Account

Posts of ✍✍ عمر الشاعر ✍✍

newest first

#1090Text

Forwarded from አል ኢፋዳ ለዘመድ ለባዳ

ታላቅ ብስራት ለሙስሊሙ ማህበረሠብ፣ ለየት ባለ መልኩ ለሱኒዮችና ሱና ወዳጆች በሙሉ إعلان هام وبشرى سارة لجميع أهل السنة في أرض الهجرتين بلاد الحبشة. ✍ ታላቅ የኢጅትማዕ ጥሪ‼️ በእለተ እሁድ ታህሳስ 4/4/2019 ⭕️👉አጓጊውና ሁሌም በናፍቆት የሚጠበቀው ታላቁ የኢጅትማዕ ፕሮግራም በአይነቱ ልዩ በሆነ መልኩ በሌራ ከተማ ምዕራብ አዘርነት ሼይኽ አቡ ዐብደላህ ሙሰፋ ቢን ፋሪስ አል- ጀበሊ የሚቆሙበት የሆነው ታላቁ መርከዝ አል-ነጃሺ በታላቅ ዝግጅትና ላቅ ባለ ድምቀት ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። ተጋባዥ እንግዶች፦ _ ታላላቅ ክቡራን መሻይኾች፣ _ ተናፋቂ ኡዝታዞችና ወደኸይር የሚጣሩ ዱዓቶች _ ታዋቂ ገጣሚዎች፣ _ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የክብር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአላህ ፍቃድ ይታደሙበታል ። #ሌራ በክቡር እንግዶችዋ ትሆናለች #ሌላ ☞ ሌራ  በአህለ ሱና  ዳዕዋ ትደምቃለች ። سيكون بإذن الله تعالى اجتماع كبير لجميع أهل السنة والجماعة في بلاد الحبشة بتأريخ الحبشة 4/4/2019 الموافق إن شاء الله رجب 3/ 7 / 1448 ه.   ይህንን ጥሪ የሰማችሁ ሁሉ ላልሰሙት በማሰማት የአጅሩ ተቋዳሽ እንድትሆኑ ጥሪያችን ነዉ። 👉🏼ቦታ፦ ሌራ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ በምዕራብ ካፌ መግቢያ 150 ገባ ብሎ ይገኛል። 👈🏼فاحرصوا على الحضور ودلوا غيركم فالدال على الخير كفاعله. https://t.me/Efadalezd_lebada/10158

Open in Telegram
Views140−91%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1087Text

Forwarded from የኡስታዝ አቡ ዐብዱልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ ቻናል

👌ለሙስሊም እህቶቻችን ከልብ የተሰጠ ምክር! 💢 ሴት ልጅ በእሷና በጌታዋ መካከል ያለውን ግንኙነት ካስተካከለች፣ አላህም በእሷና በባሏ እንዲሁም በልጆቿ መካከል ያለውን ግንኙነት ያስተካክልላታል። በዚህም መልካምና ሳሊሕ ትውልድን ታፈራለች፤ ቤቷንና ዲኗንም ትጠብቃለች። 📲 ነገር ግን በስልክ ሱስ ከተጠመደች፣ በፊልሞችና በተከታታይ ድራማዎች ውስጥ ከተዘፈቀች፣ በቲክቶክ በፌስቡክና በሌሎች ማኅበራዊ ድህረ ገፆች መካከል ያለምንም ፋይዳ ከተንከራተተች፣ ገበያዎችንና ከሌሎች ሴቶች ጋር ጥቅም አልባ ስብሰባዎችንም ከለመደች፤ ታዲያ እንዴት ሳሊሕ ትውልድን ልታሳድግ ትችላለች?! 🤳 በዝንጉ ሴት እጅ ያለ ሞባይል ስልክ እንደ ተመረዘ ቀስት ነው። ሐያዋን ይሰርቃል፣ ጊዜዋን ያባክናል፣ ልቧንም ያበላሻል፣ እሷም ሳታውቅ ቤቷን ታፈርሳለች። ስንት ቤቶች በሞባይል ስልክ ምክንያት ፈረሱ! ስንት ክብረ ንጽሕናዎች በምናባዊ ፍላጎቶችና ቅዠቶች ተደፈሩ! ስንት ቤተሰቦችስ በስልክ ሱስና በቸልተኝነት ምክንያት ተበተኑ! አንቺ አናት ሆይ! እወቂ አንቺ ማለት የኡማው መድረሳ ነሽ! ያለሽን አቅም በልጆችሽ ላይ አውይው! 👇እስኪ መለስ ብለሽ አስታውሺ👇 📌 በከፍተኛ ህመም ውስጥ የእርግዝናን ውጣ ውረድ አልፈሽ 📌 በከባድ ስቃይ አምጠሽ ወይም አራስሽን አሳልፈሽ በመስጠት በኦፕራሲዮን ተቀድደሽ የወለድሻቸው ልጆችሽ ባንቺ ቸላተኝነት የመጣ ሲበላሹ አያሳዝኑሽም ነገስ አይቆጭሽም እባክሽ ቆም በይና ያለፈው ስህተቴ ይብቃ ብለሽ አስተውለሽ የተበላሸውን አርመሽ የወደፊቱን አስተካክዪ! ምክሬ ነው ማሳሰቢያ፦ ስልክ በራሱ ክፉ አይደለም፤ አጠቃቀሙ ነው መልካም ወይም ጎጂ የሚያደርገው። በተጨማሪም ይህ ምክር ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም የሚያገለግል ነው። 🫵 እባካቹ ሁላችንም ወደአላህ እንመለስ ለወንጀላችን ምህረትን እንለምን በቁርኣንና በዚክር ቢዚ እንሁን ዲናችንን እንማር ጥሩ ጓደኛ እንምረጥ ለልጆቻችን ትኩረት እንስጥ❗️ 🤳መልእክቱን ያሰራጩ፤ ምንዳን ያገኛሉ፤ በመልካምም ይታወሳሉ። ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2355

Open in Telegram
Views623−59%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1084Video
Views569−62%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#1083Photo

Forwarded from 🕋 ኢቅራእ የኡምራ ትራቭል ኤጀንሲ 🕋

✅✅  ኡምራ በ130ሺ ብር ብቻ ✅✅ 🕋 በተከበረው የረጀብ ወር ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ለመጓዝ ብልሆች ለእነሱ የሚሆን እድል ሲዘጋጅ እድሉን ለመጠቀም ለአፍታም አያመነቱም ። እነሆ የእናንተው ተወዳጁ ኢቅራእ ትራቭል ✅   ከታህሳስ 1__11 ✅ Dec 10__Dec 20 🌕 የመዲና ሆቴል መርከዚያ ውስጥ 🌕 የሀረም ሆቴል አብራጀል ኪስዋ ኢቅራእ ትራቭል ለሀረም ናፋቂ ልቦች ልዩ የሆነ እድል ተመቻችቷል እድሉን ተጠቀሙ እያለዎት ነው ። 👉በ 130ሺ ብር ብቻ ለተወሰኑ ቀናት ብቻ የሚቆይ እድል ነው ይህ ደግሞ ለእርስዎ ነው 🌕 አላህ በሰጠህ ጊዜ ተጠቅመህ የእድሜ ልክ ደስታና አይረሴ የሆኑ የትውስታ ጊዜዎችን ለተከታታይ አስር ቀናት አብረውን ያሳልፉ ዘንድ ለእርስዎና ለወዳጆችዎ  በመዲናና በመስጂደል ሀራም ሁለት ጁመዐዎችን የሚያገኙበትን እድል ከኢቅራእ ትራቭል ልዩ የሆነ  የኡምራ ፓኬጅ 👉በመደበኛ 👉 በኖርማለ 👉 በቪ አይፒ   ተዘጋጅቷል ። ✅ በሸሪዐ አዳብና በነቢያዊ ሱና አስተምህሮ መሰረት የሚገባዎትን መስተንግዶ ከኢቅራእ ትራቭል ያግኙ ። 🌕 ኢቅራእ ትራቭል የሀረም እንግዶች ምርጫ !!     0911243212 _0911683917 🔶 አድራሻ ቤተል ከተቅዋ መስጂድ አጠገብ ሒጅራ ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፍቅ ቢሮ ቁ.01 =======-----------========== https://t.me/iQRA_TOUR_AND_TRAVEL

Open in Telegram
Views569−62%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1082Text
Views1,370−9%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1081Audio
Views342−77%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1078Text

የድል መሠረት ነው                ይግባህ አንድነት የውድቀት መንገድ ነው                     አጥፋ ልዩነት የሌላን ሠው ስራ            ማዳከም መጥላት አይሆንህም ላንተ                የስኬት ውጤት የሌላን ሠው መርከዝ                     መናቅ ማንቋሸሽ ውብ አያደርገውም                        ስራህን አትዋሽ  በደንብ መረዳት              ያለብን መገንዘብ የሚያስፈልገን ሰው                  ለእኛ እንደ ምግብ በእውቀት ተክኖ                 በኢኽላስ በጥበብ የሚሠራ ሠው ነው                  ላሏህ ብሎ ከልብ ተማምኖ ተባብሮ                  ተጋግዞ በጋራ እንዲስፋፋ ዳዕዋ            ለትውልድ እንስራ ምቀኝነት ካለ             ሀሜት ጥርጣሬ የግል ስሜትን            ካስቀደምን ወሬ እንዳንሆን ፍሩ           ዛፍ ያላንድ  ፍሬ ወንድምህ ሲሳሳት            ካየኸው ሲያጠፋ ምከረው በጥበብ                ልቡን ሳታስከፋ ሠለፍይ ወንድምህ        ጉልበትህ ነው ጡንቻ ናቅ አርገህ አትየው         አታብቅል ጥላቻ የዛሬ አንድ ነት ነው            የዜሬው መዋደድ ታሪክ የሚሰራው          ለተተኪው ትውልድ በጃችን አንቆፍር          የውድቀትን ጉድጓድ     عمر الشاعر የአቡ አበደልመናንን ስድ ፁሁፍ በግጥም https://t.me/oumershaer/1078

Open in Telegram
Views1,680+12%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1076Text

Forwarded from የኡስታዝ አቡ ዐብዱልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ ቻናል

🍃 አንድነት የድል መሠረት፣ መከፋፈል የውድቀት መንገድ ነው! ወንድሞቼ! የሌላውን ስራ ማዳከም በኛ ስራና ልፋት ላይ ስኬትን አያመጣም። የሌላውን መርከዝ መውደቅ መመኘት የእኛን መርከዝ አያሳድግም። የሌላውን መልካም ሥራ ማንቋሸሽ የእኛን መልካም ሥራ አያስውብም። በደንብ መገንዘብ የሚገባን በዚህ ዘመን ከምንፈልገው በላይ የሚያስፈልገን ብዙ የሚናገሩ ሰዎች ሳይሆኑ፣ በእውቀት፣ በጥበብ፣ በትዕግሥትና በኢኽላስ የሚሠሩ ሰዎች ናቸው። እርስ በርሳችን ስንተማመን፣ ስንተባበርና የሌላውን ጥረት ስናበረታታ የዳዕዋ ሥራ ይሰፋል፤ የእውቀት ብርሃን ይስፋፋል፤ ትውልድም ይጠቀማል። ነገር ግን በምቀኝነት፣ በጥርጣሬ፣ በቂም፣ በሐሜት፣ በግል ጥቅምና ስሜት በየግል ቡድን አስተሳሰብ ከተጠመድን የምንገነባውን በራሳችን እጅ እናፈርሳለን። ስለዚህ፦ - የሌላውን መልካም ሥራ አበረታቱ። - የሌላውን ስኬት በደስታ ተቀበሉ። - በሚያስፈልግበት ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተረዳዱ። - አንድ ወንድም ስህተት ሲታይበት በጥበብና በእውነተኛ ምክር አስተካክሉ። - ከግል ስሜትና ከዓለማዊ ጥቅም በላይ የዲንን ጥቅም አስቀድሙ። 👌ታሪክ ትምህርት ሰጪ ነውና የአንደሉስ ታሪክ እንዳንዘነጋው ይህ ታሪክ ሲታወስ ልብን ከማድማቱ ጋር ከሚያስገነዝበን ትልቅ ትምህርት ውስጥ ከላይ አንድነት እንዳለው እያመሳሰለ በውስጥ የተለያየ ልብ ያለው ማኅበረሰብ ከውጭ ሀይሎች የሚመጣበትን ፈተና ለመቋቋም ይቸገራል። የታሪክ ሙሁራን በድርሳናቸው እንዳስቀመጡት በአንዳሉስ የነበሩትን ሙስሊሞች ሊወጋቸው የመጣ ጠላት ሁሉ ድል እየናፈቀው ተሸንፎና ውርደትን ተከናንቦ ይመለስ ነበር። ነገር ግን የውድቀታቸውና የመዳከማቸው ዋና ምክንያት በመካከላቸው የነበረው የቅናትና የምቀኝነት መበራከት፣ ከመጠን ያለፈ አለመግባባት፣ቅጥ ያጣ መጠላላትና ፍትሐዊነትን ማጣት ነበር። አዎን እራሳችንን እንመርምር ልባችንን ከተጠቀሱት መርዛማ በሽታዎች እናፅዳ ከተባበርን፣ ከተናበብን ፣ከተከባበርና ከተዋደድን ተያይዘን እናድጋለን ዳዕዋው ይለመልማል ስኬታማም እንሆናለን ነገር ግን በትንሹም በትልቁም ከተናቆርን ከተናናቅን ከተቀናናንና ከተጠላላን እመኑኝ ተያይዘን እንወድቃለን ማንኛችንም ብቻውን ቀና ሊል አይቻለውም የጠላትም መሳቂያ እንሆናለን ሰለፍይ ወንድምህ ጡንቻህ ነው ረዳትህ ነው አሳንሰህ አትየው ወደድክም ጠላህም እገዛው ያስፈልግሀል ረዥሙን የዳዕዋ ጉዞ ብቻዬን እወጣዋለው ብለህ እንዳትሸወድ 👉 የዛሬ የትብብር ሥራችን የነገው ትውልድ ታሪክ ነው። እንገንባ እንጂ አናፍርስ፤ እናስታርቅ እንጂ አናጣላ፤ እንተባበር እንጂ አንከፋፈል። والسلام ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2321

Open in Telegram
Views614−59%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1074Text

ወንድም ለወንድሙ ጋሻ ነው መከታ ጠላት ይመክታል እንኳንስ አርማታ ያንድነትን ውጤት ተመልከት ሲያፈራ የማይታሰብ ነው በሁለት ቀን ስራ ሁሉም ወንድምህ ነው ከሁሉም ተግባባ ብርታተት የሚሆነን ፍቅር ነው መሀባ በንፁህ ልቦና ተዛድ በሱና ዘር ቀለም ሳትለይ በውቡ እስልምና ይቺን አጭር ሂዎት ይቺን አጭር ጊዜ ተዋዶ ማለፍ ነው እንደጫጉላሚዜ ኡስታዝ አቡየህያ ኤሊያስ ገራድ ለጉሮሮው አፍያ ይስጥልን ሶመድ ተካፍሏል ቢሆንም በሳይለንት ሙድ የዛሬው ዚያራ በኛ አይቆጠርም እንደገና ናልን ጨምረህ ቮሉዩም ይደክማል ለሱና ባለው ሙሉአቅም ይክፍላል መስዋትታሞኳን አይተኛም አሏህ ነው የቸረው ይቀበለው ከሪም ከተማ አይልገጠር ይጓዛል በታክሲ ትራንስፖርእንጂ መችገራለት ሀይሲ አሸይኽ አብደልመናን ወዚሩ ሀሊድ አንደበተሩቱዕ ትግስቱ አይናድ አለን በሳል ወንድም በፈላህ መስጂድ ኡስታዝ አቡ አማር የፉርቃኑ ጀግና እየታገለነው የበኩሉን ሚና አረሳሁዎትም ሸህ ሙሴ ተራራ አሏህ ይሹመዎት አርጎ ሙፍቲሌራ የማይደክም ሸህነው ሌትተቀን ቢያቀራ አሏህ ይክፈትልህ በዱንያም ባኺራ ማነው አቡሰልማን አዲሱ መስዑሉ ስለሱ አላወራም ይበቃዋል አቅሉ ከየት እስከየት ነው ግዛትህ ክልሉ አቡሙሳም አሉ አያውቁም ክልከላ ለሁሉም ክፍት ነው የሸቱ ባቄላ ሁሉንም ዱዓቶች ማንሳት ነበር ቀላል እንዳይረዝምባችሁ ፈርቼ ነው መለል ሸገር ቡታጅራ ከወልቂጤ ሌራ ካዳማ ከሸሞ ወንድም ከሳንኩራ ወራቤ ወላይታ በሱንይ ኩራ ከሁሉም አቅጣጫ መተዋል ሊያግዙ በነሻጥ በወኔ ደቂቃ ማይፈዙ ምንዳችሁን አሏህ ይፃፈው አዚዙ ያንድነት መሰረት ያንድነት ወጋግራ ለአሏህ መዋደድ ነው ብሎ ለአኺራ እንደ መርከዛችን መሀባን እንገንባ በአርሽ ጥላስር ጀነት እንድን ገባ በስተመጨረሻም ኺታም ለኡስታዜ የልብህ ተሳክቷል በወንድሞች ጊዜ አልሀምዱ ሊላህበል ሄደኮ ትካዜ አሏህ ሲያገራልህ የፈጠረህ ኻሊቅ ወደፊት እያየህ ካለ መጨናነቅ ለመርከዙ አንድ ፎቅ ለቤትም አንድ ፌቅ መጨመሩ አይቀርም ካለ ያሏህ ተውፊቅ ኒያው እንደ ሠማይ ወኔው እንዳንበሳ ሲጋብዝ አያስብ ሲሰጥ የማይሳሳ የሙዘሚል ልጅ ነው አያቱ ሸህሙሳ የመርከዝህን ሀቅ ጠብቅ እንዳትረሳ      عمر الشاعر https://t.me/oumershaer/1074

Open in Telegram
Views8,000+432%vs avg
Forwards—
Reactions21
Comments—
#1073Text

Forwarded from قناة الشيخ سلمان بن صالح العماد

# حاجة أهل اليمن إلى التفاؤل الحسن إنَّ من أعظم المصائب أن يُهزم الإنسان في نفسه قبل أن يُهزم في واقعه، وأن يستولي اليأس على قلبه حتى يرى الباطل قدرًا لا يُدفع، والظلمَ سلطانًا لا يزول! وإنَّ مما ابتُلي به كثيرٌ من أهل اليمن، مع طول أمد المحنة، واشتداد وطأة الظلم، وتسلُّط جماعة الحوثي المارقة وتمددها، أن تسلَّل اليأس إلى بعض النفوس، حتى كاد بعضهم يظن أن ليل هذه الفتنة لا فجر له، وأن سلطان الظالمين لا نهاية له! وهذا من ضعف النظر في سنن الله، وقصور التأمل في عواقب التاريخ؛ فكم من قوةٍ ظنَّ أصحابها أنها لا تُقهر، فإذا بها أثرٌ بعد عين! وكم من سلطانٍ أحكم الظالمون بناءه، فهدمته سنن الله من حيث لم يحتسبوا! قال تعالى: ﴿وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنْتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ﴾ [آل عمران: ١٣٩]. أيها اليمنيون الصابرون : إنَّ تمدُّد الباطل لا يعني خلوده، وتأخُّر الفرج لا يعني امتناعه، وإمهال الظالم لا يعني إهماله؛ فالله سبحانه يُملي ولا يُهمل، ويبتلي ولا ينسى، ويُديل الأيام بين عباده لحِكَمٍ بالغة. قال تعالى: ﴿وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسِ﴾ [آل عمران: ١٤٠]. فلا تجعلوا من طول المحنة دليلًا على دوامها، ولا من شدة البلاء برهانًا على استحالة زواله؛ فإنَّ لله في خلقه سننًا لا تتبدل، وإنَّ للعاقبة أهلًا لا تخطئهم إذا حققوا أسبابها. قال سبحانه: ﴿وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَى﴾ [طه: ١٣٢]. غير أن التفاؤل المحمود ليس أمانيَّ تُخدِّر العزائم، ولا أحلامًا تُعطِّل الأسباب؛ وإنما هو يقينٌ بوعد الله، يبعث على إصلاح النفوس، وتوحيد الصفوف، وجمع الكلمة، وإقامة العدل، والصبر والثبات، والتعاون على البر والتقوى. فأحسنوا الظنَّ بربكم، ولا تُسيئوا الظنَّ بمستقبل بلادكم، ولا تجعلوا من واقع اليوم حكمًا نهائيًّا على الغد؛ فما بين ظلمة الليل وإشراقة الفجر إلا أجلٌ قدَّره الله. وإنَّ يمننا الذي أنهكته الفتن، وأثقلته الجراح، وأضناه طول الانتظار، لجديرٌ بأبنائه أن يجمعوا كلمتهم، ويصلحوا ذات بينهم، ويستمسكوا بدينهم، ويأخذوا بأسباب النجاة؛ فإنَّ الأمم لا تنهض باليأس، ولا تُستردُّ الحقوق بالتفرُّق، ولا تُبنى الأوطان بالأحقاد. وختامًا: قد يطول ليل الظلم، ولكنه لا يملك أن يُطفئ شمس الحق، وقد تعلو راية الباطل حينًا، ولكن علوَّها ليس دليلًا على صحة طريقها ولا ضمانًا لبقائها. فيا أهلنا وإخواننا ، لا تيأسوا من روح الله، ولا تقنطوا من رحمته، وأصلحوا ما بينكم وبين ربكم، وما بينكم وبين إخوانكم؛ فإنَّ وعد الله حق، والعاقبة للتقوى، والله غالبٌ على أمره ولكن أكثر الناس لا يعلمون. أبو سليمان سلمان بن صالح العماد الجمعة: 19/ جمادى الأولى/ 1448

Open in Telegram
Views746−50%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1072Audio
Views630−58%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#1068Text

የስላቭ ሙሊት ድግስ አዋጅ ስሙ ይድረስ ጋብዟችኋል ኡስታዝ ቂልጦ ሱና መርከዝ ሾፌር ንዳው ቆስቁስ መርከዝ ቶሎ ድረስ ስንት ሰው ለባጢል ስንት ሀገር ይጓዛል ንብረቱን ጉልበቱን        ሳይሰስት ያፈሳል አንተ ግን ላሏህ ነው               ጀነትን ፍለጋ ቶሎ ፈጥነህ ድረስ             ነፍስያን ተዋጋ ለልጆቻችን ነው             ያውም ለአኺራ የየድርሻችንን            እንጣል አሻራ ተዘጋጅ በወኔ      ኒያህንም ጥመድ ሶስት አራት ቀን ነው                ብናደርግ ጅሀድ በሰይፍ እንዳይመስልህ                     ባካፋነው  መናድ ሲሚንቶናአሻዋን          ቀላቅለህ በጠጠር አይዞህ ወንድሜ      ማቡካት ነው በሚክሰር ተሸክሞ ላይታች አታስብ አለን ዊንች በሀይላችን ሳይሆን ባሏህ እንመካ በቁጥራችን ሳይሆን በአሏህ በረካ አብሽሩ እናያለን ህልማችን ሲሳካ እደጊ እንዳትቆሚ በዒልም ለምልሚ ያበባሽ መዓዛ የፍሬሽ በረካ ለጠላት ይድረሰው አውሮፓ አሜሪካ ሁሌም አሏህ ያርግሽ የኸይር ፋብሪካ ሱና መርከዛችን ፏበይ እንደ መካ عمر الشاعر https://t.me/oumershaer/1068

Open in Telegram
Views878−42%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—