
አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የሰው ልጅ ልብ ነው የገጣሚ ሀገር...! @Run_Viva_Run
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 5, 2026 | 564 |
| Nov 25, 2026 | 186 |
Latest posts
Forwarded from Âb Ěł
https://vt.tiktok.com/ZSbQWhXKW/ ለውድድር ያቀረብነው ስራ ነው እየገባቹ ማድረግ የምትችሉትን በማድረግ ድጋፋቹን አሳዩን🤗 THANK YOU @kabfilmproduction
Open in TelegramForwarded from Abrham F. Yekedas
https://www.tiktok.com/@kabfilmproduction?_r=1&_t=ZS-9A7Qgjkst0f በቅርቡ የምንለቃቸውን ስራዋች በቲክቶክ እንዲደርሳቹ ከወዲሁ follow በማድረግ ድጋፋቹን አሳዩን THANK YOU 🙏😊
Open in Telegram"ዛሬ ግቢ በቃ! ይኸው ብር አይደለ?" ከኪሴ አምስት መቶ ብር አውጥቼ ሰጠሁዋት... ተቀብላኝ ወደ ደረቴ በትናው "ብላው... አሁን ስራዬን ልስራበት ተወኝ።" ብላ መለሰችው። "እሺ ዛሬ ከእኔ ጋ ነሽ..." ብዬ ተኮሳተርኩ "ትችላለህ....ለማኝ አይደለሁም...ገባህ!::" ከመሽታ ቤቱ ወጣች። ሂሳብ ከፍዬ ተከተልኳት:: "ትንሽ በእግር እንሂድ?" አልኳት። መጠጥ ስለጠጣች ውስጧ ስካር አለ:: "ሰውዬ....በርዶኛል" አለች። ኮቴን አውልቄ አለበስኳት...ዝም አለች።ኮቴን ካለበስኳት በኃላ ብርዱ ውስጤ ድረስ ተሰማኝ። እሷ እንዴት እንደቻለችው ፈጣሪ ይወቀው። ቃል ሳናወጣ መጓዝ ጀመርን። ### የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ምሽት ላይ ነበር ከጓደኞቼ ጋ እንዝናና ብለን ወጥተን አይቻት ፍቅር የያዘኝ...ሴተኛ አዳሪ ናት።ደስ አይልም አይደል?...የፍቅር ነገር ሆነና አዙሮ ምን ላይ እንደጣለኝ እኔም አልገባኝም....እሷንም ምን የህይወት ድጥ ወስዶ እዚህ ጋ እንደዘፈቃት ባላውቅም ልጅነቷና ውበቷን ማንም ሰው የሚስማማበት ነው:: ያኔ አብረን አሳለፍንና ምንም ሳይፈጠር ብር ሰጥቻት ብቻ ተለያየን። ተምራለች፣ በወሬያችን መሀል ጣል የምታደርጋቸው ሀሳቦች እንደገረሙኝ ነበር የተለየሁዋት....ሳምንት ሙሉ ከሀሳቤ ልትጠፋ አልቻለችም። ስልኳን ተቀብዬ ስለነበር በሳምንቱ ደወልኩላት...ራሴን ካስታወስኳት በኃላ አወቀችኝ። "እንገናኝ..." አልኳት "ያው ቢሮዬ መጥተህ አግኘኛ..." ብላ ሳቀች። መራር ቀልድ ሆነብኝ ሳቋን እስክትጨርስ ጠበቅኳት..."ሄሎ ምነው ዝም አልክ?" አለች "እ....ሌላ ቦታ ብንገናኝ....ቅር ካላለሽ" "ክፈል እንጂ ....ምን ቅር ይለኛል..." አለች... ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋሁ። ወደቀጠርኳት ካፌ ስትመጣ ድጋሚ ሳያት ልቤ ደነገጠ አወራን ከፈልኳት ሄደች:: ማታ ደወልኩላት ከስልኳ ጀርባ ሙዚቃ ይሰማል ትንሽ አውርተን ስልኩን ዘጋሁት...ቀናሁ...ማን እየነካት ይሆን የሚለው እንቅልፍ ነሳኝ:: አድሬ ዋልኩና በንጋታው ያለችበት ሄድኩ:: እየተፈጠረብኝ ያለውን ነገር ነገርኳትና እየወደድኳት እንደሆነ ገለፅኩላት... ከት ብላ ሳቀች:: "ወንዶች ስትባሉ ግን..." ብላ አሁንም መንከትከቷን ቀጠለች:: "ምነው?..ሰው ነኝ አንቺም ሰው አይደለሽ እንዴ...? ይሄ እኮ ሊፈጠር የሚችል ነገር ነው። "አትቀልድ ባክህ...ለእንደዚህ መጃጃል ከሆነ የፈለከኝ አጠገቤ እንዳደርስ... ለወር ያህል ነው የእናንተ አበድኩልሽ፣ ሞትኩልሽ...በል ቻው" ወደተጠቃቀሰችው አንድ ደንበኛ ጋር ሄደች::ሂሳብ ከፍዬ ወጣሁ ውስጤ ሲጨስ ይታወቀኛል ' ፍቅር ነው?፣ ቅናት ነው?፣ወይስ እሷ ያሰበችው አይነት ጊዜያዊ ስሜት?' ቤቴ ገባሁ። በንጋታው ደወልኩላት "ምንድነው?" አለችኝና ስልኩን በጆሮዬ ዘጋችው። 'እውነትም ምንድነው?' ጠየቅኩት ራሴን ለማንም ተሰምቶኝ የማያውቀው ስሜት እንዴት ለእሷ ሲሆን ተሰማኝ?...አፍቅሬያታለሁ::' ባለችበት ቦታ መመላለስ አበዛሁ... እንኳን እሷ በዙሪያዋ ያሉት እሷን መሰል ሴቶች አወቁኝ..."መጣልሽ" ይሏታል:: ከሌለችም "ትመጣለች ጠብቃት" ይሉኛል:: ከቀን ቀን ፍላጎቴ ለእሷ ብቻ መሆኑን ስላወቁ አንዷም ሴት ወደ እኔ አትጠጋም:: እንግዲህ የምጠብቃት ከሌላ ወንድ ጋ ተኝታ እስክትመለስ ነው:: ዕንባ እየተናነቀኝ እጠብቃታለሁ። አንድ ቀን ስትመለስ ፊቷ አለቀስኩ...ሳቀች፣ ስለሳቀች አኮረፍኳት ሳምንት ካለችበት ቦታ ራቅኩኝ። 'አጠገቧ ብደርስ ውሻ ነኝ።' ያልኩት ልጅ በሳምንቱ ናፈቀችኝና ሄድኩ.... "ከእኔ ምን ጎድሎብሽ ነው?" ብዬ ጠየኳት። "በወንዶች ምን ያልጎደለብኝ አለ?...ትዕግስት ካለህ ጠብቀኝ።" አለች ፊቷን አኮሳትራ...ግራ መጋባቴን ስታይ መልሳ ሳቀች። ታገስኩኝ... ### አንድ የዝናብ ጠብታ ግንባሬ ላይ አረፈችና አባነነችኝ። ምን ይህል ዝም ተባብለን በእግር እንደሄድን እንጃ...ሰማዩ ዳመና እንዳዘለ በጭለማ ውስጥም ያስታውቃል... "አትጫወቺም...ዝም አልሽ?" "ልመንህ..?" አለችኝ። ዞር ብዬ አየሁዋት:: ዓይኗ ዕንባ አቅርሯል:: "ማለት..?" አልኩኝ " ሰልችቶኛል ይሄንን መንገድ ወደኃላ ባልመለስበት ደስ ይለኛል... ግን ደግሞ አንተ እስከመቼ እንደምትቀበለኝ አላውቅም... ነገ ፍቅርህ ሲበርድ በዛሬው ማንነቴ መልሰህ ልትለካኝ ትችላለህ። ገባህ?.... ታድያ ልመንህ?" አየችኝ....አየሁዋት ዕንባዋ ፈሰሰ ከጉንጯ ጠረግኩት....እጇ ላይ ሸክም መስሎ የታየኝን ቦርሳዋን ተቀበልኳትና.…. ዝም አልኩ። መልሼ ዞር ብዬ ሳያት መሬት መሬቱን እያየች እየተራመደች ነው። ይሄ ህይወት እንደማይገባት የአየሁዋት ቀን ነበር የተረዳሁት...መራራ እውነት እንደ ፊልም እያየሁ ጠብቄያታለሁ...ታገስ ያለችኝ ቀን ትዕግስቱን እንዲሰጠኝ ፈጣሪን ለምኛለሁ... እንደበደለችኝ ውስጤ በተሰማኝ ቁጥር ልክ ይቅርታ አድርጌላታለሁ...ነገ ክፉ ጎረቤት ስሟን ቢያጠለሽብኝ ምን ይህል ከለላ ልሆናት እንደምችል በምናቤ ስንቴ ተመልክቻለሁ...የእመቤት ኑሮ እንደማኖራት ለራሴ ቃል ገብቻለሁ... ካየሁዋቸው ንፁህ ከተባሉ ሴቶች በላይ አፈቅራታለሁ። "እኔ በህይወት እስካለሁ ይሄን መንገድ ወደኃላ አትመለሺበትም...።" ቀና ብላ አየችኝ...ከሆዷ ፈንቅሎ የወጣ ዕንባ በዓይኖቿ ፈሰሰ... ወደጎኔ አስጠግቼ አቀፍኳት... ወደፊት መጓዛችንን ቀጠልን...ወደቤቴ ላገባት። Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
Open in Telegramእያንደረደረን ልክ እንደ ቁልቁለት እንዲህ እንደዋዛ ዓመት መስሎ ዕለት የጣልነውን ሳንለይ የያዝነውን ሳናይ "እንኳን አደረሰን፣ አዲስ ዓመት ሰናይ" ብለን ተሸናግለን፥ አ ለ ን! Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
Open in Telegram






