Account
Fuad Muna (Fuya)

Fuad Muna (Fuya)

የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ! በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት! ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14 ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Username
@fuadmu
Category
Blogs
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers15,244
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR22.93%30-day average

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 29, 20263,750
Oct 30, 20264,050
Nov 1, 20264,070
Nov 5, 20263,590
Nov 14, 20262,020

Most viewed this month

  1. 01
    Views4.07K
    Forwards—
    Reactions23
    Comments—
  2. 02
    Views4.05K
    Forwards—
    Reactions20
    Comments—
  3. 03
    Views3.75K
    Forwards—
    Reactions25
    Comments—
  4. 04

    ስሜ አይገለፅ ያለች እህት ስለ ሲማ እንዲህ ስትል ሀሳቧን አካፍላናለች። «ሰላም አለይኩም fu ስለ ሲማ ለመግለፅ ለምን ጊዜ እነደፈጀብኝ አላውቅም አንብቤ ሳልጨርሰው ነው ስለ ሲማ ብዙ ማለት የጀመርኩት በእያንዳንዱ ምእራፍ ላይ perspectiveኤን እያስቀመጥኩ ነበር የጨረስኩት ንባብ ብቻ ሆኖ as a normal book እንዳንተላለፍ ማለት ነው በዛ ሁሉ ጥልቅ የንባብ አለም ውስጥ ብዙ ስሜትን ተጋርቻለሁ:: 'የአኺራንም ሀያትን ሚዳስስ እንደሆነ ተረድቼው ስለነበር ሁሉም ገፀ ባህሪያት መሞታቸው ከመገረም በዘለለ በፍርሀት ነበር ከአንዱ ወደ አነዱ የተሸጋገርኩት... :ሲማ በሁሉም የህይወት ክፍል ላይ በኔ ህይወት ውስጥ ሁሌም ስትነሳ ትኖራለች cus ምታወሳው ምንኖርበትን አለም ሁሉ ስለሚዳስስ በሁሉም conversation ውስጥ መካተቷ ግድ እንዲል ሆኖብኛል...ሲማ የሚመጣውን ብቻ አስጠንቃቂ ሳትሆን ከብዙ አመት በፊት የነበረ ስህተቴን በብዙ እንድቀርፍ ረድታኛለች አልሀምዱሊላህ🥀 °ከሁሉም fu አንተንም በስጦታ መልክ ትልቋን ሲማን ላበረከተችልኝ እህቴ ከታላቅ ክብር ጋ አመሰግናለሁ... #ቀለምህ አይንጠፍ አሻራህ ለዘላለም ከበላ ጠብቆ ሙራድህን ይሙላልህ ለዚህ ትልቅ መፅሀፍ እናመሰግናለን ባስተላለፍክልን ሁሉ አላህ ተጠቃሚ ያርገን:: #በመጨረሻም ሁሌም ቢሁስኒል ኺታም ስል ቋጭቸዋለሁ:ሰላም::» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

    Text
    Views3.59K
    Forwards—
    Reactions23
    Comments—

Latest posts

#4239Text

ስሜ አይገለፅ ያለች እህት ስለ ሲማ እንዲህ ስትል ሀሳቧን አካፍላናለች። «ሰላም አለይኩም fu ስለ ሲማ ለመግለፅ ለምን ጊዜ እነደፈጀብኝ አላውቅም አንብቤ ሳልጨርሰው ነው ስለ ሲማ ብዙ ማለት የጀመርኩት በእያንዳንዱ ምእራፍ ላይ perspectiveኤን እያስቀመጥኩ ነበር የጨረስኩት ንባብ ብቻ ሆኖ as a normal book እንዳንተላለፍ ማለት ነው በዛ ሁሉ ጥልቅ የንባብ አለም ውስጥ ብዙ ስሜትን ተጋርቻለሁ:: 'የአኺራንም ሀያትን ሚዳስስ እንደሆነ ተረድቼው ስለነበር ሁሉም ገፀ ባህሪያት መሞታቸው ከመገረም በዘለለ በፍርሀት ነበር ከአንዱ ወደ አነዱ የተሸጋገርኩት... :ሲማ በሁሉም የህይወት ክፍል ላይ በኔ ህይወት ውስጥ ሁሌም ስትነሳ ትኖራለች cus ምታወሳው ምንኖርበትን አለም ሁሉ ስለሚዳስስ በሁሉም conversation ውስጥ መካተቷ ግድ እንዲል ሆኖብኛል...ሲማ የሚመጣውን ብቻ አስጠንቃቂ ሳትሆን ከብዙ አመት በፊት የነበረ ስህተቴን በብዙ እንድቀርፍ ረድታኛለች አልሀምዱሊላህ🥀 °ከሁሉም fu አንተንም በስጦታ መልክ ትልቋን ሲማን ላበረከተችልኝ እህቴ ከታላቅ ክብር ጋ አመሰግናለሁ... #ቀለምህ አይንጠፍ አሻራህ ለዘላለም ከበላ ጠብቆ ሙራድህን ይሙላልህ ለዚህ ትልቅ መፅሀፍ እናመሰግናለን ባስተላለፍክልን ሁሉ አላህ ተጠቃሚ ያርገን:: #በመጨረሻም ሁሌም ቢሁስኒል ኺታም ስል ቋጭቸዋለሁ:ሰላም::» እናንተም ሀሳባችሁን @Fuadmuna ላይ አጋሩኝ። መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views3,590+3%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4238Text
Views4,070+16%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#4237Text
Views4,050+16%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#4236Text
Views3,750+7%vs avg
Forwards—
Reactions25
Comments—
#4235Text

ከሲማ ገፆች! ፉአድ ሙና . ‹‹የፊትና የኋላ ጉዳይ እንጂ ሁሉም የአዲስ አበባ ሙስሊም ጉዞ ወደ ኮልፌ ነው፡፡›› ይላሉ የከተማዋ ነዋሪዎች! ከኢድ ሰላትም በላይ የከተማው ህዝብ ፊርቃው … አንጃው … ግራንጃው … ሳይታወሰው የሚሰበሰብበት ቦታ ነው … ኮልፌ! በሃይማኖት ሲከፋፈር የነበረው … አንድ መስጂድ አልሰግድም ያለው ሳይቀር … ኮልፌ ገብቶ አንድ አፈር ይንተራሳል … አንድ ግድግዳ ይጋራል፡፡ ኮልፌ የሰው ልክ ማሳያ … ኮልፌ … የአንድነት ብፌ! ኮልፌ የሰው ልጅ ፊርቃውን ትቶ ሙስሊም ነኝ የሚልበት ስፍራ ነው፡፡ የኮልፌ መላዕክትም ሃይማኖትህ ምንድነው ነው እንጂ ፊርቃህ ምንድነው አይሉም፡፡ ኮልፌ ላይ ሀብትህ ብዙ አይፈይድም፡፡ የሚቆፈረው ጉድጓድ ለሟች እንጂ ለእገሌ ተብሎ አይቆፈርም፡፡ ጀናዛህ የደረሰበት ጉድጓድ ውስጥ ይጣላል፡፡ጀናዛው ተቀበረ ትባላለህ፡፡ ልክ የዝሁር ሰላት እንደደረሰ … የ*** ጀናዛ ወደ መስጂድ ተወሰደ፡፡ ኮልፌ ኢማም ሀሰን መስጂድ … የሬሳ መሸጋገሪያ ይመስላል፡፡ ይህን መስጂድ ሳይዘይር አፈር የሚንተራሰው ጀናዛ ጥቂት ነው፡፡ መስጂዱ ከዋና ስሙ ይልቅ በቅፅል ስሙ ይታወቃል፡፡ አዲሱ መስጂድ ይሉታል፡፡ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ተቀፅላ አሁንም ሁለት አስር ዓመታትን ተሻግሮ እንኳን አልተፋታውም፡፡ እዚህ መስጂድ ጀናዛ ሰላት የሌለበት ቀን የለም፡፡ የ*** ጀናዛ ወደ ሬሳ ማስቀመጫ ክፍል ገባ፡፡ የዝሁር ሰላት ለመስገድ የገባው … የወዳጁን ሬሳ ይዞ ሊቀብር የመጣው … ሁሉም በኢማም ሀሰን መስጂድ ውስጥ ይተራመሳል፡፡ የጀናዛ ማስቀመጫ ክፍሉ በር ተከፈተ፡፡ ኢማሙ ከሬሳዎቹ ፊት ቆሙ፡፡ ከ*** ውጪ ሌሎች አራት ጀናዛዎች ነበሩ፡፡ ሁሉም ሰገደ፡፡ ማራቸው ሲል ተማፀነ፡፡ የዝሁር ሰላት እንደተጠናቀቀ … ሁሉም ሬሳውን ተሸክሞ ወደ መቃብሩ ገባ፡፡ የ*** ቀብር ላይ ብዙ ሰው ተገኝቷል፡፡ አባቱ ጎበዝ ነጋዴ ስለሆኑ በርካታ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ ከፊሉ ቀብር ላይ ያሲን ይቀራል፡፡ ከፊሉ ላይ ስለ ቀብር አስከፊነት ይሰበካል፡፡ መቻቻል የታየበት ቀብር ነበር፡፡፡ ሀሀሀሀ ድንጋይ የተወራወረ የለም፡፡ ጥሎ ለመሄድ ሰው አይጣላም፡፡ ሰው የሚጣላው አንስቶ ለመሄድ ነው፡፡ እዚህ ጋ የሚገኝ ጥቅም የለም፡፡ ጠንካራ ሳንቲም ቢኖረው መወራወራቸው አይቀርም፡፡ መሀይምነት ለፅንፈኝነት ያጋልጣል፡፡ ፅንፈኝነት ደግሞ ጥሎ መነሳትን እንጂ አብሮ መቆምን መቀበል ያቅረዋል፡፡ ወደድሽም ጠላሽም ኮልፌ አንድ ላይ ትቆሚያታለሽ! ጊዜሽ ሲደርስ ደግሞ አንድ ላይ ትጋደሚያለሽ! ያኔ ልብ ካለሽ የኮልፌ መላዕክት ‹‹ሃይማትኖሽ ምንድነው?›› ብለው ሲጠይቁ ‹‹አንጃ ነኝ! … ግራንጃ ነኝ!›› ብለሽ መልሽ! እዚህ ከአብሮነት እንደፎረፍሽው … እዚያ ከጀነት ትፎርፊያለሽ! እነሱ የሚሰግዱበት መስጂድ አልሰግድም ያልሽ ሁላ … እነሱ የገቡበት ጀነት አልገባም ትዪ እንደሆነ እናያለን! ወላጅ፣ ዘመድ፣ የቅርብ ጓደኛ … ያነባል፡፡ ሌላው አፈር እየተሸከመ ያግዛል፡፡ ከፊሉ ትቶት የመጣውን ስራ በስልክ ይጨርሳል፡፡ የእኔም እጣ ይኸው ነው የሚለው በጣም ጥቂት ነው፡፡ አፈር ተማሰ … ያሲን ተቀራ … ዳዕዋ ተደረገ … ሁሉም አንድ በአንድ … የቅርቡን ሰው ጥሎ ሄደ፡፡ የሰው ልጅ ግን የመጨከን አቅሙ ደስ ይላል፡፡ አፈር ውስጥ ይጥልሀል … ወደ ቤት ሄዶ በስምህ የታረደውን ሰደቃ ይበላል፡፡ የእርሱ ተራ እስኪደርስ … እንዲህ ነው! የታደልናቸው ነብይም ﷺ ሰሂህ ቡኻሪ ላይ ባለ ሀዲስ ሞትን በተመለከተ «ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችውን ማስታወስን አብዙ፤ ሞትን!›› ይላሉ፡፡ ሰው ግን ቀብር ፊት ቆሞ እንኳን ሞት ትዝ አይለውም፡፡ ምግብ አላስበላ የሚለው የቀብር ህይወት ጅማሮ ከፊቱ እየተከወነ ይርበዋል፡፡ ‹‹ኧረ ፀሀዩ ጨረሰን … እንሂድ በቃ!›› የሚለው ብዙ ነው፡፡ አላህ እንኳን የነገሩን ከባድነት እያስጠነቀቀ... የገባው ጥቂት ነው፡፡ «አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡›› (ሙናፊቁን፣ 10-11) የኛ ድግስ ቅርብ መሆኑ የታየው የለም። የደረሰ ጊዜ ማምለጥ የለም፡፡ የቅርብ ወዳጁ ሞት … የእድሜ እኩዮቹ መቀጠፍ ያስተማረው ትንሽ ነው፡፡ ትንሽ ደግሞ የጀነት ቋንቋ ነው፡፡ የጀነት ኮድ ትንሽ ነው፡፡ ትንሾች ናቸው የሚገባቸው! … ትንሾች ናቸው የሚያመልጡት! ትንሽ … ትንሽ! ጥድፊያው ከትንሾቹ ለመሆን ነው፡፡ *** መፅሀፉን ያልገዛችሁ @sima_book ላይ መሸመት ትችላላችሁ። . @Fuadmu

Open in Telegram
Views3,810+9%vs avg
Forwards—
Reactions69
Comments—
#4234Text
Views3,450−1%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#4232Text
Views4,470+28%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#4231Text
Views3,250−7%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#4230Text
Views3,630+4%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—

All posts

Connections