“ጾም ዕረፍተ ነፍስን ትሰጣለች፡፡ ለሽማግሌዎች ውበትን ታጎናጽፋቿለች፤ ወጣቶችን በቀና ጎዳና ትመራቿለች፤ ማስተዋልን ትለግሳቿለች፤ ኹሉንም ሰው እንደ ዘውድ እንደ አክሊል ያማረ የተወደደ ታደርገዋለች፡፡ እንግዲያውስ ዛሬ ምንም ዓይነት ሁካታ አይኑር፡፡ ሁካታስ ይቅርና ምልክቱም አይኑር፡፡ ገደላን ለማንሣት ወይም የምግብ ዓይነትን ለማንጋጋት የሚራወጥ ማንም አይገኝ፡፡ ኹሉም ሰው ከእንደዚህ ዓይነት ግብር ይራቅ፡፡ ከተማችን እንደ ተወደዱ ቈነጃጅት አመለ ሸጋና የምትማርክ ትኹን፡፡ በአንድ ሌሊት ውስጥ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ ስመለከትና የትናንቱን ጫጫታ ሳስታውሰው ጾም እንደ ምን ያለች ፍቱን መድኃኒት መኾኗን ዐይቼ በእጅጉ እደነቃለሁ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው አመለካከት እንደ ምን እንደምትቀይር ተመልክቼ በእጅጉ መደነቅን ይይዘኛል፡፡ የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም፣ የጌቶችን ብቻ ሳይኾን የባሮችም፣ የወንዶችን ብቻ ሳይኾን የሴቶችንም፣ የባለጸጎችን ብቻ ሳይኾን የድኾችንም፣ ቃለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ብቻ ሳይኾን የማያውቁትንም እንደ ምን ልበ ንጹሀን እንደምታደርጋቸው ተመልክቼ አብዝቼ እደነቃለሁ፡፡ የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም ብዬ መናገሬስ ስለ ምንድን ነው? ነገሥታትም ከነዘውዳቸውና ከነሙሉ ማዕርጋቸው ኾነው ራሳቸውን ለጾም ስለሚያስገዙ ነዋ! ዛሬ በባለጸጋውና በድኻው ማዕድ ልዩነት የለውም፡፡ ኹሉም ሰው ተርታ ኑሮን የሚመራ ነው፡፡ የቅምጥልነትን ሕይወት የሚመራ የለም፡፡ ታይታን የሚፈልግ የለም፡፡ ኹሉም ሰው በቤቱ ካለው የሰባ ፍሪዳና ወይን ይልቅ እዚህ በቤተ ክርስቲያን ያለውን ሰማያዊውን ማዕድ ሽቶ የመጣ ነው። ✍በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ✍ @MoaeTewahedoB
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 92 |
| 4 h | 178 |
- After 1 hour92
- Total to date178