Account

Posts of መራኁት

newest first

#476Photo
Views1,120−55%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—
#475Text
Views1,540−38%vs avg
Forwards—
Reactions144
Comments—
#471Video
Views3,040+23%vs avg
Forwards—
Reactions72
Comments—
#467Text
Views3,990+61%vs avg
Forwards—
Reactions63
Comments—
#466Photo

Forwarded from መራኁት

የምህረት ካብ በፈረሰበት ፥ መዓት እንደ ቀላይ በፈሰሰበት ዘመን ሆኜ የምፅናናው ፥ የምሕረት ኪዳን መሆንሽን ሳስብ ነው :: እውቀት አያረካም ፥ ጥበብም የነፍስን ሀቂቃ አይሞላም ፥ ስምሽ ግን የክፉ ቀን ጥላ ነው :: ብዙው ነገር ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ፥ ልጅሽ ግን ለመኖር የሚገፋ ኃይል ነው :: ትክክለኛው መንገድ ለሥጋ አይመችም ፥ አንቺን ማየት ግን ለእውነት ያስጨክናል :: ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ናት ፥ ፈተናው ማብቂያ የለውም ፥ ጣዕምሽ ግን ሁሉን ያዘነጋል :: ነጣቂው ብዙ ነው ፥ ተኩላና ድቡ ከመቆጠር በላይ ነው ፥ ዘርፋፋ ቀሚስሽ ግን ማእበሉን ያስመልጣል :: ሕግ ተናለች ፥ የሰው ዋጋው ከቁስ ቀሏል ፥ ልባችን የእንባ ቋት ሆኗል ፥ በእንባ የተቃጠለ ፊትሽን ማየት ግን ፅናት ያዋርሳል ፣ ዝቅታን ያስረሳል ፡፡ ዓለም ስታደናቅፈን ፥ ማን ሰበሰበን ፣ በሰቀቀን ስንውተረተር ፥ ማን አረጋን ፣ ልንወድቅ ስንፍገመገም ፥ ማን ምርኩዝ ሆነን ፣ ጥም ሲበረክት ፥ ማን ጽዋውን አዘነበለልን ፣ ባይተዋርነት በአንጀታችን ሲላወስ ፥ ማን ደገፈን ፣ የበደል ዕዳችንን ሳይጠየፍ ፥ ማን አቀፈን ፣ የከሸፉ ቀኖቻችን በማን እስትንፋስ ተቀብተው ሕያዋን ሆኑ ፣ በርኖስ ካጠለቀው ቀያችን ፥ ፀሐይ ስትፈነጥቅ ማን ጠፈር ሆነን ፣ በፊቱ ለመቆም ሞገስ ስናጣ ፥ ማን መቃረቢያ አዋሰን ፣ የመርገም ጨርቃችንን ማን በፍታ ጣለበት ፣ አንቺ አይደለሽ ? ወይንሽ ዘወትር አይጎድልም ፥ ምልጃሽ በእንከን አያባራም ፥ እናትነትሽ ፅልመት ያጠራል ፥ ሰላምሽ ከዕንቁ ፀዳል ያበራል ፥ ፈልጌሽ አላጣሁሽም : ጠርቼሽ በኀፍረት አላጎነበስኩም : የትኛውም አቀበት ላይ ብቻዬን አልተውሽኝም ፥ ማርያም ስል እጠግባለሁ ። “ አመ ይመጽዕ ወልድኪ በደብረ ፅዮን ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን “ Via: Dereje Zeleke

Open in Telegram
Views4,630+87%vs avg
Forwards—
Reactions64
Comments—
#465Text

እኔ ክርስቲያን ተብሎ መጠራትን እወዳለሁ ክርስቲያን ሆኖ መኖርን እወዳለሁ መላ ሕይወቴን እንደ አባቶቼ እንደ ሐዋርያት ትምህርት ክርስቲያን ሆኖ መዋልና ማደርን እወዳለሁ እንደ አባቶቼ እንደ ሐዋርያት ክርስቲያን ሆኖ በመቃብር ውስጥ ማረፍን እወዳለሁ በትንሣኤዬም ጊዜ ከአባቶቼ ከሐዋርያት ጋር ክርስቲያን ሆኖ መነሣትን እወዳለሁ በደብረ ጽዮንም በአባቶቼ በሐዋርያት አጠገብ ሆኖ መቀመጥን እወዳለሁ። የቅዱሳን ዜና ክብራቸውን እናገር ዘንድ ፍቅር ያስገድደኛል። መናፍቃንንም እዘልፋቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል ክርስቶስንም አመሰግነው ዘንድ ፍቅር አምልኮቱ ያስገድደኛል። ሰይጣንን አወግዘው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን እከተላቸው ዘንድ ፍቅረ እግዚአብሔር ያስገድደኛል። በደለኞችንም እሸሻቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። ሰማዕታትን አመሰግናቸው ዘንድ ፍቅረ ሃይማኖት ያስገድደኛል። ሟርተኞችን እዘልፋቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። መጽሐፈ ምሥጢር 10:2

Open in Telegram
Views3,600+45%vs avg
Forwards—
Reactions126
Comments—
#462Text

ማቴ 1:20 VS ሜቴ 2:13?? #አንዴ_የጌታ_ከሆኑ_በኋላ_የሌላ_የማንም_መሆን_አይመችም። ቀድሞ ቀራጭ ከነበረው ለምድራዊው መንግሥት ገንዘብ ከመሰብሰብ ለሰማያዊው መንግሥት ነፍሳትን ወደመሰብሰብ ከተጠራው ከቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የተውሰዱት እኒህ ሁለት ጥቅሶች የእግዚአብሔር መልአክ የጌታ አባት ተብሎ ለመጠራት ከታደለው ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያደረገው ንግግር የተመዘገበባቸው የወንጌል ክፍሎች ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ የሁለቱ ቅዱሳን ንግግር ዓለምን ለመዋጀት ስለተጸነሰው እና ስለተወለደው ጌታ እንዲሁም ስለጸነሰችው እና ስለወለደችው ድንግል የተደረገ ነው። ጻድቅ ዮሴፍ ይጠብቃት ዘንድ እጮኛ ተደርጋ የተሰጠችው ሴት ከማን እንደጸነሰች ሳያውቅ ጸንሳ ባገኛት ጊዜ እንደ አይሁድ ሥርዓት ተወግራ ትገደል ሳይል በሥውር ሊተዋት ሲያስብ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጦ ለመጀመርያ ጊዜ አነጋገረው። 'እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ እንዳትፈራ' ሲል። ድንግል ማርያም ንጉሡን በወለደች ጊዜ ሄሮድስ ለመንግሥቱ ቀንቶ ዘመን አስሰልቶ ቀን ቆጥሮ ሕጻኑን ሊገድል ለቅሶ ብቻ በታጠቁ ሕጻናት ላይ ጦር ሲያዘምት ያ መልአክ ዳግመኛ ጻድቅ ዮሴፍን በሕልም አነጋገረው። ንግግሩ ግን ተቀይሯል 'ሕጻኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ'። እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዓይናማ ካልሆንን ልዩነቱን አናስተውለው ይሆናል ምሥጢሩ ግን ግሩም ነው። መልአኩ ነገር ያውቃል። ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗ ለዮሴፍም ለዓለምም ሳይገለጥ በፊት ጻድቁን ሲያናግረው 'እጮኛህን' ነበር ያለው። ጌታችንን ከወለደች በኋላ ግን የጌታ እናቱ እንጂ የዮሴፍ እጮኛ ተብላ አትጠራም። 'እጮኛህን' ሳይሆን 'የሕጻኑን እናት ይዘህ ሽሽ' ተባለ። የአብን ሙሽራ የዮሴፍ እጮኛ የሚላት ማን ነው? ንጉሥ ውበቷን የወደደላትን (መዝ 45:9-10) ያለ እናት የወለደውን አንድያ ልጁን ያለ አባት የወለደችለት መደምደሚያውን የዮሴፍ ልጆች እናት የሚላት የቱ አንደበት ነው? ወንጌላዊው ዮሐንስ ከመልአኩ ተምሮ ለ14 ዓመት ቤቱ የኖረችውን ሴት በስሟ ሊጠራት እንኳ አልደፈረም። 'የጌታዬ እናቱ፣ የኢየሱስ እናት' አላት እንጂ። የጌታ ከሆኑ በኋላ የሌላ የማንም መሆን አይመችም። በ80 ቀንሽ በልጅነት ማኅተም ታትመሽ ሥጋውን ከሥጋሽ ደሙን ከደምሽ አዋሕደሽ የኢየሱስ ከሆንሽ በኋላ የኃጢአት እና ለኃጢአት ጌታዋ ለሆነ ለዲያብሎስ ራስሽን መስጠት እንዴት አስቻለሽ? ለአገልግሎት ተለይተህ በቅዱስ ጳውሎስ ጫማ ውስጥ ቆመህ የሰማእታት መጀመርያ የዲያቆናት አለቃ የእስጢፋኖስ ማእረግ ተሰጥቶህ የክርስቶስ ከሆንክ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰህ የዓለም መሆን እንዴት ተመቸህ? አንተስ ወዳጄ ከክርስቶስ ደም ይልቅ መጠጥ እንዴት ማረከህ? ፣ ከእጣኑ ይልቅ ትምባሆ እንዴት አወደህ?፣ ከዝማሬ ይልቅ ዳንኪራ ለምን ተመቸህ? የክርስቶስ ከሆንክ በኋላ እንዴት የጠላት ሆነህ ተገኘህ? ለሕይወት ከተባልክ በኋላ እንዴት ለሞት ታጨህ? እንዴት ተመቸህ? እንዴት ተመቸኝ?! ጌታ ሆይ አንተ ወደ ራስህ መልሰኝ እንጂ እኔ መመለስ የምችል አይደለሁም። መልካም ወርኀ ጽጌ (2015 ዓ.ም)

Open in Telegram
Views5,980+142%vs avg
Forwards—
Reactions61
Comments—
#459Text
Views6,350+157%vs avg
Forwards—
Reactions124
Comments—
#458Text
Views6,520+163%vs avg
Forwards—
Reactions190
Comments—
#456Photo
Views5,990+142%vs avg
Forwards—
Reactions26
Comments—