እቴ —— ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤ ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤ ... እቴ ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ። እቴ እጄን ብትፈልጊ እግሬን ብትፈልጊ አንገቴን ደረቴን ተሰጥኦ ሀሳቤን ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ ያስቀርልኝ ዓይኔን አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን። 🤗 -——————————————— ✍ በእውቀቱ ስዩም እንደጻፈው እነሆ እስኪ ፈገግም በሉ ወገን፤ ሠናይ ሰሞን 😊
Open in TelegramPosts of ንስር ሕክምና
Forwarded from የጤና ወግ - የጤና መረጃ
👶 የጨቅላ ሕፃናት አደገኛ ምልክቶች ✅የጨቅላ ሕፃናት ጤና በተለይም በመጀመሪያዎቹ 28 ቀናት ከፍተኛ ትኩረት ይፈልጋል። አደገኛ ምልክቶችን በጊዜ ማወቅ እና ፈጣን የሕክምና እርዳታ መፈለግ ሕይወትን ሊያድን ይችላል። 🚨ከተጠቀሱት አደገኛ ምልክቶች አንዱን እንኳን በጨቅላ ሕፃንዎ ላይ ካስተዋሉ፣ ሳይዘገዩ ወደ ቅርብ ጤና ጣቢያ ወይም ሆስፒታል ይውሰዱ። ምልክቱ በራሱ ይጠፋል ብለው አይጠብቁ፤ የቤት ውስጥ ሕክምናንም ተጠቅመው አስፈላጊ ህክምናን አያዘግዩ። ✅የጨቅላ ሕፃናትን አደገኛ ምልክቶች፣ መቼ እርዳታ መፈለግ እንዳለብዎ እና ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚያብራራውን ይህን ተግባራዊ የጤና መረጃ ያንብቡ፣ ያጋሩ እና ለሌሎች ወላጆችም ያድርሱ። ምልክቶቹን ይወቁ። በጊዜ እርምጃ ይውሰዱ።
Open in TelegramForwarded from የጤና ወግ - የጤና መረጃ
👁 ግላኮማ (Glaucoma) – ዝምተኛው የእይታ ሌባ! ግላኮማ የዓይን ነርቭን በመጉዳት ቀስ በቀስ የእይታ አድማስን የሚያጠብ እና በመጨረሻም የዓይን ብርሃንን ሊያጠፋ የሚችል በሽታ ነው። ብዙ ጊዜ ግልጽ ምልክት ሳያሳይ ስለሚያድግ፣ ቀድሞ መመርመር እጅግ አስፈላጊ ነው። 🔎 ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች፣ በቤተሰብ ውስጥ የግላኮማ ታሪክ ያላቸው እና ሌሎች ተጋላጭነቶች ያሉባቸው ሰዎች መደበኛ የዓይን ምርመራ ማድረግ ይገባቸዋል። 🚨 አስቸኳይ ማሳሰቢያ፦ ድንገተኛ ከባድ የዓይን ሕመም፣ የራስ ምታት፣ የዓይን መቅላት ወይም የዕይታ መደብዘዝ ካጋጠመዎት፣ ወዲያውኑ ወደ ቅርብ ሆስፒታል ወይም የዓይን ሕክምና ማዕከል ይሂዱ። አይኖችዎን ይጠብቁ፤ በጊዜ ይመርመሩ፤ የታዘዘልዎትን ሕክምና ሳያቋርጡ ይከታተሉ! ይህንን ጠቃሚ የጤና መረጃ ያንብቡ፣ ያጋሩ እና ለሌሎችም ያድርሱ።
Open in Telegram#ሕይወትን_በሕክምና_ቁጥሮች 🧬 ሕይወት በየዕለቱ ስትከብደን እና አቤቱታዎችን ስናበዛ፣ ከራሳችን አልፈው ከባድ ፈተናን የሚጋፈጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንም እኛንም ያበረቱናል ፤ ለእነርሱም እናስፈልጋቸዋለንና ይህንን እውነታ መዘንጋት የለብንም፤ እስኪ እንዲህም እናስብ፦ 🎗️ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች አዲስ ካንሰር እንዳለባቸው ታውቆ ከበሽታው ጋር ከፍተኛ የሕክምና ትግል ላይ ናቸው፤ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትም በተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች አሊያም በጽኑ ሕክምና ክፍል ሕመምን በመቋቋም በጀግንነት በመታገል እያሸነፉ ይገኛሉ እና ብርታትን ተስፋ መሰነቅን ከእነርሱ በላይ ማንም ሊያስተምረን የሚችል የለም፤ የእውነተኛውን ጸሎትም ከእምነት ተቋማት ይልቅ በሆስፒታሎች ግድግዳ ወደ አምላክ ይደረሳል። 🌍 ስማኝማ ወዳጄ "እድለ ቢስ ነኝ፣ መጥፎ ዕድል ብቻ ነው የሚያጋጥመኝ ብለህ እስኪ አታማርር ሰምተህ ነውን... የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ እንደሚያሳየው ከ 43 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችንን ፍጹም ስውራን (Blind) የኾኑት በልበ ብርሃንነት ለዓለማችን የሚቻላቸውን ኹሉ እያበረከቱ ነውና ብርታትን ከእርሱ እንማር፤ ቀን መውጣቱንና መጥለቁን በዓይናቸው ማየት የማይችሉበት ቢኾንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ወገኖቻችን ከልቦና ጨለማነት ወጭተው ሕይወትን እየታገሏት ነውና ንሳማ እንበርታ። 🧑 "ዛሬ በጣም ደክሞኛል፣ ነገ እሰራዋለሁ እያልን ጊዜያችን አናባክን... በየቀኑ ከ170,000 በላይ የሚጠጉ ሰዎች በተለያዩ አጣዳፊ የጤና እክሎች (እንደ የልብ ድካም፣ ድንገተኛ ስትሮክ) የሕይወታቸው ሕቅታ ያልፋልና ነገ የሚባል ቀን ለእኛ በእርግጠኝነት አለመሰጠቱን የሕክምናው ዓለም በየዕለቱ ይመሰክራል። 💡 "ሕይወቴ ፈራረሰችብኝ፣ ተበላሸች ብለንም ተስፋ አንቁረጥ አይዞኝ በዓለም ዙሪያ ከ 2 ቢሊዮን በላይ ሰዎች አስተማማኝ የመጠጥ ውኃ አያገኙም፤ በንፁሕ ውኃ እጥረት ምክንያት ብቻ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናትን ለገዳይ ተላላፊ በሽታዎች ተጋልጠው ያሉባት ስራችን ብዙ ሰራተኞቹ ግን ጥቂት የኾንባት ዓለም ውስጥ ነንና እንደገና እንበርታ እስኪ አይዞን ጓድ 📖 "አንድ ትንሽ ነገር ሲጠፋብን ቀኔ ተበላሸ ብለን ለምንስ እንበሳጫለን ከ200 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን እኮ ፍጹም ቤት አልባ (Homeless) በመሆናቸው ከለላ የሌለው የጎዳና ሕይወትን በብርድና በፀሐይ የሚሰቃይ ሕይወትን እየገፉ ነውና በል እንበርታና ለእነርሱም መከታ የምንኾንበት ጊዜ ይመጣልና። 🧠 በሥነ-ልቦና ሕክምና ውስጥ አመስጋኝነት (Gratitude) የአእምሮን የቅመሞች ኬሚስትሪ በማጣጣም ጭንቀትን (Stress) የሚቀንስ ወሳኝ ሕክምና ነውና በል እንበርታ ወንድምሰው ፤ ነገ የተሻለ ይኾናልና። 🤲 ያለንበትን ጤና፣ እስትንፋስ እና ዕድል ሁልጊዜም ማስታወስ ከየትኛውም መድኃኒት በላይ ለነፍስ ፈውስ ነውና አይዞኝ... መልካም የጤና፣ የደስታ እና የሰላም ውሎ መግባት ይኹንልን! ❤️ @NisirHikimna
Open in Telegram#ነፃ_ሕክምና 🔹🔹🔹🔹🔹 ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ CSI (Children's Surgery International) ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካ ሀገር በሚመጡ ስፔሻሊስትና ሰብስፔሻሊስት ሀኪሞች ከጥቅምት 29/2019 እስከ ህዳር 04/2019 ዓ.ም Ø በአፈጣጠር ወይም በአደጋ ምክንያት ለተከሰተ የጆሮ ቅርፅ ችግር Ø የከንፈርና የላንቃ ክፍተት (መሰንጠቅ) ችግር Ø በተፈጥሮ ወይም በአደጋ ምክንያት የአፍንጫ መጣም Ø የአንገትና ፊት አካባቢ እብጠት፣ መጣመም ወይም ጠባሳና መሰል ችግር Ø ላለባቸው ታካሚዎች የነፃ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል። በመሆኑም ችግሩ ያለባችሁ ወገኖች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እያልን በ29/02/2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:00 በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንድትገኙ እናሳስባለን። ቀድሞ ወረፋ ለመያዝ በጥበበ ግዮን ስፔሻላንዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 65 ዘወትር በስራ ሰዓት መመዝገብ ይችላሉ። © ባዳዩ- ጥበበ ግዮን ሆስፒታል
Open in TelegramForwarded from ንስር ሕክምና
ጠቅላላ ማውጫ (መድብል) ከዚህ በፊት ንስር ሕክምና ቻናል ላይ ተብራርተው የተቀመጡ ጽሑፎችን በቅደም ተከተል በቀጣዮቹ ማስፈንጠሪያዎች (links) በቀላሉ ማግኜት ትችላላችሁ። ቅጽ-፩ 👇 https://t.me/nisirhikimna/1149 ቅጽ-፪ 👇 https://t.me/nisirhikimna/1150 ቅጽ-፫ 👇 https://t.me/nisirhikimna/1151 ስለጤናችን እውነታዎችን ይወቁ፤ የሚሹትን ይጠይቁ፤ ለእውቀት ያንብቡ፤ሌሎችም ያስነብቡ! በግል ለማማከር እነሆ ==> @Nisirad ©ንስር ሕክምና - @nisirhikimna
Open in TelegramForwarded from Eagle Medical Care
#BreastcancerAwareness ወርኃ ጥቅም የጡት ካንሰር ግንዛቤ ወር ይባላል እነሆን በጡት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ጉዳዮች ላይ በዘርፉ ማንኛውም ጥያቄዎች ካሉዎ ከፍተኛ አንቱታን ያተረፉትን ዶ/ር አምሳሉ ሞላ (የጡት እና ኢንዶክራይን ቀዶ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪም) በኤግል ሜዲካል ገጽ ላይ ገብተው በግልዎ ሚስጥርዎ በተጠበቀ መልኩ ማማከር ይችላሉ። 👇👇👇 EagleMedicalCare.com/Book
Open in TelegramForwarded from ንስር ሕክምና
መልካም ዜና እነሆን 🎉🎆🎉 ለጤናዎ ቅድሚያ አለንዎ፤ ሐኪሞቻችንም ከእርስዎ ጋር ናቸው! 🩺 ከቤትዎ ሳይወጡ ከሰብ-ስፔሻሊስት፣ ከስፔሻሊስት የየዘርፉ ሐኪሞችዎ ጋር ይማከሩ! በEagle Medical Care የሕክምና ወረፋ እና የጉዞ ድካም ቀርቷል። ለምን Eagle Medical Care? ✅ ፈጣን ተደራሽነት ➻ ጊዜዎን ይቆጥቡ! ✅ አማናዊ ሐኪሞች - የጤና ችግርዎን የሚረዱ ሰርክ ዝግጁ ናቸው! ✅ ምቹ የርቀት አገልግሎት - ከየትኛውም ቦታ ኾነው እነሆ በፈለጉት ጊዜ ያማክሩ! አሁኑኑ ይጎብኟቸው፦ 🌐 www.Eaglemedicalcare.com
Open in TelegramForwarded from Eagle Scholars
ዛሬን በደስታ እንኑር ፤ በስራችን በውሏችን ከጎናችን ያሉትን ሁሉ እንጠያየቅ፤ አይዞህ አይዞሺ እንባባል! 🕊️ ለአእምሯችን እረፍትን ለስራ ባልደረቦቻችንና ጓዶቻችንም ሁሉ ፈገግ ያለን ፊት እንለዋወጥ 😊 ደስ የሚል ቀን ይሁንልን 🌹🤲
Open in TelegramForwarded from Eagle Scholars
#የሊቃውንትጉባኤ የ1927 የሶልቬይ ጉባኤ (Solvay Conference) ፎቶግራፍ በታሪክ ውስጥ «እጅግ በጣም ብልህ ሰዎች የተነሱት ፎቶ» በመባል የሚታወቅ ሲኾን በዚህ ጉባኤ ላይ በወቅቱ የነበሩት የዓለማችን ታላላቅ የፊዚክስ ሊቃውንት ተሰብስበው ስለ ኳንተም ፊዚክስ (Quantum Mechanics) ሕጎች እና ንድፈ-ሐሳቦች በሰፊው ተወያይተዋል፡- 🥇 የኖቤል ተሸላሚዎች፡ በፎቶው ውስጥ ከሚታዩት 29 ሳይንቲስቶች መካከል 17ቱ የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ናቸው (ወይም በኋላ ላይ አሸንፈዋል)። 🧑🔬 አልበርት ኤይንስታይን (Albert Einstein): በፎቶው መሐል አካባቢ የተቀመጠ ሲኾን በወቅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ዝናን ያተረፈ ሳይንቲስት ነበረ። 👨🔬 ማሪ ኪዩሪ (Marie Curie): በስብሰባው ላይ የተገኘችው ብቸኛዋ ሴት ሳይንቲስት ስትኾን፡ በኹለት የተለዩ የሳይንስ ዘርፎች (በፊዚክስ እና በኬሚስትሪ) የኖቤል ሽልማት በማሸነፍ በታሪክ ብቸኛዋ ሰው ናት። 🧑🔬👨🔬 ሌሎች ታዋቂ ሳይንቲስቶች፡ ኒልስ ቦር (Niels Bohr)፣ ቨርነር ሃይዘንበርግ (Werner Heisenberg)፣ ኤርቪን ሽሮዲንገር (Erwin Schrödinger) እና ማክስ ፕላንክ (Max Planck) ይገኙበታል። እውቀት ነጻ ያወጣል! @EagleScholars
Open in Telegram#ከእንጥል_ቆራጭ_ያላስመለጠው_ስብከቴ✍️ ኢንተርን ሳለሁ ... ከዕለታት በአንደኛው ቀን በPediatrics/NICU attachment... 4.2kg ጩጨዋ Neonatal sepsis ታማ admitted ኾነቺና በደንብ ተንከባክበን ድና በቃ ወደቤት ልንልካቸው ይገባል ተብሎ...Our pediatrician "ዶክ በቃ በደንብ ምክር ስጧቸውና ወደቤት discharge ትኹን!" እኔም እንደተባልኩት ያው ያነበብኳትንና የማውቃትን ኹሉ የሳይንስ ስብከቴን ከመጻሕፍት እያጣቀስኩ ነገረኛ ነኝ ይሰሙኝ መስሎኝ 🤭😊 "... ማማዬ እንግዲህ በቃ በደንብ ድናለቺ ወደቤታችሁ ልትሄዱ ነው፤ አስከትቡ፤ ፀሐይ አሙቁ ፤ እስከ6 ወር የጡት ወተት ብቻ መቼም አይጠፋችሁም ኣ ..." ምናምን ብቻ ሌላም ብዙ ብዬ በመጨረሻም "... እንዲያው አደራችሁን እንጥል እንዳታስቆርጡ!" አልኩላችሁና ወደቤት መላክ... ከዚያስ አትሉኝም በበነጋታው ምሽት ላይ ጨቅላዋ እራሷን ስታ ደም በደም ኾና በሚያሳዝን ኹኔታ Duty time እኛው ጋር እንደገና ከቺ 😔... ያው ኹሉም ሰው ተሯሩጠን she had been again readmitted with Aspiration Pneumonia + Hypovolemic shock 2°Acute Blood Loss (Severe Anemia) ብቻ እንደምንም የNICU Team ተረባርቦላት ጨቅላዋ ታከመቺ፥ ደምም ተገኝቶ ተሰጣትና እንደምንም ተረፈቺልንና ወላጆቿ የኾነ ቀን እንዲሁ round ጨርሰን ወደ Motherside ተመልሳ ታቅፋት እያጠባቻት ሲያዩኝ እየተጠቋቆሙ አፍረው ተሸፈኑ... ያው እኔም በኩራት ጀነን ብዬ ነገር ነገር ሊለኝ አፍኜ በውስጤ 🤭 ግን ያው ጩጨዋ በመትረፏ ደስ ብሎኝ ግን እንደምንም ጠብ ጠብ ብሎ የጠማኝን ብናደድባቸውም ፈገግ አልኩና ... " እኔ የምልሺ እኅቴ "ግን ለምንስ ያን ያክል ቁሜ ነገሬያችሁ እንዲህ አደረጋችሁ".... ከዚያማ ሴትዮዋ ሆይና "... አይ ዶክተር ኧረ ይቅር በሉኝ አዎን ነግረኸኝ ነበርና ብላ በረጅሙ ተነፈሰቺ ... የባህል ባለመዳኒቱ ሰውዬ በአጋጣሚ እንኳን በሰላም ወለድሺ ሊለኝ ቤታችን መጥቶ ሊጠይቀኝ ማለት ነው፤ እሽ አልኩ ወደ ግድግዳው እየተጠጋው '...ደሞ ልጅቷንም አሟት ኖሮ አይይ፤ እስኪ ልያት አለና... ኧረ ኧረ አንቃሯ/እንጧሏ ወርዶ ኖሯል አይይ ያው ሐኪሞቹ በመዳኒት ነካክተው ለጊዜው ማስታገስ ነውና ቶሎ እንዲሁ ካልተቆረጠላት ድጋሚ ከተነሳበት ብዙም ምልክት ሳያሳይ ይገድላታል፤ ነገሩ እነርሱም ሸሽገው ያስቆርጣሉ' ብሎኝ" ... ኧ😳 መቼስ እኔም በውስጤ አዘንኩና ያው ጩጨዋን አክመናት ተሽሏትም አይደል እንደገና ፈገግ ብዬ ግን ስንት አስከፈላችሁ ማለት ባል ሆይና ፈጠን ብሎ 1000 ብር .... 🤭 ኧረ ይመቼው በና የአራድዬ ልጅ ... ያ ሰውዬ he can't even read and write እኮ...ሁ ሁይ 😂 ✍️ዋናው ነገሩ ከዚህ ላይ ነው፤ ለማንኛውም የጩጨዋ አባት is a PhD holder and Mother is an MSC graduate. 🤭
Open in TelegramDo you believe it? 😜 Most of ሕዝቤ around here said "YES" as ይህ የአብዛኞቻችን ታሪክ ነውና... በቃ ሴት የላከው ጅብ አይፈራም አለ የጦብያ ሰው ሲተርት 🤭
Open in Telegram#ወገንፍቅርምመድኃኒትነው። ፡ የሰው ልቡ በዓት እልፍኝ ነው ማረፊያ፣ ለወዳጅ ጥጥ አልጋ፡ የተቀበቀበ በሽቦ መግረፊያ፣ ያ'ነው መኖሪያው ፡ አንዱ ላንዱ ወገን፡ ቢጤውን ጋልቦ ነው፡ ሚመለከት ነገን። መኖሪያሽ ልቤ ነው ፤ ልቤ ደግሞ ሙሴሽ! © አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
Open in TelegramForwarded from Eagle Scholars
ሐኪም አነቃቂ ንግግር ቢናገር የሚለው 😀 " #አንተተአምረኛሰው በአንድ ወቅት፣ ከአባትህ የወጣው ከ40 እስከ 300 ሚሊዮን የሚጠጋ የስፐርም ሴል ወደ እናትህ ማህፀን ሲገባ ከባድ የሞት ሽረት ውጊያ ገጥሞት ነበር። የማህፀን ውስጥ አሲዳማነትና የተከላካይ ሴሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ወዲያውኑ አጠፏቸው። ወደ እንቁላሉ የደረሱት ጥቂት መቶዎች ብቻ ናቸው። እዚያም ቢሆን አስገራሚ ነገር ተፈጠረ፤ መጀመሪያ የደረሱት ስፐርሞች የእንቁላሉን ጠንካራ የውጪ አካል ለመስበር ሲታገሉ እራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ወደቁ። ያንተን ግማሽ ዲኤንኤ (DNA) የያዘውና አንተን የፈጠረው ስፐርም ግን፣ በትክክለኛው ሰዓት ደርሶ ሌሎች በከፈቱት መንገድ ሰርጎ ገባ። አንተ የተፈጠርከው ከ300 ሚሊዮን እጅግ ጠባብ በሆነ ተአምራዊ እድል ነው!" 1️⃣ ያለ ምንም አጋዥ አሸነፍክ፤ ያኔ እጅና እግር፣ ዓይንና ጭንቅላት ሳይኖርህ በዚያ ጨለማ ውስጥ መድረሻህን አውቀህ ሮጠህ አሸነፍክ: ሰርተፍኬት፣ እውቀትና የሚረዳህ ሰው ሳይኖር በባዶ ማንነትህ ብቻህን ድል አደረግክ። 2️⃣ አስበው የሞት አፋፍን አልፈህ ተረፍክ፡በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፅንሶች በማህፀን ውስጥ ሲቋረጡ፣ አንተ ግን 9 ወር ሞላህ፤ በወሊድና በልጅነት በሽታዎች ብዙ ህፃናት ሲቀሩ፣ አንተ 5 አመት ሞላህ። በአለም ላይ በየቀኑ በበሽታና በአደጋ ብዙዎች ሲያልፉ፣ አንተ ዛሬም በህይወት አለህ። 👉 ታዲያ ዛሬ ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ? ዛሬ የሆነ ነገር ሲበላሽ የምትደነግጠውና በራስ መተማመን የምታጣው ለምንድነው? አሁን እኮ ለማሰብ የሚያስችል ጭንቅላት፣ ለመስራት የሚያግዝ እጅና እግር አለህ። ትምህርት፣ ሰርተፍኬት፣ ስልክና የሚረዱህ ሰዎች አሉህ። ያኔ ምንም ያልነበረው አንድ ነጠላ ሴል 300 ሚሊዮን ተወዳዳሪዎችን ጥሎ ካሸነፈ፣ ዛሬ ሁሉንም ነገር ይዘህ እንዴት እጅ ትሰጣለህ? አንተ ተሸናፊ አይደለህም፤ የማሸነፍ ታሪክህን የረሳህ ሻምፒዮን እንጂ! 🙏 ጀግናዬ ለማሸነፍ ይህንን ያህል የታገለውን ህይወትህን ዛሬ አሳልፈህ አትስጠው። ተስፋ አትቁረጥ!" 😎😇
Open in TelegramForwarded from Eagle Scholars
የተለያዩ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች በአጋጣሚ ተጠራርተው አንድ አውሮፕላን ውስጥ ይገናኛሉ። የአውሮፕላኑ በሮች ከተዘጉ በኋላ ለበረራ ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ተሰጠ።ወዲያውም አስከትሎ ተናጋሪው እንዲህ አለ "ክቡራን ተሳፋሪዎች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች። ይህ ልትበሩበት የተሳፈራችሁበት አውሮፕላን የተገጣጠመው በተማሪዎቻችሁ ሲሆን የሚያበሩትም የእናንተው ተማሪዎች ናቸው።" አላቸው። በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሮቹ ተደናገጡ። ሁሉም ወደ ተዘጋው በርና ወደ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች በመሮጥ ነፍሳቸውን ለማትረፍ መፍጨርጨር ጀመሩ። በዚህ ሁሉ ግርግር ግን አንድ ፕሮፌሰር ተረጋግቶ ተቀምጧል። ይህን መረጋጋት የተመለከተ የአውሮፕላኑ ረዳት አብራሪ ፕሮፌሰሩ ለምን እንዳልተደናገጠ ጠየቀው። ፕሮፌሰሩም በኩራት "ፕሌኑን የገጣጠሙት የእኔ ተማሪዎች ናቸው።" አለው። ረዳት አብራሪው: "በሚገባ አስተምረኻቸዋል ማለት ነው?" ፕሮፌሰሩ: አላስተማርኳቸውም..!! ረዳት አብራሪው: እና ምን አረጋጋህ? ፕሮፌሰሩ : አውሮፕላኑ አይበርም..!! ✍ (እዚሁ መንድር ያገኘሁት ጽሁፍ ነው)
Open in Telegram