Посты канала ፈለገ ጥበባት
40 አመታት በጫካ ብቻቸውን ኤርትራዊው መናኝ እኔ ናቡቴ ቀኑን ሙሉ በሰሜን ተራሮች ገደላማ አፋፍ ላይ ስንከራተት ውዬ መንገድ ጠፋብኝ። በዛ ላይ አጥንት ሰባሪ የበረዶ ቁር፣ ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ እና ከባድ ጨለማ ተተካብኝ። ተስፋ ቆርጬ በጨለማው ጫካ ውስጥ ስንከራተት ነበር ድንገት ከሩቅ ያቺን አሮጌ የሳር ጎጆ ያየኋት…እጂግ አስፈሪ ለሊት እና ለልብ የሚከብድ የናቡቴ አደራ። ወደ ቤቱ ስጠጋ ግን ፍርሃት መላ አካላቴን ወረረው። በሩን ከፍቼ ስገባ ያገኘሁት ነገር ግን ከጠበቅሁት በላይ ነበር፦👉 ከ40 ዓመታት በላይ ብቻቸውን የኖሩ የድሮ የኤርትራውያን የአማጽያን መሪ የነበሩ ረጅም ነጭ ጺም ያላቸው ኤርትራዊ አዛውንት በጫካ ውስጥ ብቻቸውን !👉 ከዓዱሊስ እስከ ናቅፋ፣ ከኮሀይቶ እስከ አክሱም የተዘረጋው የጥንት ብራና ሚስጥር እና የካርታ መዳረሻ!👉 እና በእጄ ላይ ካለው አደራ ጋር ፍጹም አንድ የሆነ ምስጢራዊ ቁልፍ… “አንተ የምትፈልገው ነገር ከኢትዮጵያ ተራሮች ብቻ አልጀመረም…” ብለው ታሪካቸውን ነግረውኝ ሳያበቁ… ምን ገጠመኝ? ከ40 ዓመት በኋላ የተከፈተው የሰሐል ምስጢር፣ የተመዘዘው ሰይፍ እና ወደ ጨለማው ዋሻ የተደረገው ሽሽት…የእኔ የ ናቡቴ እውነተኛ የአባቶቸ አደራ እና ፍለጋ ገጠመኞቸ ዛሬ ማታ የሚለቀቀውን ትንፋሽ የሚቆራርጥ ሙሉ ታሪክ ከ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ! 👇👇 ይለቀቃል https://youtube.com/channel/UCTNR1xTehgZFOMc5dtc-7SA እኔን በውስጥ መስመሬ ለማግኘት ይህ ነው @Nabuti21
Открыть в Telegramተጓዢን ይቀላቀሉ ...ከዚህ ቀደም በተለያዩ ኢትዮጵያ ቦታወች እየተጓዝኩ የእኔ የናቡቴ እውነተኛ ፍለጋ የማደርስበት ይህንን አዲሱን ተጓዢ የዪቲብ ቻናል አስተዋውቁት ለወዳጂ ጓደኞቻችሁ ሸር አርጉት በዚህ እገዛችሁን እሻለሁ። ይህንን የምታነቡ ተከታታየቸ በፈለገ ጥባት ሲቀርቡ የነበሩ እውነታኛ ገጠመኞቸ እና እጂግ አጓጊ እና ታምራዊ ታሪኮች ሁሉ በዚሁ በተጓዢ ይቀርብላችኋል። አጋሩት ሊንኩን ላኩላቸው እንሰባሰብ https://youtube.com/channel/UCTNR1xTehgZFOMc5dtc-7SA
Открыть в Telegramሰላም በመላው አለም የምትገኙ ተከታታዮቸ እንዴት ናችሁ። ለወራት በተለያዩ ቦታወች እየተጓዝኩ ነበር በዚህም ምክኒያት ጠፍቸ ነበር። አሁን ላይ ወደ ቀደም ስራችን እንመለሳለን ቪዲኦውችን እና እጂግ አስደናቂ የጉዞ ታሪኮቸን አቀርብላችሁ አለሁ። @Nabuti21 ላይ እገኛለሁ
Открыть в Telegram“ መሃሉ ዳር ይሆናል…” ሰሞኑን በሰሜን ጫፍ ነበርኩ ፤ ድንገት “ና” ተብየ ነበር የተጓዝኩት። በአሲንባ ተራሮች፣ በጉንዳጉንዴ ዋሻዎች፣ በገርአታ ቋጥዮች መካከል የተባልኩትን ጉዳይ እየፈጸምኩ ሳለ፣ ካለሁበት ዋሻ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑ ደበሎ ለባሽ ባህታዊ በአርምሞ የሚኖሩ ፤ መናኝ አዛውንት በለሊት ወደ እኔ መጡና በለሆሳስ ጠሩኝ ልጀ ናቡቴ — «በል ልጄ፣ ተነስ! ቶሎ ሂድ፤ ቀኑ ሳይመሽብህ፣ ጨለማው ሳይበረታ፣ ኩብኩባው ሳይፈለፈል፣ አንጣው ከማደርያው ሳይወጣ ከተማዋን ሳያስጨንቃት በል ተነስ ሂድ ብለው ባረኩኝ ..፤ ቃላቸው ሚስጥር የጦርነትንና የውጥረት ጥላ ማጥላቱን ሲነግሩኝ ነው። እንዲሁ ይሆናል በዛ በዘመኑ ፤ መሃሉ ዳር ይሆናል። ከሰሜን የተነሳ ከባድ ነፋስ ይመጣል፤ በመብራት ያሸበረቁ ፤ በጥጋብ የኖረችው የመ በለቲቱ ከተማ ወዮላት፤ ሳቱ ከሩቅ ነው እኔ ጋ አይደርስም ያለቸው ሃሳዊቷ ከንአን ሳይ ይነድባታል፤ የከተማይቱን ቤቶች ይናውጣሉ፣ ጋጋታና ሁካታ የበዛባት ከተማ ትናጣለሽ ፤ የመንገዶቿም አቧራ ወደ ሰማይ ያነሳል። ሰዎቿም ግራ ተጋብተው፦ “ይህ ምንድን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። ከሩቅ የሰማነው በዚህ ፍጥነት ከእኛ ደረሰን? ይላሉ ከሰሜን የሚመጣው ነፋስ ግን ተራ ነፋስ ብቻ አይሆንም፤ የተደበቀውን ይገልጣል፣ የተከማቸውን ያናውጣል፣ በሰዎች ልብ ውስጥ የተሸሸገውንም ያወጣል። ኢሳይያስ እንደሚል፦ “እነሆ፣ እግዚአብሔር በፍጥነት የሚመጣ ደመና ላይ ይመጣል…” እና ከሩቅ የሚመጣው ነገር የዘመኑ ምልክት ይሆናል። ከዚያም የነፋሱ ድምፅ ይሰማል፤ በከተማይቱ እንደ ጂራፍ የሚጮህ ነፋስ እንደ አንበሳ የሚያጓራ ኩብኩባ ይከባታል። ከፍ ያለው ይናወጣል፣ የተመካው ይፈተናል፣ ሰውም ከራሱ ጋር ለብቻው ይቆማል። መሃሉም ዳር ይሆናል፤ ነፋሱም በከተማይቱ ያለ ልማዱ ይነሳል። ነገር ግን የሚያስፈራው ራሱ ነፋሱ አይደለም— ነፋሱ ኃይሉን ጨርሶ ካለፈ በኋላ፣ በምድሪቱ ላይ የሚቀረው ጥሬ እውነት ነው። ሃሳብ አስተያየትወ @Nabuti21 ላይ ይደርሰኛል
Открыть в Telegram🌍🎒 አዲሱ የጉዞ እና የፍለጋ ጉዞችን የምንጀምርበት ጊዜ ነው! ቀጣይ የተቋረጡ ፕሮግራሞች በዚህ በኩል ይቀርባሉ ተጓዢ —የተሰኘውን አዲሱን የYouTube ቻናላችንን ጀምረናል! 🔎🏔️ በመንገዳችንም የተደበቁ ቦታዎችን፣ የተረሱ ታሪኮችን፣ ጥንታዊ ቅርሶችን፣ ትውፊቶችን እና አሁንም መልስ ያላገኙ ምስጢሮችን እንፈልጋለን። 📍 ታሪኩ ወደተፈጠረበት ቦታ እንሄዳለን። 👥 ሰዎችን እናዳምጣለን። 📜 ማስረጃዎችን እንፈልጋለን። 🎥 ያገኘነውን በልዩ የቪዲዮ ታሪክ እናቀርባለን። ይህ የጉዞ ቻናል ብቻ አይደለም። የፍለጋ ጉዞ ነው! 🔎🌍 🇪🇹 ተጓዢ — ወደ ቦታው እንጓዝ፣ ታሪኩን እንፈልግ፣ እውነቱን እንግለጥ! 🔔 አሁኑኑ Subscribe ያድርጉን እና ከተጓዢ ጋር ይጓዙ! 👉 YouTube Channel: https://youtube.com/channel/UCTNR1xTehgZFOMc5dtc-7SA 🎒 ተጓዢ — ጉዞው አሁን ይጀምራል!
Открыть в Telegram🔥 ጠብቁኝ… ይህ ተራ ታሪክ አይደለም! አንድ የቆየ ሰነድ… አንድ የተረሳ አደራ… እና እስካሁን ያልተመለሰ ጥያቄ። ናቡቴ ከቤቱ ወጥቶ ኢትዮጵያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ይጓዛል። በጥንታዊ ገዳማት፣ በተራራ ጫፎች፣ በጥልቅ ሸለቆዎች እና በተረሱ መዛግብት ውስጥ… ናቡቴ አንድ ምስጢር እየፈለገ ሌላ ምስጢር ያገኛል። ግን የሚያገኘው ነገር… በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የተጠቀሰችው ኢትዮጵያ… ስሟ ብቻ ሳይሆን ታሪኳም እስከ ዛሬ የሚያስገርም ጥያቄ አለው። በምድሯ ስር ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ በተራሮቿ የተደበቁ ታሪኮች፣ በብራናዎቿ የተጠበቁ ትውስታዎች… እና ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ምስጢራዊ አደራዎች። እነዚህ ሁሉ አንድ ቦታ ላይ ይገናኛሉን? ኢትዮጵያን እንደሚያውቅ ያስብ የነበረውን አእምሮ ሊቀይረው ይችላል። 👁️ ሰነዱ ምን ይደብቃል? 🗝️ አደራው ለምን ተሰጠ? 🏔️ እውነቱ የት ተቀብሯል? በYouTube ላይ… 🔥 ጠብቁኝ። ጉዞው ገና አልጀመረም—እኛ ግን በሩን አንኳኩተነዋል። 🇪🇹🔎
Открыть в Telegram🕯️ ጠብቁኝ… አንድ ታሪክ እነግራችኋለሁ ከሀገሬ ለመውጣት እያሰብኩ ነበር። ከዚህ ሁሉ ነገር ርቄ፣ ያለፈውን ሁሉ ትቼ፣ በሌላ ሀገር አዲስ ሕይወት ለመጀመር እስከመጨረሻው ወስኜ ነበር። ግን ሰው እቅዱን ያወጣል… ሕይወት ደግሞ ሌላ ታሪክ ትጽፋለች። በዚያ መካከል፣ ከቀድሞ የትምህርት ጊዜዬ ጋር የተያያዙ መልእክቶች መድረስ ጀመሩ። እድሎች… የትምህርት እድሎች… ሙሉ የሚደገፉ እድሎች። እኔ ግን አንድ ጥያቄ ብቻ ነበረኝ፦ “እኔ የምሸሸው ከሀገሬ ነው? ወይስ ከራሴ?” እናም ታሪኩ ወደ ሌላ አቅጣጫ ተለወጠ። ከጣና ሐይቅ ዳርቻ እስከ ጎንደር ምሽት… ከጥንታዊ ገዳማት እስከ አንድ ምስጢራዊ ብራና… ከማይታወቀው ሰው እስከ “እውነቱን እንጂ ሀብቱን አትፈልግ” የሚለው መልእክት… ይህ ተራ ታሪክ አይደለም። ምን ተደብቆ ነበር? ማን እውነቱን ለመደበቅ ፈለገ? የብራናው ምስጢር ከጣና ጋር ምን ያገናኘዋል? እና ከሀገር ለመውጣት የወሰነው ሰው ለምን ወደዚህ ጉዞ ተመለሰ? ጠብቁኝ… የተሸሸገውን ታሪክ አንድ በአንድ እንፈታዋለን።
Открыть в Telegram