Account

Posts of Fuad Muna (Fuya)

newest first

#4239Text

ስሜ አይገለፅ ያለች እህት ስለ ሲማ እንዲህ ስትል ሀሳቧን አካፍላናለች። «ሰላም አለይኩም fu ስለ ሲማ ለመግለፅ ለምን ጊዜ እነደፈጀብኝ አላውቅም አንብቤ ሳልጨርሰው ነው ስለ ሲማ ብዙ ማለት የጀመርኩት በእያንዳንዱ ምእራፍ ላይ perspectiveኤን እያስቀመጥኩ ነበር የጨረስኩት ንባብ ብቻ ሆኖ as a normal book እንዳንተላለፍ ማለት ነው በዛ ሁሉ ጥልቅ የንባብ አለም ውስጥ ብዙ ስሜትን ተጋርቻለሁ:: 'የአኺራንም ሀያትን ሚዳስስ እንደሆነ ተረድቼው ስለነበር ሁሉም ገፀ ባህሪያት መሞታቸው ከመገረም በዘለለ በፍርሀት ነበር ከአንዱ ወደ አነዱ የተሸጋገርኩት... :ሲማ በሁሉም የህይወት ክፍል ላይ በኔ ህይወት ውስጥ ሁሌም ስትነሳ ትኖራለች cus ምታወሳው ምንኖርበትን አለም ሁሉ ስለሚዳስስ በሁሉም conversation ውስጥ መካተቷ ግድ እንዲል ሆኖብኛል...ሲማ የሚመጣውን ብቻ አስጠንቃቂ ሳትሆን ከብዙ አመት በፊት የነበረ ስህተቴን በብዙ እንድቀርፍ ረድታኛለች አልሀምዱሊላህ🥀 °ከሁሉም fu አንተንም በስጦታ መልክ ትልቋን ሲማን ላበረከተችልኝ እህቴ ከታላቅ ክብር ጋ አመሰግናለሁ... #ቀለምህ አይንጠፍ አሻራህ ለዘላለም ከበላ ጠብቆ ሙራድህን ይሙላልህ ለዚህ ትልቅ መፅሀፍ እናመሰግናለን ባስተላለፍክልን ሁሉ አላህ ተጠቃሚ ያርገን:: #በመጨረሻም ሁሌም ቢሁስኒል ኺታም ስል ቋጭቸዋለሁ:ሰላም::» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views3,590+3%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4238Text
Views4,070+16%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4237Text
Views4,050+16%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#4236Text
Views3,750+7%vs avg
Forwards—
Reactions25
Comments—
#4235Text

ከሲማ ገፆች! ፉአድ ሙና . ‹‹የፊትና የኋላ ጉዳይ እንጂ ሁሉም የአዲስ አበባ ሙስሊም ጉዞ ወደ ኮልፌ ነው፡፡›› ይላሉ የከተማዋ ነዋሪዎች! ከኢድ ሰላትም በላይ የከተማው ህዝብ ፊርቃው … አንጃው … ግራንጃው … ሳይታወሰው የሚሰበሰብበት ቦታ ነው … ኮልፌ! በሃይማኖት ሲከፋፈር የነበረው … አንድ መስጂድ አልሰግድም ያለው ሳይቀር … ኮልፌ ገብቶ አንድ አፈር ይንተራሳል … አንድ ግድግዳ ይጋራል፡፡ ኮልፌ የሰው ልክ ማሳያ … ኮልፌ … የአንድነት ብፌ! ኮልፌ የሰው ልጅ ፊርቃውን ትቶ ሙስሊም ነኝ የሚልበት ስፍራ ነው፡፡ የኮልፌ መላዕክትም ሃይማኖትህ ምንድነው ነው እንጂ ፊርቃህ ምንድነው አይሉም፡፡ ኮልፌ ላይ ሀብትህ ብዙ አይፈይድም፡፡ የሚቆፈረው ጉድጓድ ለሟች እንጂ ለእገሌ ተብሎ አይቆፈርም፡፡ ጀናዛህ የደረሰበት ጉድጓድ ውስጥ ይጣላል፡፡ጀናዛው ተቀበረ ትባላለህ፡፡ ልክ የዝሁር ሰላት እንደደረሰ … የ*** ጀናዛ ወደ መስጂድ ተወሰደ፡፡ ኮልፌ ኢማም ሀሰን መስጂድ … የሬሳ መሸጋገሪያ ይመስላል፡፡ ይህን መስጂድ ሳይዘይር አፈር የሚንተራሰው ጀናዛ ጥቂት ነው፡፡ መስጂዱ ከዋና ስሙ ይልቅ በቅፅል ስሙ ይታወቃል፡፡ አዲሱ መስጂድ ይሉታል፡፡ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ተቀፅላ አሁንም ሁለት አስር ዓመታትን ተሻግሮ እንኳን አልተፋታውም፡፡ እዚህ መስጂድ ጀናዛ ሰላት የሌለበት ቀን የለም፡፡ የ*** ጀናዛ ወደ ሬሳ ማስቀመጫ ክፍል ገባ፡፡ የዝሁር ሰላት ለመስገድ የገባው … የወዳጁን ሬሳ ይዞ ሊቀብር የመጣው … ሁሉም በኢማም ሀሰን መስጂድ ውስጥ ይተራመሳል፡፡ የጀናዛ ማስቀመጫ ክፍሉ በር ተከፈተ፡፡ ኢማሙ ከሬሳዎቹ ፊት ቆሙ፡፡ ከ*** ውጪ ሌሎች አራት ጀናዛዎች ነበሩ፡፡ ሁሉም ሰገደ፡፡ ማራቸው ሲል ተማፀነ፡፡ የዝሁር ሰላት እንደተጠናቀቀ … ሁሉም ሬሳውን ተሸክሞ ወደ መቃብሩ ገባ፡፡ የ*** ቀብር ላይ ብዙ ሰው ተገኝቷል፡፡ አባቱ ጎበዝ ነጋዴ ስለሆኑ በርካታ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ ከፊሉ ቀብር ላይ ያሲን ይቀራል፡፡ ከፊሉ ላይ ስለ ቀብር አስከፊነት ይሰበካል፡፡ መቻቻል የታየበት ቀብር ነበር፡፡፡ ሀሀሀሀ ድንጋይ የተወራወረ የለም፡፡ ጥሎ ለመሄድ ሰው አይጣላም፡፡ ሰው የሚጣላው አንስቶ ለመሄድ ነው፡፡ እዚህ ጋ የሚገኝ ጥቅም የለም፡፡ ጠንካራ ሳንቲም ቢኖረው መወራወራቸው አይቀርም፡፡ መሀይምነት ለፅንፈኝነት ያጋልጣል፡፡ ፅንፈኝነት ደግሞ ጥሎ መነሳትን እንጂ አብሮ መቆምን መቀበል ያቅረዋል፡፡ ወደድሽም ጠላሽም ኮልፌ አንድ ላይ ትቆሚያታለሽ! ጊዜሽ ሲደርስ ደግሞ አንድ ላይ ትጋደሚያለሽ! ያኔ ልብ ካለሽ የኮልፌ መላዕክት ‹‹ሃይማትኖሽ ምንድነው?›› ብለው ሲጠይቁ ‹‹አንጃ ነኝ! … ግራንጃ ነኝ!›› ብለሽ መልሽ! እዚህ ከአብሮነት እንደፎረፍሽው … እዚያ ከጀነት ትፎርፊያለሽ! እነሱ የሚሰግዱበት መስጂድ አልሰግድም ያልሽ ሁላ … እነሱ የገቡበት ጀነት አልገባም ትዪ እንደሆነ እናያለን! ወላጅ፣ ዘመድ፣ የቅርብ ጓደኛ … ያነባል፡፡ ሌላው አፈር እየተሸከመ ያግዛል፡፡ ከፊሉ ትቶት የመጣውን ስራ በስልክ ይጨርሳል፡፡ የእኔም እጣ ይኸው ነው የሚለው በጣም ጥቂት ነው፡፡ አፈር ተማሰ … ያሲን ተቀራ … ዳዕዋ ተደረገ … ሁሉም አንድ በአንድ … የቅርቡን ሰው ጥሎ ሄደ፡፡ የሰው ልጅ ግን የመጨከን አቅሙ ደስ ይላል፡፡ አፈር ውስጥ ይጥልሀል … ወደ ቤት ሄዶ በስምህ የታረደውን ሰደቃ ይበላል፡፡ የእርሱ ተራ እስኪደርስ … እንዲህ ነው! የታደልናቸው ነብይም ﷺ ሰሂህ ቡኻሪ ላይ ባለ ሀዲስ ሞትን በተመለከተ «ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችውን ማስታወስን አብዙ፤ ሞትን!›› ይላሉ፡፡ ሰው ግን ቀብር ፊት ቆሞ እንኳን ሞት ትዝ አይለውም፡፡ ምግብ አላስበላ የሚለው የቀብር ህይወት ጅማሮ ከፊቱ እየተከወነ ይርበዋል፡፡ ‹‹ኧረ ፀሀዩ ጨረሰን … እንሂድ በቃ!›› የሚለው ብዙ ነው፡፡ አላህ እንኳን የነገሩን ከባድነት እያስጠነቀቀ... የገባው ጥቂት ነው፡፡ «አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡›› (ሙናፊቁን፣ 10-11) የኛ ድግስ ቅርብ መሆኑ የታየው የለም። የደረሰ ጊዜ ማምለጥ የለም፡፡ የቅርብ ወዳጁ ሞት … የእድሜ እኩዮቹ መቀጠፍ ያስተማረው ትንሽ ነው፡፡ ትንሽ ደግሞ የጀነት ቋንቋ ነው፡፡ የጀነት ኮድ ትንሽ ነው፡፡ ትንሾች ናቸው የሚገባቸው! … ትንሾች ናቸው የሚያመልጡት! ትንሽ … ትንሽ! ጥድፊያው ከትንሾቹ ለመሆን ነው፡፡ *** መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views3,810+9%vs avg
Forwards—
Reactions69
Comments—
#4234Text
Views3,450−1%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#4232Text
Views4,470+28%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#4231Text
Views3,250−7%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#4230Text
Views3,630+4%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4229Text

ሀፊዛ ስለ ሲማ እንዲህ ስትል ሀሳቧን አካፍላናለች «You Nailed it Fuy👏👏 Who could truly understand a young generation,if not someone from their own? ሲማ ልክ እንደ ጥርስ ቡርሽ ናት ከማንም ጋር የማልዋዋሳት ምክንያቱም እንደ ሌላ መፅሐፍ ተነቦ ሚታለፍ አደለም በየገፁ የነፍስ ስንቅ የሚሆኑትን ደጋግሜ ለማስታወስ ለኔፍሴ ኖትም(Note) የያዝኩበት ነፍሴ ስትደክም የፃፍኩትን ከፍቼ ማስታውስባት ናት:: ሲማ በወንጀል በር ላይ ለምንመላለስ ወጣቶች በ አላህ ላይ ተፋ ላለመቁረጥ በወንጀል ብዛት መፀፀት ለደከማት ነብስ የ አላህን መሀሪነት ማስታወሻ ናት:: وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ) ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ(በመመለሰ) ተጸጸቱ። (ኑር፣ 31)» 💧በጃእፈር እና በከድር በሁለቱ ነብሶች የማውቃቸው ያክል ነው ስቅስቅ ብየ ያለቀስኩ ደክሞኝ ያውቃል መሞት ፈልጌ አውቃለሁ አለመኖር እረፍት መስሎኝ ያውቃል እኔን የሆኑ እነሱን የሆንኩ መሰለኝ:: ከሆኑ ሰዎች ጋር አስተዋወቅከኝ የኔ አይነት ነፍስ ያላቸው ከዛ ቀስ በቀስ ከተገባበት ደስታ ከሚመስል ጥፋት ወደ ሞት ከሞት በኋላ ቅጣት.....የኔ ነፍስስ? አርጅተን የምንሞት ብዙ ጊዜ ያለን የሚመስለን ጥፋት ላይ ያለን ወጣቶች..... ብቻ ፉዬ መፅሐፍ ማንበብ ባይገራልኝም ደጋግሜ ላነበው የምችለው የነፍስ ሲዋክ የሆነ መፅሐፍ ነው:: Actually, I have many more thoughts, but I held back because I felt I had already said too much.☺️» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views3,730+7%vs avg
Forwards—
Reactions33
Comments—
#4228Photo
Views4,570+31%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#4226Text
Views4,490+28%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#4224Text
Views4,800+37%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4223Photo

አዩብ ከደሴ ስለ ሲማ እንዲህ ሲል ሀሳቡን አካፍሎናል። «ኡመር ስለ ፊርቃ ልዩነቶች ሲያወራ ውስጤ ያለውን የገለፀልኝ ያክል ነው ደስ ያለኝ እንደዚህ አይነት ልዩነቶች አይገባኝም ለሚሉ በዙሪያችን ላሉ ሰዎች በምን መልኩ ማስረዳት እንዳለብኝ አስተምሮኛል ። ሌላው ደግሞ ችላ ለተባሉ የሴቶች መስጂድ ትኩረት እንዲሰጣቸው የኢብሮን እህት ሀሳብ እጋራለሁ ቢያንስ ከወንዶች ያነሰ እንዳይሆን ማድረግ አለብን የሁላችንም ሀላፊነት ነው። ​Generally ሲማ በልብወለድ ሕይወት ባላቸው ገጸ-ባህሪያትና ታሪኮች አማካኝነት የሞትን ቅርብነትና የዱንያን አላፊነት በጥሩ ሁኔታ ያሳየ ድንቅ ሥራ ነው። ታሪኩን እያነበቡ የገጸ-ባህሪያቱን ውጣ ውረድ መከታተል ብቻ ሳይሆን፣ የራስን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ዝግጅት እንድንፈትሽ ያደርጋል። ሞት ድንገተኛና ቅርብ መሆኑን፣ ለዚያም መልካም ሥራዎችን በመሥራትና ወደ አላህ በመመለስ ዘወትር ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ያስገነዝባል። መንፈሳዊ ጥንካሬንና አስተንትኖን የሚጭር፣ እያንዳንዱ ሰው ሊያነበው የሚገባ አስተማሪ መጽሐፍ ነው! ፉየ እናመሰግናለን ከማለት ውጭ ምን እላለሁ ረበል ዓለሚን በቅኑ ጎዳና በቀጥተኛው መንገድ ያኑረን ፣ኻቲማችንንም ያማረ ያድርገው ። አዩብ ነኝ ከወሎ መዲና ደሴ» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views5,490+57%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4222Text

አዱ ሀለ ስለ ሲማ እንዲህ ስትል ሀሳቧን አካፍላናለች «Aselamu aleykum werehmetullahi weberekatuh fuad tsihufochihn kebefit jemre New yemiketatelew edmen le guadegnaye enam betam new yemwedilh Allah yichemrih yareb. Sile Sima bizu ken bizu lemalet felge Neber gn kalatoch liyagzugn alchalum zare gn eski limokir siman gena kemejemeriyaw begugut sitebkat yeneberech metsihaf nat egna Hager memtat yechalechiwm bene mikniyat new😊 ena eskemanebat betam chekuye sitmeta birr yelegnim Neber be dube wesje new yanebebkuat kemeguaguate yetenesa, gn Alhamdulillah tekeflual😁 Sima hulum sew endi aynet gisatse bemiyasfelgew seat yetetsafech liyyu akerareb yalat wudd metsihaf nat demo betam yegeremegn neger sile kiyama huneta be daewa ena beteleyayu minchoch abzagnaw sew yawkal gn ye Sima akerareb leyet Yale ena ke a'emro litefa yemaychil huno aginchewalehu ena ena degmo sile fırka yabrarahibet hasab yelele New yewededkut ene behiwete ende Sima ke a'emro yemaytefa ena hulem anbibugn anbibugn yemil metsihaf getimogn ayawkm ye ametu mirttt metsihaf byewalehu Alhamdulillah siman endaneb lefekedelign Geta🥰. Enam fufu Allah kheyr jezahin yikfelih yarebi endi aynet tsihufochin lemetsf hulem aydkemih Allah yatenkirih rejim edmen ke desta gar Allah yiwefikih bi'erih ayntef Allah kegonih yihun yarebbb🤲» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views4,930+41%vs avg
Forwards—
Reactions18
Comments—
#4221Photo
Views4,450+27%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—