السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 📢 CALLING ALL GC MALE STUDENTS OF HAWASSA UNIVERSITY! We warmly invite all GC male students from Hawassa University Main Campus and Institute of Technology (IoT) to join our Telegram community. This platform aims to connect students, share important information, exchange ideas, explore opportunities, and encourage knowledge-sharing and mutual support. 🌙 A Reminder from the Sunnah The Prophet Muhammad ﷺ said: «المؤمن للمؤمن كالبنيان يشد بعضه بعضًا» A believer to another believer is like a building whose different parts strengthen one another. — Sahih al-Bukhari and Sahih Muslim Let us build a community based on respect, knowledge, cooperation, and unity. 📌 JOIN OUR TELEGRAM COMMUNITY: 🔗https://t.me/HUMSJ_GC 📢 Kindly share this invitation with other GC students to help us reach everyone. جزاكم الله خيراً وبارك الله فيكم. Together in Unity, Knowledge, and Progress! 🤝
Open in TelegramPosts of ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ🌹 HawassauniversityMuslimstudents Jema'ah
(التفاخر بالأنساب ) قال رجل لزهير بن نعيم : ممن أنت يا أبا عبد الرحمن ؟ قال : ممن أنعم اللّٰه عليه بالإسلام قال : إنما أريد النسب . قال : فإذا نفخ في الصور فلا انساب بينهم يومئذ ولايتساءلون "
Open in Telegramالسلام عليكم ورحمة الله وبركاته🌙✨ ♻️አዲስ እና ታላቅ የደርስ ማስታወቂያ 📢 " أفلا يتدبرون القرآن ولو كان من عند غير الله لوجدوا فيه اختلافا كثيرا " «ቁርኣንስ አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር።» (ሱረቱ አን-ኒሳእ፡ 82) የቁርአንን ቃላት እና ጥልቅ መልእክት ማወቅ ሕይወትን ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያሻገር 💡፣ የነፍስ ዕረፍት እና የልብ ዋጋ ነው። የአላህን ቃል ትርጉም ተረድቶ መማር ማለት ከእሱ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር 🤲፣ የሕይወትን ትክክለኛ ጎዳና ማግኘት እና የሁለት ዓለም ዕድለኝነትን መቀዳጀት ማለት ነው። 🌟 በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው እና ልባችንን በዕውቀት ያለመልማል በለን በእጂጉ ተስፋ የምናደርገው ይህ የቁርአን ተፍሲር (ትርጉም እና ትንተና) መርሃ ግብር፣ በቁርአን ዕውቀታቸውና የቂርኣት አቀራረብ ጥራት በሚታወቁት በኡስታዝ አብዱሰላም ሼክ ሐሰን እነሆ ዛሬ ቅዳሜ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በላቀው አላህ ፈቃድ የሚጀምር መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን። ስለሆነም ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች 🎓፣ ተማሪዎች እና የከተማችን ነዋሪዎች መላው የቁርአን ወዳጆች በዚህ ታላቅ እና መንፈሳዊ ማዕድ ላይ በመገኘት የእውቀት አድማሳችሁን አስፉ ነፍሳችሁን የእውቀት ማእድ መግቡ ብለን ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን። * ደርሱን የሚሰጡት፡ ኡስታዝ ዐብዱስሰላም ሸይኽ ሐሰን * 📍 ቦታ፡ አልሁዳ የተማሪዎች መስጂድ * 📅 ዕለት፡ ቅዳሜ እና እሁድ * ⏰ ሰዓት፡ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ ይህንን መልዕክት ለሌሎች በማድረስ እና ሼር በማድረግ በኸይር ስራ ላይ አብረውን ይሁኑ :: ወስሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ
Open in Telegramالسلام عليكم ورحمة الله وبركاته ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ያደረጋችሁ ወንድምና እህቶቻችን፦ በቅድሚያ አላህ በሰላም ያምጣችሁ እያልን፤ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እናንተን ለመቀበል ዝግጅታችንን ጨርሰን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን። ማንኛውንም ድጋፍ እንዲሁም ስለ ግቢውና ህብረታችን መረጃ (Information) ለማግኘት እነዚህን የተመደቡ የህብረታችን አባላት ማግኘት ትችላላችሁ:: 👉 Main Campus ☎️ 0942213321(አቡዱረዛቅ) 👉 Techno Campus ☎️ +251925882521 (ዐማር) 👉Daye campus ☎️ +251953841218 (Abdurrehman) 👉Wendogenet campus ☎️ 0974019239 (Hayder) 👉Awada campus ☎️ 0994366361 (Ahmadin Ibrahim) 👉Agriculture campus ☎️ 0951525785 (Abubeker Nesredin) 👉Riferral Campus ☎️ 0987447440 (Semeredin Khelil) 🧕 ለእህቶች ልዩ ማስታወሻ፦ አዲስ የምትገቡ እህቶች የሴት ተወካዮችን ለማግኘት በየግቢ ተወካዬች ስልክ ቁጥር ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት 🌹 አላህ በሰላም ያገናኘን! https://t.me/hawassauniversitymuslimstudentso
Open in TelegramForwarded from Al Hidaya The Channel Media Of Sunnah Jama'a founded by students at Hawassa University
السلام عليكم ورحمة اللله وبركاته. ቀልባችን በናፍቆት ተንጠልጥሎ ቀናትን እየቆጠርን በጉጉት ስንጠብቅ፤ ወደ ሃዋሳ ለመሄድ ግማሽ ቀን ሲቀር በተደወለ አንድ ስልክ የቤተሰብ ሞት በድንገት ተነገረን። እናማ ሳወልድ በግዴ የጉዞዬን አቅጣጫ ወደ ደሴ አደረግኩ። ውድ ወንድምና እህቶቼ በሁለት ነገር ውስጤ አዝኗል። እናንተን በመለየቴ እና በሞተው ቤተሰቤ። አላህ ይማረው። አረሕማን መልካም ኢጅቲማዕ እና ወየልካም ያድርገው። ወሰላም 👌
Open in TelegramForwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወረፋን አለመጠበቅ ~ ወረፋ በሚጠበቅበት የትኛውም ቦታ ላይ የቀደሙ ሰዎች እያሉ በጉልበትም ይሁን በመሸወድ ቀድሞ መግባት ነውረኛ ተግባር ነው። የታክሲ፣ የውሃ፣ የክፍያ ቦታዎች፣ ሃኪም ቤቶች፣ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች፣ ... ከኛ የቀደሙ ተገልጋዮች እያሉ በየትኛውም ጤነኛ ባልሆነ መንገድ ቀድሞ ተጠቃሚ መሆን አላህን ለሚፈራ ሰው ሞኝነት እንጂ ብልጠት አይደለም። ይልቁንም ነፍሰ ጡር እና ልጅ የያዙ እናቶችን፣ ህመምተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አዛውንቶችን ማስቀደም አጅር ያለው ተግባር ነው። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
Open in Telegramاللَّهُمَّ عَافِيَةً تُصَاحِبُ أُمِّي وَأَبِي كَظِلِّهَا አላህ ሆይ! ለእናቴና ለአባቴ እንደ ጥላ የሚከተላቸውን ጤና ስጣቸው። رَبِّ إِنَّ وَالِدَيَّ خَيْرُ مَنْ أَحْسَنَ إِلَيَّ فَجُدْ عَلَيْهِمَا بِإِحْسَانِكَ وَجَازِهِمَا عَنَّا خَيْرَ مَا جَزَيْتَ ጌታዬ ሆይ! ወላጆቼ ለእኔ መልካም ካደረጉልኝ ሁሉ የበለጡ ናቸውና በቸርነትህ መልካሙን ነገር ሁሉ ወፍቃቸው፤ ለእኔ ሲሉ ላደረጉልኝም በጎ ነገር ሁሉ የተሻለውን ምንዳ ክፈላቸው። እኔ ደካማው ባሪያህ የነሱን ውለታ ምንም አድርጌ ልፍለው አልችልም ያያያያረብ . . . ! https://t.me/qewlenlleyyna https://t.me/qewlenlleyyna
Open in Telegramወደ ካንፓስ አድስ ገቢ ለሆኑ እህቶች የተጫረች ነች። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ #የካንፓሷ___እንግዳ!! ➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤ ጥንቃቄ አድርጊ በግ ተራ እንዳቴጂ፡ የነቃሁኝ መስሎሽ እንዳትገረጂጂ፡ ለአንች አይመጥንሽም መቆም ከበግ ተራ፡ የሸይጧን መረብ ነው የወንጀል ጎተራ፡ ➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠ ከወንጀል ቦታ ላይ አንች መገኘትሽ፡ መሆኑን እወቂ አላህን ማመፅሽ፡ ቆም ብለሽ አስቢ እህቴ ልምከርሽ፡ በኒቃብሽ ደምቀሽ ከወንጀል ራቂ ፡ ጀግና እንስት ሁኝ የድንሽ ጠባቂ፡ ➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠ ከወንጀሉ ቦታ ቆመው ምታያቸው፡ አላህን ያመፁ ደፋር ህዝቦች ናቸው፡ ሸይጧንን አርገዋል ሩል ሞደላቸው፡ ሸይጧን አታስደስች እህቴ አደራሽን፡ በጂልባብሽ ደምቀሽ ጠብቂው ክብርሽን፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ምርጥ የሱና ወጣት ትዳር ለመፈለግ፡ መጠንከር አለብሽ ፤ በሀቅ ላይ መፅናት ከወንጀል መሸሸግ፡ በሱና መጠንከር ከቢድዐ ማፈግፈግ፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ከካንፓስ ስትገቢ ጥንቃቄ አድርጊ፡ በምታይው ነገር እንዳትበረግጊ፡ ርቄ ሔጃለሁ ብለሽ አትጃጃይ፡ አለብሽ ጠባቂ ከላይ ሁሉን የሚያይ፡ በፍፁም አትገኝ ፤ ከቆሻሻ መስሪያ ከርክሰት ቦታ ላይ፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ለምን ትገኛለሽ ፈጣሪን ከረሳ አላህን ካመፀ፡ ልብሱን ከቀደደ ፀጉሩን ከቀረፀ፡ ይህ ወንጀል ነውኮ ኸረ ተመከሪ፡ አጀልሽ ሣይመጣ ተይ አላህን ፍሪ፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ አንችም እንዳትቀኒ በበግ ተራው ስራ፡ ቆፍጣና ሴት ሁኝ በእምነቷ እምትኮራ፡ እህህ በአንዳንድ እህቶችስ ፤ ስንቱን ጉድ ሰማሁት!?? አንጀቴ እያረረ ስንቱንስ አየሁት!?? ኸረ በአላህ! በአላህ! በአላህ! እህቶቼ! ከመከፋት ውጭ ምናባቴ ልበል፡ ከካፊሩ ወጣት ፍቅር ስትቀበል፡ ሙስሊሙ ለትዳር ደፍሮ ሲጠይቃት፡ ቀልድና ጨዋታ ሣቅ ሲተናነቃት፡ ኸረ ተመከሪ ካንች አይጠበቅም፡ ሙስሊም ኒካህ እንጂ ዝሙትን አያውቅም፡ ➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠ ወንጀል አትድፈሪ በፍፁም አትመጭ፡ ትዳርሽን አክብሪ አድበሽ ተቀመጭ፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ለማንኛውም የግቢ እንግዳዋ፡ የኢስላም ባለቤት አስተዋይ ጀግናዋ፡ እየመከርኩሽ ነው ታገሽ ውድዋ፡ ➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳➳ ሙስሊሚቷ እህቴ ወጣቷ ኮረዳ፡ በግ ተራ እንዳቴጂ የካንፓሷ እንግዳ፡ <======================> ኑረድን አል–አረቢ(2012) ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ https://t.me/nuredinal_arebi https://t.me/nuredinal_arebi ➖➖➖➖➖➖➖➖
Open in Telegramአሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ 🌙✨ የዳዕዋ ጥሪ 📢 ውድ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ (የሜይን እና ቴክኖ ካምፓስ) ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ (በተለይ አዲስ ገቢ ፍሬሽማን ወንድምና እህቶቻችን) 👋🎓 በመጀመሪያ ደረጃ እንኳን ወደ ሁለተኛው ቤታችሁና ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ እንኳን በሰላም መጣችሁ! 💐✨ የትምህርት ዘመናችሁ የስኬት፣ የሰላም እና የበረካ እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን መልካም የአቀባበል መልእክታችንን እናስተላልፋለን። በመቀጠልም ይህንን አዲስ የካምፓስ ህይወታችሁን በደስታና በጥንካሬ እንድትጀምሩ የሚረዳችሁ ትልቅና ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል! 🎁🎉 ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ 🕌 ልዩ ልምድ ባላቸው ኡስታዛችን የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል። 🌟 በዕለቱ የዩኒቨርሲቲ ቆይታን (University Life) በብቃት ማሳለፍ፣ የዕለት ተዕለት ጭንቀቶችን (Tension) መቋቋም፣ ዲናችንንና ዱንያችንን እንዴት ጎን ለጎን አብረን ማስኬድ እንዳለብን ጥልቅ ማብራሪያ ይሰጥበታል። 📚💡 በግቢ ቆይታቸው ብዙ ልምድ ባላቸውና ራሳቸውም የዩኒቨርሲቲ ህይወትን ባሳለፉት በተከበሩት ኡስታዝ ኸድር የሚቀርብ በመሆኑ፣ ልብ የሚነካና እጅግ አስተማሪ ፕሮግራም ይሆናል! 🎙️❤️ 👥 ማን ሊገኝ ይችላል? ሴቶችም ወንዶችም (ሁሉም ተማሪዎች በክብር ተጋብዛችኋል!) 📍 ቦታ፡ የተማሪዎች መስጅድ (አል-ሁዳ መስጅድ) ⏰ ሰዓት፡ ነገ ከመግሪብ ሰላት በኋላ ወዲያውኑ 🌙 ሁላችሁም ሳትቀሩ እንድትገኙና የዚህ በረካ ተካፋይ እንድትሆኑ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! እንዳትቀሩ! 🤝 ጀዛኩሙላሁ ኸይረን! 🤲 የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዐ
Open in Telegram(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም። "ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።" (13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል። "የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።" (14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ። "የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።" (15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አስተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት። ሰላም! = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Open in Telegramጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች ~ ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል። ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል። ① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ። "አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።" "ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።" ② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ። ③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው። "ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።" ④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው። "ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።" ⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ። "Education is a better safeguard of liberty than a standing army." ⑥ ራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ። አንተ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም። "ራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።" ⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሃብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል። እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮችን ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው። "ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።" "አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ ራስህ እያለፍክ ነው።" ⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ ራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ። "ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።" ⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ። ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ። "ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።" (10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ ቴኳንዶ፣ የእጅ ሙያዎች፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ። "ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።" (11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን። "ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።" "ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"
Open in Telegram✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨ 📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን። 🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው። በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን። 🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡ የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ: https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6 ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡- ✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ። ✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ። 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡- 📚 Main campus =>ሀሰን ☎️ 090 632 6702 =>አቡዱረዛቅ ☎️ 0942213321 =>ነቢል ☎️ 096 999 0090 =>ጂፋር affan orromo ☎️ +251972575000 💻 Techno campu =>ዐማር ☎️+251925882521 =>መስዑድ affan oromo ☎️ +251937517651 =>አስዓድ ☎️ 0963298664 🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር ☎️ +251925882521 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። 🌹 አላህ በሰላም ያገናኘን 🤲🌹 🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉
Open in TelegramForwarded from Hawassa University Muslim Students Jemea (HUMSJ) official channel.
ልዩ የደዕዋ ጥሪ 📢 የተወደዳችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎችና የጀመዓችን ወንድም እና እህቶች! 🎓👥 በትምህርት ዘመናችሁ አላህን የምትፈሩበትን ስንቅ የምትይዙበት፣ ከአካዳሚክ ህይወት ጋር በዲናችሁ ላይ ጥንካሬን የምታጣመሩበትና የምትተዋወቁበት ልዩ አጋጣሚ ነው! 🤲✨ 📌 ፕሮግራም አድራሻ፡ 📅 ቀን፡ ነገ ሰኞ 🕒 ሰዓት፡ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ሶላት 📍 ቦታ፡ አል ሁዳ የተማሪዎች መስጂድ 🕌 ✨ ጓደኞችዎን ይዘው በመምጣት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ! 🕌📚
Open in TelegramForwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እህቶቻችንን ለማነው የምንተዋቸው? ~ "ባለ ዲኗን ምረጥ" የተባለው እንዲተገበር እንጂ ወሬ ለማሳመር አይደለም። ነፍስያህን እያስቀደምክ በሰንካላ ምክንያቶች ለመሸፋፈን አትሞከር። ባለ ዲኗ እህትህን ለመጥፎ ምርጫ እየገፋህ፣ አልባሌ ቦታ ላይ ስትወድቅ ጠብቀህ ጭንቅላትህን ብትነቀንቅ ምን ትርጉም አለው?! ወንድሜ ነብያዊው ምክር ዋጋ ይሰጠው። "ባለ ዲኗን ምረጥ።" ትርጉሙና ዋጋው ብዙ ነውና። ይህንን ስታደርግ ለራስህም፣ ለልጆችህም፣ ለምታገባት እህትህም፣ ለማህበረሰብህም ትልቅ ውለታ እየዋልክ እንደሆነ እወቅ። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 20/2012) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
Open in TelegramForwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አሰላሙ ዐለይኩም ~ ባለፈው ሳይመቸኝ በመቅረቱ የተላለፈው ሰይድ ቁጥብን የሚመለከተው ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3፡00 ላይ ይኖራል። በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ :- የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
Open in TelegramForwarded from قَولًا لَيّنًا (A B)
1. ፊደላትን በስም እና በሐረካት በዝርዝር ከመበተን ይልቅ ቀጥታ በድምፃቸው ማነበብ እንድችሉ ይረዳል። ምሳሌ፡ በኑራኒያ «ጂም ፈትሃ ጀ» የሚለውን፣ በመደኒያ ቀጥታ «ጀ» ብሎ በማንበብ አላስፈላጊ ልፋትን ያስቀራል። 2. ረጅም ቀመሮችን በጭንቅላት ለመያዝ የአእምሮ ጫናን አይፈጥርባቸውም ለዚህም ልጆች ወዲያውኑ ቃላትን በቀላሉ እንድይዙ ያደርጋል ። ምሳሌ፡كَتَبَ የሚለውን ቃል ለማንበብ፦ በኑራኒያ «ካፍ ፈትሃ ከ፣ ታ ፈትሃ ተ፣ ባ ፈትሃ በ» ብለው ከመድከም ይልቅ በመደኒያ ቀጥታ «ከ - ተ - በ» ብለው በፍጥነት አያይዘው ያነባሉ። 3. የፊደላት ቅርጽ መቀያየርን በቀላሉ ያሳውቃቸዋል ይህ ማለት ፊደላት ከመጀመሪያ፣ ከመካከል እና ከመጨረሻ የሚኖራቸውን ቅርፅ በግልጽ ያሳያል። ምሳሌ፡«ع» የሚለው ፊደል ብቻውን ሲፃፍ (ع)፣ ከመጀመሪያ (عـ)፣ ከመካከል (ـعـ)፣ እና ከመጨረሻ (ـع) የሚኖረውን ቅርፅ ጎን ለጎን በማስቀመጥ ያለማምዳቸዋል። 4. ከቀላል ወደ ከባድ ደረጃ በደረጃ ያሸጋግራል፤ ከአንድ ፊደል ወደ ሁለት፣ ከሁለት ወደ ሶስት ፊደል ደረጃ በደረጃ ያሸጋግራል። ምሳሌ፡ በመጀመሪያ «በ»፣ በመቀጠል «በ-ተ»፣ በመጨረሻም «በ-ተ-ረ» (بَتَرَ) በማድረግ ያለ ስጋት ያሰለጥናቸዋል። 5. የሐረካት ድምፆችን በቀላሉ ለመለየት ያስችላቸዋል (ፈትሃህ፣ ዶማሀህ፣ ከስራሀህ)። ይህ ማለት ከቃኢደቱንኑረኒያህ በተለየ መልኩ የሐረካዎችን ልዩነት በድምፅ ደረጃ ብቻ ወዲያውኑ እንዲለዩ ያደርጋል። ምሳሌ፡«بَ» (በ)፣ «بُ» (ቡ)፣ «بِ» (ቢ) በማለት የሐረካውን ለውጥ በምላስ ላይ ወዲያውኑ ያለማምዳቸዋል። "ባ ፈትሃ በ" ብሎ መድከም ቀረ ማለት ነው። 6. ስኩን ያለበትን ፊደል ከፊቱ ካለው ፊደል ጋር ቀጥታ ማጣመርን ያስተምራል። ምሳሌ፡«أَلْ» ለማንበብ «ሀምዛ ፈትሃ ላም ስኩን አል» ሳይባል፣ ቀጥታ «አል» ብሎ በማንበብ ያሳጥራል ለምላስም ቀላል ይሆናል። 7. የተንዊን (የ’ን’ ድምፅ) አነባበብ ማቅለል፤ተንዊን ማለት በቃሉ መጨረሻ ላይ የሚጨመር የ'ን' ድምፅ መሆኑን በተግባር ማሳየት ነው። ምሳሌ፡ "ባ ፈትሀተይን በን" ከማለት ይልቅ በቀጥታ «بً» (በን)፣ «بٌ» (ቡን)፣ «بٍ» (ቢን) በማለት በድምፅ ብቻ እንድጠሩት ያደርጋል። 8.የልጆችን የስነ-ልቦናዊ ፍርሃት ማስወገድ:- ህጻናት በአጭር ጊዜ ተረድተው ወደሚቀጥለው ገጽ ብዙም ሳይቆዩ በቀላሉ ስለሚያልፉ የስኬተኝነት ስሜት ያድግባቸዋል።በሁለት ሳምንት ውስጥ ሙሉ ቃላትን ማንበብ ሲጀምሩ «ቁርኣን ቀላል ነው» የሚል እምነትን ያደብራሉ። 9. ለአጠቃላይ የአረብኛ ቋንቋ ንባብ መሰረት ይሆናል: ለቁርኣን ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአረብኛ መጽሐፍ ንባብ መንገድ ይከፍታል። ደርሶቹ አጭርና ግልጽ በመሆናቸው ህጻናት ሳይሰለቹ ይማራሉ። 💥 አጠቃላይ ከላይ ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉ ሌሎችንም የቂርኣት ህግጋቶች በጣም በቀላል መልኩ እና ግልፅ በሆነ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበበት ለጀማሪዎች የሚሆን ድንቅ ኪታብ ነው። ኪታቡ በ pdf👇👇👇 https://t.me/qewlenlleyyna/70 https://t.me/qewlenlleyyna https://t.me/qewlenlleyyna
Open in Telegram