Кабинет

Посты канала ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

сначала новые

#5280Видео
Просмотры262−81%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#5277Фото
Просмотры654−53%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч295
6 ч654
  1. Через 1 час295
  2. Через 6 часов654
  3. Всего сейчас654
#5276Фото

ከ 107 ዓመት በፊት በሀገራችን የተከሰተውን የህዳር በሽታ (ስፓኒሽ ፍሉ) ወረርሺኝ ለመከላከል የአ/አ ከተማ ማ/ቤት ያወጣው ማስታወቂያ ፩. ለዚህ ለዛሬ በሽታ ነጩን የባሕር ዛፍ ቅጠሉን እየቀቀላችሁ ማታ ስትተኙ በላቦቱ ታጠኑ፡፡ ደግሞ የባሕሩን ዛፍ ቅጠል እርጥቡን በብዙ አድርጋችሁ በቤታችሁም ውስጥ በየደጃችሁም እያነደዳችሁ አጭሱበት። ፪. አይነ ምድራችሁን ሳትቆፍሩ አትቀመጡ አይነ ምድር ተቀምጣችሁ ስትነሡ ባይነ ምድራችሁ ላይ የባሕር ዛፍ ቅጠል ጣሉበት ያልጣላችሁበት እንደሆነ ከአይነ ምድራችሁ ላይ እንደገና በሽታ ይነሣል። ፫. ባትታመሙም ብትታመሙም ውሀ እያፈላችሁ በውስጡ ጨው እየጨመራችሁ ጠዋትና ማታ አፉችሁን ተጉመጥመጡ ፬. ውሻ ድመት በቅሎና ፈረስ ሌላም ይህን የመሰለ ሁሉ በሞተባችሁ ጊዜ ሽታው በሽታ ያመጣልና ቅበሩት። ፭. ሰው የሞተችሁ እንደሆነ መቃብሩን በጣም አዝልቃችሁ ሳትቆፍሩ አትቅበሩ በጣም ሳትቆፍሩ የቀበራችሁ እንደሆነ አውሬና ውሻ እያወጣ ይበላዋል ሽታውም ከዛሬው የበለጠ በሽታ ያመጣብናል። ፮.በቤቱ ሰው የታመመበት ሰው ወደ ማ/ቤት ድረስ እየመጣ አለዋጋ መድኃኒቱን ይውሰድ በማናቸውም ምክንያት የሚያድን እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን የሚያድን እግዚአብሔር ነው ብሎ መድኃኒት አላደርግም ማለት እግዚአብሔርን መፈታተን ይሆናልና መድኃኒት አናደርግም አትበሉ መድኃኒትንም የፈጠረልን እግዚኣብሔር' ነው፡፡ ፯.ደግሞ ከመቃብር ላይ በሽታ እንዳይነሣ ብሎ መንግሥታችን በቸርነቱ ብዙ ኖራ በየቤተክርስቲያኑ አስመጥቶልናልና በመቃብሩ ውስጥ ሬሳውን አግብታችሁ በላዩ ጥቂት አፈር ጨምራችሁ በአፈሩ ላይ ኖራውን አልብሱና ከዚያ በኋላ አፈር መልሱበት ኖራው የሬሳውን ሽታ ያጠፋውና በሽታ እንዳይነሣ ይሆናል። ሕዳር ፳ ፲፱፻፲፩ ዓ.ም የአ/አ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዳይሬክተር ኅሩይ ወ/ሥላሴ

Открыть в Telegram
Просмотры922−33%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#5272Фото

ከሶሰት ጊዜ በላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ እንዲሁም 11ኛው የአ/አ ከተማ ከንቲባ የነበሩት ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋሪያት " ታከለ ታገለ " አስደናቂ ታሪክ...... ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋሪያት በጣሊያን ወረራ ወቅት ዱር ቤቴ ካሉ አርበኞች አንዱ ናቸው። ታከለ ወ/ሐዋሪያት ታከለ የአክሊሉ፣ የመኮንን፣ የአካለ ወርቅ የሐብተወልድ ዘመድ ነው፡፡ ሦሥቱ ወንድማማቾች የኃይለስላሴ የቅርብ ሆነው “አቤት ጃንሆይ” “እሺ ጃንሆይ” ሲሉ እሱ ግን እምቢ ባይ ሆነ!በተለይ ንጉሱ ከጣሊያን ጋር በነበረው ጦርነት በስደት ወደ እንግሊዝ ሲሄዱ፣ታከለ ለንጉሱ የነበረው አንጀት ተበጠሰ፡፡ ”ንጉስ ሆኖ ስደት ፤ ሳል ይዞ ስርቆት” የማይሆን ነው ባይ ሆነ፡፡ ንጉሱ ከስደት ከተመለሱም በኋላ አስሬ እየታሰረ፣ አስሬ የሚፈታ የእስር ደምበኛ ሆነ፡፡ ቢሆንም ግን ንጉሱ አይጨክኑበትም ነበር አሉ ፤ ወደውም አይደለም! ታከለ ጠንቋዮች ጋር ጎራ ይልና ፤ <ታከለን የገደልክ ቀን ሦስት ቀንም አትቆይ፤ትሞታለህ> አስብሎ ለንጉሱ እንዲነግሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ንጉሱ በተቃወማቸው ቁጥር፣ ባስቸገራቸው ቁጥር ከመግደል ይልቅ በቅርብ እያሰሩ ይንከባከቡት ገቡ፡፡ ታከለ ለሀገሩ ተብሰልሳይ ፤ ባካኝ ነበር፡፡ ጦርነት በሆነ ጊዜ ለጣሊያን ምጥ ከሆኑ አርበኛች መሀል ነው፡፡ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር <ታከለ ታገለ> ብሎ በፃፈው ፅሁፉ ላይ ስለ ሀገሩ እጅግ ተብከንካኝ እና ተብሰልሳይ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የሚከተለውን አስፍሯል፡፡ ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/1JExnoUSKH/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11

Открыть в Telegram
Просмотры1 700+23%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#5270Видео
Просмотры1 510+9%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#5269Видео
Просмотры1 780+29%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#5268Фото

ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 147 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ የሆኑ ባይተዋሩ ልዑል ዓለማየሁ ከመቅደላ ጦርነት በኋላ በእንግሊዞች ተሰደው ከሚኖሩበት እንግሊዝ አገር ከ 12 ዓመት ቆይታ በኋላ በተወለዱ በ 19 ዓመታቸው ባደረባቸው የሳምባ ምች ሕመም ምክንያት ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር። ከታች በምስሉ ላይ የሚታየው የባይተዋሩ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ የነሐስ ቅርፅ ከህልፈቱ በኋላ በንግስት ቪክቶሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቶ እ.ኤ.አ በ 1879 የተሰራ ሲሆን የተቀረፀውም በእንግሊዛዊው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ፍራንሲስ ጆን ዊሊያም ሲሆን እ.ኤ.አ በሐምሌ 1880 በዊንዘር ቤተመንግስት ሰን ስራውን ጨርሶ አስረክበዋል። የዚህ የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ቅርፅ ወደ ንግሥት ቪክቶሪያ ተወዳጅ መኖሪያ (Osborne House) ኦስቦርን ሃውስ ወደ ዋይት ደሴት ውስጥ በላይኛው ኮሪደር እንዲቀመጥ ተደርጓል። www.facebook.com/share/p/1FjwYvvCnV/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala1

Открыть в Telegram
Просмотры1 840+33%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#5267Фото

ህዳር 4 ቀን 1924 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 95 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ ያደረጉት ስመጥሩ የፖለቲካው ሰው ራስ ናደው (አባ ወሎ) ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው “አባ መብረቅ” በዳግማዊ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት እና በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በተለይም በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ስመጥር የፖለቲካ ሰው ነበሩ። ራስ ናደው ትውልዳቸው በሰሜን ሸዋ ታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆነው ከአዲስጌ ቤተሰብ ነው። ራስ ናደው አባ ወሎ በውጪ ጉዳይ በነበራቸው ከፍተኛ ተሳትፎ ባሻገር ለረዥም ጊዜ የኢሉባቦር ግዛት (ገዢ) በመሆን አስተዳድረዋል። በውጪ ጉዳይ ዙሪያ በነበራቸው ተሳትፎ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ብኋላ በአሸናፊነት የወጡትን የተባበሩት ኃይል እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ የሂደውን የኢትዮጵያ ልዑክ መርተዋል። ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/1ConkF513h/ #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala #Ethiopia http://youtube.com/@tariknwedehuala11

Открыть в Telegram
Просмотры1 3800%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#5265Фото
Просмотры1 270−8%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5263Фото
Просмотры2 240+62%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#5262Фото
Просмотры1 780+29%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#5261Видео
Просмотры1 600+16%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#5260Фото

ጥቅምት 30 ቀን 1848 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 171 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ እና የወ/ሮ በለጥሻቸው ወልዴ ልጅ የሆኑት ንጉስ ኃይለመለኮት ሳህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም ምክንያት አርፈው በደብረ በግዕ የተቀበሩበት ዕለት ነበር። የሸዋው ንጉሥ ኃ/መለኮት በሰውነታቸው ግዝፈትና ጥንካሬ እንዲሁም በልባቸው ቀናነት በሸዋ ዘንድ የታወቁና የተወደዱ ንጉሥ ነበሩ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው እንደሚነግሩን ንጉሥ ኃ/መለኮት ከጥንካሬያቸው የተነሳ ኢላማ ተኩስ በሚተኩሱ ጊዜ መሳሪያውን አጠንክረው በመያዛቸው ምክንያት ጥይቱ ሲወጣ ጠምንጃቸው ለሁለት ተሰብሮ እጃቸው ላይ ቀርቶ ያውቃል። ንጉሥ ኃ/መለኮት ከአባታቸው ሞት በመቀጠል ወደንግሥናው ዙፋን ከወጡ በኋላ ሸዋን ለ 8 ዓመታት አስተዳድረዋል። በስልጣን ላይ ሳሉም ተቀናቃኝ ሊሆኑባቸው የሚችሉትን ወገኖቻቸውን በእስር ዞር እንዲያረጓቸው ከጓናቸው ያሉ ሰዎች ሲመክሯቸው "ተዉ ይሄን አላደርገውም እግዚአብሔር የወደደውን ነው የሚያስገዛው" የሚሉ ቀና እንደነበሩ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ በመጽሐፋቸው ይጠቅሳሉ። በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ በሀገሪቱ በየቦታው ያለውን የተከፋፈለ አገዛዝ ወደ አንድ በማምጣት በማእከላዊ መንግሥት ስር የምትተዳር አንዲት ሀገር ለመመስረት አስበው ከየመሳፍንቱ ጋር በሚዋጉ ጊዜ ወደ ሸዋም ሊመጡ ነው የሚል ወሬ ተሰምቶ ንገሥ ኃይለመለኮትም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ሆኖም ግን ገና ቀደም ብሎ ንጉሡ ኃ/መለኮት በጣም ታመው ነበርና እርሳቸው በጦርነቱ ሳይካፈሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩት ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባት ናቸው። #ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala http://youtube.com/@tariknwedehuala11

Открыть в Telegram
Просмотры1 500+8%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#5259Видео
Просмотры1 820+31%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#5250Фото
Просмотры1 860+34%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—