Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 4 h | 940 |
| 9 h | 1,320 |
- After 6 hours940
- Total to date1,320
Hours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 4 h | 940 |
| 9 h | 1,320 |
🚨 በጎጃምና በጎንደር ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም ማጥፋትና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ተፈጽሟል በሚል በአቶ ኢዩ ጩፋ ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ጥቆማ ቀረበ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ አቶ ኢዩ ጩፋ በሃይማኖት ስብከት ሽፋን በጎጃምና በጎንደር አካባቢ ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም የማጥፋት፣ የማዋረድና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ትናንት ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይፋዊ የወንጀል ጥቆማ አቅርበዋል። በጥቆማው ላይ እንደተመለከተው፣ ተጠሪው በኅዳር ወር 2019 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የምዕራብ፣ የምሥራቅ፣ የሰሜን ጎጃምንና የአዊ አካባቢ ሕዝብን «መተተኞች» በማለት በጅምላ መፈረጃቸውና ይህም በማኅበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱ የሕዝቡን የሥራ ትጋትና እሴት የሚያንቋሽሽ፣ እንዲሁም ተወላጆቹን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታዩ የሚያደርግ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በሌላ የስብከት መድረክ ላይ የጎንደርንና የጎጃምን ሕዝብ ዒላማ በማድረግ «የጎጃም የሌ፣ የጎንደር የሌ፤ እዚህ ቤት የገባ ሁሉ ይቀጠቀጣል፣ ይረገጣል፤ የትም ይሥራ እናፈርሰዋለን» በማለት የጥላቻና የማስፈራሪያ ንግግር ማድረጋቸው በጥቆማ ደብዳቤው ተጠቅሷል። ድርጊቱ የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግን (ስም ማጥፋትና ሕዝብን ማነሳሳት)፣ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን የሚጥስ መሆኑን ጠበቃው ገልጸው፤ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በማያያዝ ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ አጣርቶ ተጠሪውን ለፍትሕ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 964 |
| 7 h | 1,520 |
የኢትዮጵያ ነፃ አውጪ ማነው? በየቦታው የተደራጁ ጦሮች መጨረሻ ምንድነው? የሀገራችን የመጨረሻ እጣ ፈንታስ ምን ይሆን? ይህን ሀገራዊ ትንታኔ በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል👇 https://youtu.be/HMiSvO244lgSub_confirmation=1 https://youtu.be/HMiSvO244lgSub_confirmation=1
Open in Telegramጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ይሰጣሉ‼️ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት በመጪው ሐሙስ ህዳር 17/2019 ዓ.ም ያካሂዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ታውቋል።
Open in Telegramየድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ በድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። የአራት ልጆች አባት የነበረው ድምፃዊው “እንዳማረ” ፣ “አሁን ገባኝ” ፣ “ዚዮዜ” ፣ “ቀረ ድሮ” እና “ቱሪናፋ” በትግርኛ የሠራው “ናተይ” እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ የተጫወተው “ጉዳዬ” በተሰኙ የቅርብ ጊዜ የሙዚቃ ሥራዎቹ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ለአድማጮች ያደረሳቸው “10 ከ10” እና “ሰላም አላት” የተሰኙ አልበሞቹም በርካታ አድናቆትንና ተወዳጅነትን ያተረፉለት ናቸው። “የፍቅር ስጦታ” ፣ “አሁን አሁን”፣ “ግርማ ሞገሴ” እና “የኔ ደሃ” በተባሉ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎቹ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramበ Twitter (X) የተጀመረው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ለአለም የማሳወቅ ዘመጃ በመጨረሻም ፍሬ አፍርቶ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ዛሬ የኦርቶዶክሳውያኑን ግድያ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram😭አሳዛኝ ዜና! ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል። ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና መዝፈን ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል። ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል። በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል። በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር። ለባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙዚቃ አፍቃሪያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramበኢትዮጵያ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አስመልክቶ ከፍተኛ የአሜሪካ ሴናተር ስጋታቸውን ገለጹ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ሴናተር ጂም ሪሽ፣ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ገዳይ ጥቃቶችን በተመለከተ ጥልቅ ስጋታቸውን አሰምተዋል። ሴናተሩ ለፎክስ ኒውስ ዲጂታል (Fox News Digital) በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ሕይወት መጥፋት “አሰቃቂ አዝማሚያ” መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የቀጠለው አለመረጋጋትና ግጭት በንጹሐን ዜጎች ደኅንነት፣ በቀጣናዊ ሰላም እንዲሁም በአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ከባድ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምሥራቅ በሚገኘው የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ኢንደቶ በተባለ አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 34 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ታጣቂዎች በኢንደቶ በሚገኘው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በመቅረብ ሰዎች እጃቸውን እንዲሰጡ ካዘዙ በኋላ ተኩስ መክፈታቸው ተገልጿል። በጥቃቱ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ሲሆኑ፣ ሦስት የእስልምና እምነት ተከታዮችም እንደሚገኙበት የአካባቢው ምንጮች ጠቁመዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ፣ ዋሽንግተን በአርሲ ስለደረሰው የሕይወት መጥፋት መረጃው እንዳላት ገልጸው፣ በድርጊቱ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግና ጥፋተኞች በሕግ እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የቀጠለው ግጭት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ፣ ሁሉም ወገኖች ለንጹሐን ዜጎች ጥበቃ እንዲያደርጉና ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል። ንጹሐን ዜጎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው በመቀጠሉ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስጋቱን እያጠናከረ ሲሆን፣ ሴናተር ሪሽም ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆዩ የውስጥ ችግሮቿን በመፍታት ዘላቂ ሰላም እንድታሰፍን ጥሪ አቅርበዋል። ©️ፎክስ ኒውስ ዲጂታል (Fox News Digital) ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramየዐቢይ የፖለቲካና የወታደራዊ ስሌት የኢትዮጵያን ውስጣዊ መረጋጋትና ቀጠናዊ አሰላለፍ እንዴት እየፈተነው ይገኛል? በየአቅጣጫው የተከፈቱት እነዚህ ግጭቶች የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ እቅድ አካል ናቸው ወይስ ሀገሪቱን ወደ አዲስ የቀውስ ምዕራፍ እየገፏት ነው? ይህን አስገራሚ ፖለቲካዊ ትንታኔ በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል👇 https://youtu.be/mGkJb-KUKNoSub_confirmation=1 https://youtu.be/mGkJb-KUKNoSub_confirmation=1
Open in Telegramበባድሜ አካባቢ ከባድ ውጊያና የአየር ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ አብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወደ መደበኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱና የጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እየተዘረጋ ቢሆንም፣ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በባድሜ ዙሪያ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ውጊያ መቀጠሉን ቢቢሲ፣ ሮይተርስ እና ዶቼ ቬለ ዘግበዋል። ወደ ኤርትራ ግዛት የገባው የህወሓት ታጣቂ ኃይል ከኤርትራ ጦር ጋር በመሆን በአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ምንጮች ሲያመለክቱ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኩልም በድሮን ቅኝት የታገዘ የአየር ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል። ከዚህም ባሻገር፣ በተፈጠረው የጸጥታ ክፍተት ከማረሚያ ቤቶች የተለቀቁ ፍርደኞች ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለኅብረተሰቡ ደኅንነት ስጋት መሆናቸውን ዘገባዎቹ አክለው ገልጸዋል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram"ህዳር ሲታጠን" በሚል ሰበብ ቆሻሻ ማቃጠል በሕግ የተከለከለ ነው! የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በመጪው ህዳር 12 የሚከበረውን "ህዳር ሲታጠን" አስመልክቶ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡ ለዓመታት የተለመደው ቆሻሻን አቃጥሎ የማጽዳት ተግባር በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ብክለት እያስከተለ በመሆኑ ድርጊቱ ፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከባለስልጣኑ የተላለፉ ዋና ዋና ነጥቦች፡- ማቃጠል አይቻልም፡ በህዳር 12 ቀን "ህዳር ሲታጠን" ነው በሚል ማንኛውንም ዓይነት ቆሻሻ ሰብስቦ ማቃጠል በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው። ይህንን እገዳ ለማስፈጸም የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ህጉን ተላልፎ ቆሻሻ ሲያቃጥል የተገኘ አካል ላይ እርምጃ ይወሰዳል፡፡ ቆሻሻን ከማቃጠል ይልቅ፣ በእለቱ የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር በሁሉም ሰፈሮች ተንቀሳቃሽ የቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ስለሚሰጥ ቆሻሻን ለእነርሱ ማስረከብ ይጠበቅብዎታል። ስለሆነም ኅብረተሰቡ አካባቢውን እና አየሩን ከመበከል በመቆጠብ ባህሉን ከብክለት ነጻ በሆነ መንገድ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡ Via የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram#Moyalle በደቡባዊ ኢትዮጵያ ለአንድ ወር ያህል በዘለቀ የታጠቁ ኃይሎች ግጭት ምክንያት ወደ 700,000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሪታኒያው ግብረ ሰናይ ድርጅት ኢስላሚክ ሪሊፍ ዛሬ ሐሙስ አስታወቀ። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ አዲስ ባወጣው ዘገባው በኦሮሞ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ማህበረሰብ አባላት መካከል ድንበር ከተማዋ ሞያሌን ለመቆጣጠር የተፈጠረው ግጭት በከባድ መሳሪያ ወደ ታገዘ ውጊያ መሸጋገሩን ጠቅሷል። በዚህም እስካለፈው ሰኞ ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ግጭቱ ተስፋፍቶ ከከተማዋ ውጭ እስከ 300 ኪሎ ሜትር ሁለቱ ብሄሮች በሚጋሩባቸው አካባቢዎች ርቆ ማዳረሱን ዘገባው አትቷል። ግጭቱ ብርቱ ሰብአዊ ጉዳት ማስከተሉን ያመለከተው ዘገባው በተጨማሪ ከሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን 329,000 ሰዎች፣ እንዲሁም በደቡብ ኦሮሚያ ደግሞ 359,798 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ግብረ ሰናይ ድርጅቱ መዝግቧል። በግጭቱ ምክንያት በርካታ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውንና የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን የገለጸው ድርጅቱ፣ ከ50,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ መሸሻቸውን አስታውቋል። የኢስላሚክ ሪሊፍ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ኃላፊ ከድር ሙሰማ ሀምዛ እንዳሉት ሁኔታው በሁለት ብሔሮች መካከል በድንበር አካባቢ መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ለመቆጣጠር በሚደረግ ፉክክር ውስጥ ተቀስቅሷል። ግጭቱ ከተጀመረ አንስቶ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የግጭት ተቆጣጣሪው አክሌድ (ACLED) ቢያመለክትም፣ ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር ግን እስካሁን አልታወቀም። የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት በግጭቱ ዙሪያ እስካሁን ምንም ዓይነት አስተያየት አለመስጠቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramበተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከ300 በላይ ምልምል ወታደሮች በዱከም ከተማ ከነበሩበት ጊዚያዊ መጠለያ በጉቦ ማምለጣቸውን ይህም የመከላከያ ሠራዊትን እና የአካባቢው ፖሊስ የሚያስወቅስ ድርጊት ነው በማለት የአካባቢውን የፖሊስ ሃላፊ እየተውቀሰ ይገኛል። መብታቸው ተጥሶ በግድ ታፍሰው ከቤተሰቦቻቸው እስከ 250 ሺ ብር ስለከፈሉት ንፁሃን ወገኖች ግን ማንም አያወራም። አይ ሀገሬ 🇪🇹 ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramአሳዛኝ ክስተት‼️ በኮልፌ የህንፃ መደርመስ አደጋ ተከሰተ‼️ በህዳር 9/2019 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ፣ በአዲስ አበባ ኮልፌ፣ ቀራንዮ ወረዳ 03፣ ከግራር ወደ ስልጤ ሰፈር በሚወስደው መንገድ፣ ከኑር ካፌ ከፍ ብሎ በመሠራት ላይ የነበረ ህንፃ ተደርምሷል። ህንፃው የመሬት ወለሉን ጨምሮ የመጀመሪያና ሁለተኛ ፎቆቹ ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት ውለው እንደነበር ተገልጿል። በአደጋውም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በህንፃው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ስንት እንደሞቱ ወይም እንደተጎዱ እስካሁን እየተጣራ ነው። ይህ አደጋ የግንባታ ጥራትና የቁጥጥር ሥርዓት ጉዳይን በአስቸኳይ እንድንመለከት ያሳስባል። የግንባታ ደረጃና ደህንነት መስፈርቶችን የማያሟሉ ሥራዎች በተገቢው ሁኔታ መቆጣጠር አለባቸው። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram🇪🇹🇪🇷 በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር !! በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በሁለቱም አገራት መካከል ከፍተኛ የሰራዊት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንና ሁኔታው ወደ ጦርነት እንዳመራ ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል። አለምአቀፍ የግጭት ተቆጣጣሪ የሆኑት ACLED እና ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ከቀናት በፊት የኤርትራ ሰራዊት ተሳትፎ የነበረበት ውጊያ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር እንዳደረጉ በመጥቀስ ዘግቧል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramበዋግኽምራ ዞን ዝቋላ ወረዳ የከፋ ድርቅና የሰብዓዊ ቀውስ ማጋጠሙ ተገለጸ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዝቋላ ወረዳ የተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ አሳሳቢ የሰብዓዊ ቀውስ መፍጠሩን ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። በወረዳው በረሃብና በችግር ሳቢያ የሰዎች ሕይወት ማለፉን የገለጹት ነዋሪዎች፤ በጸጥታ ችግርና በጦርነት ምክንያት ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ራስን መመገብ ባለመቻሉ ችግሩ የከፋ መሆኑን አስረድተዋል። በድርቁ ሳቢያ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን የገለጹት የወረዳው ኃላፊዎች፤ ከ400 ሺህ በላይ ከብቶች ካሉባቸው ውስጥ በርካቶች መሞታቸውን እና ወቅቱን ያልጠበቀ ከባድ ዝናብና ጎርፍም ተጨማሪ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል። የወረዳው አጠቃላይ ሕዝብ ብዛት ከ89 ሺህ በላይ ሲሆን፤ ከ74 ሺህ በላይ የሚሆኑት ዕለታዊ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramበደብረ ወርቅ የመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት ተቀሰቀሰ በምሥራቅ ጎጃም፣ ደብረ ወርቅ ከተማ ዛሬ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀስቀሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ (DW) ገለፁ። እስከ ጠዋቱ አንድ ሰዓት እጅግ ከፍተኛ ዉግያ እንደነበር የገለፁት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት በደቡብ እና በሰሜን ወሎ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ አንጻራዊ መረጋጋት ማሳየቱን ከነዋሪዎች ለመገንዘብ ተችሏል። ይሁንና ለወራቶች አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖበት በነበረባቸው የጎጃም አካባቢዎች ግጭቱ እንደገና መቀስቀሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአካባቢዉ ዳግም አገረሸ በተባለዉ ከፍተኛ ዉግያ በሰዎች እና በንብረት ላይ የደረሰዉ ጉዳት ምን ያህል መሆኑ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ድረስ በዉል አይታወቅም። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram#Moyalle በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን እንዳልቆመ ተገለፀ። በትናትናው ዕለት ህዳር 7/2019 ዓ.ም በከተማዋ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ይህንን ተከትሎ በከተማዋ 02 መናኸሪያ ፊት ለፊት ብዙ ሱቆች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚህ የተነሳ ተጨማሪ ሰዎች ለመፈናቀል ተገደዋል። በሞያሌ ከተማ የሶማሌ እና የኦሮሚያ ነዋሪዎች በወሰን እንዲሁም በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ባለመግባባት ግጭት መከሰቱ ይታወቃል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramባለፈው ወር ታጣዊዎች ዮርዳኖስ (Jordan) ውስጥ በሚገኝ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ፈፅመው ዘጠኝ ክርስቲያኖችን ገድለው 34 ሰዎችን አቁስለው ነበር። ይህን ተከትሎ ሀገሪቱ የሀዘን ቀን ያወጀች ሲሆን ቡድኑን ይደግፋሉ በተባሉ ሀይሎች ላይም የአየር ጥቃት ፈፅማ ነበር። ዛሬ ደግሞ ጥቃቱን ፈፅመዋል ተብሎ የተፈረደባቸው 3 ሰዎች የሞት ፍርድ እንዳገኙ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ነው። እኛ ጋርስ? ጭራሽ "ይህ ለምን ይፈፀማል?" ብሎ ጥያቄ የሚያነሳ "አሸባሪ!" ተብሎ የሚፈረጅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramጠገዴ ወረዳ‼ ሕፃን በማገት 1.5 ሚሊዮን ብር የጠየቀው አጋች ግለሠብ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ዋለ። በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጠገዴ ወረዳ ሕዳር 1/2019ዓ.ም ሃፍቴ ይደግ የተባለውን ህፃን በማገት ቤተሰቦቹን 1.5 ሚሊየን ብር መጠየቃቸውን ተገልፆል። የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ክትትል ሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም በአለምገነት ቀበሌ የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ አጋቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ሕፃኑ ጉዳት ሳይደርስበት ከቤተሠቦቹ ጋር በሰላም መገናኘት መቻሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ዘግቧል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegramየአርሲው እንቆቅልሽ! 👉 ከተደጋጋሚው የኦርቶዶክሳውያን ጥቃት ጀርባ ማን አለ? 👉 እስካሁን ሃላፊነቱን ማን ወሰደ? ሙሉ የዜና ትንታኔውን በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል👇 https://youtu.be/fafKXH8IIWkSub_confirmation=1 https://youtu.be/fafKXH8IIWkSub_confirmation=1
Open in Telegramርብራብ ተደርምሶ የሦስት ሠራተኞች ሕይወት አለፈ‼ ዛሬ ጠዋት 4:30 ሰዓት አካባቢ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፣ ጋዜቦ አደባባይ አቅራቢያ በግንባታ ላይ ያለ ሕንጻ ርብራብ በመደርመሱ የሦስት ሠራተኞች ሕይወት ማለፉን ጌጡ ተመስገን አጋርቷል። አደጋው የተከሰተው ሠራተኞቹ በሥራ ላይ እያሉ ርብራቡ ተደርምሶ ከ12ኛ ፎቅ በመውደቃቸው ሲሆን፣ ክስተቱ በአካባቢው በነበሩ መንገደኞችና ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ፈጥሯል። ቀዳሚ ዜና ቀዳሚ ዜና
Open in Telegram