Waajjira Barnoota Kutaa Magaalaa Qiirqoositti qaama tarsiimoo qabxii Barnoota dabalataa barattoota kutaa 11ffaa fi 12ffaaf guyyaa sanbata wiirtuu kilastaaraatti kennamaa jiruuf moojuulii qophaa’e irratti hundaa’uun barsiisota barnoota kenanif kennaniif leenjii kenneera. የቂርቆስ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘወትር ቅዳሜ በክላስተር ደረጃ እየተሰጠ ለሚገኘው የማጠናከሪያ ትምህርት በተዘጋጀው ሞጁል ዙሪያ ትምህርቱን ለሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና ስልጠና ሰጥቷል ።
Open in Telegram
Kirkos curriculm
ለትምህርት ጥራት እንተጋለን We strive for the quality of education
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 21, 2026 | 1,580 |
| Nov 23, 2026 | 1,310 |
| Nov 25, 2026 | 890 |
| Nov 28, 2026 | 473 |
Most viewed this month
- Views1.58KForwards—Reactions—Comments—
- Views1.51KForwards—Reactions—Comments—
- Views1.11KForwards—Reactions—Comments—
- Views905Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
በሞዴልና ማጠቃለያ ፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ህዳር 15/2019 ዓ.ም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የ2019 ዓ.ም. የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተናዎችን ዝግጅትና አፈጻጸም የበለጠ ጥራት ባለው፣ ውጤታማና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለማከናወን ያለመ ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ የወረዳና የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘሮች፣ የፈተና አዘጋጅ መምህራን እንዲሁም የጽሕፈት ቤቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በመድረኩ የ2019 ዓ.ም. የሞዴልና ማጠቃለያ ፈተናዎች ዝግጅትና አሰጣጥን በተመለከተ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ የጋራ ውይይት ከተካሄደ በኋላ፣ በ2018 ዓ.ም. የተዘጋጁ ፈተናዎች ላይ በተካሄደው ግምገማ የተገኙ ውጤቶችን፣ ግኝቶችንና የተለዩ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን የያዘ ሰነድ ቀርቦ በጥልቀት ተወያይቶበታል። በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችና በመድረኩ የተቀመጡ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች መነሻ በማድረግ፣ ተሳታፊዎች በቀጣይ የሚከናወኑ ፈተናዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ከዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የየራሳቸውን ሚናና ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በተለይም፦ 🔹 የፈተናዎችን ጥራትና ተገቢነት ማረጋገጥ፤ 🔹 የፈተና ደህንነትንና ምስጢራዊነትን ማስጠበቅ፤ 🔹 የፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ሥርዓትን ማዘመን፤ 🔹 የተሳታፊ አካላትን የተጠያቂነትና የአፈጻጸም ሚና ማጠናከር፤ 🔹 የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሥርዓቶችን ማሳደግ፤ በዋናነት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ነበሩ። በመጨረሻም በቀጣይ መከናወን ባለባቸው ቁልፍ ተግባራትና በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓቶች ላይ ግልጽ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ለተሻለ የፈተና ጥራትና ተአማኒነት በጋራ የመሥራት ቁርጠኝነት በማሳየት ውይይቱ ተጠናቋል።
Open in Telegramለሁሉም የመንግስት እና የግል 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ2019 ዓም የተከለሰ የሬድዮ ትምህርት ፕሮግራም ስለሆነ በሰርኩላሩ መሰረት በመደበኛ የክፍለ ጊዜ ድልድል ውስጥ ተካት ተግባራዊ እንዲደረግ በጥብቅ እናሳስባለን። የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ተገቢውን ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
Open in Telegramበቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሲከበር የነበረው 21ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዛሬ የማጠቃለያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል። *** ህዳር 12/2019 ዓ.ም በዚህ ዝግጅት ላይም ቀኑን በሚመለከት የተለያየዩ የብሄር ብሄረሰብ ትርኢቶች፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎች፣ የጥያቄና መልስ ውድድሮች ተካሂደዋል። በዚህ መርሀ-ግብር ላይም የክፍለከተማው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አምደ አያሌው የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰማኸኝ አስታጥቄ ተገኝተዋል። እንዲሁም መምህራን፣,ተማሪዎች፣ የዘርፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች በመርሀ-ግብሩ ታድመዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር ተካሄዷል።
Open in Telegram