በሃይማኖትም ይሁን በብ^ሔር ሳትታጠርና አውጀብጃቢ ሳትፈልግ እንደ ውሃ ወይም እንደ ፀሐይ ወይም እንደ መሬት ሆነህ ለሁሉም የሚሆን ሥራ ይዘህ ለመምጣት የምር ጥረት ይፈልጋል:: የውስጥ ስፋትን ያሳያል:: ገበሬ እህል ሲዘራ ለቤተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለአዕዋፍም ጭምር ነው:: መታጠርን ከውስጥህ አውጣው:: ሥራህ ጊዜና ቦታ እንኳ አይገድበውም:: ለሰው ልጅ ብቻ ብለህም አትሥራ:: አጋንንትም ይጠቀም:: አታምልከው እንጂ ቢጠቀም ምን ተጎዳህ!?! ሰፊነት የፈጣሪ ባሕሪይ ነው:: ፈጥሮህ እንኳ ብታምነው ባታምነውም ያኖርሃል::
Open in TelegramHasen Injamo
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 18, 2026 | 4,610 |
| Nov 19, 2026 | 3,770 |
| Nov 20, 2026 | 4,600 |
| Nov 22, 2026 | 3,725 |
| Nov 23, 2026 | 3,780 |
| Nov 24, 2026 | 3,324 |
| Nov 26, 2026 | 2,570 |
| Nov 28, 2026 | 1,760 |
| Nov 29, 2026 | 776 |
Most viewed this month
- 01Views4.61KForwards—Reactions12Comments—
- 02Views4.6KForwards—Reactions166Comments—
- 03Views4.01KForwards—Reactions34Comments—
- 04Views3.92KForwards—Reactions63Comments—
Latest posts
ልጅ ሆነን ታናናሾቻችንን ሥራ እናሠራና የባሕር ዛፍ ቅጠል እንከፍላቸው ነበር:: ቅጠሉ እኮ እነሱም ቀጥፈው መውሰድ የሚችሉት መሆኑ ገራሚ ነው:: አልወስድም ካሉ ይኮረኮማሉ:: አሁን ያለንበት የገንዘብ ሥርዓት ተመሳሳይ ነው:: በተለይ ዐረቦች እና አፍሪካውያን ሀብታቸውን ከባሕር ዛፍ ቅጠል ባነሰ የአሜሪካን ወረቀት ይቀይራሉ:: እምቢ ካሉ ይኮረኮማሉ:: መውጫው መፍትሔ ምን እንደሆነ ለማወቅ የግድ ይህንን ሲስተም መረዳት ያስፈልጋል:: ለልጆችም ጭምር ነው መጽሓፍ ያበጀሁት:: መ-ገንዘብ 3 ለልጆች ነው የተሰናዳው::
Open in Telegramከውጭ ዕቃ ጭናችሁ (ጭን ሳይሆን መጫን ማለቴን ነው) ሰነድ እና የተጫነው ዕቃ እንደተጣረሱ ማለትም እንደተሳሳታችሁ ከገባችሁ እቃችሁ ጉምሩክ ፍተሻ እስኪደርስ ድረስ ማስተካከያ ብዙ መንገዶች አሉ:: ልዩነቶቹ የሚታለፍ ስህተት, የሚያስቀጣ, የሚያስወርስና ሊያሳስር የሚችል በሚል ሊመደቡ ይችላሉ:: አንዳንዴም ስህተቱ ከተጫነ በሗላ ከታወቀ ያለው አማራጭ ጉምሩክ ከመድረሱ በፊት ማስተካከል የግድ ነው:: አንዱ ሰፕላየር ምርቃት ብሎ ቢጨምር ወይም ኮንቴይነሩ ሳይሞላ ቀርቶ የተጫነbut መኪናም ይሁን መርከብ ሲወዛ-ወዝ ዕቃ እንዳይጎዳ ለማፈኛነት የተጨመረ ሊኖር ይችላል:: ምንም ይሁን ምን ከዶክመንት ከዕቃ ከተለየ ማጭ^በርበር ነው ተብሎ ይወሰዳል:: ስለዚህ መደናገጥ አያስፈልግም:: ሌላው ለከንግዲህ ማለትም ለዲጂታል ዘመን አዋጩ መንገድ ጽድት አድርጎ መሥራት ነው::
Open in Telegramዛሬ የአፍሪካን የክፍያ ሥርዓት (African Payment Systems) የተመለከተ እጅግ ጥሩ ኮንፈረንስ ተካፍለን ነበር። በተለይ በጉጉት ስጠብቀው የነበረ ኮንፈረንስ ነው። እያንዳንዱን ውይይት በትምህርት ክፍል ውስጥ እንዳለሁ በትኩረት ተከታትያለሁ። የአውሮፓ አገራት ወደ አንድ የክፍያ ሥርዓትና የጋራ መገበያያ ገንዘብ (ዩሮ) እንዴት እንደተሸጋገሩ ያብራሩት ዶ/ር ክሪስ ፒርክነር የዩሮ ዞንን ተሞክሮ ሲያቀርቡ ትኩረቴን በጣም ስበውታል። አውሮፓ ምን ዓይነት ፈተናዎች ገጠሟት? አፍሪካስ ከዚህ ተሞክሮ ምን መማርና ምን ማድረግ አለባት? የሚሉት ጥያቄዎች ያተኮረ አጭርና ጥልቅ ውይይት ነበር። የEthSwitch ኃላፊ አቶ ይለበስ አዲስንም ሙሉ ቀን ብቻ ሳዳምጣቸው ብቆይ ደስ ባለኝ ነበር። ለምን መሰላችሁ? እኔ ከዶላር ኢምፓየር እንዴት መውጣት እንችላለን፣ ወይስ አንችልም? የሚለውን ጥያቄ በተለያዩ ሁኔታዎች (Scenarios) በ«መ-ገንዘብ» መጽሐፌ ውስጥ በሰፊው ዳስሼዋለሁ። ግን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ የተዳሰሰውን ጉዳይ በተግባር ደረጃ የት እንደደረሰ ለማወቅ እንዲህ ባለ መድረክ ላይ ተሰብስቦ ሲቀርብልህ፣ ቁጭ ብለህ ነው የምትቀምሰው። (ቆሎ ነው ደግሞ!) ምስል፦ ዶ/ር ክሪስ ፒርክነር (CEO, Bluecode; Co-founder, European Mobile Payment Systems Association)
Open in Telegramየፊታችን ማስገኞ, ረቡዕና ሐሙስ የሚሰጠው የኢምፖርት ስልጠና ምዝገባ ሞልቷል:: የተመዘገባችሁ ምእመናን እና ምእመናት በዚያው ቴሌግራም እያንዳንዱ መረጃ ይደርሳችሗል:: እናመሰግናለን::
Open in Telegram”… ሽፈራው ጌታቸው የሚጽፈውን አታይም? ዘመድኩን ምን እንደሚል አታይም?…” ይሉኛል። ሽፈራው ጌታቸው በለው፣ ዘመድኩን በለው፣ አመዲን ጀበል በለው፣ ድእእእሮ ቦልኬያቸዋለሁ፤ ወይም unfollow አድርጌያቸዋለሁ። ምክንያቱም በሃይማኖት ጉዳይ ... አይደለም ...ሙስሊም ካልሆኑ ተናታራኪዎች ቀርቶ፣ ከሙስሊም ተናታራኪዎች ምን ልማር እችላለሁ? ምንም! ጸብ ብቻ! ያሰላም! ሶሻል ሚዲያ ላይ በተማረበት ሙያ ላይ ተመስርቶ ሐሳብ የሚያቀርብ ሰው ጥቂት ነበር። አሁን ትንሽ ይሻላል። እነዚያ እኮ መ^ንጋ ከማሰባሰብና ከመሰ^ዳደብ ውጭ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ ወይም ግብርና ምን መምሰል እንዳለበት ይጽፋሉ እንዴ? ከ50 ዓመት በፊት ስለተካሄደ ጸብ ምን ይፈይደኛል? ያለፈውን ታሪክ የምንማርበት በጎ ነገር ቢኖረው ጥሩ ነበር። ግን የድሮ በደልን ደጋግሞ ማስታወስ ለዛሬ ምን ያስተምረኛል? ከቁርሾ ታሪክ የሚማርበት ሰው ሊኖር ይችላል፤ ከስ^ድቡም የሚማር ይኖር ይሆናል። ለእኔ ግን በፋይናንስና በኢኮኖሚ ዘርፍ የምሠራ ሰው እንደመሆኔ፣ ጭራሽ ትኩረቴን ይነጥቁኛል። እንደምን መሰላችሁ የሚታዩኝ? ልክ መንገድ ላይ ስትሄዱ በቡድን የሚጯጯኹ ውሾች ይኖራሉ። አንዳንዴ ጭራሽ መንገዳችሁን ዘግተው፣ እናንተን ረስተው፣ “ዋው… ዋው… ዋው… ውውውውው!” እያሉ ያቀልጡታል። የእናንተም ግቢ ውሻ ሊጮኽ ብሎም ወጥቶ ሊቀላቀል ይችላል። ያኔ “ቡቺ፣ ና ግባ!” ምናምን ብላችሁ ድንጋይ ትወረውራላችሁ። እንዲያሳልፉዋችሁ እጃችሁን ልታወራጩም ትችላላችሁ። አንዳንዱ ሰው የውሾቹን ጸብ ተመችቶት ቆሞ ሊያይ፣ ወይም ካልቸኮለ እስኪያቆሙ ሊጠብቅ ይችላል። ውሾቹ ግን አንዳንዴ ዘለው አጥር ውስጥም ይገባሉ። ያኔ ስታባርሯቸው “ካልተባላሁ” ሊሉ ይችላሉ። አንዳንዴ ፌስቡክ ላይ ማን ከማን ጋር እንደሚጯጯኽ እንኳን አላውቅም። ብዙ ሚሊዮን ሰው እንደኔም ምን እየተካሄደ እንዳለ ላያውቅ አልያም ቸል ብሎ የሚያልፈውም ለዚያ ይመስለኛል። የእኔን ብጠቅስ፣ እንደው ተመስጬ የግብርና ባንኩ እንዴት ይቋቋም? ድሆች እስከመቼ በድህነት ይቀጥላሉ? እኔ ያለፍኩበት ድህነት ወደ ልጆቼ ሲተላለፍ እንዴት ዝም እላለሁ? አክስቶቼ፣ አጎቶቼ፣ ጎረቤቶቼ፣ ጓደኞቼ ኑሮአቸው እየባሰባቸው ነው። ይህ በዕለታዊ ምጽዋት የሚፈታ ችግር አይደለም። ምጽዋትስ እስከየት ያደርሳል? አላህ ዘንድ ምን ምላሽ አለኝ? እያልኩ አሰላስላለሁ። የትኛውን መሠረት ብናስተካክል ከዚህ ድህነት እንወጣ ይሆን? ጫጫታውም እኮ ሆድ ተኮር ነው። ታዲያ መፍትሔ የምለውን ለሰዎች በምን መልኩ አቅልዬ ላስረዳ እያልኩ እብሰለሰላለሁ። በመሃል “ዎው… ዎው…” የሚል ድምፅ ያባንነኛል። ከዚያ “ዎኦኦሽሽሽ!” ካልን ስድብ፣ ዝም ካልንም ስድብ። ምን እንደጮኸ ላላየሁት፣ ብሰማውም ለማላደምጠው ጩኸትም ቢሆን “ተላላኪ” ወይም “አለክላኪ” ነህ ብለው ይለጥፉብሃል። እንዲህ ያለ ነገር ብዙ ሰው ሳይገጥመው አይቀርም። ዶክተር ሐውለት ጋር ስናወራበት ነበር:: ምክንያቱም ፕሮፌሽናል ነገር ላይ ነው ቢዚ የምንሆነው:: ከዚያ ማለፍ የማያስችል አሳዛኝ ነገር ማባነኑ አይቀርም:: ድሮ GCA ሃይስኩል ላይ መምህር እያስተማሩ አንዱ ዱ^ርዬ ቀጥ ብሎ ተነስቶ ከክፍል ሲወጣ መምህሩ፣ “ወዴት ነህ?” አሉት። ዱር^ዬውም ቆጣ ብሎ፣ “ነገር ፍለጋ!” አላቸው። መምህሩም፣ “ብትማር አይሻልም? ነገር ዝም ተብሎ ይገኛል?” ሲሉት፣ ዱር^ዬው፣ “ምናባህ አገባህ?” አላቸው። ያው የፈለገውን ነገር ከመምህሩ አገኘ። በሩን ጉዋ አድርጎ ዘግቶ ወጣ። መምህሩ ተናደው፣ “… ይሄኔ ቤንዚን ስቦ ይሆናል እንጂ በደህናው አይደለም!” ሲሉ፣ ሌላ ዱ^ርዬ፣ “መኪና ነው እንዴ ቤንዚን የሚስበው?” ብሎ ሲነሳ፣ መምህሩ ትተው ወጡ። ምንም በማያውቁት ነገር ውስጥ ገቡ። አንዳንዴ ዝም ብሎ ማለፍ ከሁሉም ነገር ጋር መስማማት ሳይሆን፣ የራስን ጊዜና ትኩረት መጠበቅ ነው። ሕሊናህ አላስችል ሲልህ "ኧረ ተው" ማለትም ከሆነ ሰው ወይም ቡድን ጋር ግንኙነት አለው ማለት አይደለም::
Open in Telegramፎረንሲክ፡ ከምናስበው በላይ ሰፊ የእውቀት ዘርፍ! ============================== ስለ ፎረንሲክ ያለኝ ግንዛቤ እጅግ ውስን መሆኑን የተረዳሁት ሰሞኑን ነው። በቅርቡ ከቤተሰቤ አባል አንዱ የጤና ችግር አጋጥሞት ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ሄደን ነበር። በዚያም ''የፎረንሲክ ሕክምና (Forensic Medicine)'' የሚል ስያሜ አየሁ። ለእኔ አዲስ ስለነበር ትኩረቴን ሳበው። በአጠቃላይ ''ፎረንሲክ (Forensic)'' ማለት ወንጀሎችን ለመመርመር፣ የሕግ ክርክሮችን ለመፍታት እና ሕጋዊ ውሳኔዎችን ለመደገፍ ሳይንሳዊ ዘዴዎችንና ማስረጃዎችን መጠቀም ማለት ነው። (ከGemini የተገኘ ትርጓሜ) በዚያ ያገኘሁትን ሐኪም ስለ ፎረንሲክ ሕክምና ስጠይቀው፣ በሕክምና እውቀት በመታገዝ በሰው ሕይወት ወይም አካል ላይ የደረሰን ጉዳት በሳይንሳዊ መንገድ መመርመርና ለሕግ አካላት የሚያገለግል የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ እንደሆነ አብራራልኝ። ይህ ደግሞ ወደ ሌላ ሐሳብ ወሰደኝ። እኔም በቅርቡ የፎረንሲክ አካውንቲንግ (Forensic Accounting) ጥናት እያደረግሁ ነው። በአገራችን በዚህ ዘርፍ የሰለጠኑና ልዩ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች በእጅጉ ያስፈልጉናል። ምክንያቱም የፋይናንስ ወንጀሎች፣ የገንዘብ ምዝበራዎች እና ማጭበርበሮች እየተወሳሰቡ ነው። ወደፊትም ይህ ችግር ከመቀነስ ይልቅ የበለጠ የተራቀቀ መልክ ሊይዝ ይችላል። እነዚህን ወንጀሎች በትክክል ለመመርመር፣ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር የፎረንሲክ አካውንቲንግ እውቀት ወሳኝ ነው። ከዚህ ተነስቼ አንድ ሐሳብ ላቀርብ እወዳለሁ። የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ሰፊ የልዩ ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ቢያቋቁምና በሚከተሉት የፎረንሲክ ዘርፎች ሥልጠናዎችን ቢሰጥ ምን ይመስላችኋል? - ፎረንሲክ ሕክምና (Forensic Medicine) - ፎረንሲክ ሳይካትሪና ሳይኮሎጂ (Forensic Psychiatry and Psychology) - ፎረንሲክ አካውንቲንግ (Forensic Accounting) - ፎረንሲክ ኢንጂነሪንግ (Forensic Engineering) - ዲጂታል ፎረንሲክ (Digital Forensics) - ፎረንሲክ ባዮሎጂ (Forensic Biology) - ፎረንሲክ ኬሚስትሪና ቶክሲኮሎጂ (Forensic Chemistry and Toxicology) - ፎረንሲክ ፓቶሎጂ (Forensic Pathology) ወዘተ. እርግጥ ነው፣ እነዚህ ዘርፎች የተለያዩ የትምህርት ዳራዎችና ልዩ ላቦራቶሪዎችን ይፈልጋሉ። ስለዚህ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሕክምና ተቋማት እና ከሌሎች ባለሙያ ተቋማት ጋር በመተባበር ቢከናወን የበለጠ ውጤታማ ይሆናል። አንድ አገር የፍትሕ ሥርዓቷን ለማጠናከር ጠንካራ ሕግና የሕግ አስከባሪ አካላት ብቻ አይበቁም። ሳይንሳዊ ማስረጃን የሚያመነጩ፣ የሚመረምሩ እና በሙያዊ ብቃት ለፍትሕ የሚተባበሩ ባለሙያዎችም ያስፈልጋሉ። ትምህርት ከስንት ነገር ነፃ እንደሚያወጣ እኮ?! ❤️😊
Open in Telegramፎሬንሲክ አካውንቲንግ በተለይ አሁን ላይ እጅግ በጣም የሚያስፈልግ ዘርፍ ነው:: ዶክተር ለዚህ ደግሞ ያንቺ ዩኒቨርሲቲ ተገቢ ግቢ ነው::
Open in Telegramበተለይ ከንግድም ይሁን ከንብረት ጋር የተያያዙ የሗላ ሰነዶቻችሁን አጽዱ:: ነገሮች ሁሉ ዲጂታል ሲሆኑ ለጉ^ቦ አይመቹም:: ስለዚህ ወደሗላ ወደ ዲጂታል ቋት ወዳልገቡት ሰነዶች ይሄዳሉ:: ከዚያ ይደራደሩዋችሗል:: ቀጣይ ዘመን ንብረት ለያዘ እና ሒሳቡን ጽድት አድርጎ ለሄደ ጥሩ ነው:: የግል ቢዝነሶች እየተዳከሙና ወደ ካምፓኒ እያደጉ ናቸው:: ጉ^ቦ መክፈል የሚቻለው በዓይነት ማለትም በወርቅ, በአሜሪካን ዶላር, በበግና በበሬ, በስንዴና በጤፍ ሲሆን ይህም በሬዎቹ ተመዝግበው እስኪያልቁ ነው:: በአቋራጭ መክበር ይከብዳል:: ላለመከሰስ ጥረት አድርጉ:: ምክንያቱም ዲጂታል ንቅሳት (Digital tattoo) ከየትኛውም ንቅሳት በላይ ቆ^ሻሻ ነው:: ወንጀለኛነታችሁን አንዴ ፋይዳችሁ ጋር ከተያያዘ ሥራ ለመቀጠር ሁላ ትቸገራላችሁ:: እስሮች ዲጂታል ይሆናሉ:: አውቶቡስ ውስጥ ስትሰርቅ ከተያዝክና ከተፈረደብህ በቀጣይ ትራንስፖርት መጠቀም አትችልም:: ገና ካርድህን ስታስነካው "Rejected” ይልሃል:: በቂ ገቢ ሳይኖርህ ካቅምህ በላይ ቤት ልከራይ ስትል ውልና ማስረጃ ጋር reject ትደረጋለህ:: አቅምህን እወቅ ይልሃል ሲስተሙ:: ይህ የምላችሁ ነገር ከ10 ዓመታት በፊት ስለ ንግድ ፈቃድ አወጣጥ ስጽፈው እንደነበረው ዓይነት ነው:: ከመሬት ተነስተህ በሌለህ ካፒታል ንግድ ፈቃድ ማውጣት አትችልም:: 10 ሺህ ብር ኖሮህ የ50 ሺህ ንግድ ፈቃድ ስታወጣ እንደ ብሔራዊ ባንክ አየር ላይ አርባ ሺህ ማተም ቻልክ ማለት ነበር ድሮ:: አሁን የለም:: ባንክ ላይ ብር እያለህ እንኳ ለንግድ ፈቃድ ብሎክ ለማስደረግ ያለው ምልልስ ... ቢያንስ ሁለት ሦስቴ ባንክ እና ንግድ ቢሮ ትመላለሳለህ:: በተቻለ መጠን ከወንጀል ተጠንቀቁ:: የሗላ የተዝረከረከ ነገር አጽዱ::
Open in Telegram