/አ ከተማ ማ/ቤት ያወጣው ማስታወቂያ ፩. ለዚህ ለዛሬ በሽታ ነጩን የባሕር ዛፍ ቅጠሉን እየቀቀላችሁ ማታ ስትተኙ በላቦቱ ታጠኑ፡፡ ደግሞ የባሕሩን ዛፍ ቅጠል እርጥቡን በብዙ አድርጋችሁ በቤታችሁም ውስጥ በየደጃችሁም እያነደዳችሁ አጭሱበት። ፪. አይነ ምድራችሁን ሳትቆፍሩ አትቀመጡ አይነ ምድር ተቀምጣችሁ ስትነሡ ባይነ ምድራችሁ ላይ የባሕር ዛፍ ቅጠል ጣሉበት ያልጣላችሁበት እንደሆነ ከአይነ ምድራችሁ ላይ እንደገና በሽታ ይነሣል። ፫. ባትታመሙም ብትታመሙም ውሀ እያፈላችሁ በውስጡ ጨው እየጨመራችሁ ጠዋትና ማታ አፉችሁን ተጉመጥመጡ ፬. ውሻ ድመት በቅሎና ፈረስ ሌላም ይህን የመሰለ ሁሉ በሞተባችሁ ጊዜ ሽታው በሽታ ያመጣልና ቅበሩት። ፭. ሰው የሞተችሁ እንደሆነ መቃብሩን በጣም አዝልቃችሁ ሳትቆፍሩ አትቅበሩ በጣም ሳትቆፍሩ የቀበራችሁ እንደሆነ አውሬና ውሻ እያወጣ ይበላዋል ሽታውም ከዛሬው የበለጠ በሽታ ያመጣብናል። ፮.በቤቱ ሰው የታመመበት ሰው ወደ ማ/ቤት ድረስ እየመጣ አለዋጋ መድኃኒቱን ይውሰድ በማናቸውም ምክንያት የሚያድን እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን የሚያድን እግዚአብሔር ነው ብሎ መድኃኒት አላደርግም ማለት እግዚአብሔርን መፈታተን ይሆናልና መድኃኒት አናደርግም አትበሉ መድኃኒትንም የፈጠረልን እግዚኣብሔር' ነው፡፡ ፯.ደግሞ ከመቃብር ላይ በሽታ እንዳይነሣ ብሎ መንግሥታችን በቸርነቱ ብዙ ኖራ በየቤተክርስቲያኑ አስመጥቶልናልና በመቃብሩ ውስጥ ሬሳውን አግብታችሁ በላዩ ጥቂት አፈር ጨምራችሁ በአፈሩ ላይ ኖራውን አልብሱና ከዚያ በኋላ አፈር መልሱበት ኖራው የሬሳውን ሽታ ያጠፋውና በሽታ እንዳይነሣ ይሆናል። ሕዳር ፳ ፲፱፻፲፩ ዓ.ም የአ/አ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዳይሬክተር ኅሩይ ወ/ሥላሴ
Open in Telegramከሶሰት ጊዜ በላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ እንዲሁም 11ኛው የአ/አ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋሪያት " ታከለ ታገለ " አስደናቂ ታሪክ...... ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋሪያት በጣሊያን ወረራ ወቅት ዱር ቤቴ ካሉ አርበኞች አንዱ ናቸው። ታከለ ወ/ሐዋሪያት ታከለ የአክሊሉ፣ የመኮንን፣ የአካለ ወርቅ የሐብተወልድ ዘመድ ነው፡፡ ሦሥቱ ወንድማማቾች የኃይለስላሴ የቅርብ ሆነው “አቤት ጃንሆይ” “እሺ ጃንሆይ” ሲሉ እሱ ግን እምቢ ባይ ሆነ!በተለይ ንጉሱ ከጣሊያን ጋር በነበረው ጦርነት በስደት ወደ እንግሊዝ ሲሄዱ፣ታከለ ለንጉሱ የነበረው አንጀት ተበጠሰ፡፡ ”ንጉስ ሆኖ ስደት ፤ ሳል ይዞ ስርቆት” የማይሆን ነው ባይ ሆነ፡፡ ንጉሱ ከስደት ከተመለሱም በኋላ አስሬ እየታሰረ፣ አስሬ የሚፈታ የእስር ደምበኛ ሆነ፡፡ ቢሆንም ግን ንጉሱ አይጨክኑበትም ነበር አሉ ፤ ወደውም አይደለም! ታከለ ጠንቋዮች ጋር ጎራ ይልና ፤ <ታከለን የገደልክ ቀን ሦስት ቀንም አትቆይ፤ትሞታለህ> አስብሎ ለንጉሱ እንዲነግሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ንጉሱ በተቃወማቸው ቁጥር፣ ባስቸገራቸው ቁጥር ከመግደል ይልቅ በቅርብ እያሰሩ ይንከባከቡት ገቡ፡፡ ታከለ ለሀገሩ ተብሰልሳይ ፤ ባካኝ ነበር፡፡ ጦርነት በሆነ ጊዜ ለጣሊያን ምጥ ከሆኑ አርበኛች መሀል ነው፡፡ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር <ታከለ ታገለ> ብሎ በፃፈው ፅሁፉ ላይ ስለ ሀገሩ እጅግ ተብከንካኝ እና ተብሰልሳይ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የሚከተለውን አስፍሯል፡፡ ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/1JExnoUSKH/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramላሊበላ ከተማ በዘመኗ -- 1974 ዓ.ም | Lalibela City; in 1982. በቪዲዮ ላይ በከተማዋ የቀብር ስነስርአት ሲፈፀም ፣ የላሊበላ ውቅር አበያት ቤተክርስቲያናት ፣ የገበያ ቦታዎች እና የአየር መንገድ ማረፊያ ይታያል #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Lalibela http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramበትግራይ የሚገኘው ጥንታዊው እና ታሪኻዊው የደብረ-ዳሞ ገዳም ፤ ለ 82 ዓመታት ያህል በገዳሙ ውስጥ ያገለገሉ መነኩሴ ስርዓተ ቀብራቸው በሚፈፀምበት ወቅት ፤ 1962 ዓ.ም The ancient Debre-Damo Monastery in Tigray; A monk who served in the monastery for 82 years is being buried; in 1970. #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 147 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ የሆኑ ባይተዋሩ ልዑል ዓለማየሁ ከመቅደላ ጦርነት በኋላ በእንግሊዞች ተሰደው ከሚኖሩበት እንግሊዝ አገር ከ 12 ዓመት ቆይታ በኋላ በተወለዱ በ 19 ዓመታቸው ባደረባቸው የሳምባ ምች ሕመም ምክንያት ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር። ከታች በምስሉ ላይ የሚታየው የባይተዋሩ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ የነሐስ ቅርፅ ከህልፈቱ በኋላ በንግስት ቪክቶሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቶ እ.ኤ.አ በ 1879 የተሰራ ሲሆን የተቀረፀውም በእንግሊዛዊው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ፍራንሲስ ጆን ዊሊያም ሲሆን እ.ኤ.አ በሐምሌ 1880 በዊንዘር ቤተመንግስት ሰን ስራውን ጨርሶ አስረክበዋል። የዚህ የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ቅርፅ ወደ ንግሥት ቪክቶሪያ ተወዳጅ መኖሪያ (Osborne House) ኦስቦርን ሃውስ ወደ ዋይት ደሴት ውስጥ በላይኛው ኮሪደር እንዲቀመጥ ተደርጓል። www.facebook.com/share/p/1FjwYvvCnV/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala1
Open in Telegramህዳር 4 ቀን 1924 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 95 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ ያደረጉት ስመጥሩ የፖለቲካው ሰው ራስ ናደው (አባ ወሎ) ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው “አባ መብረቅ” በዳግማዊ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት እና በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በተለይም በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ስመጥር የፖለቲካ ሰው ነበሩ። ራስ ናደው ትውልዳቸው በሰሜን ሸዋ ታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆነው ከአዲስጌ ቤተሰብ ነው። ራስ ናደው አባ ወሎ በውጪ ጉዳይ በነበራቸው ከፍተኛ ተሳትፎ ባሻገር ለረዥም ጊዜ የኢሉባቦር ግዛት (ገዢ) በመሆን አስተዳድረዋል። በውጪ ጉዳይ ዙሪያ በነበራቸው ተሳትፎ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ብኋላ በአሸናፊነት የወጡትን የተባበሩት ኃይል እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ የሂደውን የኢትዮጵያ ልዑክ መርተዋል። ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/1ConkF513h/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramየልብስ ስፌት ባለሞያዎች በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፤ በወርሃ መስከረም 1958 ዓ.ም Tailors in Addis Ababa City, October 1965. #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramአዲሱን የመሬት ማሻሻያ አዋጅ በመደገፍ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በመዲናዋ ጎዳናዎች ላይ የድጋፍ ሰልፍ በወጡበት ወቅት ፤ መጋቢት 16 ቀን 1967 ዓ.ም Residents of Addis Ababa march through the streets of the city in support of the new land reform proclamation. 25 March 1975. #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ በዘመኗ ፤ 1986 ዓ.ም Addis Abeba City; in 1994. #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramየእንግሊዝ መንግስት ለጀግናው ኢትዮጵያዊ አርበኛ ኮሎኔል አብዲሳ አጋ በኢትዮጵያ እና በሀገረ ጣሊያን በርሃ ላይ ለሰራው ጀግንነትና ለፈፀመው ጀብድ የተፃፈለት የአርበኞች የምስክር ወረቀት (Patriots certificate) ደብዳቤ ቅፅ ፣ የካቲት 13 ቀን 1939 ዓ.ም #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramጥቅምት 30 ቀን 1948 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 71 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሕንድ ተወላጆች በማኅትማ ጋንዲ ስም ያቋቋሙት የማዋለጃ ሆስፒታል በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ተመርቆ የተከፈተበት ዕለት ነበር። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramየጅቡቲ ፕሬዝዳንት ሀሰን ጉሌድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ጓድመንግስቱ ኃይለማርያም እና ባለቤታቸው ወይዘሮ ውብባንቺ ቢሻው አቀባበል ሲያርጉላቸው ፤ መጋቢት 9 ቀን 1973 ዓ.ም President Hassan Gouled of Djibouti being welcomed by President Mengistu Hailemariam and his wife, Woyzero Wubanchi Bishaw, upon his arrival in Ethiopia for an official visit; March 18, 1981. #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramጥቅምት 30 ቀን 1848 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 171 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ እና የወ/ሮ በለጥሻቸው ወልዴ ልጅ የሆኑት ንጉስ ኃይለመለኮት ሳህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም ምክንያት አርፈው በደብረ በግዕ የተቀበሩበት ዕለት ነበር። የሸዋው ንጉሥ ኃ/መለኮት በሰውነታቸው ግዝፈትና ጥንካሬ እንዲሁም በልባቸው ቀናነት በሸዋ ዘንድ የታወቁና የተወደዱ ንጉሥ ነበሩ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው እንደሚነግሩን ንጉሥ ኃ/መለኮት ከጥንካሬያቸው የተነሳ ኢላማ ተኩስ በሚተኩሱ ጊዜ መሳሪያውን አጠንክረው በመያዛቸው ምክንያት ጥይቱ ሲወጣ ጠምንጃቸው ለሁለት ተሰብሮ እጃቸው ላይ ቀርቶ ያውቃል። ንጉሥ ኃ/መለኮት ከአባታቸው ሞት በመቀጠል ወደንግሥናው ዙፋን ከወጡ በኋላ ሸዋን ለ 8 ዓመታት አስተዳድረዋል። በስልጣን ላይ ሳሉም ተቀናቃኝ ሊሆኑባቸው የሚችሉትን ወገኖቻቸውን በእስር ዞር እንዲያረጓቸው ከጓናቸው ያሉ ሰዎች ሲመክሯቸው "ተዉ ይሄን አላደርገውም እግዚአብሔር የወደደውን ነው የሚያስገዛው" የሚሉ ቀና እንደነበሩ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ በመጽሐፋቸው ይጠቅሳሉ። በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ በሀገሪቱ በየቦታው ያለውን የተከፋፈለ አገዛዝ ወደ አንድ በማምጣት በማእከላዊ መንግሥት ስር የምትተዳር አንዲት ሀገር ለመመስረት አስበው ከየመሳፍንቱ ጋር በሚዋጉ ጊዜ ወደ ሸዋም ሊመጡ ነው የሚል ወሬ ተሰምቶ ንገሥ ኃይለመለኮትም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ሆኖም ግን ገና ቀደም ብሎ ንጉሡ ኃ/መለኮት በጣም ታመው ነበርና እርሳቸው በጦርነቱ ሳይካፈሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩት ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባት ናቸው። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramየቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም (ሌ/ኮ) በሞስኮ ጉብኝት ሲያደርጉ ፤ ህዳር 7 ቀን 1971 ዓ.ም Former Ethiopian President Mengistu Hailemariam (Lt. Col.) During a visit to Moscow; November 16, 1978 #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegramግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ በተለያዩ ግዜያት እና ቦታዎች ላይ በጦር መሳሪያዎች የኢላማ ልምምድ ሲያደርጉ እንዲሁም በጦር ግንባር ከአርበኞቻቸው ጋር ሆነው መሳሪያ ሲተኩሱ የሚያሳዩ ፎቶዎች ፤ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11
Open in Telegram