ከተመቻችሁ፡ https://www.lrb.co.uk/the-paper/v48/n21/christopher-clark/shouldered-umbrellas?utm_campaign=5191640_20261118NewIssue&utm_medium=email&utm_source=LRB%20email&dm_i=7NIQ,339W8,2E2990,88G1X,1,0,0,0
Open in TelegramPosts of ጦብያን በታሪክ
የአጼ ቴዎድሮስን ልጅ አለማየሁን ከመቅደላ ወደ እንግሊዝ ሲወስዱት በአእምሯችሁ ሳሉት። ቀይ ባሕርን አልፈው ካይሮ ገብተው ከዛ ደግሞ ተነስተው ሜዲተሬንያንን እያቋረጡ ናቸው። በፊት ከምጽዋ ሱዌዝ ካናል እስኪደርሱ አለቃ/ደብተራ/ ዘነብ እና ሌሎች ከሕጻኑ ጋር አብረው የነበሩ ተንከባካቢዎቹ ነበሩ። ሱዌዝ ላይ ግን እንዲወርዱ እና ወደ ምጽዋ እንዲመለሱ ተደርገዋል። ምክንያቱ አልታወቀም። አለቃ ዘነብ የጻፏቸው ደብዳቤዎችም መውረዳቸውን እና አለማየሁ መቀየሙን ፈረንጆቹ እንደነገሯቸው ነው እንጂ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይገልጹም። አንድ ካሳ የተባለ ጠባቂ ብቻ ነበር የቀረው ከአለማየሁ ጋር። ከዛ ውጪ ብዙ ሕጻናት ነበሩ እንዲሁ ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ መንገድ ላይ የነበሩ፡ እንደ child trafficking ነገር። ታድያ Urgent የተባለች መርከብ ላይ ሆነው ሮበርት ናፕየር ይሄን የ6/7 ዓመት ሕጻን ለማጫወት ኳስ ነገር ጠቅልሎ ይሠራና ይወረውርለታል። ሕጻኑ ግን ምንም አይደንቀውም፣ ንቅንቅ አይልም። ናፕየር እራሱ እየተነሳ ያመጣል ኳሱን። በኋላ ምነው ሲሉት እንዲህ ብሎ ይመልሳል፡ «የንጉሥ ልጅ አይደለሁ እንዴ? ለምንድነው የምነሳውስ? ሂጄ የማመጣውስ?»። ቁጭት ቢጤ ከ፡ The Prince and The Plunder: How Britain took one small boy and hundres of treasures from Ethiopia, Andrew Heavens, ገጽ 102
Open in Telegramሂሩት አባቷ ማንነው ሙሉ በሙሉ ትዊተር ላይ ተለቋል። ልጅ ቢንያምን እናመሰግናለን። https://x.com/JegnaAnbessa/status/2122348007299715480/video/1?s=35
Open in Telegramሰላም everybody ባለፉት አስራ ምናምን ዓመታት ስለሚታዩት የFar Right ቡድኖች እና የዓለም የፖለቲካ ሁኔታ መረዳት ለምትፈልጉ ይሄን መጽሐፍ ልላክላችሁ ብዬ ነው። የሚገርም ሥራ ነው። ከአሜሪካ (እነ ኮንዶሊዛ ራይስ፣ የሁቨር ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ምናምን)፣ ብራዚል እና አርጄንቲና (እነ ሚሌ፣ እነ ቦልሶራኖ) እናም ጀርመን እና ፈረንሳይ ባለሀብት የገንዘብ እና ሀብት ጉዳይ ዋና ጥያቄያቸው እንደሆነ እና እሱን ከIQ ፖለቲካ ጋር አገናኝተው (ማለትም አንዳንድ ሕዝብ የበለጠ እና የተሻለ አእምሮ/የማገናዘብ አቅም አለው ስለዚህ ወይ እናጥፋው ወይ ከኛ ያነሰ መብት ይሰጠው)፣ የመንግሥትን ኃይል ለመቀነስ የሚሠሩ እንደሆኑ (ለምሳሌ ወርቅ በመሸመት ከዛም በመሸጥ እና የዶላር እና ዩሮን አቅም በመተቸት) ያሳየናል። ስደተኛ ውጣ ምናምን ትርፍ ጥያቄዎች መሆናቸውንም እንዲሁ። አሪፍነቱ በጣም ብዙ ጽሑፎችን ማጣቀሱ ላይ ነው፡፡ ከፈለጋችሁ እና ከተመቻችሁ፡
Open in Telegramኃይሌ ገሪማ ዳይሬክት ያደረጉት 8 ሰዓት ያህል ርዝመት ያለው ዶክዩመንተሪያቸው አሁን አውሮፓ እየታየ ነው። ሙሉ በሙሉ የት እንደሚገኝ እንጃ ግን ማስታወቂያውን ሹፉ፡ Black Lions - Roman Wolves / ጥቁር አንበሳ - የሮማ ተኩላ ይባላል። (ዛሬ ሮም ዩኒቨርሲቲ ሳፒየንዛ እየታየ ነው፤ እሳቸውም አሉ። እዛ ገደማ ያላችሁ ወዳጆች ካላችሁ ብቅ ማለት ትችላላችሁ። ቀን 4 ሰዓት ነው የጀመረው ገና እሰከ ማታ 1 ሰዓት ይቀጥላል) https://www.youtube.com/watch?v=sb9Nuqw6C4U&t=3s
Open in TelegramThe Rest is History podcast ስለ አፄ ቴዎድሮስ ሦስት ተከታታይ ፕሮግራሞችን ሠርተዋል። ቆንጅዬ ነው። ቴዲ ስለ ክሪምያ ጦርነት በጣም obsessed እንደነበረ እዚህ ነው የተማርኩት — ሴባስቶፖል የሚለውን ስም ከየት እንዳመጣው እስከዛሬ አለመጠየቄም ገርሞኛል። ሲመቻችሁ፡ ክፍል 1 ይኸው። ተከታዮቹን እዛው ታገኟቸዋላችሁ። https://podcasts.apple.com/de/podcast/the-rest-is-history/id1537788786?i=1000789062329
Open in Telegramሰላም ጤና፡ የዚህን ድረገጽ ባለቤት የሚያውቅ አለ? ቆንጅዬ ሥራ ነው ግን አንዳንድ መጻሕፍት አሉ በሕግ ሊያስጠይቋቸው የሚችሉ እዛ ላይ በነጻ ያሉ https://www.habeshahistory.com/encyclopedia
Open in Telegramፕሮፍ ታደሰ ታምራት ኸንቲንግፎርድ የተባለ ሰው የጻፈውን መጽሐፍ እንዴት አብጠልጥለው ሪቪው እንዳደረጉት እዩማ። የዛሬ 35 ዓመት ገደማ ነው የተጻፈው ግን ቢሆንም እግዚኦ 😂
Open in Telegram