Account

Posts of AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

newest first

#1749Photo

✝እንኳን አደረሳችሁ ! ☞ወርኀ ኅዳር ቡሩክ፤ ወአመ ፲ወ፪፦ ✝በዓል ዐቢይ ወክቡር ለዘመደ ክርስቲያን፦ በእንተ ዕበዩ ወክብሩ ለመልአክ ንጹሕ፥ ዐቢይ ወክቡር፥ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት፥ ሊቆሙ ለኃይላት ሰማያውያን፥ መሐሪ ወርኅሩኅ ለዘመደ እጓለእመሕያው፥ ኃያል ወልዑለ መንበር (ረዳኤ ምንዱባ፥ ወሰዋቄ ትንቱናን) ✝ተዝካረ ተአምር ዘገብረ፥ መልአክ ክቡር፥ ሚካኤል ሊቅ፥ ሊቀ መላእክት፥ ርዕሰ ኩሎሙ ኃይላት ሰማያውያን፥ ርኅሩኀ ልብ ወመስተሣህል፥ ለነገደ ያዕቆብ እስራኤል፥ ዘመርሆሙ መዓልተ በዐምደ ደመና፥ ወኩሎ ሌሊተ በብርሃነ እሳት (ዘረድኦ ለኢያሱ እስከ አጥፍኦሙ ለነግሥተ ከነዓን) ✝ወተዝካረ በዓሎሙ ለቅዱሳን፦ ማቴዎስ ሐዋርያ ወወንጌላዊ፥ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ወሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ላሊበላ ጻድቅ ወመስቀል ክብራ፥ ወሠምራ ክርስቶስ ብጽዕት፥ ማር ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ምሥራቃዊ፥ ወማር ድሜጥሮስ ድንግል ❖ ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወነቢይ፥ ወወልደ ነዌ፥ ኢያሱ/አውሴ መስፍን፥ መድኀኒቶሙ ለእስራኤል፥ ዘቀተለ ነገሥተ፥ ወአውረሶሙ ርስተ ለሕዝቡ፥ ወዓዲ ዘአቀመ ፀሐየ በገባዖን፥ ወወርኀ በቆላተ ዔሎም፥ ረድኡ ለቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ዘርዕዮ ለሚካኤል በኢያሪኮ)

Open in Telegram
Views222−52%vs avg
Forwards1
Reactions—
Comments0
#1748Text

+አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ኃያል ወመስተጋድል፥ ወብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር ዮሐንስ ወልደ ዘካርያስ፥ መጥምቀ መለኮት፥ ወጸያሔ ፍኖት፥ ወነቢየ ልዑል፥ ሐዋርያ ወካህን ወሰማዕት፥ ባሕታዊ መምህር ወመገሥጽ፥ ዘኢያደሉ ለገጽ፥ ወዘየዐቢ እምትውልደ አንስት፥ ዘወደሶ እግዚኡ (አስተርእዮተ ርዕሱ በደብረ ማኅው፥ በምድረ ግብጽ) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር አባ ፊላታዎስ ጠቢብ፥ ሊቀ ጳጳሳት ዘሀገረ እስክንድርያ፥ ሰባኬ ሃይማኖት፥ ወመምህረ ወንጌል፥ ወመተርጉመ መጻሕፍት ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ጻድቅ ወንጹሕ ወድንግል፥ ማር አባ ዳንኤል ዘአስቄጥስ፥ ጳጳስ ዘብሔረ ኢትዮጵያ ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ማር አባ ባሕራን ቀሲስ፥ ብእሲ የዋህ፥ መፍቀሬ ጸሎት ወምጽዋት(ፍቁረ ቅዱስ ሚካኤል) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ፍቁር ወመስተጋድል፥ ወመፍቀሬ እግዚአብሔር፥ ማር ዱራታዎስ ቡሩክ፥ ዘሀገረ ቆሎንያ፥ ዘያፈቅር ምጽዋተ (ዘአስተርአዮ ሚካኤል) ✝ቅድስት ወቡርክት፥ ስብሕት ወብጽዕት፥ ክብርት ወልዕልት፥ መፍቀሪተ ክርስቶስ መድኅን፥ ቴዎብስታ ጻድቅት (ብእሲቱ) ✝አብ ዐቢይ ወክቡር፥ ጻድቅ ወንጹሕ፥ ጽሙድ ወመስተጋድል፥ ማር ሐፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ፥ መፍቀሬ እግዚአብሔር ልዑል፥ ወመፍቀሬ እሙ ድንግል፥ ወርቱዓ ሃይማኖት፥ ወንጉሠ ኢትዮጵያ፥ ዘሐነጻ ለአትሮንሰ ማርያም (ወልዱ ለጻድቅ ዘርዓ ያዕቆብ፥ ወአቡሁ ለማር ናዖድ) ✝ቅድስት ወቡርክት፥ ስብሕት ወብጽዕት፥ ክብርት ወልዕልት፥ መፍቀሪተ ክርስቶስ መድኅን፥ ዕሌኒ ንግሥት፥ ዘብሔረ አግዓዚ (ብእሲቱ) ✝ክቡራን ወዐቢያን፥ መፍቀርያነ ክርስቶስ፥ ጻድቃን ንጹሐን (ሰብአ ቤቱ ለማር በእደ ማርያም) ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ። ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

Open in Telegram
Views194−58%vs avg
Forwards0
Reactions1
Comments0
#1747Text

በዘመናችን ያሉ ሐሰተኛ ነቢያትን እንዴት መለየት ይቻላል? በብሉይ ኪዳን ነቢያተ ሐሰትና ነቢያተ ጽድቅ የሚለዩበት መገለጫ ነበራቸው። ከመገለጫዎቹ አንዱ የተናገሩት የትንቢት ቃል ሳይፈጸም ከቀረ ነቢያተ ሐሰት እንደሆኑ ይታወቃል። ይህ ግልፅ የሆነ መለያቸው ነበር፤ ነቢዩ ዮናስ ነነዌ ሄዶ መስበክ ያልፈለገበት ምክንያት አንዱ ይህ ነበር፤ ይኸውም የነነዌ ሀገር በሦስት ቀን ውስጥ ትቃጠላለች ትገለበጣለች ብዬ ብሰብክና እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎላቸው የተናገርኩት ቃል ሳይፈጸም ቢቀር፤ ነቢየ ሐሰት ልባል አይደለምን ብሎ ለስሙ ተጠንቅቆ አልሰብክም ያለበት ምክንያት ለዚሁ ነበር (ዘዳ ፲፰፥፳ ፤ ዮና ፩፥፩)። ባዕድ አምልኮን የሚከተል፤ ሕዝብን የሚሸነግል፤ በክፉ መንፈስ የሚመራ፤ ስለራሱ የሚያወራ ሲሆንና አካሄዱ ክፉ ከሆነ ያ ነቢይ ነቢየ ሐሰት ነው፡፡ ዛሬ በዘመናችን የምናያቸው ነቢያት ከእነዚህ ይመደባሉ፤ ለሕዝቡ የማይራሩ እነርሱ ቁርጥና ክትፏቸውን በልተው ጠጃቸውን ጠጥተው በባዶ አንጀቱ ሊሰማቸው የተሰበሰበውን ሕዝብ "ጌታ እንዲህ ብሎኛልና እንዲህ አድርግ" እያሉ በጠራራ ፀሐይ የደሀውን ገንዘብ እየመዠገጉና የዋሁን ማኅበረሰብ በኀጢአት እያስወጉ የራሳቸውን ክብር እየቆለሉ ሌላውን እያቃለሉ፤ ግብዝ ሕዝባቸውን እያታለሉ የሚኖሩ ነቢያተ ሐሰት ናቸው — (ዘዳ ፲፫፥፩ ፤ ፩ኛ ነገ ፳፪፥፲፱ ፤ ኤር ፳፫፥፱)። ኀጢአት በበዛ ጊዜ ስለፍርድ ስለሰላም የሚተነብይ ከሆነ ይህ ማለት ኀጢአት እየሠሩ ጣዖት እያመለኩ የእግዚብሔር ቁጣ እንደሚመጣ በመናገር ፋንታ ሰላምና ደስታ ይሆንላችኋል፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው እያለ ሕዝቡን የሚያታልል ከሆነ ያ ነቢይ ሐሰተኛ ነቢይ ነው፡፡ የትንቢቱ ቃል ከመንፈሳዊነቱ ይልቅ ሥጋዊነቱ የሚያመዝን ከሆነ ለምሳሌ ሥራ ታገኛለህ፤ ትዳር ታገኛለህ፤ ውጭ ሀገር ትሔዳለህ፤ ሀብታም ትሆናለህ እነዚህን የመሳሰሉት ነገሮች፤ ትንቢት ከሚባሉ ይልቅ ሟርት ይባላሉ። ሕዝ ፲፫፥፫ ፤ ኤር ፳፫፥፲፮ ፤ ኤር ፮፥፲፫)። ግለሰቡ ከራሱ ጥቅምና ክብር አንጻር የሚናገር ከሆነ ወይም ዛሬ በየመናፍቃኑ አዳራሽ እንደምናየው ትንቢት እናገራለሁ ባዩ የሚናገረው ትንቢት የራሱን ጥቅም ለማሟላት ክብሩን ለማስጠበቅ የሚናገር ከሆነ፤ ለምሳሌ «ዕገሊትን ታገባለህ ተብያለሁ» በማለት የፈለጉትን ማድረግ፤ ወይም ይህን ያህል ብር ታገኛለህ ተብያለሁና አድርጉ የሚል ከሆነ ያ ነቢይ ሐሰተኛ ነቢይ ነው (ሚክ ፫፥፲፩) ምክንያቱም ከእውነተኞች ነቢያት እንዲህ ዐይነት ጠባይና ዓመል ታይቶ አይታወቅም፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ነቢያት እነኤልያስ፣ እነኢሳይያስ፣ ሌሎችም ነቢያት እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሕጉን የሚያከብሩ ለእግዚአብሔር ያደሩ ምንም ሀብት ጥሪት የሌላቸው እግዚአብሔርን ሀብት ጥሪት አድርገው የኖሩ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ስለ ራሱ ታሪክና ክብር የተናገረ ነቢይ የለም። ጉዳዩ (የትንቢቱ መልእክት) ከእግዚአብሔር ጋራ በምንም መልኩ የማይገናኝ ከሆነ ለምሳሌ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከማስፋፋት፤ ነገረ ሃይማኖትን ከማስተማር፤ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ከመመለስ፤ የንስሐ ሕይወትን ከመስበክ የራቀ ከሆነ ይህ ትንቢት አይባልም። ምክንያቱም የትንቢት መጨረሻ ግቡ ሰውን ወደ ሃይማኖት ማምጣት፤ ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘትና ንስሐን መስበክ ነው (ኢሳ ፴፭፥፭)። ትንቢቱ ከሰው መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፍጹም ግንኙነት የሌለው ከሆነ ያ ሰው ያለምንም ጥርጥር ነቢየ ሐሰት ነው፤ ዛሬ መናፍቃን እንደሚያደርጉት በዓለም ስለሚደረጉ ሁነቶችና ወቅታዊ ጉዳዮች ማንነታቸውንና ተቀባይነታቸውን ለማጉላት ሲሉ የሚተነብዩ (የሚያሟርቱ) ሰዎች አሉ። ለምሳሌ በዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የዓለም ሕዝብ ትኩረት የሚስቡ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች ሊሆን ይችላል አስቀድሞ ዕገሌ ያሸንፋል ዕገሌ አያሸንፍም የሚባሉት ነገሮች እነዚህንና የመሳሰሉ ሁሉ «ሟርት» ይባላሉ እንጂ ትንቢት አይባሉም፤ እንዲሁም ግለሰቡ ያለበትን ሁኔታና ፍላጎቱን በማየት ግምት መስጠት፤ ለምሳሌ የጤና ጉድለትን በሚመለከት የኑሮ ደረጃን፣ ሀብትን፣ ሥልጣንን በሚመለከት አስቀድሞ ግምት በመውሰድ የሚነገሩ ሁሉ ይህ ትንቢት አይባልም (ኤር ፭፥፴) ስለዚህ ዛሬ ትንቢት እንናገራለን ነቢያት ነን የሚሉ ሁሉ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ የሐሰት ነቢያት መሆናቸውን በዚህ ቃል መዝኖ ማወቅ ይቻላል። ዳግመኛም ሐሰተኞች ነቢያት እንደሚነሡ ክርስቶስ ለሐዋርያት፣ ሐዋርያት ለሰብአ አርድእት ከዚያም በኋላ ተላውያነ ሐዋርያት በየዘመናቸው አስጠንቅቀዋል (ማቴ ፯፥፲፭ ፤ ፪ኛ ጴጥ ፪፥፩ ፤ ፩ኛ ዮሐ ፬፥፩)። ስለዚህ ከኅሊናቸው ሰሌዳ ከልቡናቸው ጓዳ አንቅተው የሚናገሩ፤ ሳይላኩ ተልከናል ብለው ራሳቸውን ነቢያት አድርገው የሾሙትን ነቢያተ ሐሰት እንዳንቀበል የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ያዝዘናል፦ ❝እኔ የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ፤ እነሆ ከምላሳቸው ትንቢት አውጥተው እርሱ ይላል በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፤ እነሆ ሐሰት በሚያልሙ በሚናገሩም በሐሰታቸውና በድፍረታቸው ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግዚአብሔር እኔም አላኳቸውም አላዘዝኳቸውም ለእነዚህ ሕዝብ በማናቸውም መልኩ አይረቧቸውም❞ — በማለት የሐሰት ነቢያት ለሕዝብ ደኅንነት ጠንቅ ለሀገር ሰላም ጭንቅ መሆናቸውን ተናግሯል። በተለይ በዘመናችን በየመናፍቃን አዳራሽ እንደምንሰማው "ነገ ሀብታም ትሆናለህ፤ እንዲህ የሚባል ድርጅት ያንተ ይሆናል" እያሉ በኑሮ ሂደት ሳይሠሩ ሳይደክሙ መበልጸግን የሚያስመኙ ሕዝብን መረን የሚያደርጉ፤ ስንፍናን የሚያስተምሩ ዘረፋን የሚያስፋፉ፣ የደሀን ገንዘብ የሚገፉ በአዕምሮ የሰነፉ ዳተኞች ነቢያት መሆናቸውን አውቀን ከእነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት እንድንርቅ ያስጠነቅቀናል (ኤር ፳፫፥፳፫)። እኛም ቤት በስመ አጥማቂ፣ በስመ ሰባኪ ክርስቶስን እንዲሰብኩ ታምነው በተሰጣቸው ዐውደ ምሕረትና መንጋ ላይ "እኔ እንዲህ ሆኜ፣ እንዲህ አድርጌ ..." እያሉ ራሳቸውን ብቻ የሚያገንኑ 'አገልጋዮች' ቁጥራቸው ብዙ ነው። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ! ዲ/ን ኃይለራጉኤል

Open in Telegram
Views306−33%vs avg
Forwards2
Reactions5
Comments0
#1743Photoalbum

Forwarded from አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

No text

Open in Telegram
Views598+31%vs avg
Forwards1
Reactions—
Comments—
#1742Photoalbum

Forwarded from አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

No text

Open in Telegram
Views567+24%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments—
#1741Photoalbum

Forwarded from አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

No text

Open in Telegram
Views587+28%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments—
#1740Photoalbum

Forwarded from አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

No text

Open in Telegram
Views568+24%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments—
#1739Photoalbum
Views522+14%vs avg
Forwards0
Reactions2
Comments0
#1738Text

Forwarded from ያሬዳውያን

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 የጥቅምት 8 የሁለተኛው ሳምንት ማኅሌተ  ጽጌ በዓለ ፬ቱ እንስሳ ወኪሮስ ገዳማዊ ሥርዓተ ማኅሌት አማርኛ ትርጓሜ ክፍል ፪ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ማኅሌተ ጽጌ እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተኣምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ @EOTCmahlet ትርጉም ነጭ እና ቀይ የሆንሽ ጽጌ በንጽሕናና በተኣምር ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ  ልጅሽን ታቅፈሽ ነዪ ። ርግቤ ሆይ ከሀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ ። መልካም የሆንሽልኝ ሆይ ከደስተኛ መልአክ ከገብርኤል ጋራ እና እንዳንቺ ሩኅሩኅ ከሆነ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነዪ ። @EOTCmahlet ወረብ፦ ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/ ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/ ትርጉም፦ ርግቤ ሆይ ነዪ ከሚካኤል ጋራ ነይ።  መልካም የሆንሽልኝ ሆይ ከደስተኛ መልአክ ከገብርኤል ጋራ እና እንዳንቺ ሩኅሩኅ ከሆነ ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ጋራ ነዪ ። ዚቅ በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም። ትርጉም፦ ማርያም!! ከልቤ ኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከሚካኤል እና ከገብርኤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከሱራፌል እና ከኪሩቤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ከልጅሽ ከአማኑኤል ጋር በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ፤ ማርያም!! ዓለምን ሁሉ ለማረጋጋት በፍቅር አንድነት ( በሰላም) ነይ። ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡ ትርጉም የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል ። ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/ ትርጉም፦ ከዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የአበባ አክሊል ማርያም የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት ነሽ ። ዚቅ፦ ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት @EOTCmahlet ትርጉም፦ ከሴቶች ይልቅ ከፍ ከፍ ትላለች ። የሰማዕታት እናታቸው ነች ። የመላእክት እኅታቸው ነች ። የነገሥታት መድኃኒታቸው ነች ።  ለካህናት ንጹሕ አክላለቸው ነች ። የከዋክብት ብርሃናቸው ነች ። ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ። @EOTCmahlet ወረብ፦ ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም /፪/ ማርያም ከመ ዖፍ ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ/፪/ @EOTCmahlet ትርጉም ማርያም ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ብቻዋን በግብፅ ተራሮች ውስጥ ትንከራተታለች፤ የሕፃናትም ደም በመንገዷ ሁሉ ይፈሳል። @EOTCmahlet ዚቅ፦ አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ። @EOTCmahlet ትርጉም ልጅሽን አቅፈሽ ከሰይፍ ባሸሸሽ ጊዜ፤ ከዓይኖችሽ እንባ ከጉንጮችሽም ወዝ እንደ ዝናም እየወረደ ተራሮችን እንደ ወፍ ዞርሽ። @EOTCmahlet @EOTCmahlet መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ። @EOTCmahlet ትርጉም ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ከአርያም በላይ ያለ የአምላክ የጥበቡ ብዛት  እጅግ የሚያስደንቅ ነው ። የጥበቡ ብዛት እጅግ የሚያስደንቅ ነው ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። ሰማይን በሚያበሩ  ከዋክብቶች ያስዋበ /የከለለ / ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። ምድርንም ንጹሕ በሆኑ አበባዎች አስዋባት ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ። በእርሷ ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን ሠራ ። ምሕረቱን በእኛ ላይ ገለጠ ።   @EOTCmahlet አመላለስ፦ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/ ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/ @EOTCmahlet ትርጉም የቅዱሳን መዓዛቸው በሸለቆዎች ውስጥ እንዳለ እንደ ሱፍ አበባ ነው ። ቀንሞስ የተባለ ሽቱን ናርዶስ ከተባለ ሽቱ ጋር አፈሩ ። 👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet   #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

Open in Telegram
Views1,026+124%vs avg
Forwards3
Reactions2
Comments0
#1737Text

Forwarded from ያሬዳውያን

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ አመ አሚሩ ለጥቅምት ዘቀዳማይ ጽጌ በዓለ ልደታ ወራጉኤል ስርዓተ ማኅሌት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ለማንኛውም ወርኃዊ እና አመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ ..................................................... ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። @EOTCmahlet መልክአ ሥላሴ ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም። @EOTCmahlet ዚቅ፦ ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎም፤ናርዶስ ጸገየ ዉስተ አፍሆሙ፤ @EOTCmahlet @EOTCmahlet በላይ ቤት የሚባል መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡ @EOTCmahlet ዚቅ መግቢያ ዘማኅሌተ ጽጌ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፤ተሠርገወት ምድር   (🌹#በህብረት_ሁሉም🌹) በስነ ጽጌያት፤ለመርዓዊሃ ትብሎ መርዓት፤ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት። @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ፦ ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ  እምዓጽሙ፤ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ወበእንተዝ ማርያም ሶበ  ሐወዘኒ ጣዕሙ፤ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ መዓዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ ሶበ ሶበ ሐወዘኒ/፪/ ወበእንተዝ ማርያም አኅሊ ለተዓምርኪ/፪/ @EOTCmahlet ዚቅ፦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ ወመንክር ስብሐቲከ፤ለዕረፍት ሰንበት ሠራዕከ፤ @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ(በላይ ቤት)፦ ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ @EOTCmahlet ዚቅ፦ ሰአሉ ለነ ሐና ወኢያቄም ዘወለድክምዎ ለማርያም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም @EOTCmahlet @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ። @EOTCmahlet ወረብ፦ እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ ፍኖተ ነፈርዓፅ/፪/ ማዕከለ ማኅበር እዜምር ማዕከለ ማኅበር/፪/ @EOTCmahlet ዚቅ ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን። @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ /፪/ አመ  ቤተ  መቅደስ ሠናይትየ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/ @EOTCmahlet ዚቅ፦ ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ፤ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ። @EOTCmahlet ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ  መንግሥቱ/፪/ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ዚቅ በወርቅ ወበዕንቁ ወበከርዴን ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት ወነገስት ይትቀነዩ ለኪ ትርሢተ መንግስቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት @EOTCmahlet ዓዲ ዚቅ ርግብ ፀዓዳ ዘዕንቁ ድዳ፤ወዘጳዝዮን ማኅፈዳ፤ተወልደት ዮም በምድረ ይሁዳ፡፡ @EOTCmahlet ሰቆቃወ ድንግል በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕፀተ ግጻዌ ዘአልቦ፤ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንቦ፤ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ ለኩለሄ ረከቦ፤ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ @EOTCmahlet @EOTCmahlet ወረብ፦ ከማሀ ኀዘን ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ኀዘን/፪/ ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ ዓይነ ልብ ዘቦ/፪/ @EOTCmahlet ዚቅ፦ እወ አማን እምውሉደ ሰብእ አልቦ፤ምንዳቤ ወግፍዕ ዘከማኪ በዉስተ ኩሉ ዘረከቦ፤ @EOTCmahlet መዝሙር ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ትዌድሶ መርዓት፤እንዘ ትብል ነዓ ወልድ እኁየ፤ ንፃዕ ሐቅለ፤ትዌድሶ መርዓት ንርዓይ ለእመ ጸገየ ወይን፤ወለእመ ፈረየ ሮማን፤ትዌድሶ መርዓት አሠርገወ ሰማየ በከዋክብት፤ወምድረኒ በስነ ጽጌያት፤ትዌድሶ መርዓት እስመ ውእቱ ወልድ ዋሕድ፤እግዚአ ለሰንበት፤ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ፤ ወልድ እኁየ ቃለከ አዳም። @EOTCmahlet አመላለስ፦ ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ/፪/ ወልድ እኁየ ቃለከ አዳም/፬/ @EOTCmahlet 👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet   #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

Open in Telegram
Views986+115%vs avg
Forwards2
Reactions3
Comments1
#1736File

Forwarded from ምስባክ ወማኅሌት

No text

Open in Telegram
Views643+40%vs avg
Forwards4
Reactions2
Comments0
#1735Photo

Forwarded from Dn. HaileRaguel

ዘመነ ጽጌ ጽጌ ማለት 'ጸገየ – አበበ' ከሚለው ከግዕዝ የተገኘ ሲሆን አበባ ማለት ነው:: በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮና በቅዱስ ያሬድ የዜማ ይትበሃል መሠረት ደግሞ ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለው ወቅት ሲሆን ይኸውም አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም አርባ ቀን ይሆናል:: ይህ ወቅት «ወርኃ ጽጌ» ወይም «ዘመነ ጽጌ» ተብሎ ይጠራል። በእነዚህ ስሞናት በቤተ ክርስቲያን የሚነበቡ ምንባባት የሚዘመሩት መዝሙራት የሚሰበኩት ስብከከቶች የሚቆመው ማኅሌት ሁሉ ምድርን በጽጌያት ማሸብረቁን የሚገልጽ ይሆናል:: ወርኃ ጽጌ የተባለበት ምክንያት መጀመሪያ አበቦች የሚገለጡበትና ተራሮችን የሚያስጌጡበት መዐዛቸውን የሚሰጡበት ወቅት በመሆኑ ወቅቱንና ወራቱን በማስገንዘብ ከዘመኑ አንጻር «ጽጌ» ተብሏል:: የአበባ ተፈጥሮ ከፍሬ ነው፤ የፍሬ ተፈጥሮ ከአበባ ነው። ሁለቱም ግን የሚወለዱት በዕለተ ሠሉስ ከተፈጠሩት ዕዕዋት፣ ሣርና አትክልት ወገን ነው። ይህም የአበባን ስነ ተዋልዶ ያሳያል:: በትርጓሜየችን ደግሞ አበባና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌዎች ናቸው፤ ፍሬ ያለ አበባ አበባም ያለፍሬ መገኘት እንደማይችል ሃይማኖትም ያለ ምግባር፤ ምግባርም ያለ ሃይማኖት ዋጋ የማያሰጥ መሆኑን ያመለክታል:: ከዋክብት እንደ ዕንቊ ፈርጥ ሆነው ሰማይን እንደሚያስውቡት፣ አበባዎችም ምድርን የሚያስጌጡ መሆናቸውን ንጉሡ ሰሎሞን በመኃልዩ፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በወንጌሉ፤ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በድጓው በደንብ አድርገው በሚገባ ገልጸውልናል:: የአበቦች ሕብረ መልክዕና የተፈጥሮ ባሕርያቸው ውበት እጅግ አስደናቂ ስለሆነ ለአፍአዊ ዐይን ብቻ ሳይሆን ለውስጣዊ ዐይነ ልቡና ተስፋ ሆነው መንፈስን በማደስ የሕይወትን ሐመልማል ያሳያሉ፡፡ እነሆ ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ፤ መፀው ሲገባ፤ በመብረቅና በነጎድጓድ እየታጀበ በበረዶና በውርጭ እየተመራ ምድርን በጉም፤ ሰማይን በደመና አሽጎ ሰውን፤ እንስሳትንና አዕዋፍን በብርድና በቆፈን አስሮ ሦስት ወር አንቀጥቅጦ የገዛው ዝናም ወደ ኋላ ይመለሳል፤ ወፎችና አሞሮች ከስደት ይመለሳሉ! ዘግተው የከረሙት ከዋሻቸው ይወጣሉ፤ የመስቀል ወፍም ካባዋን ደርባ ብቅ ትላለች። የወንዞች ድንፋታና የሸለቆዎች ሽለላ በዝምታ ይዋጣል፣ አሣዎችና ጓጉንቸሮች ወደ ቦታቸው ወደ ባሕር ጠልቀው ይገባሉ፤ እግረኞችም ከሩቅ ዘመዳቸው ጋር ይጠያየቃሉ፡፡ ተራሮችና ኮረብቶች፣ ዱሮችና ጫካዎች የሚጎበኙበት፤ ሽማግሌዎች የመንፈስ መታደስ የሚያገኙበት፣ ሕፃናት የሚፈነድቁበት፤ ነፋሳት ከዛፎች ጋር የሚጫወቱበት፤ ለፈትል የተዘጋጀ ንድፍ መስሎ አልፎ አልፎ የሚታየው የደመና ክምር፣ የወፎች ዝማሬ፣ የፋፋቴዎች ፍሰት የጎብኝዎችን ልቡና የሚያረካበት፣ ብሩህ ቀን ይሆናል። በተራሮችና በሸንተረሮች ላይ በልዩ ልዩ ቀለማት ያሸበረቀ አበባ ይዘረጋል፤ ምድርም አደይ አበባን ተከናንባ ትፈነድቃለች። የአተሩና የባቄላው አበባ፤ የስንዴና የሽንብራ ቡቃያ ይታያል፤ የተፈጥሮ መዐዛቸው በምሥራቅና በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ ይናኛል፣ የጨለማ መጋረጃ ተቀዶ የብርሃን መጋረጃ ይዘረጋል፤ ደመናው፤ ጉሙ፤ ጭጋጉ፣ ብርዱና ውርጩ ይሸኛሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ወርኃ ክረምቱ ካለፈ በኋላ ያለውን ድባብ ሲገልጥ:- ❝ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርግወት ምድር በስነ ጽጌያት ሎቱ ይደሉ ስብሐት ለአምላከ ምሕረት ኀለፈ ክረምት ወገብዓ ዝናም ድኅሬሁ ወአስተርአዩ ጽጌያተ ገዳም አዕደወ እክል ወበጽሐ ጊዜሁ ለማዕረር — ክረምት አለፈ፤ በረከት ተተካ (ጸና ተተከለ) ምድር በአበቦች ውበት ተሸለመች ተገጠች። ለምሕረት አባት ለእርሱ ክብር ምስጋና ይገባል። ክረምት አለፈ፤ ዝናብም ወደ ኋላው ሔደ። የገዳም አበቦች ታዩ ተገለጡ። የእህል እጆች የአዝመራ ጊዜው ደረሰ።❞ — በማለት ወርኃ መስከረም ገበሬው የድካሙን ፍሬ አይቶ የሚደሰትበት ምሕረት በረከት የሚተካበት የደስታ ዘመን መሆኑን ዘምሯል፡፡ ስለዚህም ነገር ሰሎሞን የአበባን ውበት በማድነቅ በመሐልይ መዝሙሩ ላይ:- ❝እስመ ናሁ ክረምት ጎለፈ ወዝናም ገብአ ድኅሬሁ ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ፣ ቃለ ማዕነቅ ተሰምዐ በምድርነ፣ በለስ እውጽአ ሠርፀ፣ አውያን ጸገዩ፤ ወወሀቡ መዐዛ — ኧእነሆ ክረምት አለፈ፤ ዝናሙም ተመለስ፣ አበባዎች በምድራችን ተገለጡ፤ የአጨዳ ጊዜ ደረሰ፤ በለስም ጎመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዐዛቸውንም ሰጡ❞ — ብሎ በምሳሌ ፍዳና መርገም እንዳለፈ አበባ ክርስቶስ እንደተገለጠ፤ የምሕረትና የቸርነት ጊዜ እንደ ደረሰ ያስረዳል፡፡ — መኃ ፪፥፬። ዘመነ መጸው ይዞት የሚመጣው የአበባ ውበት እንዲህ ያለ ተናፋቂና ተወዳጅ መንፈስን ካሉበት ዓለም በተመስጦ ወደ ሌላ የምርምር ዓለም አዛውሮ የአዕምሮን አውታሮች ለአዲስ የፍልስፍና ሐሳብ የሚያዘጋጅ የእግዚአብሔርን ባሕርያዊ ኪነ ጥበብ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን ነው:: ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም ስለ አበባ የዘመራቸውን መዝሙራት በልዩ ልዩ ምሳሌነት እንዲህ ሲል አቅርቦአቸዋል:- ❝ክልኤ አጥባትኪ ከመ ክልዔ ዕጕለ መንታ ዘወይጠል ዘይትረአይ ውስተ ጽጌያት — ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ በአበባዎች መካከል እንደ ተሰማሩ እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው፡፡❞ — በማለት ሁለት ጡቶች የተባሉ ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን መሆናቸውን በምሥጢር ተናግሯል፡፡ — መኃ ፫፥፲፩። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ከላይ ያየነውን የሰሎሞንን ዝማሬ መነሻ አድርጎ በድጓው እንዲህ ሲል ተቀኝቷል:- ❝ከናፍሪሁ ጽጌ አለ ያውኅዛ ከርቤ ፍጹመ፧ ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነቱ ውስተ አብያተ አፈው ይርዓይ ገነተ ወያስተጋብዕ ጽጌያተ — ከንፈሮቹ ፈጽሞ ከርቤን እንደሚያፈሱ አበቦች ናቸው፤ ወንድሜ ወልድ የአትክልቱን ቦታ ይጎበኝ ዘንድ አበባዎችንም ይሰበስብ ዘንድ ወደ ሽቶ ቤቶች ወደ አትክልቱ ቦታ ወረደ።❞ ­— በማለት በድጓው ዘምሯል:: መኃ ፬፥፭። አንድምታውን ስናይ  «ወንድሜ ወልድ» የምትለው ፩ኛ. ቤተ እስራኤል፣ ፪ኛ. ቤተ ክርስቲያን ናት። ‹‹ገነት›› የተባለች ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ዳግመኛም:- ❝ወረደ ወልድ እኁየ ውስተ ዘርዐ ሙኅዝ፣ ኀበ ፈረየ አክያሞስ ይርአይ ለእመ ጸገየ ወይን፤ ወለእመ ፈረየ ሮማን — ወንድሜ ወልድ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ ያይ ዘንድ ወደ ገውዝ አትክልት ቦታ ወረደ::❞ — በማለት ዘምሯል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ሰሎሞንን ተከትሎ እንዲህ ብሏል:- ❝እምይእዜሰ ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፣ ቀንሞስ ምስለ ዕንጐታት ዘዚአሁ መዐዛሁ፣ ወዘዚአሁ ጥዑም ፄናሁ — ከእንዲህ ወዲህስ ክረምት አለፈ፤ በረከት ተተካ፤ ወይን አበበ፣ ሮማንም አፈራ፤ የሽቶ ዕንጨት ከትርንጎ ጋር መዐዛውም የባሕርዩ የሆነ፣ ሽታውም ጣፋጭ የሆነ አፈራ::❞ — በማለት ወቅቱ የበረከት የደስታ የብሩህ ተስፋ ወቅት መሆኑን ተናግሯል:: መኃ ፬፥፲ ፤ ፬፥፴፪። እንኳን ዓመቱን ሙሉ ለምንናፍቃት ለወርኃ ጽጌ አደረሳችሁ/አደረሰን። ስለ ስለ ማኅሌተ ጽጌ፣ ሰቆቃወ ድንግል ... እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ተያያዥ ትምህርቶች እንደተለመደው በዚሁ ቻናል መማማራችንን እንቀጥላለን። ዲ/ን ኃይለራጉኤል

Open in Telegram
Views912+99%vs avg
Forwards4
Reactions6
Comments4
#1734Text

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ #መዝሙር_ዝንቱ_ውእቱ_መስቀል_ከመስከረም_፲፯- #መስከረም_፳፫ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 መዝሙር ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤በጽንዓ ኃይል ወበሠናይ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኃጢአተ ይሠሪ፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤ጸርሑ ጻድቃን እምደብር ልዑል ወኃጥአነ ምድር በማዕከለ ደይን፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤ለእምነ ጽዮን ቆመ ማዕበል በዕለተ ሰንበት ገሠፃ ለባሕር፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤በዕለተ ሰንበት ገሠፃ ለባሕር ደቂቀ እስራኤል ዓደዉ በእግር፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤ደቂቀ እስራኤል ዓደዉ በእግር ንሕነ ነአምን ረድኤተ ወኃይለ፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤ንሕነ ነአምን ረድኤተ ወኃይለ ጽንዕነ ቤዛነ በማዕከለ ፀር፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን ዕፁበ ያቀልል፤ኃይልነ ወፀወንነ ወሞገስነ፤ዝንቱ ውእቱ መስቀል። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ትርጕም፦ መስቀል ይህ ነው በእውነት የጨነቀ ነገርን ያቀላል በኃይል ጽናት በበጎ ምግባር በዕፀ መስቀሉ ኃጢአትን ያስተሠርያል። ጻድቃን ከልዑል ተራራ ላይ ሆነው ጮኹ ኃጥአንም በሥቃይ መካከል ሆነው ጮኹ። ለእናታችን ጽዮን ማዕበል ቆመ በዕለተ ሰንበት ባሕርን ገሠፃት የእስራኤል ልጆች በእግር ተሻገሩ እኛም ረድኤቱንና ኃይሉን እናምናለን። መስቀል በጠላት መካከል ጽናችን ቤዛችን ነው። ይህ መስቀል ኃይላችን ፀወናችን ሞገሳችን ነው። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዓራራት በመስቀሉ አርኃወ ገነተ፤በመስቀሉ ገብረ መድኃኒተ ሰደደ አጋንንተ፤እመስቀሉ ወሪዶ ቤዘወነ፤ወሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ዕዝል ገሠፀ ባሕረ ወነፋሳተ፤ወኵሉ ፍጥረት ያከብርዋ ለሰንበት፤በኃይለ መስቀሉ አጋንንተ አውጽአ፤እለ ለምጽ አንጽሐ፤ገብረ ተአምረ፤ፈወሰ ዱያነ፤ወከሠተ አዕይንተ ዕውራን፤ወኵሎ ፈጺሞ፤አዕረፈ እግዚእነ በሰንበት። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ሰላም በመስቀሉ ወበቃሉ ገብረ ለነ ሰላመ፤ክርስቶስ መድኃኒነ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤(ለዕረፍተ) ዚአነ፤እንዘ ዝርዋን አስተጋብዓነ፤በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 የዕለቱ ምንባባት፦ ፩ቆሮ ፩፥፲ - ፍ፤ ፩ጴጥ ፬፥፩ - ፲፪፤ ግብ ፪፥፳፪ - ፴፯፤ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 የዕለቱ ምስባክ፦ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት፤ ወይድኀኑ ፍቁራኒከ። መዝ ፶፱፥፬ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ትርጉም፦ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው፤ ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፤ ወዳጆችህም እንዲድኑ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ምሥጢር፦ ለሚፈሩህና ለሚያመልኩህ ለሚጠተ ሥጋ ምልክት የሚሆን ሞተ ብልጣሶርን ሰጠሃቸው። ከመከራ ሥጋ ይድኑ ዘንድ። በሕግ በአምልኮት የሚወዱህ ከመከራ ሥጋ ይድኑ ዘንድ። አንድም፦ለሚያመልኩህ ለሚፈሩህ ለሠለስቱ ደቂቅ ለድኅነተ ነፍስ ምልክት የሚሆን ተአምራትን አደረግህላቸው። የሚወዱህ የሚያመልኩህ ሠለስቱ ደቂቅ ከእቶነ እሳት ይድኑ ዘንድ። አንድም፦ ለባህታውያን የተመውዖ አጋንንት (የአጋንንት ድል መነሣት) ምልክት የሚሆን ግራ ቀኝ ማማተብን ስመ ሥላሴን መጥራትን ሰጠሃቸው። ከፀብዓ አጋንንት/ከአጋንንት ፈተና ይድኑ ይጠበቁ ዘንድ። 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 የዕለቱ ወንጌል፦ ማር ፰፥፳፯(፴፬) - ፍ ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ አው ዘዮሐንስ አፈወርቅ 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 ➾✍እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏  💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 join and share Via ማህሌታውያን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 🇪🇹👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇🇪🇹 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚 🇪🇹👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆🇪🇹 💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚     🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪            ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥   ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧       ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

Open in Telegram
Views1,070+134%vs avg
Forwards1
Reactions4
Comments0
#1732Text

✝✝እንኳን ደስ አላችሁ✝✝✝ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ... መዝ 118:26 ውድ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ የ2018 ዓ.ም ተመራቂ እህቶችና ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ “እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።”   — መዝሙር 128፥4 እግዚአብሔርን መፍራት የተማርንባችሁ ተመራቂዎች እንኳን ለዚህች ለምትናፍቋት ቀን አደረሳችሁ!!.... እዚህ ቀን ለመድረስ ቅድስት ክዳነምህረት ቤተክርስቲያን ግቢ ተደፍታችሁ ያነባችሁት የዕንባ ብዛት ትዝ ይላችኋል?..... "እንደው የነገዋን ፈተና አላጠናሁም፣ እባክሽ አሳልፊኝ" ብላችሁ ስንቴ ነው ቅድስት ክዳነምህረት ያስጨነቃቿት?😁..... አሁን በቅርቡ እንኳን የ exit ነገር አስጨንቋችሁ ስንቴ ነው የቅድስት ክዳነምህረት  የጸሎት Network ያጨናነቃችሁት?🤭..... እዚህ የደረሳችሁት በምትወዷት በእመብርሃን ምልጃ፣ በአቡነ ሀብተማርያም ረዳትነት በአምላካችሁ ፈቃድ መሆኑን መቼም እንዳትረሱ!..... በቃና ዘገሊላ ተገኝታ የጎደለውን ወይን ያስሞላች እመቤታችን እናንተንም የጎደላችሁን ነጥቦች ሞልታ እዚህ እንዳደረሰቻችሁ እንዳትረሱ! በዚህ ቀን ስለእናንተ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ወላጆቻችሁ በደስታ የሚሰክሩበት ዕለት ነው። ከእነርሱ በላይ ደግሞ ፈጥሮ፣ መግቦና አሳድጎ እዚህ ያደረሳችሁ አባታችሁ መድኃኔዓለም የሚደሰትበት ዕለት ነው። ለምን ተደሰቱ ካላችሁ ዋጋ የተከፈለበት ነገር አብቦ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር ስለሌለ ነው። ስለዚህ አሁንም ዋጋ የከፈሉላችሁን አባትና እናቶቻችሁን (የሥጋ ወላጆቻችሁ፣ አባታችሁ መድኃኔዓለም፣ እናታችሁ እመብርሃን) ልታስደስቷቸው የምትችሉት ራሳችሁን ሰጥታችሁ አገልግሎታችሁን ስትቀጥሉ ነው። አደራችሁን አገልግሎታችሁን እንዳታቋርጡ!!! አይዟችሁ እስካሁን ያሳለፋችሁት አገልግሎት፣ ቤተ ክርስቲያን የተመላለሳችኋት እያንዳንዷ እርምጃ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቆጥራለች። ምክንያቱም “እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።”(ዕብራውያን 6፥10) እግዚአብሔር ደግሞ ዋጋን የሚከፍለው በምድርም፣ በሰማይም ነውና አሁንም ለምትጀምሩት አዲስ የሥራ ሕይወት በበረከት ይጎብኛችሁ!!... በመንገዳችሁ ሁሉ እመብርሃን ከነልጇ ይቅደሙላችሁ! ስለማይነገረው ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። 👉መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!               ✨ አብርሂ አብርሂ                 ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም

Open in Telegram
Views1,977+331%vs avg
Forwards1
Reactions15
Comments0
#1731Text
Views1,608+251%vs avg
Forwards0
Reactions3
Comments0
#1730Photo

Forwarded from አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

🕊️ የዝክር እና የምስጋና መርሐግብር 🙏 “ለእግዚአብሔር ምን እመልሳለሁ? ስላደረገልኝ ውለታ ሁሉ። የመድኃኒትን ጽዋ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።” መዝሙር 116:12-13 📖 “በእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት፣ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ከሞት ከተረፍን 1 ዓመት ሆነ።” ✨ ያለፈው አመት በዚች ዕለት በግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው። ነገር ግን በዚያ ሁሉ ጨለማ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር አልተለየንም፤ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጋሻና መከታነትም ከሞት አፋፍ መልሶናል። 🙌 የተደረገልንን ታላቅ ነገር ወደ ልባችን መልሰን የምናስብበት፣ አምላካችን የምናመስግንበትና ሰማዕቱን የምንዘክርበት ልዩ ቀን ነው። 🔹 ኑ፣ በአንድነት ቆመን የምስጋና መሥዋዕት እንሰዋ! 📍 መርሐ ግብሩ መቼና የት ነው? ዛሬ፦  እሁድ ግንቦት 23 - 2018 ዓ.ም ሰዓት፦ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ቦታ፦ አምዩ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ -ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነምህረት “የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና በረከት አይለየን።” ይህንን መልዕክት ለሌሎችም Share ያድርጉ። 📢

Open in Telegram
Views1,630+256%vs avg
Forwards0
Reactions1
Comments0
#1729Text
Views1,384+202%vs avg
Forwards1
Reactions—
Comments0