Посты канала ST.GEORGE FC™🇪🇹
✌️ ቀጣይ ጨዋታ [ 𝐍𝐞𝐱𝐭 𝐌𝐚𝐭𝐜𝐡 ] ! ❤️💛 🏆 | 20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ኮካ-ኮላ ዋንጫ 🟡 ቅዱስ ጊዮርጊስ 🆚 ጋሞ ጬንቻ 🔴 🗓️ | እሁድ ህዳር 6 - 2019 ⏱️ | ቀን 8:00 🏟 | አበበ ቢቂላ ስታዲየም ድል ለታላቁ ክለባችን ሳንጃው ! ❤️💛 ትኬቱን በ Telebirr App ይቁረጡ🎫 @St_Georgefc @St_Georgefc
Открыть в Telegramበቀጣይ የሚደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ማስተካከያ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጋሞ ጨንቻ እሁድ 8 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። @St_Georgefc @St_Georgefc
Открыть в Telegram20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ኮካ-ኮላ ዋንጫ 📢ቀጣይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል 📍ነገ ሀሙስ ህዳር 3 ቀን 9:30 🏟አበበ ቢቂላ ስታድየም @st_Georgefc @st_Georgefc
Открыть в Telegramበሲቲ ካፕ የስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል! ቅዳሜ በሚጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ የተወሰኑ የአዲስ አበባ ስታዲየም ቦታዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ተደርጓል። - ዳፍ 70 ብር - ሚስማር 70 ብር - ካታንጋ 150 ብር ሌሎቹ ቦታዎች ደግሞ በነበሩበት የሚቀጥሉ ሲሆን ትኬት መቁረጥ ሲጀመሩ ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል። @St_Georgefc @St_Georgefc
Открыть в Telegramየቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች ቋሚ የአመራር ቦርድ መርጠዋል ……… የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላት ባለፈው እሁድ ጥቅምት 22/2019 በሸራተን አዲስ ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ 7 አባላት ያሉት ቋሚ የስራ አመራር ቦርድ ሾመዋል፡፡ጠቅላላ ጉባኤው ግንቦት 16/2018 ባደረገው ስብሰባ 9 አባላት ያሉት ጊዜያዊ ቦርድ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን አዲስ በፀደቀው የክለቡ መተዳደሪያ ደንብ ይህ ቁጥር ወደ 7 ዝቅ ብሎ ቦርዱ ተመስርቷል። ቀድሞ ከነበረው ቦርድ ኢንስትራክተር ስዩም ከበደ የክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው በመሾማቸው እንዲሁም አቶ ዳዊት አስፋው ባለባቸው ተደራራቢ የስራ ጫና የቦርድ ሀላፊነታቸውን ያስረከቡ ሲሆን የቀሩት 7 የቦርድ አባላትን ሹመት ግን ጠቅላላ ጉባኤው በቋሚነት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ለቀጣይ 4 አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበርን ይመራል። በእሁድ ማለዳው ስብሰባ ሹመታቸው የፀደቀላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው 👉አቶ ነሲቡ ጫኮ - ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ፕሬዚደንት) 👉አቶ ዮሀንስ ሚሊዮን - ዳሸን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት(ዋና ፀሀፊ) 👉አቶ በሀይሉ አየለ - የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንና የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር 👉አቶ እዝራ መሀሪ - ከሞሀ ፔፕሲ 👉አቶ ሰለሞን መገርሳ - ከቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ማህበር 👉አቶ ቶፊቅ መሀመድ ከክለቡ ደጋፊዎች 👉አቶ ሰለሞን ጥላሁን ከክለቡ ደጋፊዎች
Открыть в Telegramየአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዳሜ በድምቀት ይጀመራል! የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊው የከተማ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስቴዲየም በድምቀት ይጀመራል። በዘንድሮው ውድድር ምድብ 1 ላይ የተደለደለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከንግድ ባንክ፣ መቻል እና ጋሞ ጨንቻ ጋር ይፎካከራል። የመጀመሪያ ጨዋታችንን እሁድ ጥቅምት 29 ቀን ከሰዓት 10:00 ሰዓት ከንግድ ባንክ ጋር እናደርጋለን! @St_Georgefc
Открыть в Telegramቅዱስ ጊዮርጊስ የገንዘብ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት ! የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣሉ ይፋ ተደርጓል። በጨዋታው አሚን ነስሩ፣ ሻሂዱ ሙስጠፋ፣ ቢላል ገመዳ፣ ሀብታሙ ጉልላት እና ናትናኤል ዳንኤል የማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከታቸው ውሳኔው እንደተላለፈ ተገልጿል። ክለቡ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀጽ 65 (ሀ) መሰረት 5,000 (አምስት ሺህ) ብር እንዲቀጣ ተወስኗል። @St_Georgefc @St_Georgefc
Открыть в Telegram#ጥቅምት22 — #የቅዱስጊዮርጊስ ትንሳዔ ቀን.. የ91 ዓመቱ አንጋፋው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ተደጋጋሚ ሻምፒዮና ሆኖ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ጽፏል። በአህጉራዊ መድረክ ግን ከእኛ በኋላ የተመሰረቱ የሰሜን፣ የምዕራብና የደቡብ አፍሪካ ክለቦች በአደረጃጀትና በፕሮፌሽናል አወቃቀር በብርሃን ፍጥነት ቀድመውን ሄዱ። ይህ ለሁሉም ስፖርት አፍቃሪ ዘወትር እንቆቅልሽ ሆኖ ኖሯል። ከዚያ በላይ የሚያሳምመው ደግሞ፣ ለሀገራችን እግር ኳስ ነፍስ የዘራው ቅዱስ ጊዮርጊስ በፋይናንስ ቀውስ ተመታ የሚለው ዜና ነበር። ያ ዜና የደጋፊውን ብቻ ሳይሆን ስፖርቱን በቅርብም በሩቅም የሚከታተለውን ሁሉ ልብ ሰብሯል። #የሌጀንዶቹጥሪ... በዚያ አስቸጋሪ ወቅት የክለቡ የቀድሞ ሌጀንዶች ተሰባሰቡ። የክለቡ የልብ ወዳጅና ደጋፊ የሆኑትን የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጀማል አህመድን ቀጠሮ ይዘው ቢሮአቸው ድረስ ሄዱ፤ #ይታደጉን ሲሉም በትህትና ጠየቁ። #አቶጀማል ሌጀንዶቹን ሲያዩ ከሰላምታቸው በፊት እንባቸው ቀደማቸው። ክለቡን ከሩቅ ሆነው በጭንቀት ሲከታተሉት ነበርና። ውይይቱ ሁሉንም ባስደሰተ መልኩ ተቋጨ፤ የዚያን ቀን ደስታ የቀድሞ ተጫዋቾች እስከዛሬ ያስታውሱታል። #ከመዳን ወደ #ራዕይ.. ነገሮች ሁሉ ለበጎ ሆነው አለፉ። ክለቡ ከመውረድ ስጋት ተረፈ፤ ብቻ ሳይሆን ክለቡን ተቋም የማድረግ የዘመናት ምኞት በቁርጠኝነት ወደ ተግባር እንደሚገባ #በአድዋ00 መሰብሰቢያ አዳራሽ ለደጋፊው በይፋ ተበሰረ። ያን ቀን የነበረውን ስሜት ለመግለጽ ብዕር ቃል ያጥረዋል። ዛሬ ደግሞ ጊዜያዊ ቦርዱ ባለፉት 5 ወራት ያከናወናቸውን ሥራዎች በሊቀመንበሩ በአቶ ነሲቡ ጫኮ በኩል ለጠቅላላ ጉባኤው አቀረበ። ልብ የሚያሞቁ ብሥራቶች ቤቱን በደስታ አናወጡት። ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ዳሸን ባንክ፣ ፔፕሲ ኢንተርናሽናል እና DC United በቋሚ አጋርነት ክለቡን ይደግፋሉ። ከአጋሮች ብቻ #ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል። የ91 ዓመቱ አንጋፋ ክለብ ወደ 19 ዓመት ወጣትነት የተመለሰ እስኪመስል ድረስ የአዳራሹ ድባብ ሞቀ። #ባለንብረት የመሆን ጉዞ.. ክለቡን ከጊዜያዊ ጥገኝነት አላቅቆ ባለንብረት ለማድረግ ከልቡ የተጋው ውዱ የጊዮርጊስ ልጅ #አቶጀማልአህመድ፣ ከበላይ ጠባቂያችን ከክቡር ሼህ አላሙዲን ጋር ተመካክረው በሞጆ የሚገኝ ትልቅ ሆቴል ገዝተው ለዋናው ቡድን በቋሚነት የመኖሪያና የልምምድ ቦታ አድርገው ሰጡ። ይህ የዕለቱ ትልቁ ሰርፕራይዝ ነበር። የግዥው ዋና ምክንያት ደግሞ ልብ ሊባል ይገባል። በደብረ ዘይት የሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው የታዳጊዎች ማዕከል ለዘመናት ከተመሰረተበት ዓላማ ውጭ ለዋናው ቡድን ማረፊያና መለማመጃ ሲያገለግል ኖሯል። አሁን ግን ይህ በታላቁ ሰው የተመሰረተ አካዳሚ ወደ ዋና ሥራው ይመለሳል። ከመላው ሀገሪቱ በብቃታቸው የተመረጡ ወጣቶች ገብተው የሚሰለጥኑበት፣ ለክለብ፣ ለሀገርና ለዓለም አቀፍ መድረክ የሚበቁ ኮከቦች የሚፈሩበት ማሰልጠኛ ይሆናል። ይህን ራዕይ እውን ለማድረግ አቶ ጀማል በግላቸው ከፖርቹጋሉ #የሊዝበንቤኔፊካ አካዳሚ ጋር ግንኙነት ፈጥረው፣ የአጋርነት የሥራ ውል ለመፈራረም ጫፍ ላይ ተደርሷል። #ለሌጀንዶቻችን.. ይህ አንጋፋ ክለብ ዳግም ታድሶ በሁለት እግሩ መቆሙን፣ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የክለቡ የቀድሞ ሌጀንዶች ለአፍታ ቀና ብለው ቢሰሙ፣ ምንኛ ደስ ባላቸው ነበር! #የመጨረሻመልዕክት.. "የነብርን ጅራት አይዙ፤ ከያዙም አይለቁ" ይላል የአባቶች ተረት። ጀምረናል፤ አሁን መልቀቅ የለም። ፍቅር፣ ህብረት፣ አንድነትና የጋራ ጥረት #በጊዮርጊሳውያንቤት ይንገሥ! #ቅዱስጊዮርጊስ ለዘላለም ይኑር! 💛❤️💚 የክለባችን ቴክኒካል ዳይሬክተር ስዮም ከበደ
Открыть в Telegramቀጣይ ጨዋታ✌️ ኢትዮ ኤሌክትሪክ vs ቅዱስ ጊዮርጊስ እሁድ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም 9:00 ትኬቱን away በሚል ይቁረጡ http://ticket.ethiosport.pro
Открыть в Telegramየጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላት በሙሉ🎤 የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ2019 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓም በሸራተን አዲስ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ያካሒዳል። በመሆኑም በአዲሱ የአመዘጋገብ ስርአት የተመዘገባችሁና በቀድሞው አሰራር የአባልነት መስፈርቱን ለ2019 ያጠናቀቃችሁ ማስረጃውንና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ የስብሰባው ተሳታፊ እንድትሆኑ የስራ አመራር ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል። 💛❤️
Открыть в Telegram🏆 | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ተኛ ሳምንት ጨዋታ! 🔴🟡 ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-2 ሸገር ከተማ ⚫️🔴 #አማኑኤል_ኤርቦ 51' #ናትናኤል_ዳንኤል 73'
Открыть в Telegram20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ኮካ ኮላ ዋንጫ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀምራል ........... በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚደረገው የዘንድሮው ዓመት 20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ኮካ ኮላ ዋንጫ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲም ሲጀምር ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በምድብ አንድ ከመቻል፤ ጋም ጨንቻና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተደልድሏል፡፡ በመድብ ሁለት ኢትዮጵያ ቡና፤ ኢትዮጵያ መድን፤ ሀድያ ሆሳዕናና ኢትዮ-ኤልክትሪክ ተደልድለዋል፡፡
Открыть в Telegram🏆 | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ተኛ ሳምንት ጨዋታ! ⌚️ ተጠናቀቀ! 🔴🟡 ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 አዳማ ከተማ ⚪️🔴 #አብዱል_ሀሚድ 🏟 | አዲስ አበባ ስታዲየም ድል ለታላቁ ክለባችን ሳንጃው ! ❤️💛
Открыть в Telegram👏አይዞን የሳንጅዬ ልጆች በእግር ኳስ ሜዳ ላይ መሸነፍ ያለ ነው። ዋናው አቋማችን ነው.... አሁን ላይ ያለው ስብስብ ደግሞ እጅግ በጣም ማራኪና ወሳኝ ተጫዋቾችን በተገቢው ቦታ ያሰባሰበ በመሆኑና አጀማመሩንም ስላሳመሩልን የዘንድሮ ዋንጫ ከእጃችን የመውጣት አዝማሚያ ያለው አይመስልም። 👉በእንዲህ አይነት ጠንካራ ቡድን አለፍ አለፍ ብለው የሚታዩ የጨዋታ ድክመቶችና የውጤት ማጣት ጊዜያዊ ትዕይንት እንጂ ዘለቄታ አይኖራቸውም። ይልቁንም ተጫዋቾቻችንን ከመውቀስ ይልቅ ማበረታታትና ድጋፋችንን ማንፀባረቅ ለቀጣይ የተሻለ እንዲሰሩ ያግዛቸዋል። 👉 በደጋፊ መነፅርም ሲታይ አልፎ አልፎ የነጥብ መጣልና ደረጃችንን ሳንለቅ የፉክክር ስሜት መኖሩ በተደጋጋሚ ያለማቋረጥ ከማሸነፍ ከሚገኘው ድል የተሻለ ጣዕም አለው። "ብትሸነፉም አቻ ብትወጡም" "የኛን ድገፋ መቼም አታጡም" @St_Georgefc @St_Georgefc የቅዱስ ጊዮርጊሳውያን ድምፅ✌️ THE VOICE OF ST.GEORGE FANS
Открыть в Telegram