Account

Posts of ፈለገ ጥበባት

newest first

#1983Text

40 አመታት በጫካ ብቻቸውን ኤርትራዊው መናኝ እኔ ናቡቴ ቀኑን ሙሉ በሰሜን ተራሮች ገደላማ አፋፍ ላይ ስንከራተት ውዬ መንገድ ጠፋብኝ። በዛ ላይ አጥንት ሰባሪ የበረዶ ቁር፣ ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ እና ከባድ ጨለማ ተተካብኝ። ተስፋ ቆርጬ በጨለማው ጫካ ውስጥ ስንከራተት ነበር ድንገት ከሩቅ ያቺን አሮጌ የሳር ጎጆ ያየኋት…እጂግ አስፈሪ ለሊት እና ለልብ የሚከብድ የናቡቴ አደራ። ወደ ቤቱ ስጠጋ ግን ፍርሃት መላ አካላቴን ወረረው። በሩን ከፍቼ ስገባ ያገኘሁት ነገር ግን ከጠበቅሁት በላይ ነበር፦👉 ከ40 ዓመታት በላይ ብቻቸውን የኖሩ የድሮ የኤርትራውያን የአማጽያን መሪ የነበሩ ረጅም ነጭ ጺም ያላቸው ኤርትራዊ አዛውንት በጫካ ውስጥ ብቻቸውን !👉 ከዓዱሊስ እስከ ናቅፋ፣ ከኮሀይቶ እስከ አክሱም የተዘረጋው የጥንት ብራና ሚስጥር እና የካርታ መዳረሻ!👉 እና በእጄ ላይ ካለው አደራ ጋር ፍጹም አንድ የሆነ ምስጢራዊ ቁልፍ… “አንተ የምትፈልገው ነገር ከኢትዮጵያ ተራሮች ብቻ አልጀመረም…” ብለው ታሪካቸውን ነግረውኝ ሳያበቁ… ምን ገጠመኝ? ከ40 ዓመት በኋላ የተከፈተው የሰሐል ምስጢር፣ የተመዘዘው ሰይፍ እና ወደ ጨለማው ዋሻ የተደረገው ሽሽት…የእኔ የ ናቡቴ እውነተኛ የአባቶቸ አደራ እና ፍለጋ ገጠመኞቸ ዛሬ ማታ የሚለቀቀውን ትንፋሽ የሚቆራርጥ ሙሉ ታሪክ ከ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ! 👇👇 ይለቀቃል https://youtube.com/channel/UCTNR1xTehgZFOMc5dtc-7SA እኔን በውስጥ መስመሬ ለማግኘት ይህ ነው @Nabuti21

Open in Telegram
Views1,070+17%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1982Text
Views939+2%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#1980Text
Views1,030+12%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#1978Text

“ መሃሉ ዳር ይሆናል…” ሰሞኑን በሰሜን ጫፍ ነበርኩ ፤ ድንገት “ና” ተብየ ነበር የተጓዝኩት። በአሲንባ ተራሮች፣ በጉንዳጉንዴ ዋሻዎች፣ በገርአታ ቋጥዮች መካከል የተባልኩትን ጉዳይ እየፈጸምኩ ሳለ፣ ካለሁበት ዋሻ  የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑ  ደበሎ ለባሽ ባህታዊ በአርምሞ የሚኖሩ ፤ መናኝ አዛውንት በለሊት ወደ እኔ መጡና በለሆሳስ ጠሩኝ ልጀ ናቡቴ — «በል ልጄ፣ ተነስ! ቶሎ ሂድ፤ ቀኑ ሳይመሽብህ፣ ጨለማው ሳይበረታ፣ ኩብኩባው ሳይፈለፈል፣ አንጣው ከማደርያው ሳይወጣ ከተማዋን ሳያስጨንቃት በል ተነስ ሂድ ብለው ባረኩኝ  ..፤ ቃላቸው ሚስጥር  የጦርነትንና የውጥረት ጥላ  ማጥላቱን ሲነግሩኝ ነው። እንዲሁ ይሆናል በዛ በዘመኑ ፤  መሃሉ ዳር ይሆናል። ከሰሜን የተነሳ ከባድ ነፋስ ይመጣል፤ በመብራት ያሸበረቁ ፤ በጥጋብ የኖረችው የመ በለቲቱ ከተማ ወዮላት፤   ሳቱ ከሩቅ ነው እኔ ጋ አይደርስም ያለቸው ሃሳዊቷ ከንአን ሳይ ይነድባታል፤  የከተማይቱን ቤቶች ይናውጣሉ፣  ጋጋታና ሁካታ የበዛባት ከተማ ትናጣለሽ ፤ የመንገዶቿም አቧራ ወደ ሰማይ ያነሳል። ሰዎቿም ግራ ተጋብተው፦ “ይህ ምንድን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። ከሩቅ የሰማነው በዚህ ፍጥነት ከእኛ ደረሰን? ይላሉ ከሰሜን የሚመጣው ነፋስ ግን ተራ ነፋስ ብቻ አይሆንም፤ የተደበቀውን ይገልጣል፣ የተከማቸውን ያናውጣል፣ በሰዎች ልብ ውስጥ የተሸሸገውንም ያወጣል። ኢሳይያስ እንደሚል፦ “እነሆ፣ እግዚአብሔር በፍጥነት የሚመጣ ደመና ላይ ይመጣል…” እና ከሩቅ የሚመጣው ነገር የዘመኑ ምልክት ይሆናል። ከዚያም የነፋሱ ድምፅ ይሰማል፤ በከተማይቱ እንደ ጂራፍ የሚጮህ ነፋስ እንደ አንበሳ የሚያጓራ ኩብኩባ ይከባታል። ከፍ ያለው ይናወጣል፣ የተመካው ይፈተናል፣ ሰውም ከራሱ ጋር ለብቻው ይቆማል። መሃሉም ዳር ይሆናል፤ ነፋሱም በከተማይቱ  ያለ ልማዱ  ይነሳል። ነገር ግን የሚያስፈራው ራሱ ነፋሱ አይደለም— ነፋሱ ኃይሉን ጨርሶ ካለፈ በኋላ፣ በምድሪቱ ላይ የሚቀረው ጥሬ እውነት ነው። ሃሳብ አስተያየትወ @Nabuti21 ላይ ይደርሰኛል

Open in Telegram
Views2,780+203%vs avg
Forwards—
Reactions24
Comments—
#1976Text
Views1,960+114%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#1969Text
Views2,580+181%vs avg
Forwards—
Reactions27
Comments—
#1967Text

🕯️ ጠብቁኝ… አንድ ታሪክ እነግራችኋለሁ ከሀገሬ ለመውጣት እያሰብኩ ነበር። ከዚህ ሁሉ ነገር ርቄ፣ ያለፈውን ሁሉ ትቼ፣ በሌላ ሀገር አዲስ ሕይወት ለመጀመር እስከመጨረሻው ወስኜ ነበር። ግን ሰው እቅዱን ያወጣል… ሕይወት ደግሞ ሌላ ታሪክ ትጽፋለች። በዚያ መካከል፣ ከቀድሞ የትምህርት ጊዜዬ ጋር የተያያዙ መልእክቶች መድረስ ጀመሩ። እድሎች… የትምህርት እድሎች… ሙሉ የሚደገፉ እድሎች። እኔ ግን አንድ ጥያቄ ብቻ ነበረኝ፦ “እኔ የምሸሸው ከሀገሬ ነው? ወይስ ከራሴ?” እናም ታሪኩ ወደ ሌላ አቅጣጫ ተለወጠ። ከጣና ሐይቅ ዳርቻ እስከ ጎንደር ምሽት… ከጥንታዊ ገዳማት እስከ አንድ ምስጢራዊ ብራና… ከማይታወቀው ሰው እስከ “እውነቱን እንጂ ሀብቱን አትፈልግ” የሚለው መልእክት… ይህ ተራ ታሪክ አይደለም። ምን ተደብቆ ነበር? ማን እውነቱን ለመደበቅ ፈለገ? የብራናው ምስጢር ከጣና ጋር ምን ያገናኘዋል? እና ከሀገር ለመውጣት የወሰነው ሰው ለምን ወደዚህ ጉዞ ተመለሰ? ጠብቁኝ… የተሸሸገውን ታሪክ አንድ በአንድ እንፈታዋለን።

Open in Telegram
Views2,390+161%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—