Forwarded from тнσυgнт°ραι𝔫тιиg 🎞️
ጀግና ከሆንክ ምን ይላል መሰላችሁ ቅዱስ ዩሃንስ አፈወርቅ "ጀግና ከሆንህ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት" መቆጣት ከፈለክ መጀመርያ በራስህ ላይ ተቆጣ!። ልክስክስነትህን፣ ስግብግብነትህን፣ ክፋትህን፣ ዝርክርክነትህን፣ ዘማዊነትህን ተቆጣው!። ስንፍንሃን ተቆጣው!። በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት። ከዘላለም እርስትህ ለነጠቀ፤ ከልጅነትህ ለሚያዋርድህ፤ ከፈጣሪህ ለሚያጣላህ፤ እግዚአብሔርን ያህል አባት፣ ገነትህን ያህል ቦታ፣ ልጅነትህን ያህል ተድላ ደስታ ከነጠቀህና ከክብርህ ካዋረደ በሱ ላይ መጀመርያ ተነስ!። እውነቴን ልንገራችሁ ሰው መጀመርያ ከእራሱ እና ከዲያብሎስ ጋር ጦርነት ከገጠመ በአለም ላይ ያሉ ጦርነቶች ሁሉ ይጠፋሉ.. ፦አባ ገ/ኪዳን
Open in Telegram