📢ስለ ሕይወት ስኬት መንገድ ይህን ያውቁ ኖሯል? 📌🎁📌ስኬት 5ኛ dimension ነው እንዴት ከ 0 ወደ 5 እንድረስ? https://youtu.be/QjIPTrJ74cE?si=Hg2z4Wpa_gMsk_6O
Open in Telegram
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና | የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል! የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ "የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው " https://www.youtube.com/user/TheNahusenai Facebook አድራሻ fb.com/psychologyabc
Latest posts
#አሁንም_አልረፈደም ! #Share t.me/psychoet እኔ ማንም አይደለሁም ፤ እራሴንም ከሌላው ለማወዳደርና እሻላለሁ ብዬ ለመናገር ሞራሉም ብቃቱም የለኝም፡፡ ግን ግን ሰው ነኝና አንዳንድ ሁኔታዎች ይገርሙኛል፤ የሚገርመኝንና የምታዘባቸውን ነገሮች ለሌላው ባካፍል መመጻደቅ አይሆንብኝም፡፡ ህይወት ትምህርት ቤት ናት ፤ በህይወት ትምህርት ቤትነት ያወቅነውን ወይም የታዘብነውን ለሌሎች ማሳወቅና ማካፈል ሞራላዊ ግዴታም ጭምር ነው ብዬ አምናለው፡፡ ይህንን ጽሑፍ ከእዚህ መንፈስና አንድምታ ተረድታችሁልኝ እንድታነቡ አስቀድሜ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡ ተወልጄ ባደጉበት አካባቢ አንድ “አፒዮ” የሚባል ሰው ነበር፡፡ አፒዮ የቀን ሰራተኛ ሲሆን ፤ ለቤት መስሪያ የሚሆን እንጨት ከተቆረጠበት እስከሚፈለግበት ቦታ ድረስ በትከሻው ተሸክሞ ደከመኝ ሳይል የፈጀበትን ጊዜና ቀን ያህል ቢፈጅበትም እንጨቶቹን ተሸክሞ እያመላለሰ ከምር በተባለበት ስፍራ ይከምራል፡፡ ለድካሙ ዋጋ ብር አይቀበልም ጥቂት ዝርዝር ሳንቲምና ምግብ ብቻ በቂው ነው፡፡ አፒዮ እኔ እስከማውቀው ድረስ ዘመድ የለውም እንዲሁም በአካባቢው መኖሩን እንጂ ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡ ከሰው ጋር አይነጋገርም በአጠቃላይ ከማኅበራዊ ህይወት የተገለለ በእራሱ ዓለም የሚኖር ሰው ነው፡፡ ቤት የለው ፤ አንዲት ቃል ትንፍሽ አይል ብቻ ዝም ብሎ የጸጥታን ባህር የሚቀዝፍ ለሰውም ለራሱም ባይተዋር የሆነ ምስኪን ሰው፡፡ ቢርበው ራበኝ ብሎ ምጽዋት አይጠይቅም ፤ ውሃ ቢጠማው እሩቅ ተጉዞ ወንዝ ሄዶ ይጠጣል እንጂ ከማንም ጋር ግንኙነት መፍጠር አይፈልግም፡፡ የቀን ስራ ሰርቶ የሚያገኛትን ሳንቲም በድሪቶ ልብሱ ላይ ይቋጥራል፡፡ በላዩ ላይ ያለው ልብስ ድሪቶ ቢመስልም ብዙ ገንዘቦችን ቋጥሮ ይገኛል፡፡ “ግን አፒዮ ዘመድ ፤ ሚስትና ልጅ የለው ገንዘብ ምን ሊያደርግለት ያጠራቅማል?” ልጆች ሳለን ብዙዎቻችን የምንጠይቀው ጥያቄ ነበር፡፡ ታዲያ ምስኪን አፒዮ በዓመት ወይም በሁለት ዓመት አንዴ በከተማው ማዘጋጃ ቤት ጸጥታ አስከባሪዎች በግድ (አፒዮ እንደ ዝምተኛነቱ ሳይሆን አንድ ሰው አጠገቡ ደርሶ በመተናኮል ገንዘቡን ሊዘርፈው ቢነሳሳ ዘውትር ከአጁ በማትለው ቀመጥ እንካ ቅመስ ብሎ ያስገባለታል፡፡) ይያዝና ድሪቶ ልብሱ ከላዩ ላይ ይገፈፍል በእራፊ ጨርቆች የቋጠራቸው ሳንቲሞች ይፈታሉ ፤ ጸጉሩ ይቆረጣል ፤ አዲስ ጥብቆና ልብስ ይገዛለታል (ቀሪው ገንዘቡ ምን እንደሚደረግበት ፈጣሪ ይወቀው!)፡፡ እርሱ ግን በዚህ ምንም ደስተኛ አይሆንም እንዲሁም ለምን ንብረቴን ነካችሁብኝ ብሎ ያዝናል ፤ ይተክዛል ከፍ ሲልም ያለቅሳል፡፡ በአዲስ ገጽና ልብስ ለጥቂት ሳምንታት ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ አዲስ ገጽታውና ልብሶቹ እያደፉ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለሳል፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ህይወቱ በእንዲህ ቀጥላለች አሁን ይኑር አይኑር ባለውቅም፡፡ በአዲስ መስመር ሃሳባችንን ስናጠናክር በስራና በትምህርት ገበታ ብዙ አፒዮችን አውቃለው፡፡ እነኚን ከዋናው አፒዮ የሚለያቸው የተማሩ የሚባሉ ፤ በአንጻሩ የተሻለ ገቢ የሚያገኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን በትክክል ከታየ ህይወታቸው ከአፒዮ የሚለይበት ምንም መስመር የለውም፡፡ በአፒዮ ላይ ምንም መፍረድ አንችልም ምክንያቱም ለሰው ቀርቦ የማያዋየው ወይም ሌሎቻችን ልንረዳው ያልቻልነው ብዙ ግላዊ ሚስጥሮችና እንቆቅልሾች ይኖሩታል፡፡ እነኚህን ግን ምን ልላቸው እንደምችል አላውቅም (ልፈርድባቸው ሳይሆን የህይወት ትርጉም ለእነሱ ምንድን ናት የሚለውን ለማንሳት ያህል ነው፡፡) ይሰራሉ ማንም የሚያገኘውን (አንዳንዴ እንዲሁም ከማናችንም በላይ ያገኛሉ) ደመወዝ ያገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ከማኅበራዊና ዘመድ የተገለሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ማጠራቀም ትልቁ ስራቸው ነው፡፡ ለምን ገንዘብ ያጠራቅማሉ ለማለት አይደለም ገንዘብ ልንገለገልበት እንጂ ሊገለገልብን አይገባም፡፡ ልብሳቸውንና ገላቸውን አይታጠቡ አንዲት ልብስ እላያቸው ላይ እስኪወይብና እስኪያረጅ ማልያ አድርገው ይለብሳሉ፡፡ ትንሽ ገንዘብ አውጥተው ምግብ ለመብላት ለገንዘባቸው ይሳሱለታል፡፡ ብቻ እዚህ ልገልጸው የማልችላቸው ነገሮችን ሁሉ አይባቸዋለው፡፡ ባልፈርድባቸውም ያሳዝኑኛል ገንዘብ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ገንዘብ ብቻ አያኖረንም፡፡ እንደው ይቅር ምንም አታውጡ ማኅበራዊ ህይወትን እንኳን እንጋራ ሲባሉ አሻፈረኝ የሚሉ፡፡ እራስን እየበደሉ ገንዘብ ማጠራቀም አሁንም ማጠራቀም፡፡ ይህ በእውነት ጤነኝነት አይደለም ለዚህ ነው ዓለም ዓቀፉ የጤና ድርጅት “አለመታመም ጤነኝነት አይደለም” ብሉ ጤናን በተለያየ አኳሃን የሚተረጉመው፡፡ የሚገርመው ነገር እነኚህ ሰዎች ገንዘባቸውን አጠራቅመው ኋላ ላይ ጤናቸውን በገንዘብ ለመሸመት ለዘመናት ያጠራቀሙትን ገንዘብ ለህክምና ያውሉታል፡፡ “የቆጣቢን ይበላል ቆርጣሚ!” እንደሚባለው አስቀድመን ያልተንከባከብነውን ጤና በኋላ ላይ ገንዘብ ብቻ አይታደገውም፡፡ ድህነት አስቀያሚ ነገር ነው ክብርንና ማንነትን ያዋርዳል ነገር ግን የሚበላ የሚጠጣ ሳይጠፋቸው ከድህነት ጠለል በታች የሚኖሩ ሰዎች በፍጹም የጤነኝነት አይደለም፡፡ ሰው ምግብ ካልበላ ውሃ ካልጠጣ እንዴት ነው የሚኖረው ፤ ለነገስ ብለን የምናጠራቅመው ገንዘብ ነገ እንደሚያኖረን እንደምን እርግጠኛ እንሆናለን!? ከስነ-ልቦና አንጻር ከተመለከትነው ይህ እራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በገንዘብ እጦት ምክንያት ብዙ መሰረታዊ ጉዳዮቻቸው ሳይሟሉ ካደጉ በኋላ ዘመን ያንን የማጣትን ዘመን ለመበቀል ሲሉ እራሳቸውን እየቀጡ ገንዘብ ማጠራቀምን ትናንትን እንደማሸነፊያ መንገድ አድርገው ሊወስዱት ይቻላሉ፡፡ ያለነን ነገር ሁሉ ደፍፍተን ዛሬን ብቻ እንኑር ማለትም አደጋ አለው፡፡ ዛሬን በአግባቡና በመጠኑ በመኖር ነገን ማለም ብልህነት ነው፡፡ ሰው እንደ ፀሐይ ነው በጊዜ ጀምበር ይወጣል በጊዜ ጀንበር ይጠልቃል፡፡ ጀንበር ወጥታ ለመጥለቅ እንደ ወቅቶች ሁኔታ ቢለያይም ቢያንስ አስራ ሁለት ሰዓት ያህል ይፈጅባታል ሰው ግን የራሱን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጀንበሩ በእጁ ላይ ነች፡፡ የህይወት ጀንበር ከመጥለቋ በሚፊት እራስን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ማንም ሌላውን ይምሰል ወይም የሌላውን ኑሮ ይኑር ሳይሆን በአቅሙ ለመኖር ይብላ ይልበስ ሳይቸግረው እራሱን በእራሱ ቀጥቶ አያጥፍ ለማለት ነው፡፡ በገዛ እጅ እራስን አጎሳቅሎ የተጠራቀመን ገንዘብ ለህክምና ከማውጣት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት መንቃት፡፡ ሻሎም! (በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychologist
Open in Telegram🚀 የበታችነት ስሜትን ድባቅ የምንመታባቸው 6 መንገዶች! ኢንስታግራም ላይ የጓደኞችህን ፎቶ ስታይ ወይም ስራ ቦታ ካንተ የተሻለ ተከፋይ ያለ ሲመስልህ "እኔ እኮ አነሳለሁ" ብለህ አስበህ ታውቃለህ? የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአችን ሳይሆን በሂደት የምንጭነው "ቫይረስ" ነው። ይህንን ቫይረስ "Format" የምናደርግባቸው 6 ተግባራዊ መንገዶች፦ ✨ 1. በሌሎች ማረጋገጫ (Validation) ላይ ጥገኛ አትሁን የአሁኑ ህይወትህን 'ላይክ' እና 'ኮመንት' እንዲመራው አትፍቀድ። አዲስ ልብስ ለብሰህ ማንም 'አምሮብሃል' ባይለህም እንኳ የራስህ ዳኛ ራስህ ሁን። የራስህ ዋጋ የሚወሰነው በሌሎች ምላሽ አይደለም። 🧠 2. ራስህን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች ለይ ውስጥህ 'ይሄን አትችለውም' ሲልህ እንደ እውነት አትቀበለው። አስተሳሰቦችህ አንተ አይደለህም፤ አንተ የአስተሳሰቦችህ ታዛቢ ነህ። "አመሰግናለሁ ስለ ሃሳብህ፣ ግን እስኪ ልሞክረው" በማለት አሉታዊነቱን ተጋፈጠው። 📚 3. ከውድቀት ተማር (Growth Mindset) ስህተት መስራት 'ውድቀት' ሳይሆን 'ግብዓት' ነው። በፈተና ብትወድቅ "እኔ ሰነፍ ነኝ" ከማለት ይልቅ "አጠናኔ ስህተት ነበር" በል። ስህተቱ ድርጊቱ ላይ እንጂ ማንነትህ ላይ እንዳልሆነ እወቅ። 🏁 4. የፉክክርን መንፈስ ግደል አንተ 'ኦሪጅናል' ሆነህ ሳለ ለምን የሌላው 'ፎቶ ኮፒ' ለመሆን ትሞክራለህ? ትልቁ ፉክክርህ ከትናንት ማንነትህ ጋር ብቻ ይሁን። ዛሬ ከትናንቱ የተሻለ አንድ ገጽ ካነበብክ አንተ አሸናፊ ነህ! 🎨 5. ስጦታህን ለይተህ አሳድግ የበታችነት ስሜት የሚመጣው በሌለን ነገር ላይ ስናተኩር ነው። ሂሳብ ላይ ጎበዝ ባትሆንም፣ ጎበዝ ሰዓሊ ወይም ጥሩ አዳማጭ ትሆን ይሆናል። ያለህን ትንሽ ችሎታ አሳድገው፤ በችሎታህ ሰውን መርዳት ስትጀምር የበታችነት ስሜቱ በራሱ ይጠፋል። 🏥 6. ባለሙያን ማማከር (ባህልን ስበር) ጭንቀቱ ከአቅም በላይ ከሆነ ባለሙያ ማማከር 'እብደት' ሳይሆን 'ዘመናዊነት' ነው። ቁስልን ደብቆ ማከም አይቻልም። ነገሮችን ከስር መሰረታቸው ለመረዳት ቴራፒስት ማነጋገር ትልቅ ብልህነት ነው። 💡 የበታችነት ስሜትን ለማጥፋት ሚሊየነር መሆን አያስፈልግም፤ ዋናው ቁልፍ "ራስን መቀበል" ነው። ዛሬ ለራስህ ቃል ግባ፦ "እኔ ከማንም አላንስም፣ የራሴ ልዩ ቀለም አለኝ!" 🎨🌟 #SelfWorth #Mindset #OvercomingInsecurity #YouthEmpowerment #Ethiopia
Open in Telegram🛡️ የማይበገረውን ማንነት የመገንቢያ 7 ስልቶች! በራስ መተማመን 'ተሰጥኦ' ሳይሆን እንደ ጡንቻ በልምምድ የሚዳብር የስነ-ልቦና እሴት ነው። 'አልችለውም' ብለህ በመፍራት ያጣሃቸውን ዕድሎች ለመመለስ እነዚህን 7 ነጥቦች ተለማመድ፦ 🕵️♂️ 1. ተቺ ሃሳቦችን ነቅለህ አውጣ፦ አእምሮህ "አንተ ደካማ ነህ" ሲልህ እንደ ፖሊስ "ማስረጃህ ምንድነው?" ብለህ ጠይቀው። ብዙ ጊዜ እነዚህ ድምጾች የልጅነት ትችቶች እንጂ የእውነት ውጤቶች አይደሉም። 🔄 2. የውስጥ ንግግርህን 'Edit' አድርግ፦ "ሰው ይስቅብኛል" የሚለውን ሃሳብ "የማውቀውን ላካፍል ነው" በሚል ቀይረው። 'አልችልም'ን በ 'እሞክረዋለሁ' ተካው። ቃላት ጉልበት አላቸው! 🎯 3. ትኩረትህን ድሎችህ ላይ አድርግ፦ ስህተትህ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ፣ ያሳካሃቸውን ትናንሽ ስኬቶች አስብ። እርዳታ ለመጠየቅና 'አላውቅም' ለማለት አትፈር፤ ይህ የጥንካሬ ምልክት ነው። 👥 4. ዙሪያህን አጽዳ (Environment)፦ ክንፍህን የሚነጩ ሰዎች ጋር እየዋልህ መብረር አትችልም። ጉድለትህን ብቻ ከሚቆጥሩ ሰዎች ራቅና "ትችላለህ" የሚሉህን ወዳጆች ቀርብ። 🛠️ 5. ልዩ ችሎታህን አውጣ፦ ማንም ሰው ባዶ አይደለም። ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነህ። ያንን ችሎታህን አውቀህ አሳድገው፤ በዚያ ስኬታማ ስትሆን የሚሰማህ ልበ ሙሉነት ወደ ሌላው ሕይወትህ ይጋባል። 💎 6. ራስህን አክብር (Self-Pride)፦ ያሳለፍካቸው ፈተናዎችና የረዳሃቸው ሰዎች ያንተ ሀብቶች ናቸው። በነዚህ በጎ ጎኖችህ ተገቢውን ኩራት ኩራ። ራስህን ስታከብር ዓለም ያከብርሃል። 🎭 7. ሁሌም ራስህን ሁን (Authenticity)፦ ሌላውን ለመምሰል መሞከር ራስን መናቅ ነው። ተቀባይነት ለማግኘት ብለህ አትዋሽ፤ ማንነትህን በኩራት ስታሳይ እውነተኛ ወዳጆችን ታፈራለህ። 💡 በራስ መተማመን ማለት 'ፍጹም መሆን' ማለት አይደለም። በራስ መተማመን ማለት ስህተት ብንሰራም እንኳን 'እኔነታችን' እንደማይቀንስ ማወቅ ነው። ሚዛናዊ ሁን፣ አደጋን ለመጋፈጥ አትፍራ፣ ራስህን ውደድ! ✨ #SelfConfidence #GrowthMindset #Empowerment #Ethiopia #Success T.me/psychoet
Open in Telegram#ይሉኝታ እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ #ይሉኝታ_ምንድን_ነው? ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡ #የይሉኝታ_መንስኤዎች ✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት ✿በራስ መተማመን ማነስ ✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ ✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን ✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ ✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ #ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች ✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ? ✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ ✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ ✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ ✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር ✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር ✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል
Open in TelegramForwarded from ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷♂
1. ሰዎች እንዴት ሊይዙህ እንደሚገባ የምታስተምራቸው አንተው ነህ። ሰዎች የሚያደርጉት አንተ የፈቀድክላቸውን ብቻ ነው። አንድ ሰው የሚያደርግብህን ነገር ካልወደድከው፣ እስከዛሬ ምን ስትቀበል እንደነበር እራስህን መርምር። 2. "አንዳንድ ጊዜ ለችግሩ ያለህ አረዳድ ነው የበለጠ ችግር የሚሆነው።" አብዛኛው ስቃይ የሚመጣው እየሆነ ስላለው ነገር ለራስህ ከምትነግረው ታሪክ ነው። ክስተቱ በራሱ ገለልተኛ ነው።ህመሙን የሚፈጥረው ያንተ ትርጓሜ ነው።አመለካከትህን ቀይር፣ ልምድህንም ትቀይራለህ። 3. "የተጣበቅከው ምን ማድረግ እንዳለብህ ስላላወቅክ ሳይሆን፣ ምን ማድረግ እንዳለብህ እያወቅክ ለማድረግ ፈቃደኛ ስላልሆንክ ነው።" ይህ አረፍተ ነገር የማመካኛ ጨዋታን ያቆማል።በጥልቅ ስታስብ፣ቀጣዩን እርምጃህን ታውቀዋለህ። 4. "የሌሎች ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አስተያየት ያንተ ጉዳይ አይደለም።" ስለ አንተ ያላቸው ሀሳብ የሚኖረው በነሱ አይምሮ ውስጥ ነው፤ ባንተ ውስጥ አይደለም። ልትቆጣጠራቸውም ሆነ ልትቀይራቸው አትችልም። ህይወትህን የሚቀርጸው ብቸኛው አስተያየት ያንተ የራስህ ብቻ ነው። 5. "የምትሆነው በተደጋጋሚ የምትናገረውን ሳይሆን በተደጋጋሚ የምታደርገውን ነው።" ይህ አረፍተ ነገር በሀሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ይደፍናል።ልማዶችህ በተግባር የሚታዩ ማንነቶችህ ናቸው። ማንነትህ የሚወሰነው በግብህ ሳይሆን በየዕለት ውሳኔዎችህ ነው። 6. "ለመግባት የምትፈራው ዋሻ የምትፈልገውን ሀብት ይዟል።" የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው የምትሸሸው ነገር ማዶ ላይ ነው። ያ አስቸጋሪ ውይይት። ያ አስፈሪ እድል። ያ ምቾት የማይሰጥ እድገት። ትልቁ ስኬትህ ከትልቁ ፍርሃትህ ጀርባ ተደብቋል። 7. "ካሳመመህ አካባቢ ሆነህ ልትድን አትችልም።" አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ያለው አንተ ጋር አይደለም፤ ካለህበት ቦታ ሊሆን ይችላል።መርዛማ ግንኙነቶች፣ አሉታዊ አካባቢዎች እና መጥፎ ልማዶች አንተ ስለፈለግክ ብቻ አይለወጡም።አንዳንድ ጊዜ ለማደግ ቦታ መልቀቅም ጥሩ አማራጭ ይሆናል። 8. "ለመጀመሪያው ሀሳብህ ተጠያቂ አይደለህም፤ ለሁለተኛው ሀሳብህና ለመጀመሪያው ተግባርህ ግን ተጠያቂ ነህ።" በድንገት የሚመጣው ሀሳብህ ካለፈው ልምድህ የሚመነጭ ነው። ምላሽህ ግን ከምርጫህ የሚመጣ ነው።ወደ አእምሮህ ብልጭ የሚለውን ነገር መቆጣጠር አትችልም፤ ነገር ግን በዛ ሀሳብ ምን እንደምታደርግበት መቆጣጠር ትችላለህ። 9. "የምትፈልገው ነገር ሁሉ ያለው ከጽናት ማዶ ነው።" ተሰጥኦ አይደለም። እድል አይደለም። ትውውቅም አይደለም። ጽናት ነው። በየቀኑ የሚደጋገሙ ትናንሽ ድርጊቶች ተጠራቅመው አስደናቂ ውጤቶችን ይፈጥራሉ። አብዛኛው ሰው ከስኬቱ አፍ ላይ ሆኖ ያቆማል። "book 🌎 #ኢትዮጵያዊነት# @psychoet
Open in TelegramForwarded from Safe Light Initiatives
🚨 HAPPENING TODAY 🚨 We are continuing our Executive Leadership Masterclass with a session on psychology and the psychology of leadership. Today's session will be led by Mr. Nahusenai Tsedalu (PhD), Author, Psychologist, and Trainer, Founder and General Manager of Warka Link Trading and Nova Training Center. We will explore human behavior and ways of thinking, and reflect on the core qualities that help leaders connect with others and communicate their vision clearly. Leadership is driven by psychology, and the study of leadership draws on psychological theories that help us understand what makes an effective leader. If you are ready to become a leader who understands human behavior and thinking patterns and can inspire and motivate teams while driving organizational success, Register now for Cohort 12 using the link below 👇 📲 Call: 0923627762 🔗 https://shorturl.at/GmSfi #psychology #psychologyofleadership #ExecutiveMasterclass @SafeLightOfficial
Open in TelegramConnections
Similar channels
Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠@melkam_enasebPsychology7.49K- ትዳር እና ጥበባዊ ቃላቶች@tdarenatbebawikalatochPsychology1.78K
ሳይኮሎጂ | Psychology@psychologycentralPsychology59.7K
የስብዕና ልህቀት@enlighten_ethiopiaPsychology59.8K
Daniel Wodajo@daniel_wodajoPsychology74.6K
Dr. Eyob Mamo@dreyobPsychology79K
TOLY CREATIVE@tolycreative2Psychology1.07K
Карл Юнг. Лайфстайл@jung_lifePsychology9.44K