ቢገባን ትልቁ የሕይወት ጥያቄ መሆን የነበረበት ‘ ጌታ እንዲህ ሊወደኝ የተገባኝ ቆይ እኔ ማነኝ ? በዚህ ጠዋት አይኖቼን እንድከፍት ከነሙሉ ጤናዬ ከ አልጋዬ እንድነሳ ድጋሚ እንድኖር ዕድል የተሰጠኝ እኔ ማነኝ ? ’ ይሄ ቀን የተሰጠን ተገብቶን ሳይሆን ክርስቶስ ... " እንደው ከተመለሱ ዛሬ እንኳን ከጥፋት መንገዳቸው ተመልሰው ንስሃ ከገቡ ምናልባት እኔን መበደላቸው ከታወሳቸውና እና መንግስተ ሰማያትን ናፍቀው መንፈሳዊ ተግባራትን ማድረግ ከጀመሩ ያንን ዘውትር የሚያደርጉትን ኃጢአት ዛሬ እንኳን ከተዉት ደግሞም ከልባቸው እኔን ወደው ፣ ፍቅሬን አስበው ካለቀሱ ፣ ለነሱ ብዬ የከፈልኩትን የደም ዋጋ አስበው በመስቀል የሰጠኋቸውን ስጋ እና ደሜን ቢቀበሉ ። " ብሎ እንጂ እንደው እውነት የትላንት አዋዋላችን ዛሬን እንድናይ በቂ ነበር ?
Open in Telegramየአባቶች ምክር
አስተማሪ የሆኑ የአባቶች ምክሮችን ÷መንፈሳዊ ፁሑፎችን እና ትምህርቶችን የምንጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 22, 2026 | 4,327 |
| Nov 23, 2026 | 4,033 |
| Nov 24, 2026 | 3,390 |
| Nov 25, 2026 | 3,585 |
| Nov 26, 2026 | 2,895 |
| Nov 27, 2026 | 2,550 |
| Nov 28, 2026 | 1,858 |
| Nov 29, 2026 | 733 |
Most viewed this month
- 01Views5KForwards—Reactions99Comments—
- 02Views4.46KForwards—Reactions92Comments—
- 03Views4.33KForwards—Reactions66Comments—
- 04Views3.98KForwards—Reactions54Comments—
Latest posts
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 13 ቁጥር 8 ላይ " ከማንም ሰው የፍቅር እዳ አይኑርባችሁ " ብሎአል ይህንን ቃል እንዴት ተረዳችሁት ሃሳባችሁን በኮሜንት መስጫው ያስቀምጡልን!
Open in Telegram"ቤቴ በሰማይ ነው፤ ይህች ግን የሐዘን ምድር ናት" — አባ ሚና አቡድ (Fr. Mina Aboud) This world was never meant to be our final home. We journey through it with our eyes fixed on eternity, remembering that our true home is with Christ. 🤍 "ይህ ዓለም የመጨረሻ ቤታችን እንዲሆን ታስቦ አልተፈጠረም። እውነተኛ ቤታችን ከክርስቶስ ጋር መሆኑን በማስታወስ፣ ዓይናችንን በዘላለም ላይ አድርገን በዚህ ዓለም እናልፋለን። 🤍"
Open in Telegram"የወደድኩህ በጣም ዘግይቼ ነው። ቀዳማዊ ብትሆንም ምን ጊዜም አዲስ ነህ። የወደድኩህ በጣም ዘግይቼ ነው አንተ በእኔ ውስጥ እያለህ እኔ በውጪ እፈልግህ ነበር። አንተ በፈጠርከውና ባሳመርከው ውስጥ ሁሉ ያለማስተዋል እባዝን ነበር። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን አንተ ከእኔ ጋር ነበርክ እኔ ግን ከአንተ ጋር አልነበርኩም።" ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ
Open in Telegramሰው ብዙ ሲያደርገን ፣ በወደድነው ልክ ፍቅር ሳይሰጠን ፣ ትኩረት ሳይሰጠን ሲቀር ፣ በቂ እንዳልሆንን ፣ እኛ በምንፈልጋቸው ልክ ሳይፈልጉን ሲቀር ፣ ብቻ ብዙ ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማን ባደረጉ ቁጥር ... ከመከፋታችን በፊት ሁለት ነገር እናስብ ! 1 - እግዚአብሔርን በትክክልን በሆነልኝ ልክ አለመሆኔ በወደደኝ ልክ አለመውደዴ እንዲህ እየጎዳሁት ነው ። 2 - ይሄን መጥፎ ስሜት በተቃራኒው በኩል ሆኜ ሌሎች ሰዎች ይሄንኑ አይነት ነገር ውስጥ እንዲያልፉ እያደረኩ ይሆን ? ብሎ እራስን መጠየቅ ።
Open in Telegramእግዚአብሔር ስጠኝ ሚሉት ብዙ ልጆች አሉት የናፈቀው ልስጥህ ሚለው ነው። እግዚአብሔር ብዙ ተገኝልኝ የሚሉት አሉ የናፈቀው ልገኝልህ የሚሉት ናቸው።
Open in Telegramይቅርታ ግበሩለይ ተተቐየምኩም ለ ይቕርታ ክጠይቀቕክም የ ካብ ተወለኩለ ከባብ ብላዕሊ ኦርቶዶክሳዊ ይየ ማንነተይ ልበልጸኒ በኦርቶዶክሳዊነተ መንነተይ ክገልጽ ልደሊ Naaf dhiifama godhaa yoo isinitti dhaga'ame, naannoon itti dhaladhe caalaa Ortodoksii ta'uu kootu natti caala. Eenyummaa Ortodoksii kootiin ibsamuun barbaada. ይቅርታ አድርጉልኝ ከተቀየማችሁ ከተወለድኩበት አካባቢ ኦርቶዶክሳዊ ማንተቴ ይበልጥብኛል በኦርቶዶክሳዊ ማንነቴ ነው መገለፅ የምፈልገው Please forgive me if you felt offended. More than the place I was born, my Orthodox identity means more to me. I want to be defined by my Orthodox identity.
Open in Telegram