Account

Posts of Hasen Injamo

newest first

#6623Text
Views272−91%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#6622Photo
Views1,280−59%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#6621Text
Views1,760−44%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#6620Photo

ዛሬ የአፍሪካን የክፍያ ሥርዓት (African Payment Systems) የተመለከተ እጅግ ጥሩ ኮንፈረንስ ተካፍለን ነበር። በተለይ በጉጉት ስጠብቀው የነበረ ኮንፈረንስ ነው። እያንዳንዱን ውይይት በትምህርት ክፍል ውስጥ እንዳለሁ በትኩረት ተከታትያለሁ። የአውሮፓ አገራት ወደ አንድ የክፍያ ሥርዓትና የጋራ መገበያያ ገንዘብ (ዩሮ) እንዴት እንደተሸጋገሩ ያብራሩት ዶ/ር ክሪስ ፒርክነር የዩሮ ዞንን ተሞክሮ ሲያቀርቡ ትኩረቴን በጣም ስበውታል። አውሮፓ ምን ዓይነት ፈተናዎች ገጠሟት? አፍሪካስ ከዚህ ተሞክሮ ምን መማርና ምን ማድረግ አለባት? የሚሉት ጥያቄዎች ያተኮረ አጭርና ጥልቅ ውይይት ነበር። የEthSwitch ኃላፊ አቶ ይለበስ አዲስንም ሙሉ ቀን ብቻ ሳዳምጣቸው ብቆይ ደስ ባለኝ ነበር። ለምን መሰላችሁ? እኔ ከዶላር ኢምፓየር እንዴት መውጣት እንችላለን፣ ወይስ አንችልም? የሚለውን ጥያቄ በተለያዩ ሁኔታዎች (Scenarios) በ«መ-ገንዘብ» መጽሐፌ ውስጥ በሰፊው ዳስሼዋለሁ። ግን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ የተዳሰሰውን ጉዳይ በተግባር ደረጃ የት እንደደረሰ ለማወቅ እንዲህ ባለ መድረክ ላይ ተሰብስቦ ሲቀርብልህ፣ ቁጭ ብለህ ነው የምትቀምሰው። (ቆሎ ነው ደግሞ!) ምስል፦ ዶ/ር ክሪስ ፒርክነር (CEO, Bluecode; Co-founder, European Mobile Payment Systems Association)

Open in Telegram
Views2,520−20%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#6618Text

”… ሽፈራው ጌታቸው የሚጽፈውን አታይም? ዘመድኩን ምን እንደሚል አታይም?…” ይሉኛል። ሽፈራው ጌታቸው በለው፣ ዘመድኩን በለው፣ አመዲን ጀበል በለው፣ ድእእእሮ ቦልኬያቸዋለሁ፤ ወይም unfollow አድርጌያቸዋለሁ። ምክንያቱም በሃይማኖት ጉዳይ ... አይደለም ...ሙስሊም ካልሆኑ ተናታራኪዎች ቀርቶ፣ ከሙስሊም ተናታራኪዎች ምን ልማር እችላለሁ? ምንም! ጸብ ብቻ! ያሰላም! ሶሻል ሚዲያ ላይ በተማረበት ሙያ ላይ ተመስርቶ ሐሳብ የሚያቀርብ ሰው ጥቂት ነበር። አሁን ትንሽ ይሻላል። እነዚያ እኮ መ^ንጋ ከማሰባሰብና ከመሰ^ዳደብ ውጭ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ ወይም ግብርና ምን መምሰል እንዳለበት ይጽፋሉ እንዴ? ከ50 ዓመት በፊት ስለተካሄደ ጸብ ምን ይፈይደኛል? ያለፈውን ታሪክ የምንማርበት በጎ ነገር ቢኖረው ጥሩ ነበር። ግን የድሮ በደልን ደጋግሞ ማስታወስ ለዛሬ ምን ያስተምረኛል? ከቁርሾ ታሪክ የሚማርበት ሰው ሊኖር ይችላል፤ ከስ^ድቡም የሚማር ይኖር ይሆናል። ለእኔ ግን በፋይናንስና በኢኮኖሚ ዘርፍ የምሠራ ሰው እንደመሆኔ፣ ጭራሽ ትኩረቴን ይነጥቁኛል። እንደምን መሰላችሁ የሚታዩኝ? ልክ መንገድ ላይ ስትሄዱ በቡድን የሚጯጯኹ ውሾች ይኖራሉ። አንዳንዴ ጭራሽ መንገዳችሁን ዘግተው፣ እናንተን ረስተው፣ “ዋው… ዋው… ዋው… ውውውውው!” እያሉ ያቀልጡታል። የእናንተም ግቢ ውሻ ሊጮኽ ብሎም ወጥቶ ሊቀላቀል ይችላል። ያኔ “ቡቺ፣ ና ግባ!” ምናምን ብላችሁ ድንጋይ ትወረውራላችሁ። እንዲያሳልፉዋችሁ እጃችሁን ልታወራጩም ትችላላችሁ። አንዳንዱ ሰው የውሾቹን ጸብ ተመችቶት ቆሞ ሊያይ፣ ወይም ካልቸኮለ እስኪያቆሙ ሊጠብቅ ይችላል። ውሾቹ ግን አንዳንዴ ዘለው አጥር ውስጥም ይገባሉ። ያኔ ስታባርሯቸው “ካልተባላሁ” ሊሉ ይችላሉ። አንዳንዴ ፌስቡክ ላይ ማን ከማን ጋር እንደሚጯጯኽ እንኳን አላውቅም። ብዙ ሚሊዮን ሰው እንደኔም ምን እየተካሄደ እንዳለ ላያውቅ አልያም ቸል ብሎ የሚያልፈውም ለዚያ ይመስለኛል። የእኔን ብጠቅስ፣ እንደው ተመስጬ የግብርና ባንኩ እንዴት ይቋቋም? ድሆች እስከመቼ በድህነት ይቀጥላሉ? እኔ ያለፍኩበት ድህነት ወደ ልጆቼ ሲተላለፍ እንዴት ዝም እላለሁ? አክስቶቼ፣ አጎቶቼ፣ ጎረቤቶቼ፣ ጓደኞቼ ኑሮአቸው እየባሰባቸው ነው። ይህ በዕለታዊ ምጽዋት የሚፈታ ችግር አይደለም። ምጽዋትስ እስከየት ያደርሳል? አላህ ዘንድ ምን ምላሽ አለኝ? እያልኩ አሰላስላለሁ። የትኛውን መሠረት ብናስተካክል ከዚህ ድህነት እንወጣ ይሆን? ጫጫታውም እኮ ሆድ ተኮር ነው። ታዲያ መፍትሔ የምለውን ለሰዎች በምን መልኩ አቅልዬ ላስረዳ እያልኩ እብሰለሰላለሁ። በመሃል “ዎው… ዎው…” የሚል ድምፅ ያባንነኛል። ከዚያ “ዎኦኦሽሽሽ!” ካልን ስድብ፣ ዝም ካልንም ስድብ። ምን እንደጮኸ ላላየሁት፣ ብሰማውም ለማላደምጠው ጩኸትም ቢሆን “ተላላኪ” ወይም “አለክላኪ” ነህ ብለው ይለጥፉብሃል። እንዲህ ያለ ነገር ብዙ ሰው ሳይገጥመው አይቀርም። ዶክተር ሐውለት ጋር ስናወራበት ነበር:: ምክንያቱም ፕሮፌሽናል ነገር ላይ ነው ቢዚ የምንሆነው:: ከዚያ ማለፍ የማያስችል አሳዛኝ ነገር ማባነኑ አይቀርም:: ድሮ GCA ሃይስኩል ላይ መምህር እያስተማሩ አንዱ ዱ^ርዬ ቀጥ ብሎ ተነስቶ ከክፍል ሲወጣ መምህሩ፣ “ወዴት ነህ?” አሉት። ዱር^ዬውም ቆጣ ብሎ፣ “ነገር ፍለጋ!” አላቸው። መምህሩም፣ “ብትማር አይሻልም? ነገር ዝም ተብሎ ይገኛል?” ሲሉት፣ ዱር^ዬው፣ “ምናባህ አገባህ?” አላቸው። ያው የፈለገውን ነገር ከመምህሩ አገኘ። በሩን ጉዋ አድርጎ ዘግቶ ወጣ። መምህሩ ተናደው፣ “… ይሄኔ ቤንዚን ስቦ ይሆናል እንጂ በደህናው አይደለም!” ሲሉ፣ ሌላ ዱ^ርዬ፣ “መኪና ነው እንዴ ቤንዚን የሚስበው?” ብሎ ሲነሳ፣ መምህሩ ትተው ወጡ። ምንም በማያውቁት ነገር ውስጥ ገቡ። አንዳንዴ ዝም ብሎ ማለፍ ከሁሉም ነገር ጋር መስማማት ሳይሆን፣ የራስን ጊዜና ትኩረት መጠበቅ ነው። ሕሊናህ አላስችል ሲልህ "ኧረ ተው" ማለትም ከሆነ ሰው ወይም ቡድን ጋር ግንኙነት አለው ማለት አይደለም::

Open in Telegram
Views3,920+24%vs avg
Forwards—
Reactions63
Comments—
#6617Text

ፎረንሲክ፡ ከምናስበው በላይ ሰፊ የእውቀት ዘርፍ! ============================== ስለ ፎረንሲክ ያለኝ ግንዛቤ እጅግ ውስን መሆኑን የተረዳሁት ሰሞኑን ነው። በቅርቡ ከቤተሰቤ አባል አንዱ የጤና ችግር አጋጥሞት ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ሄደን ነበር። በዚያም ''የፎረንሲክ ሕክምና (Forensic Medicine)'' የሚል ስያሜ አየሁ። ለእኔ አዲስ ስለነበር ትኩረቴን ሳበው። በአጠቃላይ ''ፎረንሲክ (Forensic)'' ማለት ወንጀሎችን ለመመርመር፣ የሕግ ክርክሮችን ለመፍታት እና ሕጋዊ ውሳኔዎችን ለመደገፍ ሳይንሳዊ ዘዴዎችንና ማስረጃዎችን መጠቀም ማለት ነው። (ከGemini የተገኘ ትርጓሜ) በዚያ ያገኘሁትን ሐኪም ስለ ፎረንሲክ ሕክምና ስጠይቀው፣ በሕክምና እውቀት በመታገዝ በሰው ሕይወት ወይም አካል ላይ የደረሰን ጉዳት በሳይንሳዊ መንገድ መመርመርና ለሕግ አካላት የሚያገለግል የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ እንደሆነ አብራራልኝ። ይህ ደግሞ ወደ ሌላ ሐሳብ ወሰደኝ። እኔም በቅርቡ የፎረንሲክ አካውንቲንግ (Forensic Accounting) ጥናት እያደረግሁ ነው። በአገራችን በዚህ ዘርፍ የሰለጠኑና ልዩ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች በእጅጉ ያስፈልጉናል። ምክንያቱም የፋይናንስ ወንጀሎች፣ የገንዘብ ምዝበራዎች እና ማጭበርበሮች እየተወሳሰቡ ነው። ወደፊትም ይህ ችግር ከመቀነስ ይልቅ የበለጠ የተራቀቀ መልክ ሊይዝ ይችላል። እነዚህን ወንጀሎች በትክክል ለመመርመር፣ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የፎረንሲክ አካውንቲንግ እውቀት ወሳኝ ነው። ከዚህ ተነስቼ አንድ ሐሳብ ላቀርብ እወዳለሁ። የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ሰፊ የልዩ ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ቢያቋቁምና በሚከተሉት የፎረንሲክ ዘርፎች ሥልጠናዎችን ቢሰጥ ምን ይመስላችኋል? - ፎረንሲክ ሕክምና (Forensic Medicine) - ፎረንሲክ ሳይካትሪና ሳይኮሎጂ (Forensic Psychiatry and Psychology) - ፎረንሲክ አካውንቲንግ (Forensic Accounting) - ፎረንሲክ ኢንጂነሪንግ (Forensic Engineering) - ዲጂታል ፎረንሲክ (Digital Forensics) - ፎረንሲክ ባዮሎጂ (Forensic Biology) - ፎረንሲክ ኬሚስትሪና ቶክሲኮሎጂ (Forensic Chemistry and Toxicology) - ፎረንሲክ ፓቶሎጂ (Forensic Pathology) ወዘተ. እርግጥ ነው፣ እነዚህ ዘርፎች የተለያዩ የትምህርት ዳራዎችና ልዩ ላቦራቶሪዎችን ይፈልጋሉ። ስለዚህ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሕክምና ተቋማት እና ከሌሎች ባለሙያ ተቋማት ጋር በመተባበር ቢከናወን የበለጠ ውጤታማ ይሆናል። አንድ አገር የፍትሕ ሥርዓቷን ለማጠናከር ጠንካራ ሕግና የሕግ አስከባሪ አካላት ብቻ አይበቁም። ሳይንሳዊ ማስረጃን የሚያመነጩ፣ የሚመረምሩ እና በሙያዊ ብቃት ለፍትሕ የሚተባበሩ ባለሙያዎችም ያስፈልጋሉ። ትምህርት ከስንት ነገር ነፃ እንደሚያወጣ እኮ?! ❤️😊

Open in Telegram
Views3,070−3%vs avg
Forwards—
Reactions27
Comments—
#6614Text

በተለይ ከንግድም ይሁን ከንብረት ጋር የተያያዙ የሗላ ሰነዶቻችሁን አጽዱ:: ነገሮች ሁሉ ዲጂታል ሲሆኑ ለጉ^ቦ አይመቹም:: ስለዚህ ወደሗላ ወደ ዲጂታል ቋት ወዳልገቡት ሰነዶች ይሄዳሉ:: ከዚያ ይደራደሩዋችሗል:: ቀጣይ ዘመን ንብረት ለያዘ እና ሒሳቡን ጽድት አድርጎ ለሄደ ጥሩ ነው:: የግል ቢዝነሶች እየተዳከሙና ወደ ካምፓኒ እያደጉ ናቸው:: ጉ^ቦ መክፈል የሚቻለው በዓይነት ማለትም በወርቅ, በአሜሪካን ዶላር, በበግና በበሬ, በስንዴና በጤፍ ሲሆን ይህም በሬዎቹ ተመዝግበው እስኪያልቁ ነው:: በአቋራጭ መክበር ይከብዳል:: ላለመከሰስ ጥረት አድርጉ:: ምክንያቱም ዲጂታል ንቅሳት (Digital tattoo) ከየትኛውም ንቅሳት በላይ ቆ^ሻሻ ነው:: ወንጀለኛነታችሁን አንዴ ፋይዳችሁ ጋር ከተያያዘ ሥራ ለመቀጠር ሁላ ትቸገራላችሁ:: እስሮች ዲጂታል ይሆናሉ:: አውቶቡስ ውስጥ ስትሰርቅ ከተያዝክና ከተፈረደብህ በቀጣይ ትራንስፖርት መጠቀም አትችልም:: ገና ካርድህን ስታስነካው "Rejected” ይልሃል:: በቂ ገቢ ሳይኖርህ ካቅምህ በላይ ቤት ልከራይ ስትል ውልና ማስረጃ ጋር reject ትደረጋለህ:: አቅምህን እወቅ ይልሃል ሲስተሙ:: ይህ የምላችሁ ነገር ከ10 ዓመታት በፊት ስለ ንግድ ፈቃድ አወጣጥ ስጽፈው እንደነበረው ዓይነት ነው:: ከመሬት ተነስተህ በሌለህ ካፒታል ንግድ ፈቃድ ማውጣት አትችልም:: 10 ሺህ ብር ኖሮህ የ50 ሺህ ንግድ ፈቃድ ስታወጣ እንደ ብሔራዊ ባንክ አየር ላይ አርባ ሺህ ማተም ቻልክ ማለት ነበር ድሮ:: አሁን የለም:: ባንክ ላይ ብር እያለህ እንኳ ለንግድ ፈቃድ ብሎክ ለማስደረግ ያለው ምልልስ ... ቢያንስ ሁለት ሦስቴ ባንክ እና ንግድ ቢሮ ትመላለሳለህ:: በተቻለ መጠን ከወንጀል ተጠንቀቁ:: የሗላ የተዝረከረከ ነገር አጽዱ::

Open in Telegram
Views3,430+9%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#6613Text
Views3,780+20%vs avg
Forwards—
Reactions44
Comments—
#6611Text
Views3,480+10%vs avg
Forwards—
Reactions70
Comments—
#6610Text
Views3,530+12%vs avg
Forwards—
Reactions75
Comments—
#6609Text

የወርቅ ዋጋ ለምን ቀነሰ? ወደፊትስ ምን ይጠበቃል? =============== በዓለም ገበያ የወርቅ ዋጋ ከከፍተኛ ደረጃው በኋላ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል። 2026 መጀመሪያ በወቄት ከ$5,500 አካባቢ ደርሶ የነበረው አሁን $3,500 ዶላር ላይ ነው ያለው:: ይህ ለባለሀብቶች፣ ለወርቅ አምራቾችና ለወርቅ ላኪ አገራት አስፈላጊ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው። የዋጋ ቅናሹ ዋና ምክንያቶች፦ 1. የአሜሪካ የወለድ ምጣኔ፦ የወለድ ምጣኔ ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት ባለሀብቶች ከወርቅ ይልቅ ወለድ ወደሚያስገኙ ንብረቶች እንዲያዘነብሉ አድርጓል። 2. የዶላር መጠናከር፦ ወርቅ በዶላር ስለሚሸጥ ዶላር ሲጠነክር የወርቅ ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል። ከወርቅ ወደ ዶላር shift ማድረግ ማለት ነው:: ዶላር ከወርቅ ይልቅ በቀላሉ ለማለዋወጥ ይመቻል:: 3. የትርፍ ማስመዝገብ፦ ወርቅ ከፍተኛ ዋጋ ላይ ከደረሰ በኋላ ባለሀብቶች ትርፋቸውን ለማስመዝገብ ወርቃቸውን መሸጣቸው የዋጋ ቅናሹን አባብሶታል። ወርቅ እየተሰቀለ ባለበት ወቅት ብዙ ሰው ወደ ግዢ ገባ:: ከዚያ የሆነ ቦታ ላይ ትርፉ ይበቃኛል ያሉ ሰዎች መሸጥ ጀመሩ:: 4. የኢንቨስትመንት ለውጥ፦ አንዳንድ ባለሀብቶች ከወርቅ ወደ አክሲዮን፣ ቦንድና ሌሎች የፋይናንስ ንብረቶች እየተዘዋወሩ ነው። በተለይ አሜሪካ የመንግሥት ተቋማት ሳይቀር ወደ አክሲዮኖች እየሄዱ ነበር:: ይህ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? አንድ አስፈላጊ ነገር አለ፤ የወርቅ ዓለም አቀፍ ዋጋ መቀነስ በኢትዮጵያ የወርቅ ዋጋ በተመሳሳይ መጠን ይቀንሳል ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ የወርቅ ዋጋ በሚከተሉት ይወሰናል፦ 👉🏼 የዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ። 👉🏼 የዶላርና የብር ምንዛሬ ተመን። 👉🏼 የአገር ውስጥ አቅርቦትና ፍላጎት። 👉🏼 የግዢና የሽያጭ ልዩነት። ወደፊት ምን ይጠበቃል? የዶላር ጥንካሬና የአሜሪካን ሀገር የወለድ ጭማሪ ግፊት ከቀጠለ የወርቅ ዋጋ ከዚህም ሊቀንስ ይችላል። በተቃራኒው የወለድ ምጣኔ ከቀነሰ፣ ዶላር ከተዳከመና የዓለም ኢኮኖሚያዊ ስጋቶች ከተባባሱ ወርቅ እንደገና ሊያገግም ይችላል። በተለይ ከኢራ^ን ጋር ከተጀመረ ወርቅ በጊዜያዊነት ያገግማል:: የእኔ መልእክት፦ 👉🏼 ለረጅም ጊዜ የሚያስቀምጥ ባለሀብት፦ ደረጃ በደረጃ መግዛት እንጂ ቀነሰም ለመግዛት አለመሮጥ .. ጨመረም ለመሸጥ አለመሮጥ። 👉🏼 በአጭር ጊዜ ትርፍ ለማግኘት የሚገዛ፦ የዋጋ መረጋጋት ምልክት እስኪታይ መጠበቅ ይሻላል። 👉🏼 በኢትዮጵያ ወርቅ የያዘ፦ በዓለም ዋጋ ብቻ ሳይሆን የብር ምንዛሬንም መከታተል አለበት። 👉🏼 ወርቅ ለመግዛት የሚያስብ፦ የጌጣጌጥ ወርቅ እና የኢንቨስትመንት ወርቅ የወጪ ልዩነትን ማስላት አለበት። 👉🏼 👉🏼 👉🏼 ዋናው ትምህርት፦ የወርቅ ዋጋ መውረድ ለገዢ ዕድል ሊሆን ቢችልም፤ ለወርቅ አምራችና ላኪ ግን የገቢ ችግር ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አንድ የዋጋ ለውጥ በተለያዩ የኢኮኖሚ ተዋናዮች ላይ ተቃራኒ ውጤት ያመጣል። ማስታወሻ፦ ይህ የገበያ ትንተና ነው፤ የወርቅ ዋጋ የወደፊት አቅጣጫ የተረጋገጠ ትንበያ አይደለም::

Open in Telegram
Views4,010+27%vs avg
Forwards—
Reactions34
Comments—
#6608Text

ድሮ አዲስ የሚሰልም ሰው ሱ^ኒ ወይስ ሺ^ዓ የሚል መወዛገብ ይገጥመው ነበር። አሁን ግን እጅግ ውጥንቅጡ የወጣ ነገር ውስጥ ነው የሚገባው። ሱ^ኒ ብሎ ይገባና ከሱ^ኒው ውስጥ ደግሞ ሰ^ለፊ ወይስ ሱፊ በሚል አይቆምም። የኦሮሞ ሰ^ለፊ ወይስ የአማራ ሰ^ለፊ፤ የዚህ ብ^ሔር ሱፊ ወይስ የዚያ ብ^ሔር ሱፊ ወደሚል ክፍፍል ወርዷል። በራስህ የሃይማኖት አቋም ውስጥ ሆነህ እንኳ በብ^ሔር ማንነት አታምነውም። ኢሕአዴግ የዘራው የብሔር ፖለቲካ የተደፋው መጅሊስ ውስጥ ነው። አንድ ብ^ሔር አካባቢ 50 መስጂዶች ሲፈርሱ ዝም ያለ ኡስታዝ፣ በሌላ ብ^ሔር አካባቢ ከመስጂድ ጣራ ላይ ቆርኪ ቢወድቅ ዛሩ ይነሳል። ሙስሊም ነው ብለህ በእስልምና ጉዳይ አብረኸው ስትሄድ፣ ወደ ብ^ሔሩ እጥፍ ይልብሃል። ይህ ጉዳይ እንኳንስ የዚህ ትውልድ፣ የሚቀጥለውም ትውልድ ሊፈታው ይከብዳል። ከሰሞኑ በእህታችን ዶክተር ላይ በፌክ አካውንት የተለጠፈውን ነገር አምጥተው፣ ይሻላሉ የምትላቸው ሰዎች ሳይቀሩ ወደ ብሔር ትርምስ ነው የከተቱት። የጻፈችው ሌላ የሚያዘዋውሩት ደግሞ ፍጹም ሌላ እና በፌክ አካውንት ፋብሪኬት የሆነ:: ምክንያቱም በብ^ሔር ማጥቃት ስለሚቀል:: ሙስሊም ሆነህ ... በራስህ "ሴክት" ውስጥ እንኳ የሚከላከልልህ ወይም የሚያጠቃህ ብ^ሔርህን አይቶ ነው:: አንዳንዶቹ ዱዞች የሌለ ጂ^ሃድ ላይ ያሉ ሁላ ይመስላቸዋል:: እሺ፣ ምን ይሁን? የመጅሊሱ ሽንፍላ በራሱ ሂደት እስኪጠራ ድረስ እናንተ በሙያችሁ ላይ ብቻ አተኩሩ። ምክንያቱም ሐኪም ከሆንክ ጉዳይህ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ነው። መነገድ ከፈለግህ ግንኙነትህ ከንግድ ቢሮና ከገቢዎች ቢሮ ጋር ነው። የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልግህ ከሆነም ከዚያ ጉዳይ ጋር ከተያያዙ የመንግሥት ተቋማት ጋር ትሄዳለህ። ዋናው የባንክ ጉዳይ ስለነበር በቂ መፍትሔ ጽፌልሃለሁ። ለእስልምና በመቅረብ መደበኛው ባንክ ይሻላል። አረቄን «ሀውድ» ብትለው ማስከሩን አይተውም። ስለዚህ ፈትሽ:: ወለድ በነጻው ይሻለኛል አላምንህም ካልክ፣ ከአንተ ጋር የሚባክን ጊዜ የለኝም። ሄደህ ነደህ እኔው ጋር ትመጣለህ። ቀሪው ሶላት ነው። መሬቱ ሁሉ ንጹሕ ነው። ያሻህ ንጹሕ ቦታ ላይ ስገድ:: ረመዷን በጨረቃ ነው። ጨረቃውን አይተህ ጹም። ዘካህን ደሃ ለሆነ ቅርብ ዘመድህ ስጥ። ይህ ይበልጥ ተወዳጅ ነው። በዘካ ላይ የተከለከለው Vertical ግንኙነት ብቻ ነው፤ ማለትም ለአባት፣ ለአያት፣ ለልጅ፣ ለልጅ ልጅና ለሚስት አይሰጥም። ሌላው ግን በጣም ምርጥ ዘካ ነው። ሐጅም almost online ሊሆን ነው! ስለዚህ ግንኙነትህ ከአላህ ጋር ብቻ ይሆናል። ምን ያምር ግልግል!!

Open in Telegram
Views3,880+23%vs avg
Forwards—
Reactions51
Comments—
#6607Text

የክርስቲያኖች ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን (የኖርንበት ዕውነቱን ትተን ተረቱን እንመን እንዴ?) ============= አንዳንድ ሙስሊሞች በግል ገጠመኞቻቸው፣ በብስጭታቸው ወይም በግል ግጭቶቻቸው ምክንያት የጥቂት ግለሰቦችን ባህሪ በመላ ክርስቲያኖች ላይ ለመጫን የሚሞክሩባቸውን ጽሑፎች እዚህ ሰፈር፣ ባስ ሲልም በመጽሐፍ መልክ እናያለን። እኔ ግን የሕይወት ታሪካችንን ሳይ ይህን አመለካከት መቀበል አልችልም። ከዜሮ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለተኛ ዲግሪዎቼ ድረስ ያስተማሩኝ መምህራን ከጥቂት ልዩነቶች በስተቀር በሙሉ ክርስቲያኖች ነበሩ። ምናልባትም ብዙ ቦታ 100% መምህራን ክርስቲያኖች ናቸው:: የእኔንም ጭምር:: ዜሮ ክፍል ላይ አቶ ጋሹ ተማጌ የሚባሉ ሙስሊም መምህር ለተወሰኑ ሳምንታት ፊደል አስቆጥረውናል። ከዚያ በኋላ ግን አንድም ሙስሊም የአካዳሚክስ መምሕር አልገጠመኝም:: ከማስታውሳቸው መምህራን መካከል ከ1ኛ ክፍል ብነሳ:- አክሊሉ ጥላሁን፣ ታዬ ካሳ፣ መብራት ወዬሳ (የአባቷን ስም በሰርተፊኬቴ ላይ አረጋግጣለሁ)፣ ጋሞ ለጋ … ከ4ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ጉተማ ጁጌሳ፣ ታረቀኝ ኃይለማርያም … ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አበራ ገብረማርያም (ዳይሬክተር)፣ አልጋነሽ ባራኪ፣ ተረፈ ለታ፣ ተፈሪ ተገኝ፣ ዘለቀ አጋየ … እያልን ብንቆጥር አንድም ሙስሊም አናገኝም። በሁለተኛ ደረጃም ቲቸር ተሰማ፣ ቲቸር አዕምሮ፣ ቲቸር ቢምረው፣ ቲቸር ማቲው፣ ቲቸር ራጄንድራ፣ ቲቸር አለሙ፣ ቲቸር ፈለቀ (አገጮ) እያልኩ ብዘረዝር ሁሉም ክርስቲያኖች ነበሩ። ይህ የሚያስገርመው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን የተማርኩበት የአያቴ አገር 99.9% ሙስሊም ሆኖ እንኳ መምህራኑ በሙሉ ክርስቲያኖች ነበሩ። አዲስ አበባ ውስጥ ኮሌጅም ሆነ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩኝ መምህራንም ክርስቲያኖች ነበሩ። በሰነዶቼ ላይ የሙስሊም መምህር ስም ያየሁት በMSc ትምህርቴ የዲዘርቴሽን ዲፌንስ ወቅት ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ከሊፋ የውጭ ገምጋሚ (External Examiner) ሆነው በመገኘት ነበር። እነዚህ ሁሉ ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ የተወጡት ሚና በሃይማኖት ያልተገደበ ስለነበር እኔም ብችል የተሻልኩ ልሆን እንጂ ሌላ ገደብ ውስጥ ልገባ አያስችለኝም:: እውቀት አስተምረውኛል፣፣ ለዛሬው ማንነቴ መሠረት ጥለውልኛል። አልተቋረጠም:: ልጆቻችንንም እያስተማሩ ናቸው:: *** እኔ ግን እንደ ውኃ፣ እንደ አፈር፣ እንደ ፀሐይና እንደ ጨረቃ፤ በአጠቃላይ እንደ ፈጣሪያቸውና ፈጣሪያችን አላህ ሳያዳላ እንደሚያኖረን ለሁሉም በርኅራኄ መኖርን እመርጣለሁ። ውኃ የሰውን ሃይማኖት አይጠይቅም። ፀሐይም በዚህ ብሔ^ር ወይም በዚያ ሃይማኖት ላይ ብቻ ልውጣ አትልም። አላህም አምነውኛል የሚላቸውንም ይሁን ክደውኛል የሚላቸውንም ይመግባል፤ ልጅ ይሰጣል። በግሌ መጽሐፍ ስጽፍ ለሙስሊሞች ብቻ አልጽፍም። ለሙስሊሞች የጻፍኳቸው የፋይናንስ መጻሕፍት ኢስላማዊ መረጃዎች ስለተጠቀምኩ ክርስቲያኖች ካነበቡዋቸው በሚል ዐረብኛ ቃላት በሙሉ በቅንፍ ትርጉማቸን አስቀምጫለሁ:: ከዚያ በማስከተል የማውቀውንና የተረዳሁትን እውቀት ክርስቲያን ወገኖቼም እንዲያውቁት በስፋት ሄድኩበት። ምክንያቱም እውቀት የሃይማኖት ድንበር የለውም። ከዜሮ ክፍል እስከ ሁለተኛ ዲግሪዬ ድረስ ያስተማሩኝ መምህራንና የተቀበሉኝ ቤተሰቦች ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብኝ። አለብንም! ⸻ እኔ ሙስሊም ነኝ። ምናልባትም እምነታቸውንና ሃይማኖታቸውን ከሚያጠብቁ ሰዎች መካከል ልመደብ እችላለሁ። ሆኖም የሃይማኖት መመሪያዬ ቁርኣንና የነቢዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم አስተምህሮ ነው እንጂ የብስጩና ቂመ^ኛ ግለሰቦች ባህሪ ሊሆን አልፈቅድም። ለእስልምና ዋነኛው የመመሪያ ምንጭ 114 ምዕራፎች ያሉት ቁርኣን ነው። በተለመደው የኩፋ ቆጠራ 6,236 አንቀጾች አሉት። ከቁርኣን በተጨማሪ የነቢያችን صلى الله عليه وسلم ንግግሮችና ተግባራት የተሰበሰቡባቸው የሐዲስ መጻሕፍትም ለሙስሊሞች ሌላ የመረጃ ምንጭ ናቸው። እዚህ ላይ አንድ ነገር ማስታወስ ያስፈልጋል። የሐዲስ ስብስቦች በተለያዩ ዘመናት የተዘጋጁ ሲሆን በነቢዩ ዘመንም የግል የሐዲስ ጽሑፎች ነበሩ። በኋላ ምናልባትም ከ180 ዓመታት በኋላ የተደረገው ሰፊ ስብስብና ምደባ ግን በተለያዩ የሐዲስ ሊቃውንት ሥራ ቀጥሏል። አሁን ላይ ከቁርኣን ቀጥሎ የሚጠቀሱ የሀዲስ ሰነዶች ከነቢያችን صلى الله عليه وآله وسلم መሻገር 230 ዓመታት በሗላ የተሰበሰቡ ናቸው:: ስለዚህ በእነዚህ የሐዲስ ስብስቦች ውስጥ ርኅራኄን፣ ፍትሕንና መልካም ሰብዕናን የሚጻረር ነገር ሲያጋጥማችሁ ከነቢያችን صلى الله عليه وآله وسلم እንዳልሆኑ እርግጠኛ ሁኑ። ምንጩን፣ የሐዲሱን ትክክለኛነትና የተነገረበትን አውድ መመርመር ያስፈልጋል። ከሳቸው ስፋትና ርኅራሄን እንጂ አታገኙም::ሸይኾቻችን እነሙፍቲ ዑመር የዚያ ባሕር ቅጂ ናቸው:: በአንዳንድ ጥናት የቁርኣን 97% አናቅጽ ስለእምነትና መልካም ሥራ፣ መልካም ሰብዕና፣ ፍትሕ፣ ርኅራኄ፣ ይቅርታ፣ ለድሆች መድረስና ለሰው ልጆች መልካም መሆን ያስተምራል። የጦ^ርነት ሕጎችን የሚመለከቱ አንቀጾችም በተወሰኑ ታሪካዊ አውዶች ውስጥ የተገለጹ ናቸው። ቁርኣንንና የነቢዩን صلى الله عليه وسلم አስተምህሮ በትክክል የተረዳ ሰው በጥላቻ ላይ ሕይወቱን መመሥረት የለበትም። ከዚህም በላይ አላህ በቁርኣን ውስጥ ስለ ክርስቲያኖች የገለጸበት ውብ አንቀጾች አሉ። በሱረቱል ማኢዳ 5፥82 ላይ ለሙስሊሞች በፍቅር ቅርብ ከሆኑት መካከል «እኛ ክርስቲያኖች ነን» የሚሉትን የሚጠቅስና ጸባያቸውን የሚያብራሩ መልእክቶች አሉ። ይህም በእምነት ልዩነት መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት እንድናስብ ያደርገናል። እኔ የምለው ይህን ነው። የክርስቲያኖችን ውለታ በመዋል ባንቀድማቸው እንኳ ለመመለስ እንጣር። ባንችል እንኳ እንደ መምሕር እናክብር። እንከባበር። በመልካም ሥራ እንሽቀዳደም። ሰውን በሃይማኖቱ ሳይሆን በሰብዕናውና በሥራው እንመዝን። የጥቂት ሰዎችን ጥፋት በሙሉ ማኅበረሰብ ላይ አናላክክ። በሙስሊሞችም በኩል የሚታዩ የውሱን ፖለቲከኞችን ግብረገባዊ ያልሆነ እንካ ሰላንቲያ የመላ ሙስሊም ሐሳብና አስተሳሰብ እንዳይመስል:: ውለታን ማስታወስ ሰብዓዊነት ነው። ልዩነትን አክብሮ አብሮ መኖር ደግሞ ጥበብ ነው። እስልምናችንን መለካት ያለብን ምን ወደ ለአላህ ቀርበናል ... ምንስ ያህል ከነቢያችን صلى الله عليه وسلم ጸባይ ወርሰናል ብለን እንጂ ምን ያህል ሙስሊም ያልሆኑትን ጠ^ላን ሊሆን አይችልም:: ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ::

Open in Telegram
Views4,600+46%vs avg
Forwards—
Reactions166
Comments—
#6606Text
Views3,770+20%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#6601Photo
Views4,610+46%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—