Posts of Saint George Fans || የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች

newest first

#49011Photo
Views69−90%vs avg
Forwards1
Reactions20
Comments0
#49008Photo
Views2,614+289%vs avg
Forwards1
Reactions23
Comments0
#49002Photo
Views391−42%vs avg
Forwards2
Reactions38
Comments—
#49000Photo
Views268−60%vs avg
Forwards0
Reactions19
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h193
10 h268
  1. After 1 hour193
  2. Total to date268
#48999Photoedited
Views431−36%vs avg
Forwards1
Reactions28
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
6 h391
14 h431
  1. After 6 hours391
  2. Total to date431
#48997Photo
Views446−34%vs avg
Forwards0
Reactions19
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
7 h358
24 h446
  1. After 6 hours358
  2. After 24 hours446
  3. Total to date446
#48996Photoedited

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች ቋሚ የአመራር ቦርድ መርጠዋል! የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላት ባለፈው እሁድ ጥቅምት 22/2019 በሸራተን አዲስ ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ 7 አባላት ያሉት ቋሚ የስራ አመራር ቦርድ ሾመዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ግንቦት 16/2018 ባደረገው ስብሰባ 9 አባላት ያሉት ጊዜያዊ ቦርድ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን አዲስ በፀደቀው የክለቡ መተዳደሪያ ደንብ ይህ ቁጥር ወደ 7 ዝቅ ብሎ ቦርዱ ተመስርቷል። ቀድሞ ከነበረው ቦርድ ኢንስትራክተር ስዩም ከበደ የክለቡ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው በመሾማቸው እንዲሁም አቶ ዳዊት አስፋው ባለባቸው ተደራራቢ የስራ ጫና የቦርድ ሀላፊነታቸውን ያስረከቡ ሲሆን የቀሩት 7 የቦርድ አባላትን ሹመት ግን ጠቅላላ ጉባኤው በቋሚነት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ለቀጣይ 4 አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበርን ይመራል። በእሁድ ማለዳው ስብሰባ ሹመታቸው የፀደቀላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናቸው - አቶ ነሲቡ ጫኮ - ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ፕሬዚደንት) - አቶ ዮሀንስ ሚሊዮን - ዳሸን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት(ዋና ፀሀፊ) - አቶ በሀይሉ አየለ - የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንና የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር - አቶ እዝራ መሀሪ - ከሞሀ ፔፕሲ - አቶ ሰለሞን መገርሳ - ከቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ማህበር - አቶ ቶፊቅ መሀመድ ከክለቡ ደጋፊዎች - አቶ ሰለሞን ጥላሁን ከክለቡ ደጋፊዎች @St_George_Fans @St_George_Fans

Open in Telegram
Views456−32%vs avg
Forwards0
Reactions21
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h59
8 h359
25 h456
  1. After 1 hour59
  2. After 6 hours359
  3. After 24 hours456
  4. Total to date456
#48995Text

Forwarded from Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

ከደስታው መልስ ወደ እውነታው ስንመለስ‼️ ………… እሁድ ማለዳ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤያችን በርካታ አስደሳች ዜናዎችን ሰምተን ስንደሰት ውለን አድረናል፡፡ ደስታው የሚቀጥል ቢሆንም አሁን ደግሞ ቆም ብለን ከክለባችን እውነታዎች ጋር ልንፋጠጥ ግድ ይላል፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ እውነታዎችን ደግሞ የምናገኛቸው በጉባኤው ላይ በተሰማው የኦዲት ሪፖርት ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ እውነታዎች የማያስደስቱ ብሎም የሚያስደነግጡ እና የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ መንግስተአብ እና ዳንኤል በተሰኘ የተመሰከረት የኦዲት ተቋም ላለፉት ወራት ሲከናወን የከረመው የኦዲት ስራ በድርጅቱ አመራሮች ሲቀርብ የፈረሰኛው ደጋፊ በጸጥታ ሰምቷል፡፡ በሪፖርቱ መሀል አንድ ጊዜ ብቻ ስቋል፡፡ያቺ ሳቅም የምጸት እና በውስጧ ቁጣን ያዘለች ሳቅ ነበረች፡፡ ፈረሰኞቹ የሳቁት ኦዲተሩ የክለቡ ጽ/ቤት ያለበትን ቦታ ኦርጂናል ካርታ ማግኘት እንዳልቻለ በገለጸበት ወቅት ነው፡፡በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ጠቅላላ ጉባኤ የታደሙት ፈረሰኞች የሳቁት የንብረታቸው ካርታ ባለመገኘቱ ተደስተው አይደለም ፥ ይሄ ሳቅ የምጸት እና የቁጣ ሳቅ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ረጋ ብለው ሪፖርቱን ያቀረቡት ኦዲተር ፈረሰኞቹ ያዳመጡት በሀዘኔታ እና አግራሞት ነበር፡፡ 👉ለመሆኑ ሪፖርቱ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምን ይላል? ኦዲተሩ በግልጽ እንዳስረዱት ሪፖርቱ ከፈረንጆቹ 2017 እስከ 2026 ድረስ ያለውን የጊዜ ክልል ነው፡፡የ10 አመት ሪፖርት ነው ማለት ነው፡፡ በእርግጥ የ2026 የበጀት አመት ገና ስላልተጠናቀቀ ሪፖርቱ 10ኛውን አመት ሙሉ ለሙሉ አላካተተም፡፡ዘጠኙ አመታት ግን በሪፖርቱ በሚገባ ታይተዋል፡፡ኦዲተሩ ወደ ሪፖርቱ ዝርዝር ከመግባታቸውም በፊት ኦዲቱ በባለሙያዎች ቋንቋ የምርመራ ኦዲት (investigative audit) እንደሚባል እና መለያውም IS 4400 እንደሚሰኝ አሳውቀዋል፡፡ ኦዲተሩ የኦዲት አይነቱን ካስረዱ በኋላ የቀጠሉት ወደ ዝርዝሩ ነበር፡፡አሳዛኙ ክፍልም ከዚህ በኋላ የተሰማው ነበር፡፡ከሰማናቸው አሳዛኝ ነገሮች ጥቂቱን እንዘርዝር - ኦዲቱ በሸፈናቸው አመታት ውስጥ አንድም የቦርድ ውሳኔን የሚያሳይ ቃለ ጉባኤ ማግኘት አልቻለም፡፡ ስለዚህም ውሳኔዎች በምን አግባብ ሲወሰኑ እንደነበር ማወቅ አልተቻለም፡፡ - የክለቡ ንብረት ያለቦርድ ውሳኔ እና ውሳኔውን የሚያሳይ ቃለ ጉባኤ ሳይያዝ ከህግ ውጭ ተሽጠዋል፡፡ - ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች ያለ ምንም ይፋዊ ጨረታ ተሽጠዋል፡፡ - ክለቡ የሚተዳደርበት የስራ መመሪያ (operaton manual) ተፈልጎ ማግኘት አልተቻለም፡፡ - ተጫዋቾች በሚፈርሙበት ወቅት በምን መንገድ እንደተመለመሉ የሚያሳይ (scouting report) አልተገኘም፡፡ - የደጋፊዎች የአባልነት መረጃዎች በተደራጀ መልኩ ተሰንዶ አልተቀመጠም፡፡ - ከህግ ውጭ ለተከታታይ 8 አመታት የክለቡ ጠቅላላ ጉባኤ መካሄዱን የሚያሳይ ቃለ ጉባኤ ማግኘት አልተቻለም፡፡ - የክለቡ ወጪዎች እና የባንክ መዝገቡ አልተናበበም፡፡ - ክለቡ የሚንቀሳቀስበት በጀት ሰነድ አልተገኘም ፥ በጀቱ እና ወጪው ተነጻጽሮ ከበጀቱ ምን ያህል እንደተጠቀመ የሚያሳይ ሪፖርትም አልተገኘም፡፡ - ክፍያዎች በማን እንደተጠየቁ ፥ እንደጸደቁ እና እንደተፈጸሙ የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘም፡፡ - የስራዎች ርክክብ አመላካች ሰነድ አልተገኘም፡፡ - ለክለቡ ስቴድየም መስሪያ የተሰጠው መሬት በአግባቡ አልተያዘም ፥ አጥር እና ቅጥር የለውም ፥ ባለፉት አመታት ክለቡ ለስቴድየሙ ግንባታ የሚሆን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥቻለሁ ቢልም ወጪውን የሚገልጽ ስራ መሬት ላይ አልታየም፡፡ - የክለቡ ጽ/ቤት ኦርጂናል ካርታ አልተገኘም፡፡ - ክለቡ ንብረቱን የሚመዘግብበት እና የሚቆጣጠርበት አሰራር አልተገኘም፡፡ - በክለቡ ስም ከውጭ የገቡ እቃዎች የጉምሩክ ዲክላራሲዮን አልተገኘም፡፡ - በክለቡ ግምጃ ቤት ያለ ንብረት ተቆጥሮ ያለበት ሰነድ አልተገኘም፡፡ - በክለቡ ስም የተገዙ ንብረቶች ለማን እንደተሰጡ እና ምን አይነት ጥቅም ላይ እንደዋሉ የሚያሳይ ሰነድ የለም፡፡ - የተጫዋቾች ደሞዝ ከክለቡ አካውንት ውጭ በሆኑ አካውንቶች ይከፈሉ ነበር፡፡ - በሆቴሎች ያለ ደረሰኝ መጠቀም ታይቷል፡፡ማን እንደተጠቀመ እና ስንት ሰው እንደተጠቀመ በሚመለከተው አካል የተፈረመ ሰነድ አልተገኘም፡፡ - ለመንግስት መከፈል የሚገባው የደሞዝ ግብር በወቅቱ እና በአግባቡ አልተከፈለም፡፡ - የማልያ ሽያጭ ሂደቱ መዝረክረክ የሚታይበት ነው፡፡ - የክለቡ ንብረት የነበረ ሬስቶራንት አገልግሎት ሲያቆም የታክስ ክፍያው ሳይዘጋ ክፍት ሆኖ ተትቷል፡፡ - በክለቡ ስም የተመዘገበ ካሽ ሬጂስተር ማሽን የት እንዳለ አይታወቅም - ከተለያዩ አካላት መሰብሰብ የነበረበት 60 ሚሊየን ብር ሳይሰበሰብ ቀርቷል፡፡ - ከተጫዋቾች እና ቦርድ አባላት መሰብሰብ የነበረበት 25 ሚሊየን ብር አልተሰበሰበም፡፡ - 17 ሚሊየን ብር መከፈል የነበረበት ደሞዝ አልተከፈለም፡፡ - ለሆቴሎች መከፈል ያለበት 8 ሚሊየን ብር አልተከፈለም፡፡ - ውል ሳይኖራቸው ስፖንሰር የሆኑ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ኦዲተሩ በሪፖርታቸው እነዚህ ዝርዝሮች ከገለጹ በኋላ ስራው አሁንም እንዳልተጠናቀቀ ገልጸው በማጠቃለያነትም ክለቡ ስር የሰደደ የፋይናን ቁጥጥር ክፍተት (significant financial control deficiency) እንዳለበት በመግለጽ ሪፖርታቸው አጠናቅቀዋል፡፡ 👉ደጋፊዎች ምን አሉ? ከሪፖርቱ በኋላ ደጋፊዎች አስተያየታቸውን አጋርተዋል፡፡ግራ መጋባት በአስተያየታቸው ውስጥ ታይቷል፡፡"የአሁኑ ኦዲተር ብዙ መረጃዎችን ማግኘት እንዳልቻለ እያየን ነው ፥ ከዚህ ቀደሞ በሰነድ የተረጋገጠ ነው ተብሎ የቀረበልን የኦዲት ሪፖርት ታዲያ በየትኛው ሰነድ የተረጋገጠ ነው?" በማለት ከዚህ ቀደም የቀረበውን የኦዲት ሪፖርት ሙያዊ ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል፡፡ ሌሎችም አስተያያቶች ተሰጥተዋል፡፡ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው የኦዲት ይደረግ ጥያቄው የደጋፊው እንደነበር አስታውሰው የኦዲቱ አላማም እውነታውን ማውጣት እንደሆነ ገልጸው እንደ አንድ ደጋፊ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠያቂ የሆኑ አካላት ጋር የክስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ ቀጣዩን ሂደት የቦርዱ ውሳኔ ቢሆንም ጠቅላላ ጉባኤው ግን የኦዲት ስራውን እንዲቀጥል በመወሰን የኦዲቱን ጉዳይ ቋጭቷል፡፡ ጉባኤው ለጊዜው በኦዲቱ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥቶ ቢጨርስም ነገር ግን እንደ ክለብ ከዚህ የኦዲት ሪፖርት ምን ተማርን? የሚለው ጥያቄ በመላው ጊዮርጊሳውያን አእምሮ ውስጥ ቀርቷል፡፡ በእርግጥ ምን ተማርን? በቀጣይ ጽሁፍ እንመለስበታለን

Open in Telegram
Views390−42%vs avg
Forwards0
Reactions23
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h67
8 h284
25 h390
  1. After 1 hour67
  2. After 24 hours390
  3. Total to date390
#48994Photoedited
Views533−21%vs avg
Forwards0
Reactions40
Comments1
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
8 h268
25 h533
  1. After 6 hours268
  2. After 24 hours533
  3. Total to date533
#48993Photo
Views565−16%vs avg
Forwards1
Reactions50
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
9 h361
26 h565
  1. After 24 hours565
  2. Total to date565
#48992Photoedited
Views594−12%vs avg
Forwards0
Reactions44
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h217
12 h453
30 h594
  1. After 24 hours594
  2. Total to date594
#48991Photo
Views389−42%vs avg
Forwards0
Reactions20
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
4 h206
13 h389
  1. Total to date389
#48990Photoedited
Views581−13%vs avg
Forwards1
Reactions39
Comments2
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
4 h239
13 h422
31 h581
  1. After 6 hours239
  2. After 24 hours581
  3. Total to date581
#48988Photoedited
Views552−18%vs avg
Forwards0
Reactions43
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
5 h179
12 h289
31 h552
  1. After 6 hours179
  2. After 24 hours552
  3. Total to date552
#48987Photo
Views275−59%vs avg
Forwards0
Reactions20
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
6 h83
13 h117
32 h275
  1. After 6 hours83
  2. After 24 hours275
  3. Total to date275
#48986Video
Views677+1%vs avg
Forwards0
Reactions36
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
6 h331
33 h570
67 h677
  1. After 6 hours331
  2. Total to date677
#48985Photoedited
Views608−9%vs avg
Forwards0
Reactions44
Comments0
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
7 h356
33 h543
68 h608
  1. After 6 hours356
  2. Total to date608