Кабинет

Посты канала ንስር ሕክምና

сначала новые

#2541Текст
Просмотры223−54%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#2539Файл
Просмотры271−44%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2538Файл
Просмотры256−47%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#2537Файл

Переслано из Dr. Estifanos(MD, Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры315−35%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#2534Текст

#ሕይወትን_በሕክምና_ቁጥሮች 🧬 ሕይወት በየዕለቱ ስትከብደን እና አቤቱታዎችን ስናበዛ፣ ከራሳችን አልፈው ከባድ ፈተናን የሚጋፈጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንም እኛንም ያበረቱናል ፤ ለእነርሱም እናስፈልጋቸዋለንና ይህንን እውነታ መዘንጋት የለብንም፤ እስኪ እንዲህም እናስብ፦ 🎗️ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች አዲስ ካንሰር እንዳለባቸው ታውቆ ከበሽታው ጋር ከፍተኛ የሕክምና ትግል ላይ ናቸው፤ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትም በተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች አሊያም በጽኑ ሕክምና ክፍል ሕመምን በመቋቋም በጀግንነት በመታገል እያሸነፉ ይገኛሉ እና ብርታትን ተስፋ መሰነቅን ከእነርሱ በላይ ማንም ሊያስተምረን የሚችል የለም፤ የእውነተኛውን ጸሎትም ከእምነት ተቋማት ይልቅ በሆስፒታሎች ግድግዳ ወደ አምላክ ይደረሳል። 🌍 ስማኝማ ወዳጄ "እድለ ቢስ ነኝ፣ መጥፎ ዕድል ብቻ ነው የሚያጋጥመኝ ብለህ እስኪ አታማርር ሰምተህ ነውን... የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ እንደሚያሳየው ከ 43 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችንን ፍጹም ስውራን (Blind) የኾኑት በልበ ብርሃንነት ለዓለማችን የሚቻላቸውን ኹሉ እያበረከቱ ነውና ብርታትን ከእርሱ እንማር፤ ቀን መውጣቱንና መጥለቁን በዓይናቸው ማየት የማይችሉበት ቢኾንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ወገኖቻችን ከልቦና ጨለማነት ወጭተው ሕይወትን እየታገሏት ነውና ንሳማ እንበርታ። 🧑 "ዛሬ በጣም ደክሞኛል፣ ነገ እሰራዋለሁ እያልን ጊዜያችን አናባክን... በየቀኑ ከ170,000 በላይ የሚጠጉ ሰዎች በተለያዩ አጣዳፊ የጤና እክሎች (እንደ የልብ ድካም፣ ድንገተኛ ስትሮክ) የሕይወታቸው ሕቅታ ያልፋልና ነገ የሚባል ቀን ለእኛ በእርግጠኝነት አለመሰጠቱን የሕክምናው ዓለም በየዕለቱ ይመሰክራል። 💡 "ሕይወቴ ፈራረሰችብኝ፣ ተበላሸች ብለንም ተስፋ አንቁረጥ አይዞኝ በዓለም ዙሪያ ከ 2 ቢሊዮን በላይ ሰዎች አስተማማኝ የመጠጥ ውኃ አያገኙም፤ በንፁሕ ውኃ እጥረት ምክንያት ብቻ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናትን ለገዳይ ተላላፊ በሽታዎች ተጋልጠው ያሉባት ስራችን ብዙ ሰራተኞቹ ግን ጥቂት የኾንባት ዓለም ውስጥ ነንና እንደገና እንበርታ እስኪ አይዞን ጓድ 📖 "አንድ ትንሽ ነገር ሲጠፋብን ቀኔ ተበላሸ ብለን ለምንስ እንበሳጫለን ከ200 ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን እኮ ፍጹም ቤት አልባ (Homeless) በመሆናቸው ከለላ የሌለው የጎዳና ሕይወትን በብርድና በፀሐይ የሚሰቃይ ሕይወትን እየገፉ ነውና በል እንበርታና ለእነርሱም መከታ የምንኾንበት ጊዜ ይመጣልና። 🧠 በሥነ-ልቦና ሕክምና ውስጥ አመስጋኝነት (Gratitude) የአእምሮን የቅመሞች ኬሚስትሪ በማጣጣም ጭንቀትን (Stress) የሚቀንስ ወሳኝ ሕክምና ነውና በል እንበርታ ወንድምሰው ፤ ነገ የተሻለ ይኾናልና። 🤲 ያለንበትን ጤና፣ እስትንፋስ እና ዕድል ሁልጊዜም ማስታወስ ከየትኛውም መድኃኒት በላይ ለነፍስ ፈውስ ነውና አይዞኝ... መልካም የጤና፣ የደስታ እና የሰላም ውሎ መግባት ይኹንልን! ❤️ @NisirHikimna

Открыть в Telegram
Просмотры903+86%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#2532Фото
Просмотры858+77%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2531Фото
Просмотры607+25%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#2530Фото
Просмотры588+21%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#2528Фото
Просмотры647+33%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#2527Фото
Просмотры611+26%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#2526Фото

Переслано из Eagle Scholars

#የሊቃውንትጉባኤ የ1927 የሶልቬይ ጉባኤ (Solvay Conference) ፎቶግራፍ በታሪክ ውስጥ «እጅግ በጣም ብልህ ሰዎች የተነሱት ፎቶ» በመባል የሚታወቅ ሲኾን በዚህ ጉባኤ ላይ በወቅቱ የነበሩት የዓለማችን ታላላቅ የፊዚክስ ሊቃውንት ተሰብስበው ስለ ኳንተም ፊዚክስ (Quantum Mechanics) ሕጎች እና ንድፈ-ሐሳቦች በሰፊው ተወያይተዋል፡- 🥇 የኖቤል ተሸላሚዎች፡ በፎቶው ውስጥ ከሚታዩት 29 ሳይንቲስቶች መካከል 17ቱ የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ናቸው (ወይም በኋላ ላይ አሸንፈዋል)። 🧑‍🔬 አልበርት ኤይንስታይን (Albert Einstein): በፎቶው መሐል አካባቢ የተቀመጠ ሲኾን በወቅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ዝናን ያተረፈ ሳይንቲስት ነበረ። 👨‍🔬 ማሪ ኪዩሪ (Marie Curie): በስብሰባው ላይ የተገኘችው ብቸኛዋ ሴት ሳይንቲስት ስትኾን፡ በኹለት የተለዩ የሳይንስ ዘርፎች (በፊዚክስ እና በኬሚስትሪ) የኖቤል ሽልማት በማሸነፍ በታሪክ ብቸኛዋ ሰው ናት። 🧑‍🔬👨‍🔬 ሌሎች ታዋቂ ሳይንቲስቶች፡ ኒልስ ቦር (Niels Bohr)፣ ቨርነር ሃይዘንበርግ (Werner Heisenberg)፣ ኤርቪን ሽሮዲንገር (Erwin Schrödinger) እና ማክስ ፕላንክ (Max Planck) ይገኙበታል። እውቀት ነጻ ያወጣል! @EagleScholars

Открыть в Telegram
Просмотры681+40%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#2525Текст

#ከእንጥል_ቆራጭ_ያላስመለጠው_ስብከቴ✍️ ኢንተርን ሳለሁ ... ከዕለታት በአንደኛው ቀን በPediatrics/NICU attachment...  4.2kg ጩጨዋ Neonatal sepsis ታማ admitted ኾነቺና በደንብ ተንከባክበን ድና በቃ ወደቤት ልንልካቸው ይገባል ተብሎ...Our pediatrician "ዶክ በቃ በደንብ ምክር ስጧቸውና ወደቤት discharge ትኹን!" እኔም እንደተባልኩት ያው ያነበብኳትንና የማውቃትን ኹሉ የሳይንስ ስብከቴን ከመጻሕፍት እያጣቀስኩ ነገረኛ ነኝ ይሰሙኝ መስሎኝ 🤭😊 "... ማማዬ እንግዲህ በቃ በደንብ ድናለቺ ወደቤታችሁ ልትሄዱ ነው፤ አስከትቡ፤ ፀሐይ አሙቁ ፤ እስከ6 ወር የጡት ወተት ብቻ መቼም አይጠፋችሁም ኣ ..." ምናምን ብቻ ሌላም ብዙ ብዬ በመጨረሻም "... እንዲያው አደራችሁን እንጥል እንዳታስቆርጡ!" አልኩላችሁና ወደቤት መላክ... ከዚያስ አትሉኝም በበነጋታው ምሽት ላይ ጨቅላዋ እራሷን ስታ ደም በደም ኾና በሚያሳዝን ኹኔታ Duty time እኛው ጋር እንደገና ከቺ 😔... ያው ኹሉም ሰው ተሯሩጠን she had been again readmitted with Aspiration Pneumonia + Hypovolemic shock 2°Acute Blood Loss (Severe Anemia) ብቻ እንደምንም የNICU Team ተረባርቦላት ጨቅላዋ ታከመቺ፥ ደምም ተገኝቶ ተሰጣትና እንደምንም ተረፈቺልንና ወላጆቿ የኾነ ቀን እንዲሁ round ጨርሰን ወደ Motherside ተመልሳ ታቅፋት እያጠባቻት ሲያዩኝ እየተጠቋቆሙ አፍረው ተሸፈኑ... ያው እኔም በኩራት ጀነን ብዬ ነገር ነገር ሊለኝ አፍኜ በውስጤ 🤭 ግን ያው ጩጨዋ በመትረፏ ደስ ብሎኝ ግን እንደምንም ጠብ ጠብ ብሎ የጠማኝን ብናደድባቸውም ፈገግ አልኩና ... " እኔ የምልሺ እኅቴ "ግን ለምንስ ያን ያክል ቁሜ ነገሬያችሁ እንዲህ አደረጋችሁ".... ከዚያማ ሴትዮዋ ሆይና "... አይ ዶክተር ኧረ ይቅር በሉኝ አዎን ነግረኸኝ ነበርና ብላ በረጅሙ ተነፈሰቺ ... የባህል ባለመዳኒቱ ሰውዬ በአጋጣሚ እንኳን በሰላም ወለድሺ ሊለኝ ቤታችን መጥቶ ሊጠይቀኝ ማለት ነው፤ እሽ አልኩ ወደ ግድግዳው እየተጠጋው '...ደሞ ልጅቷንም አሟት ኖሮ አይይ፤ እስኪ ልያት አለና... ኧረ ኧረ አንቃሯ/እንጧሏ ወርዶ ኖሯል አይይ ያው ሐኪሞቹ በመዳኒት ነካክተው ለጊዜው ማስታገስ ነውና ቶሎ እንዲሁ ካልተቆረጠላት ድጋሚ ከተነሳበት ብዙም ምልክት ሳያሳይ ይገድላታል፤ ነገሩ እነርሱም ሸሽገው ያስቆርጣሉ' ብሎኝ" ... ኧ😳 መቼስ እኔም በውስጤ አዘንኩና ያው ጩጨዋን አክመናት ተሽሏትም አይደል እንደገና ፈገግ ብዬ ግን ስንት አስከፈላችሁ ማለት ባል ሆይና ፈጠን ብሎ 1000 ብር .... 🤭 ኧረ ይመቼው በና የአራድዬ ልጅ ... ያ ሰውዬ he can't even read and write እኮ...ሁ ሁይ 😂 ✍️ዋናው ነገሩ ከዚህ ላይ ነው፤ ለማንኛውም የጩጨዋ አባት is a PhD holder and Mother is an MSC graduate. 🤭

Открыть в Telegram
Просмотры1 050+116%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#2522Текст
Просмотры1 410+191%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
#2520Текст

Переслано из Eagle Scholars

ሐኪም አነቃቂ ንግግር ቢናገር የሚለው 😀 " #አንተተአምረኛሰው በአንድ ወቅት፣ ከአባትህ የወጣው ከ40 እስከ 300 ሚሊዮን የሚጠጋ የስፐርም ሴል ወደ እናትህ ማህፀን ሲገባ ከባድ የሞት ሽረት ውጊያ ገጥሞት ነበር። የማህፀን ውስጥ አሲዳማነትና የተከላካይ ሴሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ወዲያውኑ አጠፏቸው። ወደ እንቁላሉ የደረሱት ጥቂት መቶዎች ብቻ ናቸው። እዚያም ቢሆን አስገራሚ ነገር ተፈጠረ፤ መጀመሪያ የደረሱት ስፐርሞች የእንቁላሉን ጠንካራ የውጪ አካል ለመስበር ሲታገሉ እራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ወደቁ። ያንተን ግማሽ ዲኤንኤ (DNA) የያዘውና አንተን የፈጠረው ስፐርም ግን፣ በትክክለኛው ሰዓት ደርሶ ሌሎች በከፈቱት መንገድ ሰርጎ ገባ። አንተ የተፈጠርከው ከ300 ሚሊዮን እጅግ ጠባብ በሆነ ተአምራዊ እድል ነው!" 1️⃣ ያለ ምንም አጋዥ አሸነፍክ፤ ያኔ እጅና እግር፣ ዓይንና ጭንቅላት ሳይኖርህ በዚያ ጨለማ ውስጥ መድረሻህን አውቀህ ሮጠህ አሸነፍክ: ሰርተፍኬት፣ እውቀትና የሚረዳህ ሰው ሳይኖር በባዶ ማንነትህ ብቻህን ድል አደረግክ። 2️⃣ አስበው የሞት አፋፍን አልፈህ ተረፍክ፡በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፅንሶች በማህፀን ውስጥ ሲቋረጡ፣ አንተ ግን 9 ወር ሞላህ፤ በወሊድና በልጅነት በሽታዎች ብዙ ህፃናት ሲቀሩ፣ አንተ 5 አመት ሞላህ። በአለም ላይ በየቀኑ በበሽታና በአደጋ ብዙዎች ሲያልፉ፣ አንተ ዛሬም በህይወት አለህ። 👉 ታዲያ ዛሬ ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ? ዛሬ የሆነ ነገር ሲበላሽ የምትደነግጠውና በራስ መተማመን የምታጣው ለምንድነው? አሁን እኮ ለማሰብ የሚያስችል ጭንቅላት፣ ለመስራት የሚያግዝ እጅና እግር አለህ። ትምህርት፣ ሰርተፍኬት፣ ስልክና የሚረዱህ ሰዎች አሉህ። ያኔ ምንም ያልነበረው አንድ ነጠላ ሴል 300 ሚሊዮን ተወዳዳሪዎችን ጥሎ ካሸነፈ፣ ዛሬ ሁሉንም ነገር ይዘህ እንዴት እጅ ትሰጣለህ? አንተ ተሸናፊ አይደለህም፤ የማሸነፍ ታሪክህን የረሳህ ሻምፒዮን እንጂ! 🙏 ጀግናዬ ለማሸነፍ ይህንን ያህል የታገለውን ህይወትህን ዛሬ አሳልፈህ አትስጠው። ተስፋ አትቁረጥ!" 😎😇

Открыть в Telegram
Просмотры1 100+127%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#2519Текст

Переслано из Eagle Scholars

የተለያዩ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች በአጋጣሚ ተጠራርተው አንድ አውሮፕላን ውስጥ ይገናኛሉ። የአውሮፕላኑ በሮች ከተዘጉ በኋላ ለበረራ ዝግጁ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ተሰጠ።ወዲያውም አስከትሎ ተናጋሪው እንዲህ አለ "ክቡራን ተሳፋሪዎች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች። ይህ ልትበሩበት የተሳፈራችሁበት አውሮፕላን የተገጣጠመው በተማሪዎቻችሁ ሲሆን የሚያበሩትም የእናንተው ተማሪዎች ናቸው።" አላቸው። በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሮቹ ተደናገጡ። ሁሉም ወደ ተዘጋው በርና ወደ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች በመሮጥ ነፍሳቸውን ለማትረፍ መፍጨርጨር ጀመሩ። በዚህ ሁሉ ግርግር ግን አንድ ፕሮፌሰር ተረጋግቶ ተቀምጧል። ይህን መረጋጋት የተመለከተ የአውሮፕላኑ ረዳት አብራሪ ፕሮፌሰሩ ለምን እንዳልተደናገጠ ጠየቀው። ፕሮፌሰሩም በኩራት "ፕሌኑን የገጣጠሙት የእኔ ተማሪዎች ናቸው።" አለው። ረዳት አብራሪው: "በሚገባ አስተምረኻቸዋል ማለት ነው?" ፕሮፌሰሩ: አላስተማርኳቸውም..!! ረዳት አብራሪው: እና ምን አረጋጋህ? ፕሮፌሰሩ : አውሮፕላኑ አይበርም..!! ✍ (እዚሁ መንድር ያገኘሁት ጽሁፍ ነው)

Открыть в Telegram
Просмотры921+90%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—