Посты канала መራኁት
Переслано из ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#የንግሥ_በዓል_ጥሪ ነገ ኅዳር 17/2019 ዓም የዓለም ሁሉ መምህር የሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዓመታዊ ንግሥ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከአያት 49 ወረድ ብሎ ኩራ ጅዳ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለወልድ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የሥጋው ፍልሰት መታሰቢያ ይከበራልና ከዋዜማው አገልግሎት ጀምሮ ተገኝተን እናከብር ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን። የጎግል ማፕ መረጃ እና ስልክ፦ https://maps.app.goo.gl/vvA9GhgjpjAPcQUD7 +251913445958 +251947152583 ቴሌግራም፡ t.me/FNOAFW ቀጠሮዎን ከወዲሁ ያስተካክሉ!
Открыть в Telegramጌታዬ ሆይ የምሆነውን የማደርገውን ሁሉ እያየህ ግን እወድሃለሁ ስልህ ታምነኛለህ? እንደሚወድህ ሰውስ መኖር ለምን አቃተኝ? የበደልኩትን ብቻ ሳይሆን ገና የምበድለውን እያወቅክ ምሕረት የምታደርግልኝ እንዴት ብትወደኝ ነው? ሌሎችን ቀርቶ ራሴን ይቅር ማለት ለከበደኝ ለኔ ያንተ አካል ተብሎ መጠራት እንዴት ይሆንልኛል? እባክህ አትተወኝ። ምሕረትህ ባይገባኝም፣ ደግሜ ደጋግሜ ፍቅርህ ላይ ብዘብትም፣ አንተን ለመውደድ ያለኝን ፍላጎት ብቻ አይተህ አትተወኝ። ከፍላጎት በቀር የማቀርብልህ ምንም በጎ ነገር የሌለኝ እኔን አትጣለኝ። አንተ ያስቻልከኝ ቀን እችላለሁ አምላኬ።
Открыть в Telegramየማኅበራችን አባላት በሙሉ ሕዳር 17 ወደ ሥራ ላለመሄድ ለምን ፍቃድ እንደሞሉ ማወቅ አትፈልጉም? 😊 https://vt.tiktok.com/ZSsJUbg8x/
Открыть в TelegramПереслано из ፍኖተ አፈወርቅ (official)
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ማነው? በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ነበር። ስብከቱ እንደ ወርቅ ስለሚያንጸባርቅ «አፈወርቅ» (የወርቅ አፍ) ተባለ። በቤተ ክርስቲያናችን ከሚቀደሱት ቅዳሴያት አንዱ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው። ስለ እውነት በግዞት መከራን ተቀበለ፤ ያረፈውም «ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር ይመስገን» እያለ ነበር። ከዕረፍቱ በኋላ አጽሙ ወደ ቁስጥንጥንያ በክብር ተመልሷል። ይህንን ፍልሰተ አጽሙን በዓል ኅዳር 17 አብረን እናክብራለን። 📍 ኩራ ጅዳ፣ ከአያት 49 ወረድ ብሎ
Открыть в Telegramመንፈሳዊ እድገትን የምትፈልጉበትን ምክንያት አስተውላችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ? የምርም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ከመፈለግ ይሆን? ይህንን በተመለከተ ዛሬ አንድ አጭር video ይኖረናል። እግዚአብሔር ይፍቀድ
Открыть в Telegramቲክቶክ ላይ በጣም መጥፋቴ አሳስቧችሁ ለጠየቃችሁኝ ሁሉ በጣም በጣም እያመሰገንኩ። እግዚአብሔር ቢረዳኝ እንደ አዲስ አገልግሎት ጀምሬአለሁ። አካውንቱ ሞቶ ስለቆየ video እንዲታይ የናንተ ድጋፍ ግድ ነው ተወዳጆች። እስቲ ገብታችሁ አየት አየት አድርጉት😁 https://vt.tiktok.com/ZSp2xEgBo/
Открыть в TelegramПереслано из መራኁት
የምህረት ካብ በፈረሰበት ፥ መዓት እንደ ቀላይ በፈሰሰበት ዘመን ሆኜ የምፅናናው ፥ የምሕረት ኪዳን መሆንሽን ሳስብ ነው :: እውቀት አያረካም ፥ ጥበብም የነፍስን ሀቂቃ አይሞላም ፥ ስምሽ ግን የክፉ ቀን ጥላ ነው :: ብዙው ነገር ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ፥ ልጅሽ ግን ለመኖር የሚገፋ ኃይል ነው :: ትክክለኛው መንገድ ለሥጋ አይመችም ፥ አንቺን ማየት ግን ለእውነት ያስጨክናል :: ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ናት ፥ ፈተናው ማብቂያ የለውም ፥ ጣዕምሽ ግን ሁሉን ያዘነጋል :: ነጣቂው ብዙ ነው ፥ ተኩላና ድቡ ከመቆጠር በላይ ነው ፥ ዘርፋፋ ቀሚስሽ ግን ማእበሉን ያስመልጣል :: ሕግ ተናለች ፥ የሰው ዋጋው ከቁስ ቀሏል ፥ ልባችን የእንባ ቋት ሆኗል ፥ በእንባ የተቃጠለ ፊትሽን ማየት ግን ፅናት ያዋርሳል ፣ ዝቅታን ያስረሳል ፡፡ ዓለም ስታደናቅፈን ፥ ማን ሰበሰበን ፣ በሰቀቀን ስንውተረተር ፥ ማን አረጋን ፣ ልንወድቅ ስንፍገመገም ፥ ማን ምርኩዝ ሆነን ፣ ጥም ሲበረክት ፥ ማን ጽዋውን አዘነበለልን ፣ ባይተዋርነት በአንጀታችን ሲላወስ ፥ ማን ደገፈን ፣ የበደል ዕዳችንን ሳይጠየፍ ፥ ማን አቀፈን ፣ የከሸፉ ቀኖቻችን በማን እስትንፋስ ተቀብተው ሕያዋን ሆኑ ፣ በርኖስ ካጠለቀው ቀያችን ፥ ፀሐይ ስትፈነጥቅ ማን ጠፈር ሆነን ፣ በፊቱ ለመቆም ሞገስ ስናጣ ፥ ማን መቃረቢያ አዋሰን ፣ የመርገም ጨርቃችንን ማን በፍታ ጣለበት ፣ አንቺ አይደለሽ ? ወይንሽ ዘወትር አይጎድልም ፥ ምልጃሽ በእንከን አያባራም ፥ እናትነትሽ ፅልመት ያጠራል ፥ ሰላምሽ ከዕንቁ ፀዳል ያበራል ፥ ፈልጌሽ አላጣሁሽም : ጠርቼሽ በኀፍረት አላጎነበስኩም : የትኛውም አቀበት ላይ ብቻዬን አልተውሽኝም ፥ ማርያም ስል እጠግባለሁ ። “ አመ ይመጽዕ ወልድኪ በደብረ ፅዮን ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን “ Via: Dereje Zeleke
Открыть в Telegramእኔ ክርስቲያን ተብሎ መጠራትን እወዳለሁ ክርስቲያን ሆኖ መኖርን እወዳለሁ መላ ሕይወቴን እንደ አባቶቼ እንደ ሐዋርያት ትምህርት ክርስቲያን ሆኖ መዋልና ማደርን እወዳለሁ እንደ አባቶቼ እንደ ሐዋርያት ክርስቲያን ሆኖ በመቃብር ውስጥ ማረፍን እወዳለሁ በትንሣኤዬም ጊዜ ከአባቶቼ ከሐዋርያት ጋር ክርስቲያን ሆኖ መነሣትን እወዳለሁ በደብረ ጽዮንም በአባቶቼ በሐዋርያት አጠገብ ሆኖ መቀመጥን እወዳለሁ። የቅዱሳን ዜና ክብራቸውን እናገር ዘንድ ፍቅር ያስገድደኛል። መናፍቃንንም እዘልፋቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል ክርስቶስንም አመሰግነው ዘንድ ፍቅር አምልኮቱ ያስገድደኛል። ሰይጣንን አወግዘው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። የክርስቶስ ደቀመዛሙርትን እከተላቸው ዘንድ ፍቅረ እግዚአብሔር ያስገድደኛል። በደለኞችንም እሸሻቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። ሰማዕታትን አመሰግናቸው ዘንድ ፍቅረ ሃይማኖት ያስገድደኛል። ሟርተኞችን እዘልፋቸው ዘንድ መንፈሳዊ ቅንዓት ያስገድደኛል። መጽሐፈ ምሥጢር 10:2
Открыть в Telegramአልተኛችሁም ወይ? በ youtube SPOT church ላይ አሁን live program እንዳለ ሰምታችኋል? እስቲ እነሱንም እናገልግል፣ እዛ እንገናኝ😊
Открыть в Telegramማቴ 1:20 VS ሜቴ 2:13?? #አንዴ_የጌታ_ከሆኑ_በኋላ_የሌላ_የማንም_መሆን_አይመችም። ቀድሞ ቀራጭ ከነበረው ለምድራዊው መንግሥት ገንዘብ ከመሰብሰብ ለሰማያዊው መንግሥት ነፍሳትን ወደመሰብሰብ ከተጠራው ከቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የተውሰዱት እኒህ ሁለት ጥቅሶች የእግዚአብሔር መልአክ የጌታ አባት ተብሎ ለመጠራት ከታደለው ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያደረገው ንግግር የተመዘገበባቸው የወንጌል ክፍሎች ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ የሁለቱ ቅዱሳን ንግግር ዓለምን ለመዋጀት ስለተጸነሰው እና ስለተወለደው ጌታ እንዲሁም ስለጸነሰችው እና ስለወለደችው ድንግል የተደረገ ነው። ጻድቅ ዮሴፍ ይጠብቃት ዘንድ እጮኛ ተደርጋ የተሰጠችው ሴት ከማን እንደጸነሰች ሳያውቅ ጸንሳ ባገኛት ጊዜ እንደ አይሁድ ሥርዓት ተወግራ ትገደል ሳይል በሥውር ሊተዋት ሲያስብ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጦ ለመጀመርያ ጊዜ አነጋገረው። 'እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ እንዳትፈራ' ሲል። ድንግል ማርያም ንጉሡን በወለደች ጊዜ ሄሮድስ ለመንግሥቱ ቀንቶ ዘመን አስሰልቶ ቀን ቆጥሮ ሕጻኑን ሊገድል ለቅሶ ብቻ በታጠቁ ሕጻናት ላይ ጦር ሲያዘምት ያ መልአክ ዳግመኛ ጻድቅ ዮሴፍን በሕልም አነጋገረው። ንግግሩ ግን ተቀይሯል 'ሕጻኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ'። እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዓይናማ ካልሆንን ልዩነቱን አናስተውለው ይሆናል ምሥጢሩ ግን ግሩም ነው። መልአኩ ነገር ያውቃል። ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗ ለዮሴፍም ለዓለምም ሳይገለጥ በፊት ጻድቁን ሲያናግረው 'እጮኛህን' ነበር ያለው። ጌታችንን ከወለደች በኋላ ግን የጌታ እናቱ እንጂ የዮሴፍ እጮኛ ተብላ አትጠራም። 'እጮኛህን' ሳይሆን 'የሕጻኑን እናት ይዘህ ሽሽ' ተባለ። የአብን ሙሽራ የዮሴፍ እጮኛ የሚላት ማን ነው? ንጉሥ ውበቷን የወደደላትን (መዝ 45:9-10) ያለ እናት የወለደውን አንድያ ልጁን ያለ አባት የወለደችለት መደምደሚያውን የዮሴፍ ልጆች እናት የሚላት የቱ አንደበት ነው? ወንጌላዊው ዮሐንስ ከመልአኩ ተምሮ ለ14 ዓመት ቤቱ የኖረችውን ሴት በስሟ ሊጠራት እንኳ አልደፈረም። 'የጌታዬ እናቱ፣ የኢየሱስ እናት' አላት እንጂ። የጌታ ከሆኑ በኋላ የሌላ የማንም መሆን አይመችም። በ80 ቀንሽ በልጅነት ማኅተም ታትመሽ ሥጋውን ከሥጋሽ ደሙን ከደምሽ አዋሕደሽ የኢየሱስ ከሆንሽ በኋላ የኃጢአት እና ለኃጢአት ጌታዋ ለሆነ ለዲያብሎስ ራስሽን መስጠት እንዴት አስቻለሽ? ለአገልግሎት ተለይተህ በቅዱስ ጳውሎስ ጫማ ውስጥ ቆመህ የሰማእታት መጀመርያ የዲያቆናት አለቃ የእስጢፋኖስ ማእረግ ተሰጥቶህ የክርስቶስ ከሆንክ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰህ የዓለም መሆን እንዴት ተመቸህ? አንተስ ወዳጄ ከክርስቶስ ደም ይልቅ መጠጥ እንዴት ማረከህ? ፣ ከእጣኑ ይልቅ ትምባሆ እንዴት አወደህ?፣ ከዝማሬ ይልቅ ዳንኪራ ለምን ተመቸህ? የክርስቶስ ከሆንክ በኋላ እንዴት የጠላት ሆነህ ተገኘህ? ለሕይወት ከተባልክ በኋላ እንዴት ለሞት ታጨህ? እንዴት ተመቸህ? እንዴት ተመቸኝ?! ጌታ ሆይ አንተ ወደ ራስህ መልሰኝ እንጂ እኔ መመለስ የምችል አይደለሁም። መልካም ወርኀ ጽጌ (2015 ዓ.ም)
Открыть в Telegramንግሥት ዕሌኒ የክርስቶስን መስቀል ፍለጋ ያደረገችው ጉዞ የጽኑ ፍቅር መገለጫ ነው። ከጽኑ ናፍቆት እና ከጌታዋ የሚያጣብቃትን ነገር በመሻት የፈጸመችው ነው። ጌታችን ሥጋው የተቆረሰበትን ደሙ የፈሰሰበትን እጸ መስቀል አጠገባችን ማግኘት ባንችል እንኳ የተቆረሰ ሥጋውን የፈሰሰ ደሙን ከራሳችን እያዋሐድን እኛም ፍቅራችንን ናፍቆታችንን መወጣት እንችላለን። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በጤና አደረሰን። ቀጣይ ዓመት ደግሞ በሰላም እንደሚያደርሰን ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።
Открыть в Telegramየጳጳሳትን ነውር ስትሰሙ ልባችሁ ለሚሸበር፣ በማንጠብቃቸው ቦታ ስናገኛቸው ለምትደነግጡ ቤተክርስቲያን ተስፋ የላትም የሚል ጭንቅት ለሚወርራችሁ እኔን ከእንደዚህ ዓይነት ድካም የገላገለኝን እና ለካ ከዚህም የባሰ አለ፣ ለካ አባቶች ከዚህም በላይ ሊያደርጉ ሊፈተኑ ይችላሉ እንድል ያደረጉኝን እና እንዳልሸበር እንዳልደነግጥ ያገዙኝን ሁለት መጻሕፍት ልጋብዛችሁ። እነሱን ካነበባችሁ በኋላ ምንም ብትሰሙ አትደነግጡም። ሁለቱም በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ የተዘጋጁ ናቸው። 1) ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ 2) ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሕይወቱ እና ትምህርቱ። እመኑኝ ታመሰግኑኛላችሁ😊
Открыть в Telegramመልዕል መራሔ ዕቅድ የ90 ቀን ዕለታዊ መራሔ ዕቅድ (planner) ሲሆን፤ የቀን ምስባክ፣ ወንጌል እና በየዕለቱ የሚታሰቡ ቅዱሳን አለው በእያንዳንዱ ቀን። በተጨማሪ መንፈሳዊ ሕይወትን ለመከታተል እና ለማሳደግ የሚያግዙ ዕለታዊ እና ወርኀዊ ቻሌንጆችን ይይዛል። ሌላው እንደማንኛውም planner የቀን ዕቅድ፣ ግብ፣ to do lists እና ማስታወሻ መያዣ ቦታ አለው። ይህንን ደብተር ከፈለጉ ለ @brain_word inbox ማድረግ ወይም 0923150109 ደውለው ማዘዝ ይችላሉ። መራኁት ነው የላከን ካላችሁ ቅናሽ ይደረጋል ተብሏል😁
Открыть в Telegram