Account

Posts of ክርስቲያናዊ ፍልስፍና

newest first

#767Text

ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከተሰቀለው ከእርሱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና... ቃሌም ስብከቴም የመንፈስን ኀይል በመግለጥ እንጂ፣ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ ይኸውም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው። በበሰሉ ሰዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህችን ዓለም ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህችን ዓለም ገዦች እውቀት አይደለም። ነገር ግን ተሰውሮ የነበረውን የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ ጥበብ ነው፤ ይህንም ጥበብ እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ለክብራችን አስቀድሞ ወሰነው። ከዚህ ዓለም ገዦች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አልተረዱትም፤ ቢረዱት ኖሮስ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር። ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤” እግዚአብሔርም ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ጨምሮ ሁሉን ይመረምራል... ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማርነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው። መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ እንዲህ ያለው ትምህርት ለእርሱ ሞኝነት ነውና። በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ፣ ሊረዳው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። “ያስተምረው ዘንድ፣ የጌታን ልብ ያወቀ ማን ነው?” እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን። @Jacobite_apologetics27

Open in Telegram
Views207−42%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#764Text

እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከምንም ይፈጥራል። እግዚአብሔር ወደ አንዳች ነገር ሊያተልቅ የፈለገውን ነገር ደግሞ በመጀመሪያ ወደ ምንምነት ይቀንሳል። ‎ ‎- ኪርክጋርድ ‎ ‎በብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዛት ከምናገኛቸው ጭብጦች መካከል አንዱ እግዚአብሔር የራሱን ኃይል ለማሳየት፣ የሰዎችን ድክመትም ለመግለጽ የሚጠቀምበት አስደናቂ መንገድ ነው። የሣራ መውለድ፣ የአጋር ከሞት መዳን፣ የጌዴዎን የጦር ድል፣ የዳዊት መንገሥ ወዘተ... እነዚህን ታሪኮች በሙሉ የሚያመስስላቸው አንድ ነገር ቢኖር፣ ፈጣሪ የአገልጋዮቹን ምኞቶች ከማሳካቱ በፊት በራሳቸው ጥንካሬ ላይ ያላቸው መተማመን ፈጽሞ እንዲፈራርስ ማድረጉ ነው። ይህ ጭብጥ ታዲያ በብሉይ ኪዳን ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ ለአዲስ ኪዳንም ዋና መሠረት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚነግረን፣ ኦሪት የተሰጠችው አማኞች ተከትለዋት እንዲድኑ ሳይሆን፣ "ኃጢአትን በመግለጽ" ፈጽመው በራሳቸው ጥረት መዳን እንደማይችሉ ለማሳየት ነበርና። ‎ ‎ታዲያ በእግዚአብሔር ላይ ያለን ጥገኝነት በመከራና በውድቀት ጊዜያት ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ እያንዳንዷን የሕልውናችንን ቅጽበት የሚመላ ነው። በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ እውነት ታምኖ መኖር ደግሞ (በተለይም የሰው ልጅ ቴክኖሎጂያዊ አቅም በፈረጠመበት በእኛ ዘመን) ትልቅ የእምነት ደረጃ የሚጠይቅ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚደርሱበት፣ በዚህ ደረጃ ላይ ለመቆየትም ያላሰለሰ መንፈሳዊ ጥረትና ትኩረትን የሚጠይቅ የእምነት ከፍታ ነው። ‎ ‎ስለዚህ፣ "እግዚአብሔር ላይ ምን ያህል ጥገኛ ነኝ?" የሚለው ጥያቄ ዘርፈብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎን የሚጠይቅና በግሌ ልወጣው የሚገባ ፈተና እንጂ፣ እንደ ቶማስ አኳይናስ ያሉ ቲዮሎጂያኖች እንደሞከሩት¹፣ ረቂቅና ውስብስብ አመክንዮአዊ ሙግቶችን ተጠቅሜ የምመልሰው ጥያቄ አይደለም። "አመክንዮአዊ እምነት/Rational Faith" የሚለውን አያዎ አካሄድ አጥብቀን መቃወም ያለብንም ለዚህ ነው። የክርስትና ጥያቄዎች በስሜት (Passion) እና ግላዊ እምነት (Personal faith) የሚመለሱ እንጂ፣ ከኢ-ወገንተኛ ፍልስፍና ጀርባ ተደብቄ የማመልጣቸው መሆን የለባቸውምና። ‎ ¹ ‎ቶማስ አኳይናስ የእግዚአብሔርን መኖር ለማረጋገጥ ከሚጠቀምባቸው ሙግቶች አንዱ፣ "አስፈላጊ ያልሆኑ (Contingent) ነገሮች በሙሉ የግድ ቀዳሚ ምክንያት ስላላቸው፣ ሰዎችን ጨምሮ ሕልውና ያላቸው ነገሮች በሙሉ ለሕልውናቸው በአንድ የበላይ ምክንያት (Supreme Cause) ላይ ጥገኛ ናቸው" የሚለው ሙግት ነው። ከላይ እንዳልኩት፣ መሰል ሙግቶች ሕያው የሆነውን የእምነት ትግል የሚገድሉ፣ ግለሰቦች ከእግዚአብሔር ጋር መታገል አቁመው፣ ምቹ ሰዋዊ ሙግቶች ላይ እንዲደገፉ የሚያደርጉ ስለሆኑ ውድቅ ሊደረጉ ይገባል። @Jacobite_apologetics27

Open in Telegram
Views443+25%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#761Photo
Views545+53%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#760Text
Views500+41%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#758Photo
Views978+175%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#756Video
Views853+140%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#754Photo

በአንድ ወቅት የኤቲዪዝም ሐዋርያ የነበረው ክሪስቶፈር ሂችንስ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‎በጣም ትዕቢተኞች ነን። አጽናፈ ዓለሙ በሙላ የተፈጠረው እኛን ታሳቢ በማድረግ ነው ብለን እናምናለን... ከዚህ ከንቱ አስተሳሰብ ለመላቀቅ ብዙ ይጠይቃል። ‎ ‎የመጨረሻዎቹ ሁለት ቃላት ("ብዙ ይጠይቃል") interesting ናቸው። ይህን የሂችንስ ንግግር ከቁብ ከቆጠርነው፣ "ዓለም ለእኛ ተብሎ ተፈጠረ" ከሚለው እይታ ለመላቀቅ አስፈላጊ የሆኑት እነዚህ "ብዙ' ነገሮች፣ ምንም ሆኑ ስንት፣ ሂችንስ በምልዓት ይዟቸዋል ማለት ነው (ያለበለዚያ እንዴት ኤቲዪስት ይሆናል?)። ‎ ‎የሂችንስን ንግግር በሌላ መልኩ መግለጽ እንችላለን፦ ‎ ‎እዚህ ግባ የሚባል ዋጋ የሌለን ፍጥረታት ነን...ይህንን መራራ እውነታ ለመቀበል የሚያስችል ብልህነት፣ ትሕትና እና ሀቀኝነት ካላቸው ጥቂት ልዩ ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱ እኔ ነኝ። ‎ ‎በብዙ ኤቲዪስቶች ላይ ለምናየው፣ የሰው ልጆችን እንደ ዝርያ እያንቋሸሹ፣ ራስን (በተለይም የአዕምሮ ብቃትን) የመኮፈስ ዝንባሌ፣ ከዚህ የተሻለ ግልጽ ምሳሌ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ከእንዲህ አይነት አባዜ ለመላቀቅ ብዙ ይጠይቃል (pun intended)። @Jacobite_apologetics27

Open in Telegram
Views676+90%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#753Photo
Views747+110%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#752Link preview
Views779+119%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#751Photo
Views809+128%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#748Photo

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም። እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ... እኔ ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና። ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ። ደቀ መዛሙርቱ። እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ በምሳሌም ምንም አትነግርም። ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። አሁን ታምናላችሁን? እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም። በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።" ዮሐንስ 16፡20-33 @Jacobite_apologetics27

Open in Telegram
Views756+113%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#741Photo
Views899+153%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—