Forwarded from ዘ ተ ሐ ር ያ ን 🧘🏻♂️
ራሳችሁን ለራሳችሁ አስመስክሩ! ራሳችሁን ለሌሎች ሰዎች ለማስመስከር የምትታገሉትን ትግል አቁሙና ራሳችሁን ለራሳችሁ አስመስክሩ፡፡ ራስን በራስ ማስመስከር ማለት ባጭሩ ካወጣነው ጤናማ የሕይወት ከፍታና የኑሮ ሁኔታ አንጻር ለመኖር ከራስ ጋር በመስማማት የምንችለውን ማድረግ ማለት ነው፡፡ የዚህ ተቃራኒ ራስን ለሌላ ሰው የማስመስከር ጡዘት የእኛን ስኬታማነት ለሰዎቹ እይታ፣ ባህሪይና ማንነት አሳልፈን በመስጠት ዳኞቹ እነሱና እነሱ ብቻ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ሩጫችንን ካልተቀበሉት የበለጠ እንሮጣለን፣ ሁኔታችን ካልጣማቸው ሌላ ሁኔታ ለመፍጠር እንታገላለን፡፡ • ምን ያህል እንደምታውቁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና በተሰማራችሁበት ዘርፍ አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል እውቀትን አዳብሩ፡፡ • ምን ያህል ጨዋ እንደሆናችሁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና ማዳበር የሚገባችሁን ጨዋ ባህሪይ በመለየት ያንን ጨዋነት አዳብሩ፡፡ • ምን ያህል ገንዘብና ሃብት እንዳላችሁ ለሌላ ሰው ለማስመስከር መታገል አቁሙና ላወጣችሁት የሕይወት ደረጃና ለምትከተሉት ዓላማ የሚመጥን የገንዘብ አቅም ላይ የመድረስን ትጋት አዳብሩ፡፡ • ምን ያህል አሪፍ የፍቅር አጋር እንደሆናችሁ ለፍቅረናችሁ ለማስመስከር መታገል አቁሙና ከአንድ እውነተኛ ፍቅረኛ የሚጠበቀው ባህሪይና ማንነት ምን እንደሆነ በመለየት ያንን አዳብሩ፡፡ ራሳችሁን ለማስመስከር የምትታገሉት ትግል የማያዛልቃችሁ፣ ስለሆናችሁትና አለኝ ስለምትሉት ነገር እንዲያዩላችሁ የምትፈልጓቸው ሰዎች መስፈርት እንደየግል እይታቸውና ባህሪያቸው የተለያየ ስለሆነ ምንም ያህል ብትታገሉም ከቁጥርም ላይከቱት ስለሚችሉ ነው፡፡ ይህ ጉዞ የማያልቅና አድካሚ ጉዞ ነው፡፡ Dr. Eyob Mamo
Open in Telegram




