Posts of መንፈሳዊ ትረካና አጫጭር ፅሁፎች
ስለ ጠላቶቻችን፣ ስለሚያሙን፣ ስለሚነቅፉን፣ ስለሚያሳድዱንና ነገሮችን ሁሉ ስለሚያከብዱብን ሰዎች ሁሉ መጸለይ ይገባናል። ይህ በቅድሚያ ልናደርገው የሚገባን ነገር ነው፤ ምክንያቱም እኛ ይቅር ካላልናቸው እግዚአብሔርም እኛን ይቅር አይለንምና። @recordingYT
Open in Telegramበመርሐ ተዋሕዶ የሐዲስ ኪዳን የታሪክ ዝግጆታችን ውስጥ የሐዋርያት ሥራ በብዛት ለመስራት ሞክረናል። ከእነዚህም ውስጥ የቅዱስ ጳውሎስ መጠራትና 3ቱ ጉዞዎቹ፤ በመጨረሻ ስለ መታሠሩና ስለ ሰማዕትነቱ ነው። የዮሐንስ ወንጌል ምንባብ ብንጀምርም መግቢያውን ገና እያዘጋጀን ነው፤ ሲደርስ እንለቃለን። የሐዋርያት ሥራም ታሪኮችን ነው ያስቀደምነውና መግቢያውን ከዮሐንስ ወንጌል መግቢያ በኋላ እንለቃለን። የዚህ ሳምንት አዲስ ቪድዮ ባይደርስልንም ከስር ያሉትን አምስት ቪድዮዎች ጋበዝናችሁ። እነዚህንም ያስቀደምነው የመልእክታትን መግቢያ ስንጀምር የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞዎችን ቀድሞ ማወቅ ስለሚያቀልልን ነውና ተመልከቷቸው። 👇👇👇 1. የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መጠራት https://youtu.be/Sc4xxOZYsUM?si=qN1VC6Dwk_wq_7Q7 2. የቅዱስ ጳውሎስ የመጀመርያው ሐዋርያዊ ጉዞ እና የመጀመርያዋ የሐዋርያት ጉባኤ https://youtu.be/Sc4xxOZYsUM?si=6dgheeQ5m1fHCBDU 3. የቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ https://youtu.be/d1xbUiMDWeM?si=G6wIlxu8eQY-Sx4e 4. የቅዱስ ጳውሎስ ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ https://youtu.be/kGVgnYmTl4U?si=I-Cv38QwjYCgwd68 5. የቅዱስ ጳውሎስ መታሠርና ሰማዕትነት (የመጨረሻው ክፍል) https://youtu.be/Es97Er-7Q_o?si=_cD9kwl_F7ldb6Ao
Open in TelegramForwarded from መርሐ ተዋሕዶ አኒሜሽን
ጥቅምት 22 ቅዱስ ሉቃስ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው። ታሪኩንና ስለ ወንጌሉ የሰራነውን መግቢያ ቪድዮ ይመልከቱ። https://youtu.be/SJaHWeBbi1Y?si=pnw81RT3MLf7MfAM
Open in Telegramልጆቻችንን ደጎች፣ ገር አሳቢዎች እና ይቅር ባዮች (እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርያት ናቸው) እንዲሆኑ፣ ቸር እንዲሆኑ፣ ባልንጀሮቻቸውን እንዲወዱ እንዲሁም ይህን የአሁኑን ዘመን እንደ ምንም ነገር እንዲቆጥሩ በምናስተምራቸው ጊዜ፤ በነፍሳቸው ውስጥ በጎነትን (ምግባርን) እናሰርጻለን፣ የእግዚአብሔርንም መልክ በእነርሱ ውስጥ እንገልጣለን። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @recordingYT
Open in Telegramእኛ እዚህ ምድር ላይ ቋሚና ዘላቂ የሆነ ቤትም ሆነ ከተማ የለንም፤ በከፍተኛ ጉጉት የወደፊቱን፣ ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌምን እንናፍቃለን። ምድራዊ ሀብቶች ሁሉ ከንቱ ናቸው። በልባችሁ ውስጥ ሁል ጊዜ አንድ ምኞት ይኑራችሁ። እርሱም ሰማያትን፣ ዘላለማዊ መልካም ነገሮችን ማግኘት ነው። ምድራዊ ሀብቶች ሁሉ ጊዜያዊና አታላይ ናቸው። ዛሬ የእኛ ነው። ነገ ደግሞ የሌላ ሰው ይሆናል። @recordingYT
Open in TelegramForwarded from መርሐ ተዋሕዶ አኒሜሽን
https://youtu.be/pidoSVWpt2s?si=H6J-AG4CoPmtulrZ እንኳን አደረሳችሁ!
Open in Telegram"The spiritual man's one and only aim is God and God alone. All his aim is to seek after God, to know Him and to love Him, to live with Him and to abide in Him, and have a relationship with Him; that God lives in His heart and that he lives in God's heart, saying to Him in love, 'there is none upon earth that I desire besides You' (Ps.73:25)" + Pope Shenouda + የመንፈሳዊ ሰው ብቸኛውና እውነተኛው ዓላማው እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ብቻ ነው። ዓላማው ሁሉ እግዚአብሔርን መሻት፣ እርሱን ማወቅና እርሱን መውደድ፣ ከእርሱ ጋር መኖርና በእርሱ ውስጥ መጽናት፣ ከእርሱም ጋር ኅብረት ማድረግ ነው፤ እግዚአብሔር በልቡ ውስጥ እንዲኖር፣ እርሱም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ እንዲኖር፤ በፍቅር እንዲህ እያለ ይናገራል ፦በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? መዝሙረ ዳዊት 73:25 » — አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ @recordingYT
Open in TelegramForwarded from መርሐ ተዋሕዶ አኒሜሽን
📢 ቪድዮችን በየአምዳቸው የተደራጁትን ለማግኘት playlist ላይ በመግባት በተከታታይ ያግኙ 🙏🙏🙏
Open in Telegram