Account

Posts of Ethio-Chamber

newest first

#18554Link preview

ዛሬ ከኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ ጋር በምክር ቤታችንና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው መካከል ያለውን ተቋማዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና የጋራ የትብብር መስኮችን ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ የትውውቅና የትብብር ውይይት አካሂደናል። በዚህ አጋጣሚም ለነበረን ገንቢና ፍሬያማ ውይይት በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በራሴ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከዚህ በተጨማሪም፣ በውይይቱ ላይ ለተገኙት ሚኒስትር ዴኤታዎችና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮች ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ፣ ላቀረቡት ገንቢ ምክረ ሐሳቦችና ከእኛ ጋር ላደረጉት ግልጽና ወዳጃዊ ውይይት ልዩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የዛሬው ውይይታችን በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ተቋማዊ የጋራ ግንዛቤን ለማስፋትና በትብብር ልንሠራባቸው የሚገቡ የጋራ የሥራ መስኮችን ለመለየት ያስቻለ አስፈላጊና ጠቃሚ መድረክ ነበር። በውይይታችን የተለዩትንና በቀጣይ በጋራ ለመፈጸም የተስማማንባቸውን አበይት የሥራ ጉዳዮች በተግባር ለማሳካት፣ ምክር ቤታችን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በቅርበትና በቅንጅት ለመሥራት ያለውን ጽኑ ፍላጎት በዚህ አጋጣሚ እንደገና ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ይህንንም ለማሳካት በተቀናጀ የአሠራር ሥርዓት፣ በቀጣይነት በሚደረግ የተቋማቱ የሥራ ግንኙነትና በጋራ ክትትል በመታገዝ በውይይታችን የተነሱትን ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤት ለማሸጋገር እንደምንሠራ አረጋግጣለሁ። በተጨማሪም፣ በውይይታችን የተነሱትን ሐሳቦች፣ የተለዩትን የትብብር አቅጣጫዎችና የተጋራናቸውን የጋራ ግንዛቤዎች ወደ ተግባር ለመቀየር የምክር ቤታችን መላው አመራርና ባለሙያዎች ዝግጁ መሆናቸውንም በዚሁ አጋጣሚ አረጋግጣለሁ። በመጨረሻም፣ ለነበረን ጥሩና ፍሬያማ ውይይት፣ እንዲሁም ለተደረገልን ሞቅ ያለ አቀባበል፣ ለክብርት ሚኒስትሯና ለሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮችና ኃላፊዎች በድጋሚ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡  +251115514005 ፋክስ፡  + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: [email protected] ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም      t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡   https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

Open in Telegram
Views588+13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h364
6 h560
9 h588
  1. After 6 hours560
  2. Total to date588
#18547Photo
Views485−7%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h305
6 h463
9 h485
  1. After 6 hours463
  2. Total to date485
#18544Photo

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ECCSA) የቢዝነስ ሊደርሺፕ አካዳሚው አማካኝነት ለዳሽን ባንክ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው “Advanced Sector Analysis for Islamic Corporate Financing” የተሰኘ የሶስት ቀናት ስልጠና በዛሬው ዕለት  ተጠናቋል። ስልጠናው ተሳታፊዎች በላቀ የዘርፍ ትንተና ያላቸውን ዕውቀትና ተግባራዊ ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እንዲሁም በእስላማዊ የድርጅት ፋይናንስ አሰራር ያላቸውን አቅም እንዲያጠናክሩ በማለም የተሰጠ  ነበር። የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርጰቤት የባለሙያዎችን ዕውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለፋይናንስ ዘርፉ ዕድገትና ልህቀት  የሚያደርገውን ተቋማዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡  +251115514005 ፋክስ፡  + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: [email protected] ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም      t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡   https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

Open in Telegram
Views537+3%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h419
7 h537
  1. After 6 hours537
  2. Total to date537
#18543Link preview

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የትውውቅና በጋራ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ። በውይይት መድረኩም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ እና ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር፣ ሌሎች የምክር ቤቱ የቦርድ አባላትና ዋና ጸሐፊ እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ አመራሮች፣ የቦርድ አባላትና ዋና ጸሐፊ ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን ምክር ቤቱ እያከናወናቸው ያሉ ዋና ዋና የለውጥ (Reform) ተግባራትና በቀጣይ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያቀዳቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ በምክር ቤቱ በኩል ገለጻ ተደርጓል። ሀገራዊ የንግድ ሥራውን የሚያሣልጡ የጋራ ሥራዎችንና የአሠራር ግንኙነቶችን ይበልጥ ለማጠናከር በምክር ቤቱና በሚኒስቴሩ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም ተነስቷል። ሚኒስትሯ ክብርት ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ፣ ምክር ቤቱ በሀገር እድገት ላይ ያለው አስተዋጽኦ እና ድርሻ የጎላ በመሆኑ ይህንን ማጎልበትና ሀገራዊ የንግዱ ማኀበረሠብ ወካይ አለኝታነቱን ማጠንከር እንደሚገባው አብራርተዋል።። በምክር ቤቱ እና በአባላቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር፣ በምርጫ ሂደቶች፣ በግራንድ ሀገራዊ ስትራቴጂ ትግበራ፣ በወጭ ንግድ ፕሮሞሽን፣ በንግድ ህጋዊነት፣ በቴክኖሎጅ ዲጂታላይዜሽን ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ የሠጡት ሚኒስትሯ ወደ ምክር ቤቱ ጠንካራና ቁርጠኛ አመራሮችን ማምጣት እንደሚገባም ገልጸዋል።። በሌላ በኩል አሁን በስራ ላይ ያለው የምክር ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ ወቅቱን ያላገናዘበ በመሆኑና ከወቅታዊ የሀገራዊ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር የተናበበ እንዲሆን ለማሥቻል አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በሂደት ላይ በመሆኑ እንዲጸድቅና የግሉ ዘርፍ ጠንካራና አቅም ያለው እንዲሆን ሀገራዊ ኢኮኖሚውም በግሉ ዘርፍ እንዲመራ ለማስቻል የሚኒስቴሩ ድጋፍ እንደማይለየው ክብርት ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። የንግድ ማኅበረሰቡ በሕግና በሥርዓት እንዲመራ፣ የኢ-ኮሜርስ ሥራዎችን እንዲሁም ኢመደበኛውን የንግድ ሥራ ወደ መደበኛ ስርዓት በመቀየር እንዲሁም የዲጂታል ሥርዓት ደኅንነትን ማረጋገጥ ትኩረት ሊሠጣቸው የሚገቡ ተግባራት መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ ምክር ቤቱ በራሱ አቅም ያለማቸው የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን አንስተዋል። የመደመር ታላቁ ስትራቴጂ ተግባራዊ ሲደረግ ዋነኛው ተዋናይ የንግዱ ማኀበረሠብ በመሆኑ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ባለፈ የአባል ምክር ቤቶች አመራሮች በስትራቴጂው ዙሪያ ዋነኛ ተዋናይ መሆን እንዳለባቸው አንስተዋል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በበኩላቸው በመንግስት በኩል የምክር ቤቱ ዋነኛ አጋር የሆነው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመሆኑ ሁለቱ ተቋማት በቅርበትና በትብብር መሥራታቸው ለንግድ ስርዓቱ መዘመንና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን በውይይቱ ላይ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ ቦርድ መዋቅራዊ ቅርጹ ኢትዮጵያን የሚመሥል ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ ይህ አመራር በርካታ መዋቅራዊ፣ ሥትራቴጂያዊና ሌሎችንም የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገቡንና ከሚኒስቴሩ ጋር እጅና ጓንት በመሆን የበለጠ ለመስራት እንደሚተጋም ገልጸዋል። የንግድ ስርዓቱን ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ የንግዱን ማኅበረሰብ ተሳትፎ ለማጠናከር፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የገበያ እድሎችን ለማሥፋት፣ በሠላም ግንባታ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ምክክር በማድረግ፣ በዲጂታላይዜሽንና በቴክኖሎጅ አጠቃቀም እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ሁለቱ ተቋማት በትብብር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል። ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡  +251115514005 ፋክስ፡  + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: [email protected] ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም      t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡   https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

Open in Telegram
Views567+8%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
5 h499
9 h567
  1. After 6 hours499
  2. Total to date567
#18534Photo
Views436−17%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
5 h374
9 h436
  1. After 6 hours374
  2. Total to date436