Account

Posts of Kirkos curriculm

newest first

#5340Photo
Views473−56%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5339Photo

በሞዴልና ማጠቃለያ ፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ህዳር 15/2019 ዓ.ም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የ2019 ዓ.ም. የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተናዎችን ዝግጅትና አፈጻጸም የበለጠ ጥራት ባለው፣ ውጤታማና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለማከናወን ያለመ ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ የወረዳና የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘሮች፣ የፈተና አዘጋጅ መምህራን እንዲሁም የጽሕፈት ቤቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በመድረኩ የ2019 ዓ.ም. የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተናዎች ዝግጅትና አሰጣጥን በተመለከተ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የጋራ ውይይት ከተካሄደ በኋላ፣ በ2018 ዓ.ም. የተዘጋጁ ፈተናዎች ላይ በተካሄደው ግምገማ የተገኙ ውጤቶችን፣ ግኝቶችንና የተለዩ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን የያዘ ሰነድ ቀርቦ በጥልቀት ተወያይቶበታል። በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችና በመድረኩ የተቀመጡ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች መነሻ በማድረግ፣ ተሳታፊዎች በቀጣይ የሚከናወኑ ፈተናዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ከዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የየራሳቸውን ሚናና ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በተለይም፦ 🔹 የፈተናዎችን ጥራትና ተገቢነት ማረጋገጥ፤ 🔹 የፈተና ደህንነትንና ምስጢራዊነትን ማስጠበቅ፤ 🔹 የፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ሥርዓትን ማዘመን፤ 🔹 የተሳታፊ አካላትን የተጠያቂነትና የአፈጻጸም ሚና ማጠናከር፤ 🔹 የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሥርዓቶችን ማሳደግ፤ በዋናነት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ነበሩ። በመጨረሻም በቀጣይ መከናወን ባለባቸው ቁልፍ ተግባራትና በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓቶች ላይ ግልጽ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ለተሻለ የፈተና ጥራትና ተአማኒነት በጋራ የመሥራት ቁርጠኝነት በማሳየት ውይይቱ ተጠናቋል።

Open in Telegram
Views905−16%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5334Photo
Views1,510+40%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#5326Photo
Views1,580+47%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—