ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከተሰቀለው ከእርሱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና... ቃሌም ስብከቴም የመንፈስን ኀይል በመግለጥ እንጂ፣ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ ይኸውም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኀይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው። በበሰሉ ሰዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህችን ዓለም ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህችን ዓለም ገዦች እውቀት አይደለም። ነገር ግን ተሰውሮ የነበረውን የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ ጥበብ ነው፤ ይህንም ጥበብ እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ለክብራችን አስቀድሞ ወሰነው። ከዚህ ዓለም ገዦች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አልተረዱትም፤ ቢረዱት ኖሮስ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር። ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤” እግዚአብሔርም ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ጨምሮ ሁሉን ይመረምራል... ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ፣ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንምና፤ ይህም እግዚአብሔር በነጻ የሰጠንን እናውቅ ዘንድ ነው። እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማርነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው። መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ እንዲህ ያለው ትምህርት ለእርሱ ሞኝነት ነውና። በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ፣ ሊረዳው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። “ያስተምረው ዘንድ፣ የጌታን ልብ ያወቀ ማን ነው?” እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን። @Jacobite_apologetics27
Открыть в TelegramПосты канала ክርስቲያናዊ ፍልስፍና
ክርስትና እንዴት ዓለምን ሊያጥለቀልቅ ቻለ? የባርት ኸርማን ማብራሪያን የማልቀበልበት ምክንያት። አድምጡት፣ አጭር መልዕክት ነው። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegramእግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከምንም ይፈጥራል። እግዚአብሔር ወደ አንዳች ነገር ሊያተልቅ የፈለገውን ነገር ደግሞ በመጀመሪያ ወደ ምንምነት ይቀንሳል። - ኪርክጋርድ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዛት ከምናገኛቸው ጭብጦች መካከል አንዱ እግዚአብሔር የራሱን ኃይል ለማሳየት፣ የሰዎችን ድክመትም ለመግለጽ የሚጠቀምበት አስደናቂ መንገድ ነው። የሣራ መውለድ፣ የአጋር ከሞት መዳን፣ የጌዴዎን የጦር ድል፣ የዳዊት መንገሥ ወዘተ... እነዚህን ታሪኮች በሙሉ የሚያመስስላቸው አንድ ነገር ቢኖር፣ ፈጣሪ የአገልጋዮቹን ምኞቶች ከማሳካቱ በፊት በራሳቸው ጥንካሬ ላይ ያላቸው መተማመን ፈጽሞ እንዲፈራርስ ማድረጉ ነው። ይህ ጭብጥ ታዲያ በብሉይ ኪዳን ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ ለአዲስ ኪዳንም ዋና መሠረት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚነግረን፣ ኦሪት የተሰጠችው አማኞች ተከትለዋት እንዲድኑ ሳይሆን፣ "ኃጢአትን በመግለጽ" ፈጽመው በራሳቸው ጥረት መዳን እንደማይችሉ ለማሳየት ነበርና። ታዲያ በእግዚአብሔር ላይ ያለን ጥገኝነት በመከራና በውድቀት ጊዜያት ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ እያንዳንዷን የሕልውናችንን ቅጽበት የሚመላ ነው። በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ እውነት ታምኖ መኖር ደግሞ (በተለይም የሰው ልጅ ቴክኖሎጂያዊ አቅም በፈረጠመበት በእኛ ዘመን) ትልቅ የእምነት ደረጃ የሚጠይቅ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚደርሱበት፣ በዚህ ደረጃ ላይ ለመቆየትም ያላሰለሰ መንፈሳዊ ጥረትና ትኩረትን የሚጠይቅ የእምነት ከፍታ ነው። ስለዚህ፣ "እግዚአብሔር ላይ ምን ያህል ጥገኛ ነኝ?" የሚለው ጥያቄ ዘርፈብዙ መንፈሳዊ ተጋድሎን የሚጠይቅና በግሌ ልወጣው የሚገባ ፈተና እንጂ፣ እንደ ቶማስ አኳይናስ ያሉ ቲዮሎጂያኖች እንደሞከሩት¹፣ ረቂቅና ውስብስብ አመክንዮአዊ ሙግቶችን ተጠቅሜ የምመልሰው ጥያቄ አይደለም። "አመክንዮአዊ እምነት/Rational Faith" የሚለውን አያዎ አካሄድ አጥብቀን መቃወም ያለብንም ለዚህ ነው። የክርስትና ጥያቄዎች በስሜት (Passion) እና ግላዊ እምነት (Personal faith) የሚመለሱ እንጂ፣ ከኢ-ወገንተኛ ፍልስፍና ጀርባ ተደብቄ የማመልጣቸው መሆን የለባቸውምና። ¹ ቶማስ አኳይናስ የእግዚአብሔርን መኖር ለማረጋገጥ ከሚጠቀምባቸው ሙግቶች አንዱ፣ "አስፈላጊ ያልሆኑ (Contingent) ነገሮች በሙሉ የግድ ቀዳሚ ምክንያት ስላላቸው፣ ሰዎችን ጨምሮ ሕልውና ያላቸው ነገሮች በሙሉ ለሕልውናቸው በአንድ የበላይ ምክንያት (Supreme Cause) ላይ ጥገኛ ናቸው" የሚለው ሙግት ነው። ከላይ እንዳልኩት፣ መሰል ሙግቶች ሕያው የሆነውን የእምነት ትግል የሚገድሉ፣ ግለሰቦች ከእግዚአብሔር ጋር መታገል አቁመው፣ ምቹ ሰዋዊ ሙግቶች ላይ እንዲደገፉ የሚያደርጉ ስለሆኑ ውድቅ ሊደረጉ ይገባል። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegramየዛሬዋ ቀን፣ የወንጌልን እውነት በድርሰቶቹና በሕይወቱ የመሰከረው ሶረን ኪርክጋርድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየባት ቀን ናት። ሶረን መቃብሩ ላይ ይህ አጭር ጽሑፍ እንዲቀረጽ ተናዝዞ ነበር፦ ጥቂት ጊዜ ብቻ፣ ድል አደርጋለሁ፤ በአንዲት ቅጽበት ትግሌን ጨርሳለሁ በአበባዎች ጥላ፣ ከድካሜ አርፋለሁ ያለማቋረጥም፣ ከኢየሱሴ ጋር፣ እነጋገራለሁ @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"ክርስትና በማስረጃ ካልተረጋገጠልኝ በቀር አላምንም" የሚለው ትዕቢታዊ አቋም በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል ምናምንቴ እንደሆንን ከመዘንጋት የመነጨ ነው። እንዲህ አይነት የድፍረት ቃል የተነገረው ነቢዩ ኤልያስ ቢሆን ምን ይፈጠር ነበር? "እኔ የእግዚአብሔር ሰው እንደሆንኩ፣ እሳት ከሰማይ ትውረድ፣ እናንተንም ታጥፋ" ብሎ አይመልስምን? (2ኛ ነገሥት 1:12) እግዚአብሔር ለነቢያቱ ስልጣን እንኳን ይህን ያህል አጽንኦት ከሰጠ፣ ከተተበተብንበት የኃጢአት እስራት ሊያወጣን የመጣውን ልጁን፣ "ማስረጃ"፣ "ሙግት" ምናምን በሚል እንቶ ፈንቶ የምንፈታተነው እኛንማ ምን ያህል ፍርድ ይጠብቀን ይሆን? እምነት የክርስትና አስራ አንደኛው "ትዕዛዘ ኦሪት" ነው። ለክርስቶስ መንግሥት የተገባ እምነት እንዳለን ራሳችንን እንፈትሽ እንጂ፣ ሰዋዊ አመክንዮን ተጠቅመን የክርስቶስን አምላክነት አንፈትሽ። ጌታ እንዳለው "እርሱ እንደሆነ ካላመንንን" በኃጢአታችን እንሞታለንና (ዮሐንስ 8:24)። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegramየአልበርት ካሙ "የሲሲፈስ አፈታሪክ" ላይ የተጻፈ ኑባሬያዊ ትችት/ሂስ። ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ! https://theexistentialchristian.substack.com/p/an-existential-critique-of-albert?utm_source=share&utm_medium=android&r=8mwxjb
Открыть в Telegramክርስቶስ "ተዓምራትን ሊያደርግ ያልቻለባት" ብቸኛ አገር እምነት ያላገኘባት ናዝሬት ነበረች (ማርቆስ 6:5፣ ማቴዎስ 13:58)። የሰው አዕምሮ ከእምነት ጉድለት የተነሳ የእግዚአብሔር ኃይል ላይ ከሚጥላቸው ሐሳዊ ወሰኖች ውጪ የእግዚአብሔርን ኃይል መገደብ የሚችል አንዳች ነገር እንደሌለ ወንጌል ያስተምረናል። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤ እኔን የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ ትሆን ዘንድ፣ እኔም በእነርሱ እሆን ዘንድ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።" ዮሐንስ 17:25-26 @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegramስለ እግዚአብሔር ኢ-ወገንተኛ እውቀት ማግኘት እችላለሁ? ከሥነ-መለኮት የምርቅበት ምክንያት! https://theexistentialchristian.substack.com/p/96e?utm_source=share&utm_medium=android&r=8mwxjb
Открыть в Telegramበአንድ ወቅት የኤቲዪዝም ሐዋርያ የነበረው ክሪስቶፈር ሂችንስ እንዲህ ብሎ ነበር፦ በጣም ትዕቢተኞች ነን። አጽናፈ ዓለሙ በሙላ የተፈጠረው እኛን ታሳቢ በማድረግ ነው ብለን እናምናለን... ከዚህ ከንቱ አስተሳሰብ ለመላቀቅ ብዙ ይጠይቃል። የመጨረሻዎቹ ሁለት ቃላት ("ብዙ ይጠይቃል") interesting ናቸው። ይህን የሂችንስ ንግግር ከቁብ ከቆጠርነው፣ "ዓለም ለእኛ ተብሎ ተፈጠረ" ከሚለው እይታ ለመላቀቅ አስፈላጊ የሆኑት እነዚህ "ብዙ' ነገሮች፣ ምንም ሆኑ ስንት፣ ሂችንስ በምልዓት ይዟቸዋል ማለት ነው (ያለበለዚያ እንዴት ኤቲዪስት ይሆናል?)። የሂችንስን ንግግር በሌላ መልኩ መግለጽ እንችላለን፦ እዚህ ግባ የሚባል ዋጋ የሌለን ፍጥረታት ነን...ይህንን መራራ እውነታ ለመቀበል የሚያስችል ብልህነት፣ ትሕትና እና ሀቀኝነት ካላቸው ጥቂት ልዩ ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱ እኔ ነኝ። በብዙ ኤቲዪስቶች ላይ ለምናየው፣ የሰው ልጆችን እንደ ዝርያ እያንቋሸሹ፣ ራስን (በተለይም የአዕምሮ ብቃትን) የመኮፈስ ዝንባሌ፣ ከዚህ የተሻለ ግልጽ ምሳሌ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ከእንዲህ አይነት አባዜ ለመላቀቅ ብዙ ይጠይቃል (pun intended)። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegramሉተር "በእምነት ብቻ" ሲል ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ፈጣሪና መላእክቱ ናቸው የሚያውቁት። እኔ ግን የማመንን ያህል ከባድ ነገር ያለ አይመስለኝም። በእርግጥ አንዳንድ ቲዎሎጂያኖቻችን እንደሚያደርጉት ቆንጆ ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ፣ ቡና እየጠጡ፣ ስለ ፈጣሪ ታማኝነት ማውራት ብዙ ላይከብድ ይችላል። እንደ ኢዮብ የስቃይ መዓት ከወረደብኝ በኋላ "ቢገድለኝ እንኳን አምነዋለሁ" ብሎ መናገር ግን ሌላ ታሪክ ነው። "በእምነት ብቻ"— ልጆቿ የሚለብሱት ልብስ ሰፍታ ስትጨርስ "አሁን የቀረኝ ልጅ መውለድ ብቻ ነው" ያለችውን በቅሎ ያስታውሰኛል። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"መቼም ቢሆን ዴካርትን ይቅር አልለውም፤ ከፍልስፍናው እግዚአብሔርን ጠቅሎ ቢያስወግደው ደስ ባለው ነበር። ዓለም መጓዝ እንድትችል፣ ፈጣሪ ትንሽ ግፊት እንዲሰጣት ከማድረግ ባለፈ ለእግዚአብሔር ምንም ቦታ የለውምና።" - ብሌይስ ፓስካል በእርግጥም የአመክንዮን ሁሉን ቻይነት የሚያቀነቅኑ ፈላስፋዎችና የሥነ-መለኮት ልሂቃን፣ እግዚአብሔርን በቅርባችን እንደሚገኝ ግላዊ (Personal) አምላክ ሳይሆን፣ የፍልስፍናን እንቆቅልሽ ለመፍታት እንደሚጠቅም ምናባዊ መልስ ማየት ከጀመሩ ሰነባብቷል። በዚህ መጣጥፍ፣ አመክንዮአዊነትና የግሪክ ፍልስፍና እንዴትና ለምን እግዚአብሔርን ከአማኞች ልብ እንዳራቁት እገመግማለሁ። ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ! https://theexistentialchristian.substack.com/p/fa3?utm_source=share&utm_medium=android&r=8mwxjb
Открыть в Telegramፍሬድሪክ ኒቼ በ 1888 እንደጻፈው በሚገመት አንድ ደብዳቤ፣ ሶረን ኪርክጋርድን በስም ጠቅሶ ሥራዎቹን የማንበብ እቅድ እንዳለው ተናግሮ ነበር። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ የኒቼ እቅድ ሳይሳካ በበሽታ ተይዞ ወደቀ። ኒቼ በዙሪያው የነበሩት ክርስቲያኖች ላይ ያስተዋለው "አፍላጦናዊነት"፣ "ጸረ-ሕይወታዊነት"፣ "ተስፋ መቁረጥ"፣ "ጸረ-ተዋረድ/Anti-hierarchism" ወዘተ የግሪክ ፍልስፍና የበረዘው "ክርስትና" እንጂ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑን ቢረዳ ኖሮ፣ ስለ ክርስትና ያለው አቋም በእጅጉ ይለወጥ ነበር ብዬ አምናለሁ። "ኒቼ ኪርክጋርድን አንብቦ ቢሆን ኖሮስ?" የሚለው ጥያቄ ሁልጊዜ ከሚያስቆጩኝ ጥያቄዎች አንዱ ነው። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም። እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ... እኔ ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና። ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ። ደቀ መዛሙርቱ። እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ በምሳሌም ምንም አትነግርም። ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። አሁን ታምናላችሁን? እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም። በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።" ዮሐንስ 16፡20-33 @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"እምነት ምንድነው? ማስረጃ ተከትሎ መሄድ፣ ወይስ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ምርጫ?" አድምጡት! በጣም ጠቃሚ መልዕክት ነው። @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram"ጻድቅ ኢዮብ ሆይ፣ በወጣትነትህ ዘመን ለተጨቆኑት ሰይፍ፣ ለአረጋውያንና ለተረገጡት ደግሞ ምርኩዝ የነበርክ አንተ፣ ነገሮች ሁሉ በፈራርሱብህ ሰዓትም ሰዎችን አላሳዘንክም። በዚያን ጊዜ ለተጨቆኑት ድምፅ፣ ለደነገጡት ጩኸት፣ በፍርሃት ለተያዙት ዋይታ፣ ስቃይ አፋቸውን ለዘጋው ደግሞ መጽናኛ ሆንክ። የሰው ልብ አምቆ ስለሚይዘው ጭንቀትና ስቃይ ታማኝ ምስክር ይሆን ዘንድ፣ «በመራራ ነፍስ» ቅሬታ ለማቅረብና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታገል የደፈረ ታማኝ ተሟጋች አንተ ነህ። ይህን እውነታ ለምን እንደብቀዋለን? መበለቶችንና ወላጅ አልባ ህጻናትን ለሚበድልና ውርሳቸውን ለሚነጥቅ ወዮለት፤ ነገር ግን ሐዘን የሰበራት ነፍስ፣ ሐዘኗን እንዳትገልጽና ‘ከእግዚአብሔር ጋር እንዳትከራከር’ ጊዜያዊ የሐዘን እፎይታዋን ለሚነጥቋት በደለኞችም ወዮላቸው።" - ኪርክጋርድ @Jacobite_apologetics27
Открыть в Telegram