Account

Posts of ST.GEORGE FC™🇪🇹

newest first

#10100Text
Views1,620−17%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#10095Text
Views2,750+41%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#10093Photo

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች ቋሚ የአመራር ቦርድ መርጠዋል ……… የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላት ባለፈው እሁድ ጥቅምት 22/2019 በሸራተን አዲስ ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ 7 አባላት ያሉት ቋሚ የስራ አመራር ቦርድ ሾመዋል፡፡ጠቅላላ ጉባኤው ግንቦት 16/2018 ባደረገው ስብሰባ 9 አባላት ያሉት ጊዜያዊ ቦርድ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን አዲስ በፀደቀው የክለቡ መተዳደሪያ ደንብ ይህ ቁጥር ወደ 7 ዝቅ ብሎ ቦርዱ ተመስርቷል። ቀድሞ ከነበረው ቦርድ ኢንስትራክተር ስዩም ከበደ የክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው በመሾማቸው እንዲሁም አቶ ዳዊት አስፋው ባለባቸው ተደራራቢ የስራ ጫና የቦርድ ሀላፊነታቸውን ያስረከቡ ሲሆን የቀሩት 7 የቦርድ አባላትን ሹመት ግን ጠቅላላ ጉባኤው በቋሚነት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ለቀጣይ 4 አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበርን ይመራል። በእሁድ ማለዳው ስብሰባ ሹመታቸው የፀደቀላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው 👉አቶ ነሲቡ ጫኮ - ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ፕሬዚደንት) 👉አቶ ዮሀንስ ሚሊዮን - ዳሸን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት(ዋና ፀሀፊ) 👉አቶ በሀይሉ አየለ - የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንና የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር 👉አቶ እዝራ መሀሪ - ከሞሀ ፔፕሲ 👉አቶ ሰለሞን መገርሳ - ከቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ማህበር 👉አቶ ቶፊቅ መሀመድ ከክለቡ ደጋፊዎች 👉አቶ ሰለሞን ጥላሁን ከክለቡ ደጋፊዎች

Open in Telegram
Views2,800+43%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#10092Text
Views1,900−3%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#10091Text
Views2,160+11%vs avg
Forwards—
Reactions26
Comments—
#10090Text

#ጥቅምት22 — #የቅዱስጊዮርጊስ ትንሳዔ ቀን.. የ91 ዓመቱ አንጋፋው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ተደጋጋሚ ሻምፒዮና ሆኖ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ጽፏል። በአህጉራዊ መድረክ ግን ከእኛ በኋላ የተመሰረቱ የሰሜን፣ የምዕራብና የደቡብ አፍሪካ ክለቦች በአደረጃጀትና በፕሮፌሽናል አወቃቀር በብርሃን ፍጥነት ቀድመውን ሄዱ። ይህ ለሁሉም ስፖርት አፍቃሪ ዘወትር እንቆቅልሽ ሆኖ ኖሯል። ከዚያ በላይ የሚያሳምመው ደግሞ፣ ለሀገራችን እግር ኳስ ነፍስ የዘራው ቅዱስ ጊዮርጊስ በፋይናንስ ቀውስ ተመታ የሚለው ዜና ነበር። ያ ዜና የደጋፊውን ብቻ ሳይሆን ስፖርቱን በቅርብም በሩቅም የሚከታተለውን ሁሉ ልብ ሰብሯል። #የሌጀንዶቹጥሪ... በዚያ አስቸጋሪ ወቅት የክለቡ የቀድሞ ሌጀንዶች ተሰባሰቡ። የክለቡ የልብ ወዳጅና ደጋፊ የሆኑትን የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጀማል አህመድን ቀጠሮ ይዘው ቢሮአቸው ድረስ ሄዱ፤ #ይታደጉን ሲሉም በትህትና ጠየቁ። #አቶጀማል ሌጀንዶቹን ሲያዩ ከሰላምታቸው በፊት እንባቸው ቀደማቸው። ክለቡን ከሩቅ ሆነው በጭንቀት ሲከታተሉት ነበርና። ውይይቱ ሁሉንም ባስደሰተ መልኩ ተቋጨ፤ የዚያን ቀን ደስታ የቀድሞ ተጫዋቾች እስከዛሬ ያስታውሱታል። #ከመዳን ወደ #ራዕይ.. ነገሮች ሁሉ ለበጎ ሆነው አለፉ። ክለቡ ከመውረድ ስጋት ተረፈ፤ ብቻ ሳይሆን ክለቡን ተቋም የማድረግ የዘመናት ምኞት በቁርጠኝነት ወደ ተግባር እንደሚገባ #በአድዋ00 መሰብሰቢያ አዳራሽ ለደጋፊው በይፋ ተበሰረ። ያን ቀን የነበረውን ስሜት ለመግለጽ ብዕር ቃል ያጥረዋል። ዛሬ ደግሞ ጊዜያዊ ቦርዱ ባለፉት 5 ወራት ያከናወናቸውን ሥራዎች በሊቀመንበሩ በአቶ ነሲቡ ጫኮ በኩል ለጠቅላላ ጉባኤው አቀረበ። ልብ የሚያሞቁ ብሥራቶች ቤቱን በደስታ አናወጡት። ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ዳሸን ባንክ፣ ፔፕሲ ኢንተርናሽናል እና DC United በቋሚ አጋርነት ክለቡን ይደግፋሉ። ከአጋሮች ብቻ #ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል። የ91 ዓመቱ አንጋፋ ክለብ ወደ 19 ዓመት ወጣትነት የተመለሰ እስኪመስል ድረስ የአዳራሹ ድባብ ሞቀ። #ባለንብረት የመሆን ጉዞ.. ክለቡን ከጊዜያዊ ጥገኝነት አላቅቆ ባለንብረት ለማድረግ ከልቡ የተጋው ውዱ የጊዮርጊስ ልጅ #አቶጀማልአህመድ፣ ከበላይ ጠባቂያችን ከክቡር ሼህ አላሙዲን ጋር ተመካክረው በሞጆ የሚገኝ ትልቅ ሆቴል ገዝተው ለዋናው ቡድን በቋሚነት የመኖሪያና የልምምድ ቦታ አድርገው ሰጡ። ይህ የዕለቱ ትልቁ ሰርፕራይዝ ነበር። የግዥው ዋና ምክንያት ደግሞ ልብ ሊባል ይገባል። በደብረ ዘይት የሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው የታዳጊዎች ማዕከል ለዘመናት ከተመሰረተበት ዓላማ ውጭ ለዋናው ቡድን ማረፊያና መለማመጃ ሲያገለግል ኖሯል። አሁን ግን ይህ በታላቁ ሰው የተመሰረተ አካዳሚ ወደ ዋና ሥራው ይመለሳል። ከመላው ሀገሪቱ በብቃታቸው የተመረጡ ወጣቶች ገብተው የሚሰለጥኑበት፣ ለክለብ፣ ለሀገርና ለዓለም አቀፍ መድረክ የሚበቁ ኮከቦች የሚፈሩበት ማሰልጠኛ ይሆናል። ይህን ራዕይ እውን ለማድረግ አቶ ጀማል በግላቸው ከፖርቹጋሉ #የሊዝበንቤኔፊካ አካዳሚ ጋር ግንኙነት ፈጥረው፣ የአጋርነት የሥራ ውል ለመፈራረም ጫፍ ላይ ተደርሷል። #ለሌጀንዶቻችን.. ይህ አንጋፋ ክለብ ዳግም ታድሶ በሁለት እግሩ መቆሙን፣ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የክለቡ  የቀድሞ ሌጀንዶች ለአፍታ ቀና ብለው ቢሰሙ፣ ምንኛ ደስ ባላቸው ነበር! #የመጨረሻመልዕክት.. "የነብርን ጅራት አይዙ፤ ከያዙም አይለቁ" ይላል የአባቶች ተረት። ጀምረናል፤ አሁን መልቀቅ የለም። ፍቅር፣ ህብረት፣ አንድነትና የጋራ ጥረት #በጊዮርጊሳውያንቤት ይንገሥ! #ቅዱስጊዮርጊስ ለዘላለም ይኑር! 💛❤️💚 የክለባችን ቴክኒካል ዳይሬክተር ስዮም ከበደ

Open in Telegram
Views2,100+7%vs avg
Forwards—
Reactions21
Comments—
#10087Photo
Views2,070+6%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#10085Photo
Views3,350+71%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#10083Text
Views3,930+101%vs avg
Forwards—
Reactions40
Comments—