ድምፅ ምትሞካክሩ ልጆች አዲስ አበባም ከአዲስ አበባም ውጪ ያላችሁ አዲስ ዜና አለን። በቅርቡ ከአንድ ፕላትፎርም ጋር የምንጀምረው ፕሮጀክት ስላለ የድምፅ ብቃታችሁን ሚያሳይ ቮይስ ኢንቦክስ አድርጉ በ @Ferhanhabesha
Open in Telegram
ሀበሻ 🇪🇹
🇪🇹 ኢትዮጽያዊነታችንን የምናሳይበት 🤝 አንድነታችንን የምናጠነክርበት 🥰 ፍቅርን የምንማርበት ቻናል ነው ። ☞☞ @Ferhanhabesha
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 4, 2026 | 912 |
| Nov 5, 2026 | 1,150 |
| Nov 14, 2026 | 626 |
Most viewed this month
- 01Views1.15KForwards—Reactions1Comments—
- 02Views921Forwards—Reactions—Comments—
- 03Views914Forwards—Reactions1Comments—
- 04Views901Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
Forwarded from Hoora cast/talent Factory
🎬 ተዋናይ ይፈለጋል! CASTING CALL – LEAD & SUPPORTING ACTORS ለአዲስ የቲቪ ሲትኮም ድራማ መሪና ረዳት ተዋንያን እንፈልጋለን! HOORA CAST – hooracast.com የትወና ብቃት፣ ተሰጥኦና ጠንካራ ፍላጎት ያላቸውን አዳዲስ ተዋንያን ይፈልጋል። 📌 የስራ ዝርዝር የስራ አይነት፦ የቲቪ ሲትኮም ድራማ የገፀ ባህሪ አይነት፦ መሪና ረዳት ቋንቋ፦ አማርኛ ልምድ፦ አያስፈልግም (ጀማሪዎችም ይችላሉ!) 🎭 የሚፈለጉ ተዋንያን ሴት፦ ከ18–28 ዓመት ወንድ፦ ከ40–47 ዓመት 📅 የማመልከቻ ቀን፦ ከ25/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ 📲 እንዴት ማመልከት ይቻላል? 1️⃣ Online Registration: ከየትኛውም ቦታ በቀጥታ https://hooracast.com/register ላይ በመግባት ይመዝገቡ። 📞 ለተጨማሪ መረጃ፦ 0902 35 77 77 🌟 ተሰጥኦህን አታስቀምጥ! ልምድ ባይኖርህም ችሎታህን ለማሳየት እድሉ እዚህ ነው!
Open in Telegramየሾላ ዛፍ– Fig tree| Ethiopian Romantic Drama Movie 2026 https://youtube.com/watch?v=7_KyHKD2bM8&si=UJZugxRRfFJ-4WNm
Open in Telegram"ሴት ልጅ ፈፅሞ የማትረሳው ወንድ" (አሌክስ አብርሃም) ብዙ ወንዶች "ሴት የመጀመሪያዋን ወንድ በህይወት ዘመኗ ሁሉ አትረሳም የሚል ያረጀ ያፈጀ ነገር ሰምተው የመጀመሪያ ለመሆን ሲጋደሉ ይታያሉ!(ሲጋደሉ ይገባችኋል) ወንድ መቸስ ለጅል ድርጊቱ ሁሉ ሐውልት እንዲቆምለት የሚፈልግ ፍጡር ነው። እስኪ አሁን ላለመረሳት እንትን 😁 የሆነ ሆኖ ዛሬ የገረመኝንና ይሄን አመለካከት ውሃ የሚያስበላ ነገር አነበብኩ፤ ከአራት ሺ በላይ ሴቶች ከመላው አለም ጠይቂያለሁ ይላል ፀሐፊው ፤ እና ሴቶች ፈፅሞ የማይረሷቸው ወንዶች ብሎ አንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ምን ቢሆን ጥሩ ነው? (ምን አይነት ስክራፓጯሯሟሷ የሆነ ፆታ እንደሆነኮ) "አብሯቸው በዝናብ ውስጥ የሮጠ ወንድ ፈፅሞ አይረሱም " ይላል። ከምር ገርሞኛል። ካስቀመጠው ምክንያት አንዱ The "Us Against the World" Feeling ይለዋል። ስንፈስረው ሲዘንብ ሁሉም ሰው እየሮጠ ይጠለል የለ? በቃ እኔና አንች ሁነን ዓለም የሚፈራውን አድቬንቸር ተጋፈጥነው፣ አንች ጋር ከሆንኩ ምንም አልፈራም እንደማለት ነው ለሴቷ። ለወንዱ ደግሞ ሜካፔ ታጥቦ ፀጉሬ ተንጨባሮ ክብሬ ምናምኔ ከሚል ፍርሃት በላይ አብሬህ የትም እገባለሁ የሚል መልእክት ይፈጥርበታል። ዙሮ ዙሮ ወንዱ ዝናቡ ሲቆም ይረሰዋል ሴቷ ግን ለዘመናት በዘነበ ባጉረመረመ በጠረረ ሰዓት ሁሉ በዝናብ የቀጨመ ፀጉሯን እያከከች ታስታውሰዋለች ይላል። (እንግዲህ የሮጣችሁ መስክሩ) እኔኮ አንዲት የሰፈሬ ልጅ በተገናኘን ቁጥር ህፃናት ሁነን የሩፋኤል ዝናብ ውስጥ የቦረቅነውን ስታነሳ ማስታወሷ ይገርመኝ ነበር! እስከአሁን በዝናብ ውስጥ ሲሮጡ የተነሱትን ፎቶ የለጠፉ ፍቅረኞች አልገጠሙኝም። አላችሁ? ሞክሩት የባዝ ሩም ፎቶ ሰልችቶናል¡ የሆነ ሆኖ አሁን ሁለት ጠቃሚ ሀሳብ አለኝ ... 1. ከአሁን በኋላ ከእህቶች ጋር ራት የመብላት ዕድል ከገጠመኝ የአየር ትንብያ ቀድሜ አይቸ ነው ቀጠሮ የምይዘው፤ ዶፍ በሚወርድበት ቀን ሐምሌ 23 ወይም ነሐሴ 19 ምናምን ! ወይ በዝናብ ሩጦ ዘላለም መታወስ ነው አልያም "አባቴ በዚህ በዝናብማ አንሄድም እዚሁ እንደር?" የሚል አማራጭ ነው። እሽ አንች ቅደሚ ወደሩማችን እማየ፣ አንተ ቅደም አባየ ... የተባረከ ጥናት! 2. ሰርጎች በዝናብ ቀን አውላላ ሜዳ ላይ ቢደገሱ ፍች የሚቀንስ አይመስላችሁም? በዝናብ ውስጥ ከሮጡ ሲጋቡ አይረሳሱም፣ መንጨባረሩንም ከቀን አንድ ጀምሮ ይለምዱታል😁 ማሳሰቢያ ፦ ሴትን ልጅ ካለፍላጎቷ ዝናብ ውስጥ መጎተት የዝናብ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ነው!!
Open in TelegramForwarded from Dave Alex Wedi Korem
https://youtube.com/shorts/H-1k2--TNSw?si=MOxUft0WFkEBpiEQ ሰብስክራይብ አድርጉልኝ አጠገባቹሁ ላለ ሰው አስደርጉ ለተከታታይ ድራማ ልሰራባት ልወዳደርበት ፈልጌው ነው
Open in Telegramየኢራን ተመራማሪዎች በብርሃን አማካኝነት የካንሰር ሕዋሳትን የሚያጠፋና 80% ውጤታማ የሆነ ስማርት "ጄል" ሰሩ‼️ ይህ "ስማርት ሃይድሮጄል" (ፈሳሽ ቅባት) የጡት ካንሰር ዕጢዎችን በጥንቃቄ ኢላማ በማድረግ ለማከም የኬሞቴራፒ እና በብርሃን ላይ የተመሠረተ ሕክምናን ያጣመረ ነው። ጄሉ ከተፈጥሯዊና ከሰውነት ጋር ተስማሚ ከሆነ "ካይቶሳን" ከተባለ ንጥረ ነገር የተሠራ ነው፡፡ ስፑትኒክ እንደዘገበው መድኃኒቱን በተቆጣጠረ ሁኔታ የሚለቅ ሲሆን፣ የሌዘር ብርሃን ሲያርፍበት ይነቃቃል፡፡ በተለየ ሁኔታ የካንሰር ሕዋሳትን የሚጎዱ የኦክሲጅን ውህዶችን ያመነጫል፡፡ የተደረጉት ሙከራዎች እንደሚያሳዩት፣ ጄሉ ጤናማ ሕዋሳትን ሳይነካ ከ80% በላይ የሚሆኑትን የጡት ካንሰር ሕዋሳት ማጥፋት ችሏል፡፡ ይህ አቀራረብ ከተለመዱት የጡት ካንሰር ሕክምናዎች በተሻለ፣ አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትል እና ቀጥተኛ ዒላማውን ብቻ የሚያጠቃ አማራጭ ሊሆን ይችላል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Open in Telegramሰው ሲሸነፍ ማሸነፍ ምንድነው? የምኞት አዝመራ የደስታ መከር፤ የታጨደ ጣጣ የተወቃ ችግር፤ የሞተ መከራ፤ የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ። እያደር ጠፊ ነው፤ እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል፤ ዋጋው ይቀነሳል። ሁልጊዜ በማግኘት፤ ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመከት፤ በመግዛት በመቅጣት፤ ደስታ አይገኝም። ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ አይጠግብም። ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ፤ መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፤ ስስታም ይሆናል ለፍቶ ጥሮ ግሮ ሲያጋጥመው ዕድል። ዕረፍት አያገኝም። ሲያስብ፣ ሲያጠነጥን፣ ሲታትር፤ ሲደክም፤ አንዱን በመጨረስ መጥኖ ሌላውን፤ ያንን በመሰልቸት ሲጀምር አዲሱን፤ ያቅበዘብዘዋል፤ ትዕግሥት ይነሳዋል። ትንሽ መሰናክል እሾህ መንገዱ ላይ፤ የኑሮ ሕመም ነው የሕይቱ ሥቃይ። ያገባዋል እልክ ደሙን አስቆጥቶ፤ ንዴቱን አምጥቶ። ይተዋል ይሉኝታን ከግቡ ለመድረስ ወዲያ ወዲህ ብሎ ኃይሉን እስኪጨርስ። በመሸነፍም ነው፤ ሰው ደስታ ያለው። በመተው በመርሳት፤ በመልቀቅ በማጣት፤ በመሸሽ በመፍራት። ወደፊት ከመሔድ አውቆ በማፈግፈግ፤ ከማሰብ ለብዙ ጥቂት በመፈለግ፤ በማነስ ከማደግ። በመጣል ከማንሣት፤ በመስጠት ከመውሰድ፤ በማልቀስ ከመሣቅ በመቅረት ከመሔድ፤ ከመውጣታት በመውረድ። ከመልበስ መታረዝ፤ ከማምለጥ በመያዝ። ክብርን ለመጠበቅ ደፍሮ ከመናገር፤ አንገት በማቀርቀር። በመዋረድና በችግር ተጎድቶ፤ በመውደቅ ተገፍቶ፤ በመናቅ ተጠልቶ፤ በሐዘን፤ በድካም፤ በሕመም፤ ባርምሞ፤ አግኝቶ በመስከር በመሻር ተሹሞ፤ ያውቃል ማ መሆኑን፤ ይረዳል አቅሙን። የሕይወት ለውጥ ነው ያለ በኑሮ ላይ፤ እንደ ቀን፤ እንደ ሌት፤ እንደ መሬት ሰማይ፤ እንደ ውሀ እንደሳት እንደ ልቅሶ ሣቅ፤ እንደርጥብ ደረቅ፤ ሁሉም ተለውጦ አንጻሩን ይይዛል፤ የሚሮጠው ጊዜ ጥቂት ይታገሣል። ሰዓቱ ይቆማል፤ ደቂቃው ይተኛል። ይሸፈናል ወሩ፤ ይታሰራል ቀኑ፤ ቀስ ይላል ዘመኑ። © ገብረክርስቶስ ደስታ ሁሌም ማንበብ!
Open in TelegramConnections
Similar channels
Tiktok comments💀@tt_commentzHumor and entertainment4.74K
ዝንቅ መዝናኛ@ziniqHumor and entertainment3.66K
Kottaa Kolfaa@kottaakolfaaHumor and entertainment6.38K
4-3-3 አዝግ ኮሜንቶች 😂@azg_commentHumor and entertainment3.24K
ሀዊኔ ኢንተርቴይመንት Hawine Entertainment@hawineartpromotionHumor and entertainment2.52K
ENDERTA'S JOKE 😀@e70jokesHumor and entertainment1.97K
👼 AnyሐበሻThought 😈@naughtiesonlyHumor and entertainment1.9K
ወግ ብቻ@wegochHumor and entertainment17.1K